نُبذَةٌ فِي العَقِيدَةِ الإِسْلَامِيَّة (شَرْحُ أُصُولِ الإِيمَانِ)
አጭር ገለፃ ስለ ኢስላማዊ እምነት
بِقَلَم فَضِيلَة الشَّيخ العَلَّامَة
مُحَمَّدِ بْنِ صَالِحٍ العُثَيمِين
غَفَرَ اللَّهُ لَهُ وَلِوَالِدَيْهِ وَلِلْمُسْلِمِين
አዘጋጅ: የተከበሩ እውቁ ሸይኽ
ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል‐ዑሠይሚን
አላህ መሀርታውን እሳቸውንም ወላጆቻቸውንና መላው ሙስሊምንም ይለግሰንና
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ
አጭር ገለፃ ስለ ኢስላማዊ እምነት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው
መግቢያ
ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው። እናመሰግነዋለን፤ እገዛውንና መሀርታውን እንማፀነዋለን፤ በንሰሃም ወደ እርሱ እንመለሳለን። ከነፍሶቻችን ክፋትና ከመጥፎ ስራዎቻችን በአሏህ እንጠበቃለን። አላህ የመራውን የሚያጠም የለውም፤ ያጠመመውንም የሚመራ የለውም። ከአላህ በስተቀር በእውነት ሊያመልኩት የሚገባ አምላክ እንደሌለ፤ ብቸኛ እና ተጋሪም እንደሌለው እመሰክራለሁ። ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልዕክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ፤ የአላህ ሶለዋት በሳቸው፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸውና በቅንነት በተከተሏቸውም ላይ ሁሉ ይስፈን። ሰላሙንም ያስፍንባቸው።
በመቀጠል: የተውሒድ እውቀት እጅግ የተከበረ፣ እጅግ የላቀ፣ እጅግም ተፈላጊ እውቀት ነው። ምክንያቱም አላህን በተመለከተ ስለ አላህ፣ ስለ ስሞቹና ስለባህርያቱ እንዲሁም በባርያዎቹ ላይ ስላለው መብት ማወቅ በመሆኑ እና ወደ አላህ ለሚያደርሰው መንገድም መክፈቻው ከመሆንም አልፎ የድንጋጌው መሰረት በመሆኑም ነው።
ስለዚህም ነው መልዕክተኞች ሁሉ ጥሪያቸውን ወደዚሁ ጉዳይ ማድረግ ላይ ወጥ አቋም የነበራቸው። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿وَمَآ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِيٓ إِلَيۡهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعۡبُدُونِ25﴾
{ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡} [አል‐አንቢያእ: 25]
አላህም ስለራሱ ብቸኝነት መስክሯል፤ መላእክቶችና የእውቀት ባለቤቶችም በአንድነቱ ላይ መስክረዋል። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿شَهِدَ ٱللَّهُ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَأُوْلُواْ ٱلۡعِلۡمِ قَآئِمَۢا بِٱلۡقِسۡطِۚ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ 18﴾
{አላህ በማስተካከል የቆመ (አስተናባሪ) ሲኾን ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ መኾኑን መሰከረ፡፡ መላእክቶችና የዕውቀት ባለቤቶችም (እንደዚሁ መሰከሩ)፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡} [አሊ‐ዒምራን: 18]
የተውሒድ አንገብጋቢነት የዚህን ያህል እስከሆነ ድረስ እያንዳንዱ ሙስሊም ሊማረው፣ ሊያስተምረው፣ ሊያስተነትነው፣ ሊያምንበት ዘንድ ግድ ነው። ይህንን በማድረጉም ሃይማኖቱን ጠንካራ በሆነና ተረጋግቶ በፀና መሰረት ላይ በማነፅ ለፍሬውና ለመልካም ውጤቱ የታደለ ይሆናል።
ተውፊቁን የሚገጥመው አሏህ ነው።
አዘጋጁ
የእስልምና ሃይማኖት
የእስልምና ሃይማኖት: አላህ ነቢዩ ሙሐመድን ‐ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ‐ የላከበትና ሃይማኖቶችንም ሁሉ በእርሱ ለባርያዎቹ ሙሉ አድርጎ የደመደመበት፤ ፀጋውንም በእርሱ የተሟላ ያደረገበት፤ ከሃይማኖትም ከእርሱ ውጭ ምንም በማይቀበልበት ልክ ለነርሱ የመረጠላቸው የሆነ ሃይማኖት ነው። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَآ أَحَدٖ مِّن رِّجَالِكُمۡ وَلَٰكِن رَّسُولَ ٱللَّهِ وَخَاتَمَ ٱلنَّبِيِّـۧنَۗ وَكَانَ ٱللَّهُ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٗا 40﴾
{ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡} [አል‐አሕዛብ: 40]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል:
﴿...ٱلۡيَوۡمَ أَكۡمَلۡتُ لَكُمۡ دِينَكُمۡ وَأَتۡمَمۡتُ عَلَيۡكُمۡ نِعۡمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلۡإِسۡلَٰمَ دِينٗا...﴾
{ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ።} [አል‐ማኢዳህ: 3]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል:
﴿إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلۡإِسۡلَٰمُ...﴾
{አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፡፡} [አሊ‐ዒምራን: 19]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል:
﴿وَمَن يَبۡتَغِ غَيۡرَ ٱلۡإِسۡلَٰمِ دِينٗا فَلَن يُقۡبَلَ مِنۡهُ وَهُوَ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ85﴾
{ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡} [አሊ‐ዒምራን: 85]
በእርግጥ የላቀው አሏህ እርሱን በዚሁ ሃይማኖት እንዲገዙት በሁሉም ሰዎች ላይ ግዴታ አድርጓል። መልዕክተኛውን ሲያናግር እንዲህ ብሏቸዋል:
﴿قُلۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنِّي رَسُولُ ٱللَّهِ إِلَيۡكُمۡ جَمِيعًا ٱلَّذِي لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ يُحۡيِۦ وَيُمِيتُۖ فَـَٔامِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِ ٱلنَّبِيِّ ٱلۡأُمِّيِّ ٱلَّذِي يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَكَلِمَٰتِهِۦ وَٱتَّبِعُوهُ لَعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ 158﴾
{(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው፡- «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደናንተ ወደሁላችሁም የአላህ መልክተኛ ነኝ፡፡ (እርሱም) ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ የኾነ ነው፡፡ እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ በአላህ በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ ነቢይ በኾነው መልክተኛው እመኑ፡፡ ቅንንም መንገድ ትመሩ ዘንድ ተከተሉት፡፡»} [አል‐አዕራፍ: 158]
በሶሒሕ ሙስሊምም አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (የአሏህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
«وَالَّذِي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بِيَدِهِ لَا يَسْمَعُ بِي أَحَدٌ مِنْ هَذِهِ الْأُمَّةِ يَهُودِيٌّ وَلَا نَصْرَانِيٌّ، ثُمَّ يَمُوتُ وَلَمْ يُؤْمِنْ بِالَّذِي أُرْسِلْتُ بِهِ إِلَّا كَانَ مِنْ أَصْحَابِ النَّارِ».
"የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው እምላለሁ! ከዚህ ህዝብ መካከል ከአይሁድም ሆነ ከክርስትያኖች ውስጥ ማንም ቢሆን ስለኔ ሰምቶ፣ ከዚያም እኔ በተላኩበት (መልእክት) ሳያምን ከሞተ፣ በእርግጥ የእሳት (የጀሀነም) ነዋሪ ይሆናል።""
በሳቸው ማመን: ተልዕኳቸው እውነት መሆኑን ማወቅ ብቻ ሳይሆን አምኖ መቀበልና ዝቅ ማለትን ባካተተ መልኩ አምኖ መገኘት ያስፈልጋል፤ ለዛም ነው አቡ ጧሊብ የነቢዩን ‐ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና)‐ ተልዕኮ እውነተኝነት ከማወቃቸውና ከሃይማኖቶች ሁሉ ምርጡ መሆኑን ከመመስከራቸውም ጋር አማኝ ያልተባሉት።
ኢስላማዊው ሃይማኖት: ቀደምት ሃይማኖቶች ሁሉ የነበራቸውን በጎ ነገራቶችን አጠቃልሎ ከመያዝም አልፎ ለሁሉም ጊዜ፣ ቦታና ማህበረሰብ የሚስማማ በመሆኑ ለየት ያደርገዋል። የላቀው አላህ መልዕክተኛውን እንዲህ ሲል ያናግራቸዋል:
﴿وَأَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ مُصَدِّقٗا لِّمَا بَيۡنَ يَدَيۡهِ مِنَ ٱلۡكِتَٰبِ وَمُهَيۡمِنًا عَلَيۡهِ...﴾
{ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡} [አል‐ማኢዳህ: 48]
ለሁሉም ጊዜ፣ ቦታና ማህበረሰብ ተስማሚ ነው ስንል የኢስላምን መመርያ አጥብቆ መያዝ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ያለን ማህበረሰብ በጎ እሴት አይጎዳም እንዲያውም ያሻሽልላቸዋል ማለታችን እንጅ አንዳንድ ሰዎች እንደፈለጉት ለየጊዜው፣ ለየቦታው ወይም ለየማህበረሰቡ ህግ ተገዥ ይሆንላቸዋል ማለታችን አይደለም።
የእስልምና ሃይማኖት: መመርያውን አጥብቆ ለያዘ ሰው አላህ እንደሚረዳውና ከሌላውም ሁሉ አስበልጦ ከፍ እንደሚያደርገው ዋስትና የገባለት ትክክለኛው ሃይማኖት ነው። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿هُوَ ٱلَّذِيٓ أَرۡسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلۡهُدَىٰ وَدِينِ ٱلۡحَقِّ لِيُظۡهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡمُشۡرِكُونَ 9﴾
{እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን በመምሪያ (መጽሐፍ) በእውነተኛው ሃይማኖትም (በኢስላም) ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ሊያደርገው የላከ ነው፡፡} [አስ‐ሶፍ: 9]
እንዲህም ብሏል:
﴿وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنكُمۡ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَيَسۡتَخۡلِفَنَّهُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ كَمَا ٱسۡتَخۡلَفَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ وَلَيُمَكِّنَنَّ لَهُمۡ دِينَهُمُ ٱلَّذِي ٱرۡتَضَىٰ لَهُمۡ وَلَيُبَدِّلَنَّهُم مِّنۢ بَعۡدِ خَوۡفِهِمۡ أَمۡنٗاۚ يَعۡبُدُونَنِي لَا يُشۡرِكُونَ بِي شَيۡـٔٗاۚ وَمَن كَفَرَ بَعۡدَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡفَٰسِقُونَ 55﴾
{አላህ እነዚያን ከእናንተ ያመኑትንና መልካም ሥራዎችን የሠሩትን እነዚያን ከእነሱ በፊት የነበሩትን እንደተካ በምድር ለይ በእርግጥ ሊተካቸው፣ ለእነሱም ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው፣ ከፍርሃታቸውም በኋላ ጸጥታን ሊለውጥላቸው ተስፋን ቃል ሰጥቷቸዋል፡፡ በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ይግገዙኛል፡፡ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው፡፡} [አን‐ኑር: 55]
የእስልምና ሃይማኖት: እምነትም መመርያም ነው። በእምነቱም ይሁን በመመርያው ደሞ እጅግ ፍፁም ነው።
1‐ በአላህ ብቸኛ ተመላኪነት የሚያዝ ሲሆን በአላህ ተጋሪ ማድረግንም ይከለክላል።
2‐ በእውነተኝነት የሚያዝ ሲሆን ከውሸትም ይከለክላል።
3‐ በፍትህ የሚያዝ ሲሆን ከግፈኝነትም ይከለክላል። ፍትህ ማለት አንድ አይነቶችን እኩል አድርጎ የሚለያዩትን ደሞ (በፍርድ) መለያየት ነው። ፍትህ ማለት አንዳንዶች "ኢስላም የእኩልነት ሃይማኖት ነው" ሲሉ ልቅ አድርገው እንደሚያስቡት ሁሉንም እኩል ማድረግ ማለት አይደለም። ምክንያቱም የሚለያዩ የሆኑትን አንድ አድርጎ መዳኘት ኢስላም የማያዘውና አድራጊውም የማይመሰገንበት የሆነ የበደል አይነት ነው።
4‐ አደራ መወጣትን የሚያዝና ክህደት (ተንኮልን) የሚከለክል ነው።
5‐ ቃልን መሙላትን የሚያዝና ቃልን ማጠፍን የሚከለክል ነው።
6‐ ለወላጆች በጎ መዋልን የሚያዝና እነርሱን ማመፅን የሚከለክል ነው።
7‐ ቅርብ የሆኑ ቤተሰቦች ጋር ዝምድና አጠናክሮ መቀጠልን የሚያዝና ዝምድና መቁረጥን የሚከለክል ነው።
8‐ መልካም ጉርበትናን የሚያዝና ክፋትን የሚከለክል ነው።
ጠቅለል ባለ መልኩ ኢስላም ላቅ ባለ መልካም ስነምግባር ሁሉ የሚያዝና ወራዳ ከሆነ ስነምግባር ሁሉ ደሞ የሚከለክል ነው። በበጎ ስራ ሁሉ የሚያዝና ከመጥፎ ስራም ሁሉ የሚከለክል ነው።
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿إِنَّ ٱللَّهَ يَأۡمُرُ بِٱلۡعَدۡلِ وَٱلۡإِحۡسَٰنِ وَإِيتَآيِٕ ذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَيَنۡهَىٰ عَنِ ٱلۡفَحۡشَآءِ وَٱلۡمُنكَرِ وَٱلۡبَغۡيِۚ يَعِظُكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ 90﴾
{አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም (ከማመንዘር)፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል፡፡} [አን‐ነሕል: 90]
የኢስላም ማእዘናት
የኢስላም ማዕዘናት: ኢስላም የተገነባባቸው የሆኑት መሰረቶች ማለት ሲሆን አምስት ናቸው:
مَذْكُورَةٌ فِيمَا رَوَاهُ ابْنُ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُ قَالَ: «بُنِيَ الْإِسْلَامُ عَلَى خَمْسَةٍ: عَلَى أَنْ يُوَحَّدَ اللَّهُ - وَفِي رِوَايَةٍ: عَلَى خَمْسٍ -: شَهَادَةِ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ، وَإِقَامِ الصَّلَاةِ، وَإِيتَاءِ الزَّكَاةِ، وَصِيَامِ رَمَضَانَ، وَالْحَجِّ». فَقَالَ رَجُلٌ: الْحَجُّ، وَصِيَامُ رَمَضَانَ؟ قَالَ: «لَا، صِيَامُ رَمَضَانَ، وَالْحَجُّ» هَكَذَا سَمِعْتُهُ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ.
ኢብኑ ዑመር -ረዲየሏሁ ዓንሁ- ከነቢዩ -ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና)- ባስተላለፉት ሐዲሥ ላይ እንዲህ በሚል ተጠቅሷል: «ኢስላም በአምስት (ማዕዘናት) ተገነባ: አላህን ብቸኛ አድርጎ ማመን ላይ…» በሌላ ዘገባ ደግሞ «"ከአምስት (ማዕዘናት) ተገነባ: ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአሏህ ባርያውና መልዕክተኛው መሆናቸውን መመስከር፣ ሶላትን ማቋቋም፣ ዘካን መስጠት፣ የረመዳንን ወር መፆም፣ ሐጅ ማድረግ ናቸው።" አንድ ሰውም "ሐጅ ማድረግና የረመዳንን ወር መፆም (ማለትዎ) ነውን?" በማለት ዘጋቢውን ጠየቀ። እሱም: "አይ የረመዳንን ወር መፆምና ሐጅ ማድረግ ነው።" አለ። በዚህ መልኩ ነው ከአሏህ መልዕክተኛ -ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና)- የሰማሁትም አለ።»
1‐ ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ ሙሐመድም የአላህ ባርያውና መልዕክተኛው ናቸው ብሎ መመስከር: በአንደበት የምስክርነት ቃልን ከመግለፅ ጋር ልክ እንደሚመለከተው ሆኖ ቁርጥ አድርጎ በልብ ማመን ነው። ይህ የምስክርነት ቃል የሚሚሰከረው የምስክር ቁጥር ከአንድ በላይ ከመሆኑም ጋር እንደአንድ የምስክርነት ቃል ተደርጎ የቀረበበት ምክንያት:
ወይ: መልዕክተኛው ከአሏህ የተሰጠውን ተልዕኮ የሚያደርስ ከመሆኑ አንፃር የአሏህ መልዕክተኛና ባርያው መሆናቸውን መመስከር ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ መመስከርን የሚያሟላ በመሆኑ ነው።
ወይም ደግሞ: ሁለቱም የምስክርነት ቃላት የትኛውም ስራ ትክክለኛና ተቀባይነት ያለው ሊሆን ዘንድ ሁለቱም የምስክርነት ቃላት መሰረታዊ ወሳኝነት ስላላቸው ነው። የትኛውም ስራ ለአሏህ ብቻ በኢኽላስ የጠራና የመልዕክተኛውን -ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና)- ፋና የተከተለ ሆኖ ካልተሰራ በቀር ስራውም ትክክል አይሆንም፤ ተቀባይነትንም አያገኝምና።
ለአሏህ በኢኽላስ ስራን በማጥራት ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም የሚለው የምስክርነት ቃል የሚረጋገጥ ሲሆን የመልዕክተኛውን ፋና በመከተል ደሞ ሙሐመድ የአሏህ ባርያውና መልዕክተኛው መሆናቸውን መመስከር የሚረጋገጥበት ይሆናል።
ይህ የምስክርነት ቃል ከሚያስገኛቸው መልካም ፍሬዎች መካከል: ቀልብም ይሁን ነፍስ ለፍጡራን የሚያጎበድድ ከመሆንና ከአላህ መልዕክተኞች ውጭ ላለ አካል (ጭፍን) ተከታይ ከመሆን ይታደጋል።
2‐ ሶላትን ማቋቋም: በፅናትና በተሟላ ሁኔታ ወቅቷን ጠብቆ ሶላት እየሰገዱ አሏህን ማምለክ ነው።
ከመልካም ፍሬዎቿ መካከልም: የቀልብ መከፈት፣ የዓይን ማረፊያ መሆኗ እና ከፀያፍና ከውግዝ ስራዎች መታደግ መቻሏ ነው።
3‐ ዘካን መስጠት: ዘካ የሚወጣባቸው ከሆኑ የገንዘብ አይነቶች ግዴታ የሆነውን ያህል ገንዘብ በመለገስ አሏህን ማምለክ ነው።
ከመልካም ፍሬዎቿ መካከልም: ነፍስን ወራዳ ከሆነው የስግብግብነት ባህሪ ማጥራትና ለኢስላምና ለሙስሊሞች ጉዳይ ማስፈፀሚያ የገንዘብ ማሟያ መሆን መቻሉ ይገኝበታል።
4‐ የረመዷንን ወር መፆም: በረመዷን የቀኑ ክፍለ ጊዜ ሊያስፈጥሩ ከሚችሉ ነገሮች በመታቀብ የላቀውን አሏህ ማምለክ ነው።
ከመልካም ፍሬዎቹ መካከልም: ነፍስ የምትወደውን ነገር የአሏህን ውዴታ ፈልጋ እየወደደችውም እንኳ መተውን ያለማምዳታል።
5‐ የተከበረውን የአሏህን ቤት መጎብኘት: የሐጅ ስርአቶችን ለማከናወን አስቦ የተከበረውን የአሏህን ቤት በመጎብኘት አሏህን ማምለክ ነው።
ከመልካም ፍሬዎቿ መካከልም: አላህን በመታዘዝ ረገድ በገንዘብም ይሁን በአካል ደረጃ ጥረት ማድረግ ላይ ነፍስን ማለማመድ መቻሏ ተጠቃሽ ነው። ለዛም ነው ሐጅ በአላህ መንገድ ከመታገል አይነቶች የሆነው።
እነዚህ የጠቀስናቸው መልካም ፍሬዎች እንዲሁም ያልጠቀስናቸውም የነዚህ መሰረቶች መልካም ፍሬዎች ማህበረሰብን ትክክለኛ በሆነው የአላህ ሃይማኖት የሚተዳደር፣ ፍጡራንን በእውነትና በፍትህ የሚኗኗር ኢስላማዊና የፀዳ ማህበረሰብ ያደርጉታል። ምክንያቱም ከተጠቀሱት ማዕዘናት ውጭ ያሉት የሃይማኖቱ ድንጋጌ እነዚህ በመስተካከላቸው የሚስተካከል ነው። የኡማው (የሙስሊሙ ማህበረሰብ) ሁኔታም የሚስተካከለው የሃይማኖታዊ ጉዳዮቹ በመስተካከል ሲሆን፣ የሃይማኖታዊ ጉዳዮቹ ከመስተካከል በተጓደለ መጠን ደግሞ ማህበራዊ ሁኔታዎቹ ከመስተካከል ይጎድለዋል።
ይህንን ማረጋገጥ የፈለገ ሰው ተከታዩን የአላህን ቃል ያንብብ:
﴿وَلَوۡ أَنَّ أَهۡلَ ٱلۡقُرَىٰٓ ءَامَنُواْ وَٱتَّقَوۡاْ لَفَتَحۡنَا عَلَيۡهِم بَرَكَٰتٖ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ وَلَٰكِن كَذَّبُواْ فَأَخَذۡنَٰهُم بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ 96 أَفَأَمِنَ أَهۡلُ ٱلۡقُرَىٰٓ أَن يَأۡتِيَهُم بَأۡسُنَا بَيَٰتٗا وَهُمۡ نَآئِمُونَ 97 أَوَأَمِنَ أَهۡلُ ٱلۡقُرَىٰٓ أَن يَأۡتِيَهُم بَأۡسُنَا ضُحٗى وَهُمۡ يَلۡعَبُونَ98 أَفَأَمِنُواْ مَكۡرَ ٱللَّهِۚ فَلَا يَأۡمَنُ مَكۡرَ ٱللَّهِ إِلَّا ٱلۡقَوۡمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ 99﴾
{የከተማዋም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር፡፡ ግን አስተባበሉ፡፡ ይሠሩት በነበሩትም ኃጢኣት ያዝናቸው። የከተማዋ ሰዎችም እነሱ የተኙ ኾነው ቅጣታችን ሌሊት ሊመጣባቸው አይፈሩምን?! የከተማዋ ሰዎችም እነሱ የሚጫወቱ ኾነው ሳሉ ቅጣታችን ቀን በረፋድ ሊመጣባቸው አይፈሩምን?! የአላህንም ማዘናጋት አይፈሩምን የአላህንም ማዘናጋት ከከሳሪዎች ሕዝቦች በስተቀር የሚተማመን የለም፡፡} [አል‐አዕራፍ: 96‐99]
እንዲሁም ታሪክም ቢሆን ማስተዋሉን ለታደሉ ሰዎችና ልቦናው ላይ ግርዶሽ ላልተጋረጠበት ሰው ጥሩ መነፅርና አስተማሪ መሆን ይችላልና ያለፈን ታሪክ አገላብጦ ይመልከት። አጋዣችን አሏህ ነው!
የእስልምና እምነት መሰረቶች
ኢስላማዊ እምነት ከፍ ብለንም እንደገለፅነው እምነትም ድንጋጌም ነው። ከመመርያዎቹ መካከልም መሰረታዊ ምሰሶዎቹን በተወሰነ መልኩ ጠቅሰናል።
የኢስላማዊው እምነት መሰረቶችም: በአላህ፣ በመላዕክቶች፣ በመፃህፍቱ፣ በመልዕክተኞቹ፣ በመጨረሻው ቀን፣ እንዲሁም በክፉም በደጉም የአላህ ቀደር ማመን ነው።
እነዚህም በአላህ ቁርአንም ይሁን በመልዕክተኛው -ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና)- ሐዲሥ ማስረጃ ያላቸው መሰረቶች ናቸው።
በአላህ ቁርአን የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿لَّيۡسَ ٱلۡبِرَّ أَن تُوَلُّواْ وُجُوهَكُمۡ قِبَلَ ٱلۡمَشۡرِقِ وَٱلۡمَغۡرِبِ وَلَٰكِنَّ ٱلۡبِرَّ مَنۡ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ وَٱلۡكِتَٰبِ وَٱلنَّبِيِّـۧنَ...﴾
{መልካም ሥራ ፊቶቻችሁን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞር አይደለም፡፡ ግን መልካም ሥራ በአላህና በመጨረሻው ቀን፣ በመላእክትም፣ በመጻሕፍትም፣ በነቢያትም፣ ያመነ ሰው… ነው፡፡} [አል‐በቀራ: 177] ስለቀደር ደሞ እንዲህ ብሏል:
﴿إِنَّا كُلَّ شَيۡءٍ خَلَقۡنَٰهُ بِقَدَرٖ 49 وَمَآ أَمۡرُنَآ إِلَّا وَٰحِدَةٞ كَلَمۡحِۭ بِٱلۡبَصَرِ 50﴾
{እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው፡፡ ትእዛዛችንም እንደ ዓይን ቅጽበት አንዲት (ቃል) እንጅ ሌላ አይደለም፡፡} [አል‐ቀመር: 49‐50]
በመልዕክተኛው -ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና)- ሱናም ነቢዩ -ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና)- ጂብሪል ስለ ኢማን በጠየቃቸው ጊዜ እንዲህ ብለው መልስ ሰጥተውታል:
«الْإِيمَانُ: أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَالْيَوْمِ الْآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ: خَيْرِهِ وَشَرِّهِ».
«ኢማን ማለት: በአላህ፣ በመላዕክቶች፣ በመፃህፍቱ፣ በመልዕክተኞቹ፣ በመጨረሻው ቀን፣ እንዲሁም በክፉም በደጉም የአላህ ቀደር ማመን ነው።»
በላቀው አሏህ ማመን
በአላህ ማመን አራት ነገሮችን ያካትታል:
የመጀመርያው: በላቀው አላህ ህልውና ማመን:
የአላህን መኖር የሚያመላክቱት ደግሞ፡- ተፈጥሮአዊ ዝንባሌ (ፊጥራ)፣ አእምሮ (ዐቅል)፣ ሃይማኖታዊ ህግጋት (ሸርዕ) እና ስሜት (ሒስስ) ናቸው።"
1‐ አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) መኖሩን አስመልክቶ የፊጥራ (ተፈጥሮአዊ ዝንባሌ) አመላካችነት፦ ሁሉም ፍጡር ምንም ቅድመ ማሰብ ወይም ትምህርት ሳይኖር በፈጣሪው የማመን ዝንባሌ ላይ ተፈጥሯል፤ ይህንን የፊጥራ መስፈርት የሚለቅቀው በልቡ ላይ ከዚህ የሚያዞረው ነገር ያጋጠመው ሰው ብቻ ነው።
«مَا مِنْ مَوْلُودٍ إِلَّا يُولَدُ عَلَى الْفِطْرَةِ، فَأَبَوَاهُ يُهَوِّدَانِهِ أَوْ يُنَصِّرَانِهِ أَوْ يُمَجِّسَانِهِ».
ይህም ነቢዩ -ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና)- እንዲህ ስላሉ ነው: «እያንዳንዱ ተወላጅ በተፈጥሯዊ እምነት ላይ ሁኖ ነው የሚፈጠረው፤ ታድያ ግና ወላጆቹ የሁዲ ወይም ክርስትያን ወይም እሳት አምላኪ ያደርጉታል።»
2‐ አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) መኖሩን አስመልክቶ አዕምሯዊ ማስረጃው፡- በእርግጥ ሁሉም ፍጡራን ያለፉትም ሆነ ወደፊት የሚመጡት ወደ ሕልውና የሚያመጣቸው ፈጣሪ ሊኖራቸው ግድ ነው። ለራሳቸውም ህልውና መስጠት አይችሉም፤ እንዲሁም አጋጣሚ ወደ ሕልውና መጡ የሚለውም አያስኬድምና።
ራሳቸውን ወደ ሕልውና ማምጣት በፍፁም የማይሆን ነገር ነው፤ ምክንያቱም የትኛውም ነገር ራሱን መፍጠር አይችልምና፤ ከህልውናው በፊት ሳይኖር እንዴትስ ለራሱ ህልውና ሊሰጥ ይችላል?!
እንዲሁም በአጋጣሚ ወደ ሕልውና ሊመጣም አይችልም፤ ምክንያቱም ማንኛውም ክስተት አስከሳች ያስፈልገዋልና። ከዚህም በላይ ፍፁም ስርአቱ፣ የተቀናጀ ውህደቱ፣ በመንስኤዎችና በውጤቶች መካከል ያለው ትስስር እና በሁሉም ፍጥረታት መካከል ያለው ውጤታማ ሂደት ይህ ፍጥረተ አለም በአጋጣሚ ወደ ሕልውና ሊመጣ እንደማይችል ግልጽ ማሳያ ነው። አንድ ነገር መጀመርያውኑ ወደ ሕልውና ሲመጣ ሥርዓት ሳይኖረው አጋጣሚ በዘፈቀደ ከተገኘ በኋላ ቀጣይ ሕልውናውና ዕድገቱ እንዴት እጅግ ወጥ ሥርዓት ሊኖረው ይችላል ተብሎ ይታሰባል?!
እነዚህ ፍጥረታት እራሳቸውን ወደ ህልውና ማምጣት ካልቻሉና አጋጣሚ መገኘታቸውም ሊሆን የማይችል ጉዳይ መሆኑን ከተስማማን ለነሱ ፈጣሪ ሊኖር ግድ ነው ማለት ነው፤ እሱም ፈጣሪ የዓለማት ጌታ አላህ ነው።
የላቀው አላህ ይህንን ምክንያታዊ ማስረጃና ቁርጥ ያለ እውነታ በሱረቱ ጡር ላይ እንዲህ ሲል ጠቁሟል፡
﴿أَمۡ خُلِقُواْ مِنۡ غَيۡرِ شَيۡءٍ أَمۡ هُمُ ٱلۡخَٰلِقُونَ 35﴾
{ወይስ ያለ አንዳች (ፈጣሪ) ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን?} [አጥ ጡር:35] በሌላ አነጋገር ያለ ፈጣሪም አልተፈጠሩም፤ ራሳቸውንም አልፈጠሩም። ስለዚህም ኃያሉ አላህ ፈጣሪያቸው መሆኑ ግድ ነው ማለት ነው። ለዚህም ነው ጁበይር ኢብኑ ሙጥዒም ረዲየሏሁ ዓንሁ (አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) ነብዩ (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ሱረቱል ጡርን እያነበቡ ሲሰማ ልክ እነዚህ አንቀጾች ላይ ሲደርሱ፡-
﴿أَمۡ خُلِقُواْ مِنۡ غَيۡرِ شَيۡءٍ أَمۡ هُمُ ٱلۡخَٰلِقُونَ 35 أَمۡ خَلَقُواْ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَۚ بَل لَّا يُوقِنُونَ 36 أَمۡ عِندَهُمۡ خَزَآئِنُ رَبِّكَ أَمۡ هُمُ ٱلۡمُصَۜيۡطِرُونَ 37﴾
{ወይስ ያለ አንዳች (ፈጣሪ) ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸው? ወይስ ሰማያትንና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም አያረጋግጡም፡፡ ወይስ የጌታህ ግምጃ ቤቶች እነርሱ ዘንድ ናቸውን? ወይስ እነርሱ አሸናፊዎች ናቸውን?} [አጥ-ጡር፡ 35-37]
ጁበይር ያኔ ሙሽሪክ ነበርና እንዲህ አለ፡ «ልቤ ወጥቶ ሊበር አለ፤ እምነት መጀመሪያውኑ ልቤ ውስጥ የገባው ያኔ ነበር።»
ይህንን በሌላ ምሳሌ እናብራራው እስኪ አንድ ሰው ከሥሩ ጅረቶች በሚፈሱባቸው የአትክልት ስፍራዎች የተከበበ በጣም ምርጥ ስለሆነ ቤተ መንግሥት ይነግርዎታል እንበል፤ ቤተ መንግሥቱ የቤት ዕቃዎች እና አልጋዎች የተሟሉለት እና በተለያዩ ጌጣጌጦች ያጌጠ ነው። ከዚያም ይህ ቤተ መንግሥትኮ በውስጡ ካለው ፍፁምነት ጋር ራሱን የፈጠረ ወይም ያለ ገንቢ በአጋጣሚ የተገኘ ነው ቢልህ፤ ያለጥርጥር እንዲህ ያለህን ሰው ይህንን ቃሉን አትቀበለውም፤ ንግግሩንም ከንቱ አድርገህ ነው የምትቆጥረው። ታድያ ይህንን እያስተባበልክ ይህ ግዙፍ ዩኒቨርስ በውስጡ ካሉት ፍጥረታት ከምድር፣ ከሰማይ፣ ከፕላኔቶቹ እና ፍፁም ከሆኑ ሁኔታዎችና ስርአቱ ጋር ራሱን በራሱ ወደ ህልውና አመጣ ወይም በአጋጣሚ የመጣ ነው ብሎ ማመን እንዴት ምክንያታዊ ሊሆን ይችላል?!
3- አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) መኖሩን አስመልክቶ ሸሪዓዊ ማስረጃው፡ ጉዳዩ ሁሉም መለኮታዊ መጻሕፍት ያረጋገጡት እውነታ ከመሆኑም ባሻገር መፅሃፎቹ በውስጣቸው የያዙት መመርያ ፍትሐዊነቱ እና የሰዎችን ጥቅም በፍፁምነት የሚያስጠብቁ ከመሆናቸውም አኳያ መመርያዎቹ ጥበበኛና ዐዋቂ ከሆነው ጌታ ዘንድ የመጡ ለመሆናቸው በቂ ማሳያ ነው። በተጨማሪም በእነዚህ መጻሕፍት ውስጥ ለወደፊቱ ስለሚፈጸሙ ክንውኖች ገልፀው ከጊዜ በኋላ ያሏቸው ጉዳዮች እውን ሆነው መታየታቸው የተናገረውን ነገር እውን ማድረግ የሚችልበት ኃያልነት ካለው ጌታ እንደመጡ ማረጋገጫ ነው።
4- የአላህን ህልውና የሚያሳዩ ህዋሳዊ ማስረጃዎች ሁለት ገፅታዎች አሏቸው፡
አንደኛ፡- አንዳንዴ ሰዎች ዱዓቸው ምላሽ ማግኘቱንና ባደረጉት ዱዓ ከገጠማቸው ጭንቀት መገላገላቸውን እንሰማለንም እንመለከታለንም፤ ይህም የአላህን ህልውና ቁርጥ ባለ መልኩ የሚያረጋግጥ ጉዳይ ነው። ጥራት ይገባውና አላህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَنُوحًا إِذۡ نَادَىٰ مِن قَبۡلُ فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ...﴾
{ኑሕንም ከዚያ በፊት (ጌታውን) በጠራ ጊዜ (አስታውስ)።} [አል-አንቢያእ፡ 76] ጥራት ይገባውና እንዲህም ብሏል፡ [ከጌታችሁ እርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ
﴿إِذۡ تَسۡتَغِيثُونَ رَبَّكُمۡ فَٱسۡتَجَابَ لَكُمۡ...﴾
«እኔ በሺህ መላእክት ተከታታዮች ሲኾኑ እረዳችኋለሁ» ሲል ለናንተ የተቀበላችሁን (አስታውሱ)።} [አል-አንፋል:9]
በሶሒሕ አል ቡኻሪይ አነስ ኢብኑ ማሊክ ረዲየሏሁ ዓንሁ (አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደዘገበው፡- «የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በዕለተ ጁምዓ ንግግር እያደረጉ ሳለ አንድ ገጠሬ ገባና፡- "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ገንዘብ ወደመ ልጆቻችንም ተራቡ አላህን ለምኑልን!" አለ። እሳቸውም እጃቸውን ወደላይ ከፍ አድርገው አሏህን ተማፀኑ፤ ወዲያውኑም ተራራ የሚመስሉ ደመናዎች ብቅ ብቅ አሉ፤ የዝናቡ ውሃ ከጢማቸው ላይ ሲንጠባጠብ እስክናየው ድረስም ከሚንበሩ ላይ አልወረዱም ነበር።
በቀጣዩ ጁሙዓም ያው ገጠሬ - ወይም ሌላ ሰው - ቁሞ እንዲህ አለ፡- "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ግንባታው ፈረሰ (ወደቀ)፣ ንብረትም (ገነዘቡም) ውሃ በላው። አላህን ለምኑልን።" የአላህ መልእክተኛም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) እጆቻቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርገው፡- "አላህ ሆይ ዝናቡን በዙሪያችን እንጂ በእኛ ላይ አታርግብን።" ወደ የትኛውም አቅጣጫ እጃቸውን ባመላከቱ ቁጥር ደመናዎቹ ይበታተኑ ነበር።»
የዱዓእ ምላሽ ማግኘት ዛሬም ድረስ የምናየው ሲሆን ይህም የሚሆነው ዱዓውን የሚያደርግ ሰው ከልቡ ወደ ጌታው ሲቀርብ እና ጥሩ ምላሽ ለማግኘት የሚያስፈልጉትን ሰበቦች ሲያሟላ ነው።
ሁለተኛ፡- ተአምር የሚባሉት ለነቢያትም ምልክት የሆኑና ሰዎችም የሚመለከቷቸው ወይም የሚሰሟቸው ወጣ ያሉ ክስተቶች ነብያቶቹን የላካቸው ለሆነው አላህ ህልውናውንም የሚያረጋግጡለት ማስረጃዎች ናቸው። ምክንያቱም የሰው ልጅ ሊያደርግ ከሚችለው ወሰን ያለፉ ነገሮች ናቸውና፤ መልክተኞቹን ለመደገፍ ሲል እንዲከሰቱ ያደረጋቸውም አሏህ ነው።
ለምሳሌ የሙሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ተአምር አላህ ባህሩን በበትሩ እንዲመታው ባዘዘው ጊዜ እሱም አደረገው ከዚያም ባሕሩ ወደ አሥራ ሁለት ደረቅ መንገዶች ተከፍሎ በመካከላቸው ያለው ውሃ እንደ ተራራ ቀጥ ያለ ነበር። ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ እንዲህ ሲል ነግሮናል፡-
﴿فَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنِ ٱضۡرِب بِّعَصَاكَ ٱلۡبَحۡرَۖ فَٱنفَلَقَ فَكَانَ كُلُّ فِرۡقٖ كَٱلطَّوۡدِ ٱلۡعَظِيمِ 63﴾
{ወደ ሙሳም «ባሕሩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክንበት፡፡ (መታውና) ተከፈለም፡፡ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ኾነ።} [አሽ-ሹዓራእ፡ 63]
ሌላው ምሳሌ የዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) በአላህ ፈቃድ ሙታንን ሕያው አድርጎ ከመቃብራቸው ሲያወጣ የታየው ተአምር ነው። ዒሳ ምን እንዳለ የላቀው አላህ እንዲህ ሲል ነግሮናል፡
﴿...وَأُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰ بِإِذۡنِ ٱللَّهِۖ...﴾
{በአላህም ፍቃድ ... ሙታንንም አስነሳለሁ።} [አሊ-ዒምራን፡ 49] አላህም እንዲህ ሲል ማናገሩን ነግሮናል፡
﴿...وَإِذۡ تُخۡرِجُ ٱلۡمَوۡتَىٰ بِإِذۡنِيۖ...﴾
{ሙታንንም በፈቃዴ (ከመቃብራቸው) በምታወጣ ጊዜ} [አል-ማኢዳህ፡ 110]
ሦስተኛው ምሳሌ ቁረይሾች ተአምር እንዲያሳያቸው ሙሐመድን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲጠይቋቸው ወደ ጨረቃዋ አመላከቱ ጨረቃዋም ለሁለት ተከፈለች። ሰዎችም ተመለከቱት በዚህ ጉዳይም የላቀው አላህ እንዲህ ሲል ነግሮናል፡
﴿ٱقۡتَرَبَتِ ٱلسَّاعَةُ وَٱنشَقَّ ٱلۡقَمَرُ 1 وَإِن يَرَوۡاْ ءَايَةٗ يُعۡرِضُواْ وَيَقُولُواْ سِحۡرٞ مُّسۡتَمِرّٞ2﴾
{ሰዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፤ ተዓምርንም ቢያዩ (ከእምነት) ይዞራሉ፡፡ (ይህ) «ዘውታሪ ድግምት ነውም» ይላሉ።} [አል-ቀመር፡ 1-2]
እነዚህ አላህ መልእክተኞቹን ለመደገፍና ተልዕኳቸውን ለመርዳት የሚያስከስታቸው ተአምራቶች የእርሱን ሕልውና በማያሻማ መልኩ የሚያረጋግጡ እውነታዎች ናቸው።
በአላህ ማመን ውስጥ የሚካተተው ሌላኛው የእምነቱ ክፍል በጌትነቱ ማመን ነው። ማለትም እርሱ ምንም አጋርና ረዳት ሳይኖረው ብቸኛ ጌታ መሆኑን ማመን ነው።
ጌታ ፍጡራኑን ሁሉ የፈጠረ፣ የሚያዝና የሚያስተዳድር ብቸኛ ነው። ከአሏህ በቀር በእውነት ሊያመልኩት የሚገባ አምላክ የለም። ማዘዝም የእርሱ ብቻ ነው። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿...أَلَا لَهُ ٱلۡخَلۡقُ وَٱلۡأَمۡرُۗ...﴾
{ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው።} [አል-አዕራፍ፡ 54] እንዲህም ብሏል፡
﴿...ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡ لَهُ ٱلۡمُلۡكُۚ وَٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا يَمۡلِكُونَ مِن قِطۡمِيرٍ﴾
{ይህ ጌታችሁ አላህ ነው። ንግሥናው የእርሱ ብቻ ነው። እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትግገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን እንኳ አይኖራቸውም።} [ፋጢር፡ 13]
በልቡ ያመነበትን የማይናገር ደረቅ ቀጣፊ ካልሆነ በስተቀር የአላህን ጌትነት የካደ አንድም የለም። ለምሳሌ ፈርዖን ለሕዝቦቹ፡-
﴿فَقَالَ أَنَا۠ رَبُّكُمُ ٱلۡأَعۡلَىٰ 24﴾
{«እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ፡፡»} ያለበትን ምሳሌ እንውሰድ። እንዲህም ብሏል፡-
﴿...يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمَلَأُ مَا عَلِمۡتُ لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرِي...﴾
{...«እናንተ ጭፍሮች ሆይ! ከእኔ ሌላ ለእናንተ አምላክን ምንም አላወቅሁም። ...} (አል ቀሶስ 38)። ይበል እንጂ እነዚህ ንግግሮቹ እውነተኛ ልባዊ እምነቱን የሚገልፁ አይደሉም። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَجَحَدُواْ بِهَا وَٱسۡتَيۡقَنَتۡهَآ أَنفُسُهُمۡ ظُلۡمٗا وَعُلُوّٗاۚ...﴾
{ነፍሶቻቸው ያረጋገጧት ሲኾኑ ለበደልና ለኩራት በእርሷ ካዱ።} [አን-ነምል፡ 14] አሏህ ስለሱ በነገረን መሰረት ሙሳም ለፊርዓውን እንዲህ ብሎታል፡
﴿...لَقَدۡ عَلِمۡتَ مَآ أَنزَلَ هَٰٓؤُلَآءِ إِلَّا رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ بَصَآئِرَ وَإِنِّي لَأَظُنُّكَ يَٰفِرۡعَوۡنُ مَثۡبُورٗا﴾
{(ሙሳም) «እነዚህን (ተዓምራቶች) መገሰጫዎች ሲኾኑ የሰማያትና የምድር ጌታ እንጂ ሌላ እንዳላወረዳቸው በእርግጥ ዐውቀሃል። እኔም ፈርዖን ሆይ! የምትጠፋ መኾንህን በእርግጥ እጠረጥርሃለሁ።» አለው።} [አል-ኢስራእ፡ 102] ስለዚህ ነበር ሙሽሪኮች በአምልኮ ላይ ቢያጋሩም በአሏህ ብቸኛ ጌትነት ያምኑ የነበሩት። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿قُل لِّمَنِ ٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهَآ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ 84 سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ85 قُلۡ مَن رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ ٱلسَّبۡعِ وَرَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡعَظِيمِ 86 سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ 87 قُلۡ مَنۢ بِيَدِهِۦمَلَكُوتُ كُلِّ شَيۡءٖ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيۡهِ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ 88 سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ فَأَنَّىٰ تُسۡحَرُونَ 89﴾
{«ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ብትኾኑ (ንገሩኝ)» በላቸው። «በእርግጥ የአላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ አትገሰጹምን?» በላቸው። «የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው?» በላቸው። «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «እንግዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው። «የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው? የምታውቁ እንደኾናችሁ (መልሱልኝ)» በላቸው። «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ?» በላቸው።} [አል-ሙእሚኑን፡ 84-89]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ لَيَقُولُنَّ خَلَقَهُنَّ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡعَلِيمُ 9﴾
{«ሰማያትንና ምድርንም ማን ፈጠራቸው» ብለህ ብትጠይቃቸው «አሸናፊው ዐዋቂው (አላህ) በእርግጥ ፈጠራቸው» ይላሉ።} [አዝ-ዙኽሩፍ፡ 9]
ጥራት ይገባውና እንዲህም ብሏል፡
﴿وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَهُمۡ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُۖ فَأَنَّىٰ يُؤۡفَكُونَ 87﴾
{ማን እንደፈጠራቸውም ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይላሉ፡፡ ታዲያ (ከእምነት) ወዴት ይዞራሉ?!} [አዝ-ዙኽሩፍ፡ 87]
የአላህ ትእዛዝ ከፍጥረተ አለማዊም ይሁን ከሸሪዓም ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ሁሉ ያካትታል። እርሱ በዓለማት ላይ ጥበቡ እንደሚያስፈርደው ያሻውን ሰሪ የነገሮች ሁሉ አስተናባሪ እንደኾነው ሁሉ የአምልኮ ተግባራትንና ንግግሮችን ፍርድም በጥበቡ መሠረት የሚያዝ የሁሉም ገዢ ነው። ስለዚህም ከአላህ ሌላ የአምልኮ ህግ አውጭ ወይም በመስተጋብሩ ጉዳይ ላይ አዛዥን ያደረገ ሰው በታላቁ ጌታ አጋርቷል። እምነቱም ትክክለኛ አይደለም።
በአላህ ላይ ሊኖር የሚገባው ሦስተኛው የእምነቱ አካል በአምላክነቱ ማመን ነው። እርሱ ብቻ አምልኮ የሚገባው አጋርም የሌለው እውነተኛ አምላክ መሆኑን ማመን ነው። "ኢላህ" ወይም አምላክ ማለት በውዴታ እና በማላቅ የሚመለክ አምላክ ማለት ነው።
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَإِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞۖ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلرَّحۡمَٰنُ ٱلرَّحِيمُ 163﴾
{አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም። (እርሱ) እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው።} [አል-በቀራህ፡ 163]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿شَهِدَ ٱللَّهُ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَأُوْلُواْ ٱلۡعِلۡمِ قَآئِمَۢا بِٱلۡقِسۡطِۚ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ 18﴾
{ አላህ በማስተካከል የቆመ (አስተናባሪ) ሲኾን ከእርሱ በስተቀር ሌላ እውነተኛ አምላክ የሌለ መኾኑን መሰከረ። መላእክቶችና የዕውቀት ባለቤቶችም (እንደዚሁ መሰከሩ)፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ እውነተኛ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው።} [አሊ-ዒምራን፡ 18] በአምልኮው ከአሏህ ጋር ባላንጣ ያደረገ ሰው አምልኮው ውድቅ ነው። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ هُوَ ٱلۡبَٰطِلُ وَأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡعَلِيُّ ٱلۡكَبِيرُ 62﴾
{ይህ አላህ እርሱ እውነት በመሆኑ ከእርሱም ሌላ የሚግገዙት ነገር እርሱ ፍጹም ውሸት በመሆኑ አላህም እርሱ የሁሉ በላይ ታላቅ በመኾኑ ነው።} [አል-ሐጅ፡ 62] አምላክ ተብለው ስለተጠሩ ብቻ አምላክነት አይፀድቅላቸውም። የላቀው አሏህ "ላት" "ዑዛ" እና "መናት" የተባሉትን ጣኦታትን በተመለከተ እንዲህ ብሏል፡
﴿إِنۡ هِيَ إِلَّآ أَسۡمَآءٞ سَمَّيۡتُمُوهَآ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلۡطَٰنٍۚ...﴾
{እነርሱ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸው ስሞች ብቻ እንጅ ምንም አይደሉም፡፡ አላህ በእርሷ (መግገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም።} [አን-ነጅም፡ 23]
ነቢዩሏህ ሁድ ዓለይሂ ሰላምም ለህዝቦቹ እንዲህ ማለቱን አሏህ ነግሮናል፡
﴿...أَتُجَٰدِلُونَنِي فِيٓ أَسۡمَآءٖ سَمَّيۡتُمُوهَآ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُم مَّا نَزَّلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلۡطَٰنٖۚ...﴾
{«እናንተና አባቶቻችሁም (አማልክት ብላችሁ) በጠራችኋቸው ስሞች አላህ በእርሷ ምንም ማስረጃ ያላወረደባት ስትኾን ትከራከሩኛላችሁን? ተጠባባቁም እኔ ከእናንተ ጋር ከተጠባባቂዎቹ ነኝና» አለ።} [አል-አዕራፍ፡ 71]
ነብዩ ዩሱፍ (ዓለይሂ ሰለም (የአሏህ ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና)) በእስር ላይ ሳሉ ለሁለቱ ባልደረቦቻቸው እንዲህ ማለታቸውንም አሏህ ነግሮናል፡-
﴿يَٰصَٰحِبَيِ ٱلسِّجۡنِ ءَأَرۡبَابٞ مُّتَفَرِّقُونَ خَيۡرٌ أَمِ ٱللَّهُ ٱلۡوَٰحِدُ ٱلۡقَهَّارُ 39 مَا تَعۡبُدُونَ مِن دُونِهِۦٓ إِلَّآ أَسۡمَآءٗ سَمَّيۡتُمُوهَآ أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بِهَا مِن سُلۡطَٰنٍۚ...﴾
{«የእስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! የተለያዩ አምላኮች ይሻላሉን ወይስ አሸናፊው አንዱ አላህ? ከእርሱ ሌላ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸውን ስሞች እንጅ አትገዝዙም፡፡ አላህ በእርሷ ምንም አስረጅ አላወረደም።»} [ዩሱፍ፡ 39-40]
ለዛም ነው መልዕክተኞች (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በእነርሱ ላይ ይስፈንና) ለህዝቦቻቸው እንዲህ ይሉ የነበሩት፡
﴿...ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُ...﴾
{«ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ለእናንተ ከርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም።»} [አል-አዕራፍ፡ 59] ሙሽሪኮች ግን ያንን አልተቀበሉም። ይልቁንም ከአሏህ ሌላ አማልክትን ያዙ - እነዚያን የውሸት አማልክቶች ማምለካቸውንና ከነርሱ እርዳታና ድጋፍን መፈለጋቸውንም ቀጠሉ።
አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ግን አጋርነታቸውን በሁለት አእምሮአዊ ሙግቶች ውድቅ አድርጓል፡-
አንደኛ፡- እነዚያ የያዟቸው አማልክት ምንም አይነት መለኮታዊ ባህሪ የሌላቸው መሆናቸውን፤ እነሱም የተፈጠሩ እና ምንም ነገር መፍጠርም የማይችሉ መሆናቸውን፤ ለሚያመልኳቸው ሰዎች እንኳ ምንም አይነት ጥቅም ማምጣትም ይሁን ጉዳትን ማስወገድ የማይችሉ መሆናቸውን፤ እነሱ በሰዎች ሕይወትም ይሁን ሞት ላይ አልያም በሰማያት ባለው አንዳች ነገር ላይ እንኳ ምንም ስልጣን የሌላቸው መሆናቸውን አሳውቆ በርሱም ተጋሪዎች ሊሆኑ ብቁ እንዳልሆኑ በመግለፅ ነው።
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةٗ لَّا يَخۡلُقُونَ شَيۡـٔٗا وَهُمۡ يُخۡلَقُونَ وَلَا يَمۡلِكُونَ لِأَنفُسِهِمۡ ضَرّٗا وَلَا نَفۡعٗا وَلَا يَمۡلِكُونَ مَوۡتٗا وَلَا حَيَوٰةٗ وَلَا نُشُورٗا 3﴾
{(ከሓዲዎች) ከእርሱም ሌላ ምንንም የማይፈጥሩን፣ እነርሱም የሚፈጠሩን፣ ለነፍሶቻቸውም ጉዳትን (ለመከላከል) ጥቅምንም (ለማምጣት) የማይችሉን ሞትንና ሕይወትንም መቀስቀስንም የማይችሉን፣ አማልክት ያዙ፡፡} [አል-ፉርቃን፡ 3]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿قُلِ ٱدۡعُواْ ٱلَّذِينَ زَعَمۡتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ لَا يَمۡلِكُونَ مِثۡقَالَ ذَرَّةٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا لَهُمۡ فِيهِمَا مِن شِرۡكٖ وَمَا لَهُۥ مِنۡهُم مِّن ظَهِيرٖ 22 وَلَا تَنفَعُ ٱلشَّفَٰعَةُ عِندَهُۥٓ إِلَّا لِمَنۡ أَذِنَ لَهُۥ...﴾
{«እነዚያን ከአላህ ሌላ (አማልክት ብላችሁ) የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም፡፡ ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸውም፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለውም፤» በላቸው። ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም።} [ሰባእ፡ 22-23]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿أَيُشۡرِكُونَ مَا لَا يَخۡلُقُ شَيۡـٔٗا وَهُمۡ يُخۡلَقُونَ 191 وَلَا يَسۡتَطِيعُونَ لَهُمۡ نَصۡرٗا وَلَآ أَنفُسَهُمۡ يَنصُرُونَ 192﴾
{ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን (በአላህ) ያጋራሉን? ለእነርሱም መርዳትን የማይችሉትን ነፍሶቻቸውንም የማይረዱትን (ያጋራሉን)።} [አል-አዕራፍ፡ 191-192]
የእነዚያ የሐሰት አማልክቶች ሁኔታ ይህ ከሆነ እነሱን እንደ አምላክ መውሰድ እጅግ ሞኝነት እና ፍጹም ስህተት ነው።
ሁለተኛ፡- እነዚያ ሙሽሪኮች አላህ ብቻውን ጌታና ፈጣሪ መሆኑን፤ የነገሩ ሁሉ ሥልጣን በእጁ የሆነና ሌሎችን ይጠብቃል እንጂ የሌሎችን ጥበቃ የማይሻ መሆኑን ያምኑ ነበር። ይህም በጌትነቱ ብቸኝነት እንዳመኑ ሁሉ በአምላክነቱ ብቸኝነትም ሊያምኑ ዘንድ የሚያስፈርድ ነው።
ልክ የላቀው አሏህ እንዲህ እንዳለን ማለት ነው፡
﴿يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱعۡبُدُواْ رَبَّكُمُ ٱلَّذِي خَلَقَكُمۡ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ21 ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَرۡضَ فِرَٰشٗا وَٱلسَّمَآءَ بِنَآءٗ وَأَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَخۡرَجَ بِهِۦ مِنَ ٱلثَّمَرَٰتِ رِزۡقٗا لَّكُمۡۖ فَلَا تَجۡعَلُواْ لِلَّهِ أَندَادٗا وَأَنتُمۡ تَعۡلَمُونَ 22﴾
{እናንተ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁን ተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና። (እርሱ) ያ ለናንተ ምድርን ምንጣፍ ሰማይንም ጣራ ያደረገ ነው፤ ከሰማይም (ከደመና) ውሃን ያወረደ በርሱም ከፍሬዎች ለናንተ ሲሳይን ያወጣ ነው፡፡ እናንተም (ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትኾኑ ለአላህ ባላንጣዎችን አታድርጉ።} [አልበቀራህ፡ 21-22]
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَهُمۡ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُۖ فَأَنَّىٰ يُؤۡفَكُونَ 87﴾
{ማን እንደፈጠራቸውም ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይላሉ፡፡ ታዲያ (ከእምነት) ወዴት ይዞራሉ።} [አዝ-ዙኽሩፍ፡ 87]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿قُلۡ مَن يَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ أَمَّن يَمۡلِكُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَمَن يُخۡرِجُ ٱلۡحَيَّ مِنَ ٱلۡمَيِّتِ وَيُخۡرِجُ ٱلۡمَيِّتَ مِنَ ٱلۡحَيِّ وَمَن يُدَبِّرُ ٱلۡأَمۡرَۚ فَسَيَقُولُونَ ٱللَّهُۚ فَقُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ 31 فَذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمُ ٱلۡحَقُّۖ فَمَاذَا بَعۡدَ ٱلۡحَقِّ إِلَّا ٱلضَّلَٰلُۖ فَأَنَّىٰ تُصۡرَفُونَ32﴾
{ «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ (ለምን ታጋራላችሁ) አትፈሩትምን» በላቸው፡፡ እርሱ እውነተኛ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ (ከእውነት) እንዴት ትዞራላችሁ!?} [ዩኑስ፡ 31-32]
በአሏህ ማመን ውስጥ የሚካተተው አራተኛው ጉዳይ በአሏህ ስምና ባህርያቱ ማመን ነው።
ይኸውም የላቀው አላህ በቁርዓን ስለራሱ ወይም መልዕክተኛው በሐዲሣቸው ስለ አሏህ የገለፁትን ስምና ባህሪያቱን ያለምንም ማዛባት፣ ያለምንም ማስተባበል፣ ያልምንም ማመሳሰል እና ዝርዝር አኳኋን ውስጥም ገብተው ሳይፈላፈሉ እንደመጣው መቀበል ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፡-
﴿وَلِلَّهِ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰ فَٱدۡعُوهُ بِهَاۖ وَذَرُواْ ٱلَّذِينَ يُلۡحِدُونَ فِيٓ أَسۡمَٰٓئِهِۦۚ سَيُجۡزَوۡنَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ 180﴾
{ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፡፡ (ዱዓ ስታደርጉ) በእርሷም ጥሩት፡፡ እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው፡፡ ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይምመነዳሉ፡፡} (አል-አዕራፍ 180)
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿...وَلَهُ ٱلۡمَثَلُ ٱلۡأَعۡلَىٰ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ﴾
{ለእርሱም በሰማያትም በምድርም ከፍተኛ ባሕርይ (አንድነትና ለእርሱ ብጤ የሌለው መኾን) አለው።}
[ሩም፡ 27]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿...لَيۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَيۡءٞۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ﴾
{የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው።} [አሽ-ሹራ፡ 11]
በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለት አይነት ጭፍሮች ስህተት ላይ ወድቀዋል።
አንዱ ጭፍራ "ሙዓጢላህ" የሚባሉት ሲሆኑ የአላህን ስሞችና ባህሪያት ማፅደቅ ፍጡር ጋር ማመሳሰል እንደሆነ በመሞገት የአላህን ስሞችና ባህሪያቱን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የሚክዱ ናቸው። ይህ ሙግታቸው ግን ከሚከተሉት ነጥቦች አኳያ ስህተት ነው፡
አንደኛ፡- ይህ ሙግት የተሳሳቱ ጭብጦችን ያስፈርዳል። ይሀውም የአሏህ ቃል እርስ በራሱ የሚቃረን ያስመስላል። አሏህ ለራሱ ስምና ባህርያቱን አፅድቋል የሚመስለው እንደሌለም ተናግሯል። እነዚያን የአሏህ ስሞች እና ባህሪያት አምኖ መቀበል ማመሳሰል ቢሆን ኖሮ የአላህ ቃል ውስጥ ግጭት እንዳለና ከፊሉ ከፊሉን ውሸት የሚያስብል ቃል እንዳለ ያስፈርድ ነበር።
ሁለተኛ፡- ስም ወይም ባህሪ በተወሰነ መልኩ የሚጋሩ ሁሉ ሙሉ ለሙሉ ተመሳሳይ ሊሆኑ ግዴታ አይደለም። ለምሳሌ ሁለት ሰዎች ባህሪያትን ሲጋሩ እናያለን፡ ሁለቱም ሰው ናቸው፣ መስማት የሚችሉ፣ ማየት የሚችሉ እና መናገር የሚችሉ ናቸው እንበል። ያ ማለት ግን በሰብአዊነት፣ በመስማት ችሎታ፣ በመመልከት ችሎታቸው እና በመናገር ችሎታቸው ተመሳሳይ ናቸው ማለት አይደለም።
(የተለያዩ) እንስሶችም እጆች፣ እግሮችና አይኖች እንዳሏቸው እናያለን። ይሁን እንጂ በስም ደረጃ ተመሳሰሉ ማለት እጆቻቸው፣ እግሮቻቸውና አይኖቻቸው የሁሉም ተመሳሳይ ነው ማለት አይደለም።
ስምና ባህሪዎቹ ተመሳሳይ ከመሆናቸውም ጋር በፍጡራን መካከል የባህርያዊ እውነታ ልዩነት መኖሩን ከተረዳን በፍጡራን እና በፈጣሪ መካከል የባህርያዊ እውነታ ልዩነት ሊኖር ግድ መሆኑ እጅግ ግልፅና ትልቅ ሀቅ ነው።
ሌላው ጭፍራ "ሙሸቢሃዎች" ናቸው። እነዚህ የአላህን ስሞችና ባህሪያት የሚያረጋግጡ ቢሆኑም የሚያረጋግጡት ግን ፍጡር ጋር ከማመሳሰል ጋር ጭምር ነው። ይህም ቀጥታ ከአንቀፆቹ የወሰዱት መልዕክት እንደሆነ ይሞግታሉ። ምክንያቱም አላህ ባሮቹን የሚያናግራቸው በሚረዱት መንገድ ነው። ይህ ሙግት ግን ለናሙና ያህል ከሚከተሉት ምክንያቶች አኳያ ስህተት ነው፡-
አንደኛ፡- አላህን ከፍጡራኑ ጋር ማመሳሰል አዕምሮም ይሁን ሸሪዓው የማይቀበለው ስህተት ነው። ታድያ ቁርኣንና ሱና የሚያስፈርዱት እንዴት ስህተትን ሊሆን ይችላል?!
ሁለተኛ፡ በርግጥም የላቀው አላህ ባርያዎቹን የሚያናግራቸው በሚረዱት መንገድ ነው፤ ማለትም በመሰረታዊ መልዕክቱ በሚገባቸው ልክ ማለት ነው። የጉዳዩን ተጨባጭ እውነታ እና ዝርዝር ሁኔታ ግን አላህ ብቻውን በእውቀቱ ከተነጠለባቸው ጉዳዮች መካከል ነው። በተለይም ስለ ማንነቱ እና ባህሪያቱ ዝርዝር አኳኋን እውቀቱ ያለው እርሱ ዘንድ ብቻ ነው።
ስለዚህም አላህ እርሱ ሰሚ መሆኑን እስከነገረን ድረስ የመስማት መሠረታዊ ትርጉሙ ይታወቃል፤ መረጃን በድምፅ መልኩ መውሰድ እንደሆነ ግልፅ ነው። ነገር ግን የአላህን መስማት ትክክለኛ ዝርዝር ሁኔታን በተመለከተ ግን አናውቀውም። በመሠረቱ የመስማት ተጨባጭ እውነታው በፍጥረታት መካከልም ይለያያል፤ በፈጣሪና በፍጥረቱ መካከልማ የበለጠ ልዩነት አለዋ።
የላቀው አሏህ ከዓርሹ በላይ ከፍ ማለቱን ስለራሱ እስከነገረን ድረስ ከፍ ማለት ትርጉሙ ምን እንደሆነ ግልፅ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ከዓርሹ በላይ ከፍ ያለው በምን አኳኋን ነው ስለሚለው ጉዳይ ተጨባጭ እውነታው እንዴት እንደሆነ እኛ በዝርዝር የምናውቀው ጉዳይ አይደለም። ምክንያቱም ከፍ ማለት በፍጡራን መካከል እንኳ ልዩነት አለው። በተረጋጋ ወንበር ላይ መደላደል በርጋጋና አስቸጋሪ በሆነች ግመል ላይ ከመደላደል ጋር በፍፁም አይገናኝም። በፍጡራን መካከል ይህ ልዩነት ካለ በፈጣሪ እና በፍጡራን መካከል ልዩነት መኖሩ እጅግ ግልፅና ጉልህ ነው።
በጠቀስነው መልኩ በላቀው አሏህ ማመን ለምእመናን ትልቅ ጥቅም ያስገኝላቸዋል፤ ከነዚህም፡-
አንደኛ፡- በአላህ አንድነት ማመኑ ከአሏህ ውጭ ማንንም እንዳይከጅልና ማንንም እንዳይፈራ በማድረግ የሚያመልከው አሏህን ብቻ እንዲሆን አስችሎት ተውሒድን ለማረጋገጥ ይረዳዋል።
ሁለተኛ፡ ለአላህ ያለውን ውዴታ እና ማላቅ በተዋቡ ስሞቹ እና በላቁ ባህሪያቱ በመሆኑ እጅግ የተሟላ ውዴታና ማላቅ ይሆንለታል።
ሶስተኛ፡ አሏህ ያዘዘውን በመታዘዝና የከለከለውን በመከልከል አሏህን በሚገባ ማምለክን ያረጋግጥለታል።
በመላእክቶች ማመን
መላእክት የማይታዩ ዓለም ናቸው። አላህ የፈጠራቸው እርሱን የሚያመልኩ ባርያዎቹ ናቸው። የጌትነት ወይም የመለኮትነት ባህሪ የላቸውም። አሏህ እነርሱን የፈጠራቸው ከብርሃን ሲሆን ለትእዛዙ ሙሉ በሙሉ ተገዥዎች እና ፈጻሚዎች እንዲሆኑ አግርቷቸዋል። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿...وَمَنۡ عِندَهُۥ لَا يَسۡتَكۡبِرُونَ عَنۡ عِبَادَتِهِۦ وَلَا يَسۡتَحۡسِرُونَ 19 يُسَبِّحُونَ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ لَا يَفۡتُرُونَ 20﴾
{ እርሱ ዘንድ ያሉትም (መላእክት) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፡፡ አይሰለቹምም፡፡ በሌሊትና በቀንም ያጠሩታል፤ አያርፉም፡፡} [አል-አንቢያእ፡ 19-20]
መልአኮች ከአሏህ በቀር ቁጥራቸውን ማንም ቆጥሮ የማይዘልቃቸው የሆኑ እጅግ ብዙ ናቸው። ቡኻሪና ሙስሊም እንደዘገቡት ከአነስ ረዲየሏሁ ዓንሁ (አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) በተላለፈ ሐዲሥ ነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) በሚዕራጅ (ባረጉት) ጉዞ ላይ ሳሉ "በይተል መዕሙር"ን (ከሰማይ በላይ ያለ ቤት ልክ በመሬት መካ ላይ እንዳለው ካዕባ አይነት ቤት) ተመለከቱ። በዚህ ቤት ላይ በየቀኑ ሰባ ሺህ መላእክት ይሰግዱበታል፤ ከወጡ ደሞ እስከቂያማ ድረስ መመለስም አይችሉም።
በመላእክት ማመን አራት ነገሮችን ያጠቃልላል፡
አንደኛ፡ በህልውናቸው ማመን ነው።
ሁለተኛ፡- እንደ ጅብሪል (ጂብሪል) አይነቱ ከመካከላቸው ስሞቻቸውን ያውቅነውን ስለእያንዳንዱ በታወቀው ስማቸው ማመን ነው። ስሞቻቸውን ያላወቅነውን ደሞ ስለነሱ እንዲሁ በጥቅሉ እናምናለን።
ሦስተኛ፡- ስለ ባህርያቸው በተነገረን ደሞ ባህርያቸውንም በተመለከተ በተነገረን ልክ በዝርዝር ማመን ነው። ለምሳሌ፡ ስለ ጂብሪል ሁኔታ ነብዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) በተፈጥሯዊ መልኩ ማየታቸውን እና ስድስት መቶ ክንፎች እንዳሉት እንዲሁም አድማሱንም እንደከደነው ነግረውናዋል።
አንድ መልአክ በአላህ ትዕዛዝ ወደ ሰው መልክ ሊለወጥም ይችላል።
كَمَا حَصَلَ لِجِبْرِيلَ عَلَيْهِ السَّلَامُ حِينَ أَرْسَلَهُ اللَّهُ تَعَالَى إِلَى مَرْيَمَ، فَتَمَثَّلَ لَهَا بَشَرًا سَوِيًّا، وَحِينَ جَاءَ إِلَى النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَهُوَ جَالِسٌ فِي أَصْحَابِهِ، جَاءَهُ بِصِفَةِ رَجُلٍ شَدِيدِ بَيَاضِ الثِّيَابِ، شَدِيدِ سَوَادِ الشَّعْرِ، لَا يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ، وَلَا يَعْرِفُهُ أَحَدٌ مِنْ أَصْحَابِهِ، فَجَلَسَ إِلَى النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَأَسْنَدَ رُكْبَتَيْهِ إِلَى رُكْبَتَيْهِ، وَوَضَعَ كَفَّيْهِ عَلَى فَخِذَيْهِ، وَسَأَلَ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنِ الْإِسْلَامِ، وَالْإِيمَانِ، وَالْإِحْسَانِ، وَالسَّاعَةِ، وَأَمَارَاتِهَا؛ فَأَجَابَهُ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَانْطَلَقَ، ثُمَّ قَالَ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «هَذَا جِبْرِيلُ؛ أَتَاكُمْ يُعَلِّمُكُمْ دِينَكُمْ».
ይህም አላህ ጂብሪልን (ዐለይሂ-ሰላም) በሰው አምሳል ወደ መርየም በላከው ጊዜ የተከሰተ ጉዳይ ነው። እንዲሁም ወደ ነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና)) በመጣ ጊዜ በሶሓቦቻቸው መካከል ሁላ ተቀምጦ እንደነበር፤ ሁኔታውም በጣም ነጭ ልብስ ለብሶ ፀጉሩ በጣም ጥቁር ሆኖ ሰው ተመስሎ መጥቶ ምንም አይነት የጉዞ አሻራ ያልታየበት እና ከሰሃቦች አንድም አላወቀውም ነበር፤ ከነብዩ (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ፊት ተቀምጦ ሁለቱን ጉልበቶቹን በነብዩ (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ደግፎ ሁለቱን እጆቹን ደግሞ ታፋዎቹ ላይ አድርጎ ከዚያም ነቢዩን ስለ እስልምና፣ ስለኢማን፣ ስለ ኢሕሳን፣ ሰዓቲቱንና ምልክቶቿንም በተመለከተ መጠየቁን፤ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለጥያቄዎቹ መልስ ከሰጡ በኋላ መሄዱን እና ከዚያም ነብዩም ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና)፡- “ይህ ጂብሪል ነው! ሃይማኖታችሁን ሊያስተምራችሁ መጥቶ ነው።" ማለታቸው በሐዲሥ የተዘገበ እውነት ነው።
ልክ እንደዚሁ አላህ ወደ ነብዩ ኢብራሂም እና ሉጥ (ዓለይሂማ ሰላም) የላካቸው መላእክቶችም የተላኩት በሰው መልክ ነበር።
አራተኛ፡- እኛን በተነገረን በአሏህ ፍቃድ ስለሚያደርጉት ተግባራቸው ማመን፤ ለምሳሌ፡ አላህን እንደሚያጠሩት እና ሳይሰለቻቸውና ሳይደክሙ ቀን ከሌት እሱን እንደሚያመልኩት ማመን ይጠበቅብናል።
አንዳንዶቹም ለየት ያለ ሃላፊነት ተሰጥቷቸው ያከናውናሉ።
ለምሳሌ፡ ጂብሪል የመለኮታዊ መገለጥ መልዕክትን የማድረስ ሃላፊነት የተሰጠው መልአክ ነው። አላህ ወደ ነብያትና መልእክተኞች የመመርያ መልዕክቱን አሲዞ የላከው እርሱን ነው።
ሌላኛው ምሳሌ፡- ሚካኤል ደሞ የዝናብና የዕፅዋት ኃላፊነት የተሰጠው መልአክ ነው።
ሌላኛው ምሳሌ፡ ኢስራፊል የሰዓቲቱ እና የትንሣኤ ቀን ቀንዱን የመንፋት ሃላፊነት የተሰጠው መልአክ ነው።
ሌላኛው ምሳሌ፡- የሞት መልአክ በሞት ጊዜ ነፍሳትን የመውሰድ ሃላፊነት የተሰጠው መልአክ ነው።
ሌላኛው ምሳሌ፡- ማሊክ በገሀነም እሳት ላይ የተሾመ መልአክ ነው፤ ጠባቂዋም እርሱ ነው።
ሌላው ምሳሌ፡- በእናቶች ማኅፀን ውስጥ ባለ ሽል ላይ ሃላፊነት የተሰጣቸው መላእክት፤ አንድ ፅንስ በእናቱ ማሕፀን ውስጥ አራት ወር ሲሞላው አላህ ወደ እርሷ መልአክን ይልካል፤ ያ መልአክም ሲሳዩን፣ ህይወቱን፣ ስራውን እና የጀነት እድለኛ ወይስ የጀሀንም እድለቢስ መሆኑን እንዲጽፍለት ያዘዋል።
ሌላው ምሳሌ፡- የሰዎችን ስራ እንዲመዘግቡ ሃላፊነት የተሰጣቸው መላእክት፤ እያንዳንዱ ሰው በቀኝ በኩል እና በግራ በኩል ሁለት መላእክት አሉት።
ሌላው ምሳሌ፡- ሙታን በመቃብራቸው ውስጥ ከገቡ በኋላ ሊጠይቁ ዘንድ ሃላፊነት የተሰጣቸው መላእክት፤ ሰው ከተቀበረ በኋላ ሁለት መላእክት ወደ ሟቹ መጥተው ስለ ጌታው፣ ስለ ሃይማኖቱ እና ስለ ነቢዩ ይጠይቁታል።
በመላእክት ማመን ትልልቅ ጥቅሞችን ያስገኛል፤ ከነዚህ መካከልም፡-
በመጀመሪያ: የአላህን ታላቅነት እና ኃያልነት ያስገነዝባል፤ የፍጡሩን ታላቅነት በመረዳት የፈጣሪውን ታላቅነት መረዳት ይቻላል።
ሁለተኛ፡- አላህ ለሰው ልጆች ባደረገው እንክብካቤ ምስጋናችንን እንድንጨምር ይረዳናል። እነዚያን ሃያል መላእክት የሰው ልጆችን በመጠበቅ፣ ስራዎቻቸውን በመመዝገብ እና የመሳሰሉትን በማድረግ የሰው አገልጋይ እንዲሆኑ አደረጋቸው።
ሦስተኛ፡- መላእክት ለላቀው አላህ ባላቸው አምልኮ ልንወዳቸው ዘንድ ይረዳናል።
አንዳንድ ያፈነገጡ ሰዎች መላእክት ፍጥረታት ውስጥ ያለው ድብቅ የጥሩ ኃይል ነው በማለት ራሳቸውን የቻሉ አካል መሆናቸውን ይክዳሉ። ይህ ሙግታቸው ግን ቁርኣንን፣ ሱናን እና በሙስሊሞች መካከል ያለውን ወጥ ስምምነት ማስተባበል ነው።
የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ جَاعِلِ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ رُسُلًا أُوْلِيٓ أَجۡنِحَةٖ مَّثۡنَىٰ وَثُلَٰثَ وَرُبَٰعَ...﴾
{ ምስጋና ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ፣ መላእክትን ባለ ሁለት ሁለት፣ ባለ ሶስት ሶስትም፣ ባለ አራት አራትም ክንፎች የኾኑ መልክተኞች አድራጊ ለኾነው አላህ ይገባው፡፡...} [ ፋጢር፡ 1 ]
የላቀው አሏሀ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذۡ يَتَوَفَّى ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَضۡرِبُونَ وُجُوهَهُمۡ وَأَدۡبَٰرَهُم...﴾
{እነዚያንም የካዱትን መላእክት ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን እየመቱ «የቃጠሎንም ስቃይ ቅመሱ» (እያሉ) በሚገድሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)፡፡ } [አል-አንፋል፡ 50]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿...وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذِ ٱلظَّٰلِمُونَ فِي غَمَرَٰتِ ٱلۡمَوۡتِ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ بَاسِطُوٓاْ أَيۡدِيهِمۡ أَخۡرِجُوٓاْ أَنفُسَكُمُۖ...﴾
{በደለኞችንም በሞት መከራዎች ውስጥ በኾኑ ጊዜ መላእክት እጆቻቸውን ዘርጊዎች ኾነው « (ለቅጥጥብ) ነፍሶቻችሁን አውጡ፤ ... » (የሚሏቸው ሲኾኑ) ብታይ ኖሮ (አስደናቂን ነገር ባየህ ነበር)} [አል-አንዓም፡ 93]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿...حَتَّىٰٓ إِذَا فُزِّعَ عَن قُلُوبِهِمۡ قَالُواْ مَاذَا قَالَ رَبُّكُمۡۖ قَالُواْ ٱلۡحَقَّۖ وَهُوَ ٱلۡعَلِيُّ ٱلۡكَبِيرُ﴾
{... ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጸም ጊዜ (ተማላጆቹ) «ጌታችሁ ምን አለ?» ይላሉ፡፡ (አማላጆቹ) «እውነትን አለ፤ እርሱም ከፍተኛው ታላቁ ጌታ ነው» ይላሉ፡፡} [ሰባእ፡ 23]
የጀነት ሰዎችን አስመልክቶም እንዲህ ብሏል፡
﴿...وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَدۡخُلُونَ عَلَيۡهِم مِّن كُلِّ بَابٖ 23 سَلَٰمٌ عَلَيۡكُم بِمَا صَبَرۡتُمۡۚ فَنِعۡمَ عُقۡبَى ٱلدَّارِ 24﴾
{... መላእክትም በእነርሱ ላይ ከየደጃፉ ሁሉ ይገባሉ። «ሰላም ለእናንተ ይኹን፡፡ (ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር!» (ይሏቸዋል)።}
[ረዕድ፡ 23-24]
ሶሒሕ ቡኻሪ ላይ ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ተላልፎ እንደተዘገበው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
«إِذَا أَحَبَّ اللَّهُ الْعَبْدَ نَادَى جِبْرِيلَ: إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ فُلَانًا فَأَحْبِبْهُ، فَيُحِبُّهُ جِبْرِيلُ، فَيُنَادِي جِبْرِيلُ فِي أَهْلِ السَّمَاءِ: إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ فُلَانًا فَأَحِبُّوهُ، فَيُحِبُّهُ أَهْلُ السَّمَاءِ، ثُمَّ يُوضَعُ لَهُ الْقَبُولُ فِي الْأَرْضِ».
«አላህ አንድን ባሪያ የወደደው ጊዜ ጂብሪልን ይጠራውና እንዲህ ይለዋል: "እኔ እከሌን እወደዋለሁና ውደደው።" ጂብሪልም ይወደዋል። ቀጥሎ ጂብሪል ሰማይ ውስጥ እንዲህ በማለት ይጣራል: "አላህ እከሌን ይወደዋልና ውደዱት።" የሰማይ ነዋሪዎችም ይወዱታል። ከዚያም ምድር ላይ ተቀባይነት ይኖረዋል።»
ቡኻሪ ላይ ባለ ሌላ ዘገባ አቡ ሁረይራህ ረዲየሏሁ ዓንሁ (አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና)) እንዲህ ብለዋል፡-
«إِذَا كَانَ يَوْمُ الْجُمُعَةِ كَانَ عَلَى كُلِّ بَابٍ مِنْ أَبْوَابِ الْمَسْجِدِ الْمَلَائِكَةُ يَكْتُبُونَ الْأَوَّلَ فَالْأَوَّلَ، فَإِذَا جَلَسَ الْإِمَامُ طَوَوْا الصُّحُفَ وَجَاءُوا يَسْتَمِعُونَ الذِّكْرَ».
«እለተ ጁሙዓ በሆነ ጊዜ መላኢካዎች በየመስጂዱ በር ላይ ሆነው ሰዎችን እንዳመጣጣቸው ቅደም ተከተል ይመዘግባሉ፤ ልክ ኢማሙ (ሚንበር ላይ) ሲቀመጡ መዝገቡን አጣጥፈው ተግሳፁን ለመስማት ይመጣሉ።»
እነዚህ ቁርአናዊና ሐዲሣዊ ጥቅሶች በግልፅ የሚያስረዱን መላዕክት አፈንጋጮቹ ከሚሉት በተቃራኒ ራሳቸውን የቻሉ አካላት መሆናቸውን ነው። ሙስሊሞችም በእነዚህ ጥቅሶች ትርጉም ላይ ወጥ በሆነ መልኩ ይስማማሉ።
በመጻሕፍቱ ማመን
"ኩቱብ" ወይም መጻሕፍቱ ስንል የ "ኪታብ" ወይም የመጽሐፍ ብዙ ቁጥር ነው። ትርጉሙም የተፃፈበት ማለት ነው።
እዚህ ላይ መፅሃፍት በመባል የተፈለጉት አላህ ለባርያዎቹ የመመሪያ ምንጫቸው ሆኖ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻው ዓለም ስኬትን ይጎናፀፉበት ዘንድ በመልእክተኞቹ በኩል በእዝነቱ ያወረደላቸውን መፃህፍት ለማለት ነው።
በመጻሕፍቱ ማመን አራት ነገሮችን ያጠቃልላል፡-
አንደኛ፡- በእውነት ከላቀው አላህ ዘንድ የወረዱ መሆናቸውን ማመን ነው።
ሁለተኛ፡ ስሞቻቸው ያወቅናቸውን መጽሐፎች በሚታወቀው ስማቸው ማመን፤ ልክ እንደ ቁርኣን ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና)) እንደወረደው፤ እንዲሁም ወደ ሙሳ (ዐለይሂ-ሰላም) እንደወረደላቸው ተውራትን ይመስል፤ ወደ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) የተወረደው ኢንጂልን ይመስል፤ ለዳውድ (ዐለይሂ-ሰላም) የተወረደው ዘቡርን ይመስል፤ ስማቸውን የማናውቃቸው መጻሕፍቶችን በተመለከተ ግን ስለነሱ በጥቅሉ እናምናለን።
ሦስተኛ፡ በውስጡ በተካተቱት ትክክለኛ መረጃዎች ማመን፤ ልክ በቁርኣን ውስጥ የተገለጸ መረጃ እና በቀደሙት ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያልተቀየረ ወይም ያልተዛባ መረጃ ካለ በዛው ማመን ይጠበቅብናል።
አራተኛ፡- ከነሱ ጀርባ ያለውን ጥበብ ተረዳንም አልተረዳን በውስጡ ያሉትን ፍርዶች እስካልተሻሩ ድረስ ወዶ መቀበል እና እጅ መስጠት ይጠበቅብናል። የተከበረው ቁርኣን የቀደሙትን ቅዱሳት መጻሕፍት በሙሉ ሽሯል።
﴿وَأَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ مُصَدِّقٗا لِّمَا بَيۡنَ يَدَيۡهِ مِنَ ٱلۡكِتَٰبِ وَمُهَيۡمِنًا عَلَيۡهِۖ...﴾
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡ {ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን።} [አል-ማኢዳህ፡ 48] (ተጠባባቂ ሲባል ማለትም በእርሱ ላይ ፈራጅ ነው።)
በዚህም መሰረት፡ በቀደሙት መጽሃፎች ውስጥ ከተቀመጡት ፍርዶች መካከል ጤናማ እና በቁርኣን ተቀባይነት ያላቸው ከሆኑት በስተቀር ማናቸውንም አንሰራባቸውም።
በመለኮታዊ መጽሐፍት ማመን ትልልቅ ጥቅሞችን ያስገኛል፤ ከነዚህም መካከል፡-
አንደኛ፡- አላህ ለሁሉም ማህበረሰብ መፅሃፍትን በመላኩ ለባሮቹ የሚያደርገውን ገደብ የለሽ እንክብካቤ ያስገነዝበናል።
ሁለተኛ፡- ለእያንዳንዱ ማህበረሰብ የሚመጥነውን ህግ በማውጣቱ በመመርያዎቹ ላይ የአላህን ጥበብ እንመለከታለን።
ልክ የላቀው አሏህ እንዲህ እንዳለን ማለት ነው፡
﴿...لِكُلّٖ جَعَلۡنَا مِنكُمۡ شِرۡعَةٗ وَمِنۡهَاجٗا...﴾
{ከእናንተ ለሁሉም ሕግንና መንገድን አደረግን።}
[አል-ማኢዳህ፡ 48]
ሦስተኛ፡ ለዚህም የላቀው አላህን ማመስገን ይጠበቅብናል።
በመልዕክተኞች ማመን
"ሩሱል" ወይም መልዕክተኞች ሲባል የ "ረሱል" ወይም መልዕክተኛ ብዙ ቁጥር ገላጭ ሲሆን ይህም መልእክት ለማስተላለፍ የተላከን ሰው ያመለክታል።
እዚህ ላይ መልዕክተኞች ሲባል የተፈለገበት አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ህግን አውርዶላቸው ለሰዎች እንዲያደርሱ ያዘዛቸውን ግለሰቦች ነው።
የመጀመሪያው መልእክተኛ ኑሕ (ዐለይሂ-ሰላም) ሲሆኑ የመጨረሻው ደግሞ ሙሐመድ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ናቸው።
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿ إِنَّآ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ كَمَآ أَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ نُوحٖ وَٱلنَّبِيِّـۧنَ مِنۢ بَعۡدِهِ...﴾
{እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን።} [አን-ኒሳእ፡ 163]
ሶሒሕ ቡኻሪይ ውስጥ በተዘገበ ምልጃን በተመለከተ ከአነስ ኢብኑ ማሊክ ረዲየሏሁ ዓንሁ (አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) በተላለፈ ሐዲሥ ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
«ذُكِرَ أَنَّ النَّاسَ يَأْتُونَ إِلَى آدَمَ؛ لِيَشْفَعَ لَهُمْ، فَيَعْتَذِرُ إِلَيْهِمْ وَيَقُولُ: ائْتُوا نُوحًا أَوَّلَ رَسُولٍ بَعَثَهُ اللَّهُ» وذكر تمام الحديث.
«ሰዎች ሊያማልዳቸው ዘንድ ወደ አደም ይመጣሉ፤ እሱም እንዲህ ብሎ ዑዝሩን ይናገራል፡ "የመጀመርያ መልዕክተኛ ወደሆነው ወደ ኑሕ ብትሄዱ ይሻላል።"» ቀጥሎም ሙሉውን ሐዲሥ ጠቀሱ
አላህ ስለ ነብዩ ሙሐመድ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብሏል፡-
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَآ أَحَدٖ مِّن رِّجَالِكُمۡ وَلَٰكِن رَّسُولَ ٱللَّهِ وَخَاتَمَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ...﴾
{ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው።} [አል-አሕዛብ፡ 40]
የላቀው አላህ መልእክተኛን ያልላከበት ወይም የቀድሞውን መልእክተኛ ሕግ እንዲያድስ ወሕይ አውርዶለት ነቢይ ያልላከበት ማህበረሰብ አልነበረም። የላቀው አሏህ እንዲህ ብላል፡-
﴿وَلَقَدۡ بَعَثۡنَا فِي كُلِّ أُمَّةٖ رَّسُولًا أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَٱجۡتَنِبُواْ ٱلطَّٰغُوتَ...﴾
{በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል።}
[አን-ነሕል፡ 36]
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿...وَإِن مِّنۡ أُمَّةٍ إِلَّا خَلَا فِيهَا نَذِيرٞ﴾
{ማንኛይቱም ሕዝብ በውስጧ አስፈራሪ ያላለፈባት የለችም።} [ፋጢር፡ 24]
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿إِنَّآ أَنزَلۡنَا ٱلتَّوۡرَىٰةَ فِيهَا هُدٗى وَنُورٞۚ يَحۡكُمُ بِهَا ٱلنَّبِيُّونَ ٱلَّذِينَ أَسۡلَمُواْ لِلَّذِينَ هَادُواْ...﴾
{እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትኾን አወረድን፡፡ እነዚያ ትዕዛዝን የተቀበሉት ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ።}
[አል-ማኢዳህ፡ 44]
መልእክተኞች ፍጡራን ሰዎች ናቸው። የጌትነት ይሁን የመለኮትነት ባህሪ የላቸውም። የመልእክተኞች ሁሉ አይነታና ከሁሉም ታላቅ ስለነበሩት ነብዩ ሙሐመድ የላቀው አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል፡-
﴿قُل لَّآ أَمۡلِكُ لِنَفۡسِي نَفۡعٗا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُۚ وَلَوۡ كُنتُ أَعۡلَمُ ٱلۡغَيۡبَ لَٱسۡتَكۡثَرۡتُ مِنَ ٱلۡخَيۡرِ وَمَا مَسَّنِيَ ٱلسُّوٓءُۚ إِنۡ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٞ وَبَشِيرٞ لِّقَوۡمٖ يُؤۡمِنُونَ 188﴾
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡ {«አላህ የሻውን በስተቀር ለእራሴ ጥቅምንም ጉዳትንም ማምጣት አልችልም፡፡ ሩቅንም (ምስጢር) የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር፡፡ እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» በላቸው፡፡ } [አል-አዕራፍ፡ 188]
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿قُلۡ إِنِّي لَآ أَمۡلِكُ لَكُمۡ ضَرّٗا وَلَا رَشَدٗا 21 قُلۡ إِنِّي لَن يُجِيرَنِي مِنَ ٱللَّهِ أَحَدٞ وَلَنۡ أَجِدَ مِن دُونِهِۦ مُلۡتَحَدًا 22﴾
{«እኔ ለእናንተ ጉዳትንም ቀጥታንም አልችልም» በላቸው፡፡ «እኔ ከአላህ (ቅጣት) አንድም አያድነኝም፡፡ ከእርሱም ሌላ መጠጊያን አላገኝም» በላቸው፡፡}
[አል-ጂን፡ 21-22]
ሰው የሚገጥመው ሁሉ ይገጥማቸዋል መታመም፣ መሞት፣ ምግብና መጠጥም ያስፈልጋቸዋል። ነቢዩ ኢብራሂም (ዐለይሂ-ሰላም) ጌታውን ሲገልፅ እንዲህ ብሏል፡-
﴿وَٱلَّذِي هُوَ يُطۡعِمُنِي وَيَسۡقِينِ 79 وَإِذَا مَرِضۡتُ فَهُوَ يَشۡفِينِ 80 وَٱلَّذِي يُمِيتُنِي ثُمَّ يُحۡيِينِ 81﴾
{«ያም እርሱ የሚያበላኝና የሚያጠጣኝ ነው። በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል። «ያም የሚገድለኝ ከዚያም ሕያው የሚያደርገኝ ነው።»} [አሽ-ሹዓራእ፡ 79-81]
ነቢዩም ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡
«إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِثْلُكُمْ، أَنْسَى كَمَا تَنْسَوْنَ، فَإِذَا نَسِيتُ فَذَكِّرُونِي».
«እኔ እንደናንተው ሰው ስለሆንኩ እናንተ እንደምትረሱት ሁሉ እኔም ልረሳ እችላለሁና ስረሳ አስታውሱኝ።»
የላቀው አላህ እነርሱን በከፍተኛ ማዕረጋቸው ላይ ሁነው ሲገልፃቸው ነብዮቹን ለሱ ባላቸው ባርነት ነው የገለፃቸው። የላቀው አሏህ ኑሕ ዓለይሂ ሰላምን ሲገልፃቸው እንዲህ ብሏል፡
﴿...إِنَّهُۥ كَانَ عَبۡدٗا شَكُورٗا﴾
{እርሱ በብዙ አመስጋኝ ባርያ ነበርና።} [አል-ኢስራእ፡ 3] የላቀው አሏህ ነቢዩ ሙሐመድን ሲገልፃቸው እንዲህ ብሏል፡
﴿تَبَارَكَ ٱلَّذِي نَزَّلَ ٱلۡفُرۡقَانَ عَلَىٰ عَبۡدِهِۦ لِيَكُونَ لِلۡعَٰلَمِينَ نَذِيرًا 1﴾
{ ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ያወረደው (አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው፡፡ }
[አል-ፉርቃን፡ 1]
የላቀው አሏህ ኢብራሂምን፣ ኢስሐቅን እና የዕቁብን ሶለሏሁ ዓለይሂም ወሰለም ሲገልፃቸው ደሞ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَٱذۡكُرۡ عِبَٰدَنَآ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ أُوْلِي ٱلۡأَيۡدِي وَٱلۡأَبۡصَٰرِ 45 إِنَّآ أَخۡلَصۡنَٰهُم بِخَالِصَةٖ ذِكۡرَى ٱلدَّارِ 46 وَإِنَّهُمۡ عِندَنَا لَمِنَ ٱلۡمُصۡطَفَيۡنَ ٱلۡأَخۡيَارِ 47﴾
{ባሮቻችንንም ኢብራሂምን፣ ኢስሐቅንና ያዕቆብንም፣ የኅይልና የማስተዋል ባለቤቶች የኾኑን አውሳላቸው፡፡ እኛ ጥሩ በኾነች ጠባይ መረጥናቸው፡፡ (እርሷም) የመጨረሻይቱን አገር ማስታወስ ናት፡፡ እነርሱም እኛ ዘንድ ከመልካሞቹ ምርጦች ናቸው።} [ሷድ፡ 45-47]
ነቢዩሏህ ዒሳን ሲገልፃቸውም እንዲህ ብሏል፡
﴿إِنۡ هُوَ إِلَّا عَبۡدٌ أَنۡعَمۡنَا عَلَيۡهِ وَجَعَلۡنَٰهُ مَثَلٗا لِّبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ 59﴾
{ እርሱ በርሱ ላይ የለገስንለት ለእስራኤለም ልጆች ተዓምር ያደረግነው የኾነ ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም።}
[አዝ-ዙኽሩፍ፡ 59]
በመልዕክተኞች ማመን አራት ነገሮችን ያጠቃልላል።
አንደኛ፡- መልእክታቸው በእውነት ከአላህ ዘንድ የመጣ መሆኑን ማመን፤ በአንዱም መልእክት የሚክድ ሰው በሁላቸውም መልዕክት ክዷል። ልክ የላቀው አሏህ እንዲህ እንዳለን፡
﴿كَذَّبَتۡ قَوۡمُ نُوحٍ ٱلۡمُرۡسَلِينَ 105﴾
{የኑሕ ሕዝቦች መልክተኞችን አስተባበሉ።} [አሽ-ሹዓራእ፡ 105] የተላከላቸው ኑሕ ብቻ ከመሆኑም ጋር እሱን ማስተባበላቸውን መልዕክተኞችን ሁሉ እንደማስተባበል ተቆጠረ። በዚህም መሰረት ሙሐመድን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያልተከተሉት ክርስቲያኖችም በተላከላቸው የመርየም ልጅ ዒሳም ክደዋል፤ ዒሳንም አልተከተሉትም። በተለይም የነቢዩ ሙሐመድን መምጣት ዒሳም አበስሯቸው የነበረ ከመሆኑም ጋር፤ ይሀውም ዒሳ ያበሰራቸው መልዕክተኛው ሙሐመድ በመጡ ጊዜ ከጥመት የሚያድናቸውና ወደ ቀጥተኛው መንገድ የሚመራቸው መልእክተኛ ሆኖ ስለሚላክላቸው ነው።
ሁለተኛ፡ እንደ ሙሐመድ፣ ኢብራሂም፣ ሙሳ፣ ዒሳ እና ኑሕ (ዐለይሂሙ -ሰላም) ያሉት ስሞቻቸው የተነገረንን በስሞቻቸው ለይተን ማመን ይጠበቅብናል። እነዚህ አምስቱ በቁርኣን የቆራጥነት ባለቤት በሚል አሏህ ሁለት ቦታዎች ላይ ለይቶ እንዲህ ብሎ የጠቀሳቸው መልእክተኞች ናቸው፡
﴿وَإِذۡ أَخَذۡنَا مِنَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ مِيثَٰقَهُمۡ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٖ وَإِبۡرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ٱبۡنِ مَرۡيَمَۖ وَأَخَذۡنَا مِنۡهُم مِّيثَٰقًا غَلِيظٗا 7﴾
{ከነቢዮችም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም ከመርየም ልጅ ዒሳም በያዝን ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን።} [አል-አሕዛብ፡ 7]
እንዲህም ብሏል፡
﴿شَرَعَ لَكُم مِّنَ ٱلدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِۦ نُوحٗا وَٱلَّذِيٓ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ وَمَا وَصَّيۡنَا بِهِۦٓ إِبۡرَٰهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰٓۖ أَنۡ أَقِيمُواْ ٱلدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُواْ فِيهِۚ كَبُرَ عَلَى ٱلۡمُشۡرِكِينَ مَا تَدۡعُوهُمۡ إِلَيۡهِۚ ٱللَّهُ يَجۡتَبِيٓ إِلَيۡهِ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِيٓ إِلَيۡهِ مَن يُنِيبُ 13﴾
{ ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን)፡፡ በአጋሪዎቹ ላይ ያ ወደርሱ የምትጠራቸው ነገር ከበዳቸው፡፡ አላህ የሚሻውን ሰው ወደእርሱ (እምነት) ይመርጣል፡፡ የሚመለስንም ሰው ወደርሱ ይመራል።} [አሽ-ሹራ፡ 13]
ስማቸው የማናውቃቸውን ደሞ ስለ እነርሱ በተነገረን ልክ እንዲሁ በጥቅሉ እናምናለን። ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا رُسُلٗا مِّن قَبۡلِكَ مِنۡهُم مَّن قَصَصۡنَا عَلَيۡكَ وَمِنۡهُم مَّن لَّمۡ نَقۡصُصۡ عَلَيۡكَۗ...﴾
{ካንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ ባንተ ላይ የተረክንልህ አልለ፡፡ ከእነርሱም ባንተ ላይ ያልተረክነው አልለ።} [ጋፊር፡ 78]
ሦስተኛ፡ በትክክል ከእነርሱ እንደመጣ የተረጋገጠን መረጃ አምኖ መቀበል።
አራተኛ፡- በተላከልን ሸሪዓ መስራት፤ ከመካከላቸው ወደ እኛ የተላከልን የመጨረሻው ነብይ የሙሐመድ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ሸሪዓ ነው። የተላኩትም ለመላው የሰው ልጆች ሁሉ ነው። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤۡمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيۡنَهُمۡ ثُمَّ لَا يَجِدُواْ فِيٓ أَنفُسِهِمۡ حَرَجٗا مِّمَّا قَضَيۡتَ وَيُسَلِّمُواْ تَسۡلِيمٗا 65﴾
{በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም፤ (ምእመን አይኾኑም)።} [አን-ኒሳእ፡ 65]
በመልክተኞች ማመን ትልልቅ ፋይዳዎችን ያስገኛል፡ ከነዚህም መካከል፡-
አንደኛ፡- ባሮቹ ወደ ቀጥተኛው መንገድ እንዲመሩና ጌታቸውን እንዴት እንደሚያመልኩ እንዲያሳዩ መልእክተኞችን መላኩ አላህ ለባሮቹ የሚያደርገውን እዝነት እና እንክብካቤ ያስረዳናል። የሰው ልጆች አእምሮ በራሱ ጊዜ ይህንን እውቀት ተመራምሮ ሊደርስበት አይችልም።
ሁለተኛ፡- ለዚህ ለዋለልን ታላቅ ፀጋ ልናመሰግነው እንደሚገባ እንረዳለን።
ሦስተኛ፡- መልእክተኞችን መውደድ፣ ማክበርና በሚገባቸው ልክ ማመስገን እንደሚገባ እንረዳለን። ምክንያቱም የአላህ መልእክተኞች በመሆናቸውና እርሱን በማምለክ፣ መልእክቱን የማድረስና ለባሮቹም ቅን ምክር የመስጠት ሃላፊነትን ስለተወጡ ነው።
አፈንጋጮች የአላህ መልእክተኞች ሰው መሆን የለባቸውም ብለው መልእክተኞቻቸውን ክደዋል። አላህ ግን ይህን ቃላቸውን ጠቅሶ እንዲህ በሚል ውድቅ አድርጎታል፡-
﴿وَمَا مَنَعَ ٱلنَّاسَ أَن يُؤۡمِنُوٓاْ إِذۡ جَآءَهُمُ ٱلۡهُدَىٰٓ إِلَّآ أَن قَالُوٓاْ أَبَعَثَ ٱللَّهُ بَشَرٗا رَّسُولٗا94 قُل لَّوۡ كَانَ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَلَٰٓئِكَةٞ يَمۡشُونَ مُطۡمَئِنِّينَ لَنَزَّلۡنَا عَلَيۡهِم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ مَلَكٗا رَّسُولٗا 95﴾
{ ሰዎችንም መሪ (ቁርኣን) በመጣላቸው ጊዜ ከማመን «አላህ ሰውን መልክተኛ አድርጎ ላከን» ማለታቸው እንጂ ሌላ አልከለከላቸውም። «በምድር ላይ ረግተው የሚኼዱ መላእክት በነበሩ ኖሮ በእነሱ ላይ (ከጎሳቸው) የመልአክን መልክተኛ ባወረድን ነበር» በላቸው።}
[አል-ኢስራእ፡ 94 - 95]
ስለዚህም የላቀው አላህ መልእክተኛውን የምድር ነዋሪዎች ወደሆኑት ሰዎች የሚልከው እንደራሳቸው ሰዎች መሆናቸውን በመናገር የነሱን ሙግት ውድቅ አደረገው። የምድር ነዋሪዎች መላኢኮች ቢሆኑ ኖሮ ነበር አላህም ለነዋሪዎቹ እንደነሱ እንዲሆን መላእክትን መልዕክተኛ አድርጎ ይልክላቸው የነበረው። መልዕክተኞቻቸውን የካዱ ሰዎች እንዲህ ማለታቸው በቁርኣን ውስጥ እንዲሁ ተተርኳል፡-
﴿...إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُنَا تُرِيدُونَ أَن تَصُدُّونَا عَمَّا كَانَ يَعۡبُدُ ءَابَآؤُنَا فَأۡتُونَا بِسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٖ 10 قَالَتۡ لَهُمۡ رُسُلُهُمۡ إِن نَّحۡنُ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَمُنُّ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦۖ وَمَا كَانَ لَنَآ أَن نَّأۡتِيَكُم بِسُلۡطَٰنٍ إِلَّا بِإِذۡنِ ٱللَّهِ...﴾
{(ሕዝቦቹም) «እናንተ ብጤያችን ሰው እንጂ አይደላችሁም አባቶቻችን ይገዙት ከነበሩት ልትከለክሉን ትሻላችሁ፡፡ ግልጽንም አስረጅ (ካመጣችሁት ሌላ) አምጡልን» አሉ። መልክተኞቻቸው ለእነርሱ አሉ «እኛ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለንም ግን አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ይለግሳል፡፡ ለእኛም በአላህ ፈቃድ እንጂ ማስረጃን ልናመጣላችሁ አይገባንም፡፡ በአላህም ላይ ምእምናኖች ይጠጉ።} [ኢብራሂም፡ 10-11]
በመጨረሻው ቀን ማመን
የመጨረሻው ቀን፡ የመጨረሻው ቀን ሰዎች ለሂሳብና ለምንዳ የሚቀሰቀሱበት የፍርዱ ቀን ነው።
እንደዛ ተብሎ የተሰየመውም ከዛ በኋላ ምንም ቀን ስለማይኖር ነው። የጀነት ሰዎች ዘላለማቸውን በስፍራቸው ይሰፍራሉ፤ የእሳት ጓዶችም ዘላለማቸውን እንዲሁ በጀሀነም ይሰፍራሉ።
በመጨረሻው ቀን ማመን ሶስት ነገሮችን ያጠቃልላል።
አንደኛ፡- ለሁለተኛ ጊዜ ጥሩንባው ሲነፋ ሙታን እንደገና ወደ ሕይወት እንደሚመለሱ በትንሣኤ ማመን ነው። ከዚያም ሰዎች ራቁታቸውን፣ ባዶ እግራቸውን እና ያልተገረዙ ሆነው በዓለማት ጌታ ፊት ይነሣሉ። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿...كَمَا بَدَأۡنَآ أَوَّلَ خَلۡقٖ نُّعِيدُهُۥۚ وَعۡدًا عَلَيۡنَآۚ إِنَّا كُنَّا فَٰعِلِينَ﴾
{የመጀመሪያን ፍጥረት እንደ ጀመርን እንመልሰዋለን፡፡ (መፈጸሙ) በእኛ ላይ የኾነን ቀጠሮ ቀጠርን፡፡ እኛ (የቀጠርነውን) ሠሪዎች ነን።} [አል-አንቢያእ፡ 104]
ከሞት መነሳት ቁርአንም ሐዲሥም ያመላከተው መላው ሙስሊም ዘንድም ወጥ ስምምነት ያለበት እውነት ነው።
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿ثُمَّ إِنَّكُم بَعۡدَ ذَٰلِكَ لَمَيِّتُونَ 15 ثُمَّ إِنَّكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ تُبۡعَثُونَ 16﴾
{ከዚያም እናንተ ከዚህ በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ። ከዚያም እናንተ በትንሣኤ ቀን ትቀሰቀሳላችሁ።}
[አል-ሙእሚኑን፡ 15-16]
ነብዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
«يُحْشَرُ النَّاسُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ حُفَاةً عُرَاةً غُرْلًا».
“ሰዎች በቂያማ ቀን በባዶ እግራቸው፣ ራቁታቸውንና ሳይገረዙ ይነሳሉ.” [ቡኻሪይና ሙስሊም ዘግበውታል]
ሙስሊሞች በሙሉ የመጨረሻው ቀን እውነት መሆኑን አምነውበታል (ተስማምተውበታል)። ሎጂክም የሚያስፈርደው እውነታ ነው። የላቀው አላህ መልእክተኞቹን የላከበት ለሆነው መመርያው ሰዎቹ በሰጡት ምላሽ መሰረት ምንዳቸውን ሊመነዳቸው ዘንድ ይህንን ቀነ ቀጠሮ ማድረጉ ሎጂካል ነው። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿أَفَحَسِبۡتُمۡ أَنَّمَا خَلَقۡنَٰكُمۡ عَبَثٗا وَأَنَّكُمۡ إِلَيۡنَا لَا تُرۡجَعُونَ 115﴾
{«የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን አሰባችሁን?» (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን?)} [አል-ሙእሚኑን፡ 115] ለነቢዩም ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብሏቸዋል:
﴿إِنَّ ٱلَّذِي فَرَضَ عَلَيۡكَ ٱلۡقُرۡءَانَ لَرَآدُّكَ إِلَىٰ مَعَادٖ...﴾
{ያ ቁርኣንን የተከፋፈለ ኾኖ ባንተ ላይ ያወረደው (አምላክ) ወደ መመለሻ (ወደመካ) በእርግጥ መላሽህ ነው።} [አል-ቀሶስ፡ 85]
ሁለተኛ፡ በሂሳብ እና በምንዳ ማመን ይጠበቅብናል፤ ሁሉም ሰው ለሰራው ስራ ተጠያቂ ይሆናል፤ ይመነዳበታልም። ይህም ቁርኣን እና ሐዲሥ የሚያመለክቱትና እንዲሁም በሙስሊሞች ወጥ ስምምነትም ጭምር የፀና ነው።
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿إِنَّ إِلَيۡنَآ إِيَابَهُمۡ 25 ثُمَّ إِنَّ عَلَيۡنَا حِسَابَهُم 26﴾
{መመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው። ከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው።} [አል-ጋሺያህ፡ 25 - 26]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿مَن جَآءَ بِٱلۡحَسَنَةِ فَلَهُۥ عَشۡرُ أَمۡثَالِهَاۖ وَمَن جَآءَ بِٱلسَّيِّئَةِ فَلَا يُجۡزَىٰٓ إِلَّا مِثۡلَهَا وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ 160﴾
{በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ } [አል-አንዓም፡ 160]
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَنَضَعُ ٱلۡمَوَٰزِينَ ٱلۡقِسۡطَ لِيَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ فَلَا تُظۡلَمُ نَفۡسٞ شَيۡـٔٗاۖ وَإِن كَانَ مِثۡقَالَ حَبَّةٖ مِّنۡ خَرۡدَلٍ أَتَيۡنَا بِهَاۗ وَكَفَىٰ بِنَا حَٰسِبِينَ 47﴾
{በትንሣኤም ቀን ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም፡፡ (ሥራው) የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢኾንም እርሷን እናመጣታለን፡፡ ተቆጣጣሪዎችም በኛ በቃ።} [አል-አንቢያእ፡ 47]
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
«إِنَّ اللَّهَ يُدْنِي الْمُؤْمِنَ، فَيَضَعُ عَلَيْهِ كَنَفَهُ - أَيْ سَتْرَهُ - وَيَسْتُرُهُ: فَيَقُولُ: أَتَعْرِفُ ذَنْبَ كَذَا؟ أَتَعْرِفُ ذَنْبَ كَذَا؟ فَيَقُولُ: نَعَمْ أَيْ رَبِّ، حَتَّى إِذَا قَرَّرَهُ بِذُنُوبِهِ، وَرَأَى فِي نَفْسِهِ أَنَّهُ هَلَكَ قَالَ: سَتَرْتُهَا عَلَيْكَ فِي الدُّنْيَا وَأَنَا أَغْفِرُهَا لَكَ الْيَوْمَ، فَيُعْطَى كِتَابَ حَسَنَاتِهِ، وَأَمَّا الْكُفَّارُ وَالْمُنَافِقُونَ فَيُنَادَى بِهِمْ عَلَى رُؤُوسِ الْخَلَائِقِ: هَؤُلَاءِ الَّذِينَ كَذَبُوا عَلَى رَبِّهِمْ، أَلَا لَعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ».
«አማኝ የትንሳኤ ቀን ወደ ጌታው ይቀርባል። አላህም በመሸፈኛ ይከልለውና ወንጀሎቹን እያሳየ "ይህንን ወንጀልህን አወቅከውን?" "ይህኛውን ወንጀልህንስ አወቅከውን?" ይለዋል። እርሱም "ጌታዬ አውቄዋለሁ።" እያለ እያመነ አለቀልኝ የሚል ስጋት ውስጥ እስኪገባ ወንጀሎቹን ያሳየዋል። አላህም "እኔ በዱንያ ውስጥ ሳለህ እንደሸሸግኩልህ ሁሉ ዛሬም ደግሞ ላንተ እምርሃለሁ።" ይለዋል። የመልካም ስራ መጽሐፉም ይሰጠዋል። ከሀዲዎችና ሙናፊቆች ግን በፍጡራን መካከል ይጠሩና "እነዚህ በአላህ ላይ ያስተባበሉ ናቸው የአሏህ እርግማን በግፈኞች ላይ ይሁን! ይባላሉ።» ቡኻሪይና ሙስሊም ዘግበውታል
ነብዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
«أَنَّ مَنْ هَمَّ بِحَسَنَةٍ فَعَمِلَهَا؛ كَتَبَهَا اللَّهُ عِنْدَهُ عَشْرَ حَسَنَاتٍ إِلَى سَبْعِ مِئَةِ ضِعْفٍ إِلَى أَضْعَافٍ كَثِيرَةٍ، وَأَنَّ مَنْ هَمَّ بِسَيِّئَةٍ فَعَمِلَهَا؛ كَتَبَهَا اللَّهُ سَيِّئَةً وَاحِدَةً».
"አንድ ሰው መልካምን ቢያስብና ቢሰራው አላህ ያችን ስራውን በአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ድረስ በመልካም ስራዎች አባዝቶ ይጽፍለታል። መጥፎ ስራ ቢያስብና ቢሰራው ደግሞ አላህ እንደአንድ መጥፎ ስራ ብቻ አድርጎ ይጽፍለታል።"
ሁሉም ሙስሊሞች ሂሳብና ምንዳ እንዳለ የጋራ ስምምነት አላቸው። አላህ መፅሃፎችን አውርዷል፣ መልእክተኞችን ልኳል፣ ባሪያዎቹ ደሞ መልእክተኞች ያመጡላቸዉን መመርያ እንዲቀበሉ እና እንዲተገብሩ ግዴታ ያደረገ እንደመሆኑ፤ አፈንጋጮችንም መፋለም ግድ እንደሆነ፣ ደማቸውም፣ ዝርያቸውም፣ ሴቶቻቸውም ገንዘባቸውም ሐላል እንደሚሆን ይፋ ከማድረጉ አኳያ መመርያውን የተገበረውና ያፈነገጠው እኩል አይሆንምና የሂሳብና የምንዳ ቀን መኖሩ ሎጂካል ነው። ሒሳብና ምንዳ ባይኖር ኖሮ ይህ ሁሉ መመርያ ከንቱ ላግጣ ይሆን ነበር፤ ጥበበኛው ጌታችን ደሞ ከዚህ የጠራ ነው። አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ይህንን አስመልክቶ እንዲህ ብሏል፡-
﴿فَلَنَسۡـَٔلَنَّ ٱلَّذِينَ أُرۡسِلَ إِلَيۡهِمۡ وَلَنَسۡـَٔلَنَّ ٱلۡمُرۡسَلِينَ 6 فَلَنَقُصَّنَّ عَلَيۡهِم بِعِلۡمٖۖ وَمَا كُنَّا غَآئِبِينَ 7﴾
{እነዚያንም ወደነሱ የተላከባቸውን (ሕዝቦች) መልክተኞቹንም በእርግጥ እንጠይቃለን። በእነርሱም ላይ (የነበሩበትን ሁሉ) ከዕውቀት ጋር በእርግጥ እንተርክላቸዋለን፡፡ የራቅንም አልነበርንም።}
[አል-አዕራፍ፡ 6-7]
ሦስተኛ፡- በጀነት እና በጀሀነም እነሱም የፍጡር ዘላለማዊ መኖሪያ መሆናቸውን ማመን ይጠበቅብናል።
ጀነት አላህ እንዲያምኑ ባዘዛቸው ነገር ላመኑ፣ አላህን ለታዘዙ እና በቅንነት ላመለኩ፣ መልእክተኛውን ለታዘዙ እና ለተከተሉ ደጋግ ምእመናኑ ያዘጋጃት የድሎት መኖርያ ናት። በውስጧም
«مَا لَا عَيْنٌ رَأَتْ، وَلَا أُذُنٌ سَمِعَتْ، وَلَا خَطَرَ عَلَى قَلْبِ بَشَرٍ».
“ዐይን ያላየው፣ ጆሮ ያልሰማው፣ የሰው አእምሮ ያላሰበውን” የደስታ ዓይነቶችን ሁሉ ይዛለች። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أُوْلَٰٓئِكَ هُمۡ خَيۡرُ ٱلۡبَرِيَّةِ 7 جَزَآؤُهُمۡ عِندَ رَبِّهِمۡ جَنَّٰتُ عَدۡنٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۖ رَّضِيَ ٱللَّهُ عَنۡهُمۡ وَرَضُواْ عَنۡهُۚ ذَٰلِكَ لِمَنۡ خَشِيَ رَبَّهُۥ 8﴾
{እነዚያ ያመኑትና መልካሞችንም የሠሩት፣ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ በላጭ ናቸው። በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች ነው፡፡ በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ (ይገቡባቸዋል)፡፡ አላህ ከእነርሱ ወደደ፡፡ ከእርሱም ወደዱ፡፡ ይህ ጌታውን ለፈራ ሰው ነው።} [አል-በይናህ፡ 7-8]
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿فَلَا تَعۡلَمُ نَفۡسٞ مَّآ أُخۡفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعۡيُنٖ جَزَآءَۢ بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ 17﴾
{ ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም.} [አስ-ሰጅዳህ፡ 17]
ጀሀነም ደግሞ አላህ በእርሱ ለካዱ እና መልእክተኞቹንም ላመፁ ወሰን አላፊ ለሆኑ ከሓዲዎች ያዘጋጃት የስቃይ መኖርያ ናት። በአዕምሮ ሊታሰብ የማይችልን የቅጣት እና የስቃይ አይነትን ሁሉ ይዛለች።
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَٱتَّقُواْ ٱلنَّارَ ٱلَّتِيٓ أُعِدَّتۡ لِلۡكَٰفِرِينَ 131﴾
{ያችንም ለከሓዲዎች የተደገሰችውን እሳት ተጠንቀቁ።} [አሊ-ዒምራን፡ 131]
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَقُلِ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكُمۡۖ فَمَن شَآءَ فَلۡيُؤۡمِن وَمَن شَآءَ فَلۡيَكۡفُرۡۚ إِنَّآ أَعۡتَدۡنَا لِلظَّٰلِمِينَ نَارًا أَحَاطَ بِهِمۡ سُرَادِقُهَاۚ وَإِن يَسۡتَغِيثُواْ يُغَاثُواْ بِمَآءٖ كَٱلۡمُهۡلِ يَشۡوِي ٱلۡوُجُوهَۚ بِئۡسَ ٱلشَّرَابُ وَسَآءَتۡ مُرۡتَفَقًا 29﴾
{«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ» በላቸው፡፡ እኛ ለበደለኞች አጥሯ በእነሱ የከበበ የኾነችውን እሳት አዘጋጅተናል፡፡ (ከጥም) እርዳታንም ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ፡፡ መጠጡ ከፋ! መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች! } [አል-ከህፍ፡ 29]
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿إِنَّ ٱللَّهَ لَعَنَ ٱلۡكَٰفِرِينَ وَأَعَدَّ لَهُمۡ سَعِيرًا 64 خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۖ لَّا يَجِدُونَ وَلِيّٗا وَلَا نَصِيرٗا 65 يَوۡمَ تُقَلَّبُ وُجُوهُهُمۡ فِي ٱلنَّارِ يَقُولُونَ يَٰلَيۡتَنَآ أَطَعۡنَا ٱللَّهَ وَأَطَعۡنَا ٱلرَّسُولَا۠66﴾
{ አላህ ከሓዲዎችን በእርግጥ ረግሟቸዋል፡፡ ለእነርሱም የተጋጋመችን እሳት አዘጋጅቷል። በእርሷ ውስጥ ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ፤ ወዳጅም ረዳትም አያገኙም። ፊቶቻቸው በእሳት ውሰጥ በሚገለባበጡ ቀን «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ» እያሉ ይጸጸታሉ።} [አል-አሕዛብ 64 - 66]
በመጨረሻው ቀን ማመን የሚያስገኛቸው በርከት ያሉ ፋይዳዎች አሉት፡ ከነዚህ መካከልም፡
አንደኛ፡- የዚያን ቀን ምንዳ ፍለጋ በጎ ነገር የመስራት መነሳሳትና ጉጉትን ይፈጥራል።
ሁለተኛ፡- የዚያን ቀን ቅጣትና ስቃይን በመፍራትና በመስጋት ኃጢአት ከመሥራትና ኃጢአትን ከመውደድ መታቀብን ያላብሳል።
ሦስተኛ፡- በመጨረሻው ዓለም ደስታን እና መልካም ምንዳን የማግኘት ተስፋ በዚህ አለም ራሱ አንዳንድ ዓለማዊ ውድቀቶች ሲከሰቱ ማጽናኛ ይሆናል።
ከሓዲዎች ከሞት በኋላ ያለውን ትንሣኤ የማይሆን ነገር ነው በሚል ሙግት ይክዱታል።
ይህ ሙግታቸው ግን ሸሪዓም፣ ህዋሳዊ ግንዛቤም ይሁን አዕምሮ ውድቅ የሚያደርገው ጉዳይ ነው።
እንደሸሪዓ የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏልና ነው፡
﴿زَعَمَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَن لَّن يُبۡعَثُواْۚ قُلۡ بَلَىٰ وَرَبِّي لَتُبۡعَثُنَّ ثُمَّ لَتُنَبَّؤُنَّ بِمَا عَمِلۡتُمۡۚ وَذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٞ 7﴾
{ እነዚያ የካዱትን በፍጹም የማይቀሰቀሱ መኾናቸውን አሰቡ፡፡ «አይደለም በጌታዬ እምላለሁ፡፡ በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ፡፡ ከዚያም በሠራችሁት ሁሉ ትነገራላችሁ፡፡ ይህም በአላህ ላይ ቀላል ነው፡፡» በላቸው።} [አት-ተጋቡን፡ 7] ይህ ጉዳይ ሁሉም መለኮታዊ መፃህፍት ሙሉ ለሙሉ የተስማሙበት ነገር ነው።
ህዋሳዊ ማስረጃው፡- አላህ ከባሮቹ የተወሰኑትን ሙታንን ወደ ሕይወት ሲመለሱ እንዲያዩ አድርጓል። ለዚህም በሱረቱል በቀራህ ውስጥ ብቻ አምስት ምሳሌዎች አሉ።
የመጀመርያው ምሳሌ፡- የሙሳ ህዝቦች እንዲህ ባሉት ጊዜ፡
﴿...لَن نُّؤۡمِنَ لَكَ حَتَّىٰ نَرَى ٱللَّهَ جَهۡرَةٗ ...﴾
{«ሙሳ ሆይ! አላህን በግልጽ እስከምናይ ድረስ ላንተ በፍጹም አናምንልህም»} [አልበቀራህ፡ 55] አላህም ገደላቸውና ከዚያም መልሶ ሕያው አደረጋቸው። በዚህ ጉዳይ አላህ የእስራኤል ልጆችን እንዲህ ሲል ያናግራቸዋል፡-
﴿وَإِذۡ قُلۡتُمۡ يَٰمُوسَىٰ لَن نُّؤۡمِنَ لَكَ حَتَّىٰ نَرَى ٱللَّهَ جَهۡرَةٗ فَأَخَذَتۡكُمُ ٱلصَّٰعِقَةُ وَأَنتُمۡ تَنظُرُونَ 55 ثُمَّ بَعَثۡنَٰكُم مِّنۢ بَعۡدِ مَوۡتِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ 56﴾
{«ሙሳ ሆይ! አላህን በግልጽ እስከምናይ ድረስ ላንተ በፍጹም አናምንልህም» ባላችሁም ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ እናንተም እየተመለከታችሁ መብረቅ ያዘቻችሁ። ከዚያም ታመሰግኑ ዘንድ ከሞታችሁ በኋላ አስነሳናችሁ።} [አል-በቀራህ፡ 55-56]
ሁለተኛ፡ የእስራኤል ልጆች የተከራከሩበት ሟችን የሚገልፀው ታሪክ ላይ ነው። የላቀው አላህ ላም እንዲያርዱና በላሚቱ ከፊል አካልም ሟችን እንዲመቱትና ሟችም ተነስቶ ማን እንደገደለው እንደሚነግራቸው አዘዛቸው። ይህንንም በተመለከት የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَإِذۡ قَتَلۡتُمۡ نَفۡسٗا فَٱدَّٰرَٰءۡتُمۡ فِيهَاۖ وَٱللَّهُ مُخۡرِجٞ مَّا كُنتُمۡ تَكۡتُمُونَ 72 فَقُلۡنَا ٱضۡرِبُوهُ بِبَعۡضِهَاۚ كَذَٰلِكَ يُحۡيِ ٱللَّهُ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَيُرِيكُمۡ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ 73﴾
{ ነፍስነም በገደላችሁና በርሷም (ገዳይ) በተከራከራችሁ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ አላህም ትደብቁት የነበራችሁትን ሁሉ ገላጭ ነው። «(በድኑን) በከፊሏም ምቱት» አልን፤ እንደዚሁ አላህ ሙታንን ያስነሳል፤ ታውቁም ዘንድ ታምራቶችን ያሳያችኋል።} [አል-በቀራህ፡ 72-73]
ሦስተኛ፡- ሞትን ፍራቻ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሆነው ቤታቸውን ትተው የሸሹ ሰዎች ታሪክ ላይ ነው። የላቀው አላህም እንዲሞቱ ካደረጋቸው በኋላ እንደገና ሕያው አደረጋቸው። ይህንንም በተመለከት አሏህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ خَرَجُواْ مِن دِيَٰرِهِمۡ وَهُمۡ أُلُوفٌ حَذَرَ ٱلۡمَوۡتِ فَقَالَ لَهُمُ ٱللَّهُ مُوتُواْ ثُمَّ أَحۡيَٰهُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَذُو فَضۡلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشۡكُرُونَ243﴾
{ ወደ እነዚያ እነርሱ ብዙ ሺሕ ኾነው ሞትን ለመፍራት ከሀገሮቻቸው ወደ ወጡት ሰዎች ዕውቀትህ አልደረሰምን? አላህም ለነርሱ «ሙቱ» አላቸው፤ (ሞቱም)፡፡ ከዚያም ሕያው አደረጋቸው፡፡ አላህም በሰዎች ላይ ባለችሮታ ነው፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያመሰግኑም።} [አልበቀራህ፡ 243]
አራተኛው ምሳሌ፡- በሞተ መንደር እያለፈ የነበረውንና አላህ መንደሪቱን ህያው አያደርጋትም ብሎ ስላሰበው ግለሰብ ታሪኩ የተወሳበት አጋጣሚ ላይ ነው። የላቀው አላህም ሰውየውን ራሱ መቶ አመት እንዲሞት አደረገውና ከዚያም አስነሳው። ይህንንም በተመለከተ የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿أَوۡ كَٱلَّذِي مَرَّ عَلَىٰ قَرۡيَةٖ وَهِيَ خَاوِيَةٌ عَلَىٰ عُرُوشِهَا قَالَ أَنَّىٰ يُحۡيِۦ هَٰذِهِ ٱللَّهُ بَعۡدَ مَوۡتِهَاۖ فَأَمَاتَهُ ٱللَّهُ مِاْئَةَ عَامٖ ثُمَّ بَعَثَهُۥۖ قَالَ كَمۡ لَبِثۡتَۖ قَالَ لَبِثۡتُ يَوۡمًا أَوۡ بَعۡضَ يَوۡمٖۖ قَالَ بَل لَّبِثۡتَ مِاْئَةَ عَامٖ فَٱنظُرۡ إِلَىٰ طَعَامِكَ وَشَرَابِكَ لَمۡ يَتَسَنَّهۡۖ وَٱنظُرۡ إِلَىٰ حِمَارِكَ وَلِنَجۡعَلَكَ ءَايَةٗ لِّلنَّاسِۖ وَٱنظُرۡ إِلَى ٱلۡعِظَامِ كَيۡفَ نُنشِزُهَا ثُمَّ نَكۡسُوهَا لَحۡمٗاۚ فَلَمَّا تَبَيَّنَ لَهُۥ قَالَ أَعۡلَمُ أَنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ 259﴾
{ወይም ያንን በከተማ ላይ እርሷ በጣራዎችዋ ላይ የወደቀች ስትኾን ያለፈውን ሰው ብጤ (አላየህምን)፡- «ይህችን (ከተማ) ከሞተች በኋላ አላህ እንዴት ሕያው ያደርጋታል» አለ፡፡ አላህም ገደለው መቶ ዓመትን (አቆየውም)፡፡ ከዚያም አስነሳው፡- «ምን ያህል ቆየህ» አለው፡፡ «አንድ ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆየሁ» አለ፡፡ «አይደለም መቶን ዓመት ቆየህ፡፡ ወደ ምግብህና ወደ መጠጥህም ያልተለወጠ ሲኾን ተመልከት፡፡ ወደ አህያህም ተመልከት፡፡ ለሰዎችም አስረጅ እናደርግህ ዘንድ (ይህንን ሰራን)፡፡ ወደ አፅሞቹም እንዴት እንደምናስነሳት ከዚያም ሥጋን እንደምናለብሳት ተመልከት» አለው፡፡ ለርሱም (በማየት) በተገለጸለት ጊዜ፡- «አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን ዐውቃለሁ» አለ።} [አልበቀራህ፡ 259]
አምስተኛ፡ ነቢዩ ኢብራሂም አሏህ እንዴት ህያው እንደሚያደርግ ያሳያቸው ዘንድ አሏህን የጠየቁበት ታሪክ ላይ ነው። የላቀው አሏህም አራት ወፎችን እንዲያርዱና ከዚያም በታትነው በዙሪያቸው ባሉ ተራራዎች ላይ እንዲያስቀምጧቸው ከዚያም እንዲጠሯቸው አዘዛቸው። ያኔ እያንዳንዱ የሰውነታቸው ቁርጥራጭ ኢብራሂም ወዳሉበት እየመጡ በመሰባሰብ ተገጣጠሙ። ይህንንም አስመልክቶ የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَإِذۡ قَالَ إِبۡرَٰهِـۧمُ رَبِّ أَرِنِي كَيۡفَ تُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰۖ قَالَ أَوَلَمۡ تُؤۡمِنۖ قَالَ بَلَىٰ وَلَٰكِن لِّيَطۡمَئِنَّ قَلۡبِيۖ قَالَ فَخُذۡ أَرۡبَعَةٗ مِّنَ ٱلطَّيۡرِ فَصُرۡهُنَّ إِلَيۡكَ ثُمَّ ٱجۡعَلۡ عَلَىٰ كُلِّ جَبَلٖ مِّنۡهُنَّ جُزۡءٗا ثُمَّ ٱدۡعُهُنَّ يَأۡتِينَكَ سَعۡيٗاۚ وَٱعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٞ 260﴾
{ኢብራሂምም «ጌታዬ ሆይ! ሙታንን እንዴት ሕያው እንደምታደርግ አሳየኝ» ባለ ጊዜ (አስታውስ፡፡) አላህ ፡- «አላመንክምን» አለው፡፡ «አይደለም (አምኛለሁ)፤ ግን ልቤ እንዲረጋ» ነው አለ፡፡ (አላህም)፡- «ከበራሪዎች (ከወፎች) አራትን ያዝ፡፡ ወደ አንተም ሰብስባቸው፡፡ (ቆራርጣቸውም)፤ ከዚያም በየኮረብታው ሁሉ ላይ ከነርሱ ቁራጭን አድርግ፡፡ ከዚያም ጥራቸው፤ ፈጥነው ይመጡሃልና፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ መኾኑን ዕወቅ» አለው።} [አልበቀራህ፡ 260]
እነዚህ ሙታን መልሰው በሕይወት እንደሚነሱ ለትንሳኤ በቂ ተጨባጭና እውነተኛ ማሳያ ምሳሌዎች ናቸው። ከዚህ ቀደም ዒሳ ዓለይሂ ሰላም በአሏህ ፍቃድ ሙታንን ወደ ሕይወት የመመለስና ከመቃብራቸው የማውጣትን ተአምር እንደተሰጣቸውም ጠቅሰናል።
አዕምሯዊ ማስረጃውም በሁለት አቅጣጫ ማየት ይቻላል።
አንደኛ፡- አላህ የሰማይና የምድር እንዲሁም በውስጣቸው ያለውን ሁሉ መጀመርያዉኑ የፈጠረ ነው። መጀመሪያውኑ የፈጠራቸው ሆኖ ሳለ ዳግም በትንሳኤ መመለሱ የሚያቅተው አይሆንም። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿وَهُوَ ٱلَّذِي يَبۡدَؤُاْ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ وَهُوَ أَهۡوَنُ عَلَيۡهِ...﴾
{እርሱም ያ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም የሚመልሰው ነው፡፡ እርሱም (መመለሱ) በእርሱ ላይ በጣም ገር ነው።} [ሩም፡ 27]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿...كَمَا بَدَأۡنَآ أَوَّلَ خَلۡقٖ نُّعِيدُهُۥۚ وَعۡدًا عَلَيۡنَآۚ إِنَّا كُنَّا فَٰعِلِينَ﴾
{የመጀመሪያን ፍጥረት እንደ ጀመርን እንመልሰዋለን፡፡ (መፈጸሙ) በእኛ ላይ የኾነን ቀጠሮ ቀጠርን፡፡ እኛ (የቀጠርነውን) ሠሪዎች ነን፡፡ } [አል-አንቢያእ፡ 104] የተበታተኑ አጥንቶች ወደ ህይወት መመለሳቸውን ለሚክድ ሰው ነቢዩ ምላሽ እንዲሰጡት ሲያዛቸው አላህ እንዲህ ብሏል፡
﴿قُلۡ يُحۡيِيهَا ٱلَّذِيٓ أَنشَأَهَآ أَوَّلَ مَرَّةٖۖ وَهُوَ بِكُلِّ خَلۡقٍ عَلِيمٌ 79﴾
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡ {«ያ በመጀመሪያ ጊዜ (ከኢምንት) ያስገኛት ሕያው ያደርጋታል። እርሱም በፍጡሩ ሁሉ (ኹኔታ) ዐዋቂ ነው» በለው።} [ያሲን 79]
ሁለተኛ፡ የምድር ክፍሎች ሞተው አረንጓዴ ለም ዛፍ የሌለው ደረቃማ የሚሆኑበት አጋጣሚ አለ። ከዚያም አሏህ ዝናብ ያዘንብና ምድርም መርበትበትን ካስተናገደች በኋላ ድጋሚ አረንጓዴ እና ሕያው ትሆናለች፤ ሁሉንም የሚያማምሩ አዝርእቶችንም ታበቅላለች። ከሞተችበት ህያው ያደረጋት አሏህ ሙታንን እንደሚያስነሳ ምንም ጥርጥር የለውም። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፡-
﴿وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنَّكَ تَرَى ٱلۡأَرۡضَ خَٰشِعَةٗ فَإِذَآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡهَا ٱلۡمَآءَ ٱهۡتَزَّتۡ وَرَبَتۡۚ إِنَّ ٱلَّذِيٓ أَحۡيَاهَا لَمُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰٓۚ إِنَّهُۥ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ 39﴾
{አንተ ምድርን ደረቅ ኾና ማየትህም ከምልክቶቹ ነው፡፡ በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ (በቡቃያዎችዋ) ትላወሳለች፡፡ ትነፋለችም፡፡ ያ ሕያው ያደረጋት ጌታ በእርግጥ ሙታንን ሕያው አድራጊ ነው፡፡ እነርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።} [ፉሲለት፡ 39]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَنَزَّلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ مُّبَٰرَكٗا فَأَنۢبَتۡنَا بِهِۦ جَنَّٰتٖ وَحَبَّ ٱلۡحَصِيدِ 9 وَٱلنَّخۡلَ بَاسِقَٰتٖ لَّهَا طَلۡعٞ نَّضِيدٞ 10 رِّزۡقٗا لِّلۡعِبَادِۖ وَأَحۡيَيۡنَا بِهِۦ بَلۡدَةٗ مَّيۡتٗاۚ كَذَٰلِكَ ٱلۡخُرُوجُ 11﴾
{ ከሰማይም ብሩክን ውሃ አወረድን፡፡ በእርሱም አትክልቶችንና የሚታጨድን (አዝመራ) ፍሬ አበቀልን። ዘምባባንም ረዣዢም ለእርሷ የተደራረበ እንቡጥ ያላት ስትኾን (አበቀልን)። ለባሮቹ ሲሳይ ትኾን ዘንድ (አዘጋጀናት)፡፡ በእርሱም የሞተችን አገር ሕያው አደረግንበት፡፡ (ከመቃብር) መውጣትም እንደዚሁ ነው።} [ቃፍ 9-11]
ከሞት በኋላ በሚሆነው ነገር ሁሉ ማመን በመጨረሻው ቀን ማመን ውስጥ የሚካተት ነው፡-
ሀ - የመቃብር ፈተና፡- የሞተው ሰው ከተቀበረ በኋላ ስለ ጌታው፣ ስለ ሃይማኖቱ እና ስለ ነቢዩ የሚጠየቅበት ጊዜ ነው። አላህ ምእመናንን በጽኑ ቃል ያጸናቸውና የሙእሚን ምላሹ፡- ጌታዬ አላህ ነው። ሀይማኖቴም እስላም ነው፤ ነብዬም ሙሐመድ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ናቸው።
በዳዮችንም አላህ ያሳስታቸዋል። የከሓዲው ምላሽ፡- "አህ! አህ! እኔ አላውቅም።" ይላል። የተጠራጣሪ ወይም የሙናፊቅ ምላሽ ደግሞ፡- "አላውቅም! ሰዎች ሲሉ ሰምቼ እኔም እንዲሁ አልኩ።" የሚል ይሆናል።
ለ- በመቃብር ውስጥ ያለ ቅጣትና ፀጋ፡- በዳዮች፣ ከሓዲዎችና መናፍቃን በመቃብር ውስጥ ይቀጣሉ። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿...وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذِ ٱلظَّٰلِمُونَ فِي غَمَرَٰتِ ٱلۡمَوۡتِ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ بَاسِطُوٓاْ أَيۡدِيهِمۡ أَخۡرِجُوٓاْ أَنفُسَكُمُۖ ٱلۡيَوۡمَ تُجۡزَوۡنَ عَذَابَ ٱلۡهُونِ بِمَا كُنتُمۡ تَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ غَيۡرَ ٱلۡحَقِّ وَكُنتُمۡ عَنۡ ءَايَٰتِهِۦ تَسۡتَكۡبِرُونَ﴾
{በደለኞችንም በሞት መከራዎች ውስጥ በኾኑ ጊዜ መላእክት እጆቻቸውን ዘርጊዎች ኾነው «(ለቅጥጥብ) ነፍሶቻችሁን አውጡ፤ በአላህ ላይ እውነት ያልኾነን ነገር ትናገሩ በነበራችሁትና ከአንቀጾቹም ትኮሩ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬ የውርደትን ቅጣት ትመነዳላችሁ» (የሚሏቸው ሲኾኑ) ብታይ ኖሮ (አስደናቂን ነገር ባየህ ነበር)።} [አል-አንዓም፡ 93]
የላቀው አሏህ የፊርዓውን ተከታዮችን በተመለከተም እንዲህ ብሏል፡
﴿ٱلنَّارُ يُعۡرَضُونَ عَلَيۡهَا غُدُوّٗا وَعَشِيّٗاۚ وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ أَدۡخِلُوٓاْ ءَالَ فِرۡعَوۡنَ أَشَدَّ ٱلۡعَذَابِ 46﴾
{እሳት በጧትና በማታ በእርሷ ላይ ይቀርባሉ፡፡ ሰዓቲቱም በምትኾንበት ቀን «የፈርዖንን ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት (ገሀነምን) አግቡዋቸው» (ይባላል)።} [ጋፊር፡ 46]
ሙስሊም ከዘይድ ኢብኑ ሣቢት ረዲየሏሁ ዓንሁ በዘገቡት ሐዲሥ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- «“አትቀባበሩም ብዬ ባልሰጋ ኖሮ እኔ የምስማውን የቀብር ቅጣት እንዲያሰማችሁ አላህን እለምነው ነበር።" ከዚያም ወደእኛ ዞር አሉና፡- "ከእሳት ቅጣት በአላህ ተጠበቁ!" አሉ፤ በቦታው የነበርንም "ከእሳት ቅጣት በአላህ እንጠበቃለን" አልን። ከዚያም "ከቀብር ቅጣት በአላህ ተጠበቁ!" አሉ። "እኛ ከቀብር ቅጣት በአላህ እንጠበቃለን" አልን። ከዚያም፡- "ከድብቁም ከጉልሁም ፈተና በአላህ ተጠበቁ!" አሉ፤ "ከድብቁም ከጉልሁም ፈተና በአላህ እንጠበቃለን" አልን፤ "ከመሲሑ ደጃል ፈተና በአላህ ተጠበቁ!" አሉን፤ "ከመሲሑ ደጃል ፈተና በአላህ እንጠበቃለን" አልን።»
በመቃብር ውስጥ ያለው ፀጋ ግን ለእውነተኛ ምእመናን ነው። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿إِنَّ ٱلَّذِينَ قَالُواْ رَبُّنَا ٱللَّهُ ثُمَّ ٱسۡتَقَٰمُواْ تَتَنَزَّلُ عَلَيۡهِمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ أَلَّا تَخَافُواْ وَلَا تَحۡزَنُواْ وَأَبۡشِرُواْ بِٱلۡجَنَّةِ ٱلَّتِي كُنتُمۡ تُوعَدُونَ 30﴾
{ እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ» በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ።»} [ፉሲለት፡ 30]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿فَلَوۡلَآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلۡحُلۡقُومَ 83 وَأَنتُمۡ حِينَئِذٖ تَنظُرُونَ 84 وَنَحۡنُ أَقۡرَبُ إِلَيۡهِ مِنكُمۡ وَلَٰكِن لَّا تُبۡصِرُونَ 85 فَلَوۡلَآ إِن كُنتُمۡ غَيۡرَ مَدِينِينَ 86 تَرۡجِعُونَهَآ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ87 فَأَمَّآ إِن كَانَ مِنَ ٱلۡمُقَرَّبِينَ 88 فَرَوۡحٞ وَرَيۡحَانٞ وَجَنَّتُ نَعِيمٖ 89﴾
{(ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ። እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትኾኑ። እኛም ግን አታዩም እንጅ ከእናንተ ይልቅ ወደእርሱ የቀረብን ስንኾን። የማትዳኙም ከኾናችሁ። እውነተኞች እንደ ኾናችሁ (ነፍሲቱን ወደ አካሉ) ለምን አትመልሷትም። (ሟቹ) ከባለሟሎቹ ቢኾንማ። (ለእርሱ) ዕረፍት፣ መልካም ሲሳይም፣ የመጠቀሚያ ገነትም አልለው።} [አል-ዋቂዓህ፡ 83-89]
ከበራእ ኢብኑ ዓዚብ ረዲየሏሁ ዓንሁ (አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) በተላለፈ ሐዲሥ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሙእሚን በቀብር ውስጥ የሚገጥመውን የሁለቱን መላእክት ጥያቄዎች ከመለሰ በኋላ እንዲህ ስላለው ሁኔታ እንዲህ ብለዋል፡- «ከሰማይ እንዲህ የሚል ተጣሪ ይጣራል፡- "ባሪያዬ እውነት ተናግሯል፤ የጀነት ጉዝጓዝ አድርጉለት፤ ከጀነት ልብስም አልብሱት፤ የጀነትንም ደጃፍ ክፍት አድርጉለት።" የጀነት ነፋስ ይነፍስለታል፤ መአዛዋም እየመጣ ያውደዋል። መቃብሩም እስከአይኑ ርቀት ድረስ ክፍት ይደረግለታል።» [አሕመድ እና አቡ ዳውድ ዘግበውታል]
አንዳንድ አፈንጋጮች በመቃብር ውስጥ ባለ ቅጣት እና ፀጋ ክደዋል፤ ቀብርን ከፍተን ሟቹን ብናየው እሱን ከተውንበት ሁኔታ ምንም ሳይቀየር መስፋትም ይሁን መጥበብ ሳይኖር ነው፤ ይህ ደሞ ከተጨባጩ እውነታ ጋር የሚጣረስ ነው አሉ።
ይህ ሙግታቸው ግን በሸሪዓዊም፣ በህዋሳዊም ይሁን በአዕምሯዊ ማስረጃ ውድቅ ነው።
ከሸሪዓዊ ማስረጃው፡- የቀብር ውስጥ ቅጣት እና ፀጋ እውነተኝነትን የሚያረጋግጡ ጥቅሶችን አስቀድመን ጠቅሰናል።
ቡኻሪይ እንደዘገቡት ኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ብለዋል "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሆነ አጥር እያለፉ ቀብር ውስጥ ያሉ የሁለት ሰዎች የስቃይ ድምፅ ሰሙ።" የሚለውን ሐዲሥ ላይ እንዲህ የሚል ይገኝበታል፡ "አንደኛቸው ከሽንት - በሌላ ዘገባም: ከሽንቱ- አይጥራራም ነበር። ሌላኛው ደግሞ ነገር በማመላለስ የሚሯሯጥ ነበር።" ሙስሊም ዘገባ ደሞ "በሽንቱ እንዳይቆሽሽ ራሱን አይጠብቅም ነበር።"
ህዋሳዊ ማስረጃው ደሞ፡- ለምሳሌ የተኛ ሰው በህልሙ ራሱን በሚዝናናበት ሰፊና ደስ የሚል ቦታ ላይ ወይም በጠባብና አስጨናቂ ቦታ ላይ እንዳለ ያያል፤ አንዳንድ ጊዜም ከሕልሙ ብርታት የተነሳ ሊነቃም ይችላል። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን እዛው ፍራሹ ላይ በክፍሉ ውስጥ እና በነበረበት ሁኔታ ላይ ሆኖ ነው የሚደሰተውም የሚጨነቀውም፤ እንቅልፍ የሞት ወንድም ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلۡأَنفُسَ حِينَ مَوۡتِهَا وَٱلَّتِي لَمۡ تَمُتۡ فِي مَنَامِهَاۖ فَيُمۡسِكُ ٱلَّتِي قَضَىٰ عَلَيۡهَا ٱلۡمَوۡتَ وَيُرۡسِلُ ٱلۡأُخۡرَىٰٓ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمًّى...﴾
{አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል፡፡ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ (ይወስዳታል)፡፡ ታዲያ ያችን ሞትን የፈረደባትን ይይዛታል፡፡ ሌላይቱንም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ይለቅቃታል፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ምልክቶች አልሉበት።} [አዝ-ዙመር፡ 42]
አዕምሯዊ ማስረጃው ደሞ፡- የተኛ ሰው ከእውነታው ጋር የሚስማማ ህልም ያያል፤ ምናልባትም ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በእውነተኛ ቁመናቸው ማየትን ይመስል -እሳቸውን በህልሙ በትክክለኛ አቋማቸው ያዬ ሰው በትክክል ራሳቸውን ነቢዩን አይቷል ማለት ነው።- ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን ተኝቶ የነበረው ሰው ከሚታየው ነገር ርቆ ክፍሉ ውስጥ ፍራሹ ላይ ከመሆኑም ጋር ነው። ይህ በዚህች አለም ላይ የሚከሰት ጉዳይ ከሆነ በቀጣዩ አለም የሚከሰት አይሆንምን?!
መቃብርን ከፍተን ብንመለከት ሟቹንም ቀብሩንም የምናገኘው እኛ በተውነው ሁኔታ ላይ ነው እንጅ የሚቀየር ነገር የለም፤ ቀብሩም ቢሆን አይሰፋም አይጠብም ማለታቸውን በተመለከተ ምላሻችን በተለያየ አቅጣጫ ነው፤ ከነዚህም መካከል፡-
አንደኛ፡ ይህን በመሰሉ ደካማ ውዥንብሮች በሸሪዓችን የመጣን እውነት መቃወም አይቻልም፤ የቀብርን ቅጣት የሚቃወም ሰው በሸሪዓ የመጣውን እውነት በተገቢው ሁኔታ ቢያጤነውና ቢረዳው ኖሮ ውዥንብሩ ደካማ መሆኑን ያውቅ ነበር። ቅሉ እንዲህ ተብሏል፡
ስንትና ስንት ጥሩ ቃልን የሚያበላሽ አለ
ዋናው መንስኤው የአረዳዱ ብልሽት ሆኖ ሳለ
ሁለተኛ፡- ከቀብር በኋላ ያለው ህይወት ህዋሳት የማይደርሱበት የሩቅ ሚስጥር ነው። በህዋሳት የሚደረስባቸው ቢሆኑማ በሩቅ ሚስጥር የማመን ጥበቡ ይቀር ነበር። በሩቅ ሚስጥር ባመኑትና ባስተባበሉት መካከልም ልዩነት አይኖርም ነበር።
ሦስተኛ፡- በመቃብሩ ውስጥ ያለውን ቅጣትም ይሁን ፀጋ እንዲሁም የቀብር መስፋትና መጥበብ የሚረዳው ሟቹ እንጅ ሌላው አይደለም። ልክ የተኛ ሰው በጠባብና አስጨናቂ ቦታ ላይ ወይም በሰፊና ዘና ያለ ቦታ ላይ መሆኑን በህልም እንደሚያየው ማለት ነው፤ በዙሪያው ያሉ ሰዎች ግን ስላለበት ሁኔታ ምንም ነገር አይመለከቱትም አይሰሙምም። ነቢዩ (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሶሃቦቻቸው መካከል በነበሩበትም ወቅት መለኮታዊ ራዕይ ይገለፅላቸው ነበር። ሱሓቦች ባይሰሙትም ነቢዩ (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ግን ወሕዩ ይደርሳቸው ነበር። አንዳንዴም መላኢካው በሰው ተመስሎ ያናግራቸው ነበር፤ ሰሐቦች ግን መላኢካውን አይመለከቱትም አይሰሙትምም።
አራተኛ: የሰዎች ግንዛቤ እንዲገነዘቡ አሏህ በገደበው ወሰን ልክ የተወሰነ በመሆኑ ህልውና ያለውን ነገር ሁሉ የሚገነዘቡ አይደሉም። ሰባቱ ሰማያት፣ ምድርና በውስጣቸው ያለው ሁሉ አላህን ያጠራሉ፣ ያመሰግኑታልም። አሏህ ያንን ይሰማል፤ አልፎ አልፎም የሚሻውን ከባሮቹ መካከል እንዲሰማው ያደርጋል። ይህ ከመሆኑም ጋር ግን የሚያደርጉትን ምስጋና ማወቅ ለኛ የሩቅ እውቀት ሁኖ ተጋርዶብናል፤ ይህንንም በተመለከተ የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿تُسَبِّحُ لَهُ ٱلسَّمَٰوَٰتُ ٱلسَّبۡعُ وَٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهِنَّۚ وَإِن مِّن شَيۡءٍ إِلَّا يُسَبِّحُ بِحَمۡدِهِۦ وَلَٰكِن لَّا تَفۡقَهُونَ تَسۡبِيحَهُمۡ...﴾
{ ሰባቱ ሰማያትና ምድርም በውስጣቸውም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያጠራሉ፡፡ ከነገርም ሁሉ ከማመስገን ጋር የሚያጠራው እንጂ አንድም የለም፡፡ ግን ማጥራታቸውን አታውቁትም፡፡ እርሱ ታጋሽ መሓሪ ነው።} [አል-ኢስራእ፡ 44] እንዲሁም ሰይጣናትም አጋንንትም በየቦታው ይዘዋወራሉ ሄድ መለስ ይላሉ፤ አጋንንት መልዕክተኛው (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ተገኘተው ቁርአንንም በጥሞና አዳምጠው ወደ ህዝባቸውም አስጠንቃቂ ሆነው ተመልሰዋል፤ ይህ ሁሉ ከመሆኑም ጋር ግን ጉዳዩን ማወቁ ለኛ የተጋረደብን ነገር ነው። ይህንንም በተመለከተ የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿يَٰبَنِيٓ ءَادَمَ لَا يَفۡتِنَنَّكُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ كَمَآ أَخۡرَجَ أَبَوَيۡكُم مِّنَ ٱلۡجَنَّةِ يَنزِعُ عَنۡهُمَا لِبَاسَهُمَا لِيُرِيَهُمَا سَوۡءَٰتِهِمَآۚ إِنَّهُۥ يَرَىٰكُمۡ هُوَ وَقَبِيلُهُۥ مِنۡ حَيۡثُ لَا تَرَوۡنَهُمۡۗ إِنَّا جَعَلۡنَا ٱلشَّيَٰطِينَ أَوۡلِيَآءَ لِلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ 27﴾
{ የአዳም ልጆች ሆይ! ሰይጣን አባትና እናታችሁን ኀፍረተ ገላቸውን ሊያሳያቸው ልብሶቻቸውን ከነሱ የገፈፋቸው ሲኾን ከገነት እንዳወጣቸው ሁሉ እናንተን አይሞክራችሁ፡፡ እነሆ እርሱ ከነሰራዊቱ ከማታዩዋቸው ስፍራ ያዩዋችኋልና፡፡ እኛ ሰይጣናትን ለእነዚያ ለማያምኑት ወዳጆች አድርገናል።} [አል-አዕራፍ፡ 27] ሰዎች ያለውን ነገር ሁሉ በእውቀት ማካለል የማይችሉ መሆናቸው እይታወቀ ስላልደረሱበት ብቻ የለም ብሎ ማስተባበል ተገቢ አይደለም።
በቀደር ማመን
ቀደር ማለት አሏህ በቀድሞ አዋቂነቱ እና ጥበቡ መሰረት ለፍጥረታቱ አስቀድሞ የሚያስቀምጠው ውሳኔ ነው።
በቀደር ማመን አራት ነገሮችን ያጠቃልላል፡
አንደኛ፡- አላህ ምንም አይነት የጊዜም ይሁን የምንም ገደብ ሳይኖርበት ሁሉንም ነገር በአጠቃላይም ይሁን በዝርዝር ስለፍጥረታቱ ድርጊትም ይሁን ስለራሱ ፈቃድ እንደሚያውቅ ማመን ነው።
ሁለተኛ፡- ይህንንም አላህ በ "ለውሐል መሕፉዝ" (ጥብቁ ሰሌዳ) ላይ እንደጻፈው ማመን ነው። እነዚህን ሁለት ጉዳዮች በተመለከተ አላህ እንዲህ ብሏል፡
﴿أَلَمۡ تَعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا فِي ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِۚ إِنَّ ذَٰلِكَ فِي كِتَٰبٍۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٞ 70﴾
{አላህ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ በእርግጥ የሚያውቅ መኾኑን አታውቅምን? ይህ በመጽሐፍ ውስጥ (የተመዘገበ) ነው፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው} [አል-ሐጅ፡ 70]
ሶሒሕ ሙስሊም ላይ በተዘገበ ሐዲሥ ዐብደሏህ ቢን ዓምር ኢብኑል ዓስ ረዲየሏሁ ዓንሁ ነቢዩ (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፡ «አሏህ የፍጡራንን እጣ ፈንታ የፃፈው ሰማያትንና ምድርን ከመፍጠሩ ሃምሳ ሺህ አመታትን ቀድሞ ነው።»
ሦስተኛ፡- እሱ የሚያደርገውንም ይሁን ፍጡራኑ የሚያደርጉትን ድርጊት በተመለከተ ሁሉም ክስተት የሚከሰተው በአላህ መሻት መሆኑን ማመን ነው። ድርጊቱንም በተመለከተ የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَرَبُّكَ يَخۡلُقُ مَا يَشَآءُ وَيَخۡتَارُۗ...﴾
{ጌታህም የሚሻውን ይፈጥራል፤ ይመርጣልም።}
[አል-ቀሶስ፡ 68] እንዲህም ብሏል፡
﴿...وَيَفۡعَلُ ٱللَّهُ مَا يَشَآءُ﴾
{አላህም የሚሻውን ይሠራል።} [ኢብራሂም፡ 27]
እንዲህም ብሏል፡
﴿هُوَ ٱلَّذِي يُصَوِّرُكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡحَامِ كَيۡفَ يَشَآءُۚ...﴾
{እርሱ ያ በማሕጸኖች ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነው።} [አሊ-ዒምራን፡ 6] የላቀው አሏህ የፍጡራኑን ድርጊት በተመለከተም እንዲህ ብሏል፡
﴿...وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَسَلَّطَهُمۡ عَلَيۡكُمۡ فَلَقَٰتَلُوكُمۡ...﴾
{አላህም በሻ ኖሮ በእናንተ ላይ ኀይል በሰጣቸውና በተጋደሉዋችሁ ነበር} [አን-ኒሳእ፡ 90]
እንዲህም ብሏል፡
﴿...وَلَوۡ شَآءَ رَبُّكَ مَا فَعَلُوهُۖ فَذَرۡهُمۡ وَمَا يَفۡتَرُون﴾
{ጌታህም በሻ ኖሮ ባልሠሩት ነበር፡፡ ከቅጥፈታቸውም ጋር ተዋቸው።} [አል-አንዓም፡ 112]
አራተኛ፡- ሁሉም ፍጥረታት ከነሙሉ አካላቸው፣ ከነሙሉ ባህሪያቸውም ይሁን እንቅስቃሴያቸውም ጭምር በአላህ የተፈጠሩ መሆናቸውን ማመን ነው። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَيۡءٖۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ وَكِيلٞ 62﴾
{አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው።} [አዝ-ዙመር፡ 62]
ጥራት ይገባውና እንዲህም ብሏል፡
﴿...وَخَلَقَ كُلَّ شَيۡءٖ فَقَدَّرَهُۥ تَقۡدِيرٗا﴾
{ሁሉንም ነገር የፈጠረና በትክክልም (በስርአት) የመጠነው አምላክ ነው።} [አል-ፉርቃን፡ 2] ኢብራሂም ዓለይሂ ሰላም ለህዝቦቹ እንዲህ ማለቱንም አሏህ ነግሮናል፡
﴿وَٱللَّهُ خَلَقَكُمۡ وَمَا تَعۡمَلُونَ 96﴾
{«አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን።»} [አስ-ሷፋት፡ 96]
በገለፅነው መልኩ ስለቀደር ማመን ማለት የሰው ልጅ በገዛ ፈቃዱና በተሰጠው ችሎታ የሚያደርጋቸው ተግባራት የሉም ማለት አይደለም። በገዛ ፈቃዱና በተሰጠው ችሎታ የሚያደርጋቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሸሪዓውም ይሁን ተጨባጩ እውነታ የሚያመለክቱት ጉዳይ ነውና።
ሸሪዓዊ ማስረጃው፡ የላቀው አሏህ የፍጡራኑን መሻት በተመለከተ እንዲህ ብሏል፡
﴿...فَمَن شَآءَ ٱتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِۦ مَـَٔابًا﴾
{የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል።}
[አን-ነባእ፡ 39] እንዲህም ብሏል፡
﴿...فَأۡتُواْ حَرۡثَكُمۡ أَنَّىٰ شِئۡتُمۡۖ...﴾
{እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ኹነታ ድረሱ።}
[አል-በቀራህ፡ 223]
የፍጡራንን ችሎታ በተመለከተም እንዲህ ብሏል፡
﴿فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ مَا ٱسۡتَطَعۡتُمۡ وَٱسۡمَعُواْ وَأَطِيعُواْ...﴾
{አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት፤ ትዕዛዙን ስሙም፤ ታዘዙም፤ ለግሱም፤ ለነፍሶቻችሁ መልካምን (ይሰጣችኋልና)፤} [አት-ተጋቡን፡ 16] እንዲህም ብሏል፡
﴿لَا يُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۚ لَهَا مَا كَسَبَتۡ وَعَلَيۡهَا مَا ٱكۡتَسَبَتۡۗ...﴾
{አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም። ለርስዋ የሠራችው አላት። በርስዋም ላይ ያፈራችው (ኀጢአት) አለባት።} [አል-በቀራህ፡ 286]
የተጨባጩን እውነታ ማስረጃ በተመለከተ ደግሞ፡ ሁሉም ሰው ነገራቶችን ሊያደርግ ወይም ሊተው የሚችልበት የተወሰነ ምርጫ እና አቅም እንዳለው ያውቃል። በፍቃዱ የሚያደርጋቸው ለምሳሌ እንደ መራመድ ያሉት ድርጊቶቹንና ያለፍቃዱ የሚያደርጋቸው እንደ መንቀጥቀጥ ባሉ ድርጊቶቹ መካከል ልዩነት እንዳለም የሚታወቅ ነው። ይሁን እንጂ የሰው ልጅ ፈቃድ እና አቅም በአላህ ፍቃድ እና ሃያልነት የሚሆን ጉዳይ ነው። ይህም የላቀው አሏህ እንዲህ ስላለ ነው፡
﴿لِمَن شَآءَ مِنكُمۡ أَن يَسۡتَقِيمَ 28 وَمَا تَشَآءُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ29﴾
{ከናንተ ቀጥተኛ መኾንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)። የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም።} [አት-ተክዊር፡ 28-29] አጽናፈ ዓለሙ ሁሉ የኃያሉ አላህ በመሆኑ ያለርሱ እውቀትና ፈቃድ በሱ ግዛት ውስጥ የሚሆን ምንም ነገር የለም።
በገለፅነው መልኩ በቀደር ማመን የሰው ልጅ ግዴታውን ላለመወጣትም ይሁን ክልክላቶችን ለመዳፈሩ ማሳበቢያ ሊሆን አይችልም። ከሚከተሉት አቅጣጫዎች አንፃርም የዚህን ሙግት ውድቅነት ማሳየት ይቻላል፡
አንደኛ የላቀው አሏህ እንዲህ ማለቱ ነው፡
﴿سَيَقُولُ ٱلَّذِينَ أَشۡرَكُواْ لَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَآ أَشۡرَكۡنَا وَلَآ ءَابَآؤُنَا وَلَا حَرَّمۡنَا مِن شَيۡءٖۚ كَذَٰلِكَ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ حَتَّىٰ ذَاقُواْ بَأۡسَنَاۗ قُلۡ هَلۡ عِندَكُم مِّنۡ عِلۡمٖ فَتُخۡرِجُوهُ لَنَآۖ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَإِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا تَخۡرُصُونَ 148﴾
{እነዚያ ያጋሩት «አላህ በሻ ኖሮ እኛም አባቶቻቸንም ባላጋራን ነበር፡፡ አንዳችንም ነገር እርም ባላደረግን ነበር ይላሉ፡፡ እንደዚሁ (እነዚህን እንደዋሹ) እነዚያ ከበፊታቸው የነበሩት ብርቱ ቅጣታችንን እስከቀመሱ ድረስ አስተባባሉ፡፡ ለእኛ ታዘልቁልን ዘንድ (ማጋራታችሁን ለመውደዱ) እናንተ ዘንድ ዕውቀት አለን? ጥርጣሬን እንጅ ሌላ አትከተሉም፡፡ እናንተ ዋሾዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም» በላቸው።} [አል-አንዓም፡ 148] ቀደር ማሳበቢያ መሆን ቢችል ኖሮ አላህም አይቀጣቸውም ነበር።
ሁለተኛ የላቀው አሏህ እንዲህ ማለቱ ነው፡
﴿رُّسُلٗا مُّبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَى ٱللَّهِ حُجَّةُۢ بَعۡدَ ٱلرُّسُلِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمٗا 165﴾
{ከመልክተኞቹ በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ አስረጅ እንዳይኖር አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች የኾኑን መልክተኞች (ላክን)፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው።} [አን-ኒሳእ፡ 165] ቀደር ለአመፀኞች ማሳበቢያ መሆን የሚችል ቢሆን ኖሮ መልእክተኞችን በመላክ ብቻ ማሳበቢያው (በአንቀፁ አስረጂ የተባለው) የሚነሳ አይሆንም ነበር። ምክንያቱም ከመልእክተኞች በኋላም ቢሆን ያው ቀደር አስረጂ (ማሳበቢያ) መሆኑ አይቀርምና።
ሦስተኛ፡- ቡኻሪይ እና ሙስሊም ከዓሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየሏሁ ዓንሁ (አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደዘገቡት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- «“የእያንዳንዳንችሁ መቀመጫ ጀነት ወይስ ጀሀነም የሚለው ተፅፎ ተቀምጧል።" ከመካከላቸውም የሆነ ሰው እንዲህ አለ፡- "ታድያ ስራችንን ትተን ቀደር ላይ እንደገፍ?" እሳቸውም፡ "በፍፁም! ስራችሁን ስሩ፤ ሁሉም (ለመቀመጫው) የተገራ ነው።" ካሉ በኋላ እንዲህ ከሚለው አንቀፅ ጀምረው አነበቡ፡
﴿فَأَمَّا مَنۡ أَعۡطَىٰ وَٱتَّقَىٰ 5﴾
{የሰጠ ሰውማ ጌታውን የፈራም} [አል-ለይል፡ 5]» [ይህ የቡኻሪ ቃል ነው] በሙስሊም ዘገባ ደሞ፡- «ሁሉም ለተፈጠረለት የተገራ ነው።» ስለዚህም ነቢዩ (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ስራችንን እንድንሰራ አዘዙና በቀደር ላይ መደገፍን ደሞ ከለከሉ።
አራተኛ፡- አላህ ባሪያዎቹን አዟልም ከልክሏልም፤ ይሁን እንጂ ከአቅማቸው በላይ የሆነነ ነገር አላስገደዳቸውም። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ مَا ٱسۡتَطَعۡتُمۡ وَٱسۡمَعُواْ وَأَطِيعُواْ...﴾
{አላህንም የቻላችሁትን የክል ፍሩት፤ ትዕዛዙን ስሙም፤ ታዘዙም} [አት-ተጋቡን፡ 16] እንዲህም ብሏል፡
﴿لَا يُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۚ...﴾
{አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም።} [አል-በቀራህ፡ 286] ሰዎች ድርጊታቸው መገደድ ላይ የተመሰረተ ቢሆን ኖሮ የመጣላቸው መመርያ በማይችሉት ነገር ማዘዝ ይሆን ነበር። ይህም ደሞ ውድቅ ነው። ይልቁንም አንድ ሰው ባለማወቅ፣ በመርሳት ወይም በመገደድ ሀጢያትን ቢሰራ ኃጢያቱ አይቆጠርበትም፤ ምክንያቱም እንዳይቆጠርበት የሚያደርግ ከአቅሙ በላይ የሆነ ምክንያት አለውና።
አምስተኛው፡ የአላህ ቀደር እስካልተፈፀመ ድረስ ማንኛውም ሰው የማያውቀው ድብቅ ሚስጥር ነው፤ አንዳች ነገርን ለማድረግ የግል ፍቃድ ግን ከድርጊቱ ቀድሞ የሚገኝ ጉዳይ ነው። ስለዚህም በግል ፈቃዱ ያደረገው ጉዳይ ቀደሩን ተንተርሶ ያደረገው ሊሆን አይችልም። ያኔ በቀደር ማሳበብ ብሎ ነገር አይሰራም ማለት ነው። የሰው ልጅ የማያውቀው ነገር ላይ መንተራስ አይችልምና።
ስድስተኛ፡ ሰዎች በዱንያዊ ጉዳያቸው የምናያቸው የሚመቻቸውን ለማግኘት ሲጥሩ እንጅ ወደ ማይመቻቸው አዘንብለው በቀደር ሲያሳብቡ አናይም። ታዲያ ለምንድነው አንዳንድ ሰዎች በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ሲሆን የሚጠቅማቸውን ነገር ትተው ወደሚጎዳቸው እያዘነበሉ ከዚያም ቀደርን ማሳበቢያ የሚያደርጉት? ሁለቱም ጉዳዮችኮ ተመሳሳይ ናቸው፤ አይደል?!
ይህንን የሚያብራራ አንድ ምሳሌ ይሀው፡
አንድ ሰው በፊትለፊቱ ሁለት መንገዶች ቢገጥሙትና አንዱ መንገድ ትርምስ፣ ግድያ፣ ዝርፊያ፣ መጨማለቅ፣ ስጋትና ረሃብ ወደሰፈነበት አገር ይመራል። ሌላው መንገድ ደሞ ሥርዓት፣ ደህንነት፣ ደስተኛ ኑሮ የሞላበት፤ መከባበር የሰፈነበት፤ ክብርም ይሁን ንብረት የሚከበርበት ወደሆነ አገር ይመራል። ሰውየው በየትኛው መንገድ ይሄድ ነበር?
በእርግጠኝነት ሰላምና ደህንነቱ ወደሚጠበቅበት ሀገር የሚያመራውን ሁለተኛውን መንገድ ይዞ ይሄድ ነበር። መቼም ማንም ጤነኛ ሰው በትርምስና ስጋት ወደተዋጠው አገር እየሄደ በቀደር አያሳብብም። ታድያ ለምንድን ነው አንዳንድ ሰዎች ወደ ጀነት የሚወስደውን መንገድ ትተው ወደ ጀሀነም በሚወስደው መንገድ እየሄዱ በቀደር የሚያሳብቡት?
ሌላ ምሳሌ፡- አንድ ጤናውን ማግኘትና ከህመሙ ማገገም የሚፈልግ ታካሚ መድኃኒት ሲታዘዝለት መድሀኒቱን ባይወደውም ይወስደዋል፤ ከተወሰኑ የምግብ ዓይነቶች ከተከለከለም ለጤንነቱ ሲል እያማረውም ይተወዋል እንጂ የታዘዘለትን መድኃኒት አልወስድም እያለ የሚጎዳውንም ምግብ እየተመገበ በቀደር አያሳብብም። ታድያ ለምንድነው አንዳንድ ሰዎች የአላህን እና የመልእክተኛውን ትእዛዝና ክልከላ እየተቃረኑ በቀደር የሚያሳብቡት?
ሰባተኛ፡- የሰው ልጅ ድርጊቱን የሚፈፅመው ቀድሞ በተወሰነ የአሏህ ውሳኔ ተገዶ ነው ብሎ የሚያምን የሆነን ሰው አንድ ዘራፊ መጥቶ ገንዘቡን በመቀማት ወይም ክብሩን በመዳፈር ጥቃት ከፈፀመበት በኋላ “ያደረግኩብህ ነገር ሁሉ መጀመርያውኑ አሏህ ስለወሰነብህ ስለሆነ እኔን አትውቀሰኝ!” ቢለው ማሳበቢያውን አይቀበለውም። ሌላው ጥቃት ፈፅሞ ከተዳፈረው በኋላ ማስረጃ ሲያደርግበት አልቀበለም ካለ ታድያ ለምንድን ነው እሱ የአሏህን ሐቅ እየተዳፈረ ማሳበቢያውን ቀደር ማድረግ የሚፈልገው?
በታሪክ ይባላል አንድ ጊዜ ለሙእሚኖች አዛዥ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ረዲየሏሁ ዓንሁ (አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) አንዱ ሌባ ሰርቆ እጁ ሊቆረጥ ዘንድ መጣለት፤ ዑመርም የይቆረጥ ትዕዛዙን ሰጠ፤ ያኔ ሰውየው፡- “ቆይ አንዴ የሙእሚኖች አዛዥ ሆይ! እንደው አላህ ቀድሮት እኮነው የሰረቅኩት።” አለ። ዑመርም (ረዲየሏሁ ዓንሁ) እንዲህ መለሱለት፡- “እኛስ አላህ ቀድሮት አይደል እጅህን የምንቆርጥልህ?!"
በቀደር ማመን ትልልቅ ፋይዳዎችን ያስገኛል፤ ከነዚህም መካከል፡-
አንደኛ፡- ትክክለኛውን ሰበብ ስናደርስ ራሱ ሰበቡ ላይ ሳይሆን አላህ ላይ እንድንመካ ያደርገናል። ሁሉም ነገር የሚፈጸመው በአሏህ ፈቃድ በመሆኑ በሰበብ መመካት የለብንም።
ሁለተኛ፡- ሰውየው ሲሳካለት በራስ መደነቅ ውስጥ እንዳይገባ ያደርጋል፤ ምክንያቱም ስኬቱ የስኬት ሰበቦችን ያገራለት አላህ የሰጠው ፀጋ በመሆኑ በራስ መደነቁ ይህንን ፀጋ የዋለለትን አሏህን ያስረሳዋልና።
ሦስተኛ፡- በሚደርስበት ቀደር ሁሉ እርጋታንና ውስጣዊ ሰላምን ያገኛል። ስለዚህም የምንወደውን ነገር ብናጣ ወይም የምንጠላው ነገር ቢከሰትብን ጭንቀት ውስጥ አንገባም፤ ምክንያቱም ሁሉም ነገር የሚፈጸመው የሰማያትና የምድር ባለቤት በሆነው አላህ እንደመሆኑ መጠን አሏህ ሁን ያለው መሆኑ ስለማይቀር ጉዳያችንን ለሱ ሰጥተን እንረጋጋለን። ይህንንም በተመለከተ የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿مَآ أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٖ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا فِيٓ أَنفُسِكُمۡ إِلَّا فِي كِتَٰبٖ مِّن قَبۡلِ أَن نَّبۡرَأَهَآۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٞ 22 لِّكَيۡلَا تَأۡسَوۡاْ عَلَىٰ مَا فَاتَكُمۡ وَلَا تَفۡرَحُواْ بِمَآ ءَاتَىٰكُمۡۗ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخۡتَالٖ فَخُورٍ 23﴾
{በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ (ማንንም) አትነካም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትኾን እንጅ፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው። (ይህ ማሳወቃችን) ባመለጣችሁ ጸጋ ላይ እንዳታዝኑ አላህም በሰጣችሁ ነገር (በትዕቢት) እንዳትደሰቱ ነው፡፡ አላህም ኩራተኛን ጉረኛን ሁሉ አይወድም።} [አል-ሐዲድ፡ 22-23]
«عَجَبًا لِأَمْرِ الْمُؤْمِنِ إِنَّ أَمْرَهُ كُلَّهُ خَيْرٌ، وَلَيْسَ ذَاكَ لِأَحَدٍ إِلَّا لِلْمُؤْمِنِ، إِنْ أَصَابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ فَكَانَ خَيْرًا لَهُ، وَإِنْ أَصَابَتْهُ ضَرَّاءُ صَبَرَ فَكَانَ خَيْرًا لَهُ».
ነቢዩም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡- "የሙእሚን ጉዳዩ እንዴት ድንቅ ነው! ጉዳዮቹ ሁሉ ለእርሱ መልካም ናቸው። ይህም ለሙእሚን እንጂ ለሌላ አይሆንም። መልካም ነገር ሲገጥመውም አላህን ያመሰግንና ነገሩ መልካም ይሆንለታል። መጥፎ ነገር ሲደርስበትም ትዕግስትን ይላበስና ነገሩም ለርሱ መልካም ይሆንለታል።"
ቀደርን በተመለከተ ሁለት ጭፍሮች አፈንግጠዋል።
አንደኛው፡ የሰው ልጅ ስራውን ሁሉ ተገዶ ነው የሚሠራው የሚሉ "ጀብሪያዎች" ናቸው። እንደነሱ አባባል የሰው ልጅ ምንም ግላዊ ፍቃድም ይሁን የተሰጠው አቅም የለው።
ሁለተኛ፡- "ቀደሪያ" የሚባሉ ሲሆኑ በነሱ አባባል መሰረት እያንዳንዱ ሰው ሙሉ ለሙሉ ራሱን የቻለ ነፃ ፈቃድና ኃይል እንዳለው እንዲሁም የአላህ ፈቃድና ኃይልም በሰው ፈቃድና አቅም ላይ ምንም የሚያሳድረው ተፅዕኖ እንደሌለ ይናገራሉ።
ለመጀመሪያው ጭፍራ ለ "ጀብሪያዎች" ከሸሪዓውም ይሁን እና ከተጨባጩ እውነታ ምላሻችንን እንደሚከተለው እንሰጣለን፡
ሸሪዓዊ ምላሻችንን በተመለከተ፡- የላቀው አላህ የሰው ልጅ የራሱ ፍቃድና ፍላጎት እንዳለው ከማረጋገጥም ባሻገር ድርጊትንም ወደ አድራጊው እያስጠጋ ገልጿል፤ የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿...مِنكُم مَّن يُرِيدُ ٱلدُّنۡيَا وَمِنكُم مَّن يُرِيدُ ٱلۡأٓخِرَةَۚ...﴾
{ከእናንተ ውስጥ ቅርቢቱን ዓለም የሚሻ አለ። ከእናንተም የመጨረሻይቱን ዓለም የሚሻ አልለ።}
[አሊ-ዒምራን፡ 152] የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَقُلِ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكُمۡۖ فَمَن شَآءَ فَلۡيُؤۡمِن وَمَن شَآءَ فَلۡيَكۡفُرۡۚ إِنَّآ أَعۡتَدۡنَا لِلظَّٰلِمِينَ نَارًا أَحَاطَ بِهِمۡ سُرَادِقُهَاۚ...﴾
{«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ» በላቸው፡፡ እኛ ለበደለኞች አጥሯ በእነሱ የከበበ የኾነችውን እሳት አዘጋጅተናል። } [አል-ከህፍ፡ 29]
የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿مَّنۡ عَمِلَ صَٰلِحٗا فَلِنَفۡسِهِۦۖ وَمَنۡ أَسَآءَ فَعَلَيۡهَاۗ وَمَا رَبُّكَ بِظَلَّٰمٖ لِّلۡعَبِيدِ 46﴾
{ መልካም የሠራ ሰው ለነፍሱ ነው፡፡ ያጠፋም ሰው በእርሷ ላይ ነው፡፡ ጌታህም ለባሮቹ በዳይ አይደለም።} [ፉሲለት፡ 46]
ከተጨባጩ እውነታ ምላሻችን ደሞ፡ ሁሉም ሰው በፈቃዱ በሚፈጽማቸው እንደ መብላት፣ መጠጣት፣ መግዛትና መሸጥ አይነት ጉዳዮቹ እና ያለምርጫው ተገዶ በሚያደርጋቸው ተግባራቱ እንደመንቀጥቀጥ፣ ትኩሳት፣ ከከፍተኛ ቦታ መውደቅ አይነት ድርጊቶቹ መካከል ያለውን ልዩነት ያውቃል። በመጀመርያው ጉዳዩ ላይ አስገዳጅ ሳይኖርበት ሆን ብሎ በራሱ ፍቃድ የሚፈጽም አይነት ድርጊት ሲሆን በሁለተኛው ጉዳይ ላይ ግን ምንም የራሱ ፍቃድ ሳይኖር የሚከሰትበት ነው።
ለሁለተኛው ጭፍራ ለ "ቀደርያዎች" ከሸሪዓውም ይሁን እና ከተጨባጩ እውነታ ምላሻችንን እንደሚከተለው እንሰጣለን፡
ሸሪዓዊ ምላሻችንን በተመለከተ፡- ሁሉንም ነገር የፈጠረው የላቀው አላህ ሲሆን የፈጠረውም በፈቃዱ ነው። ሁሉም ነገር የሚከሰተው በእርሱ ፈቃድ መሆኑንም በቁርአን ገልጿል፤ የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿...وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَا ٱقۡتَتَلَ ٱلَّذِينَ مِنۢ بَعۡدِهِم مِّنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَتۡهُمُ ٱلۡبَيِّنَٰتُ وَلَٰكِنِ ٱخۡتَلَفُواْ فَمِنۡهُم مَّنۡ ءَامَنَ وَمِنۡهُم مَّن كَفَرَۚ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَا ٱقۡتَتَلُواْ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَفۡعَلُ مَا يُرِيدُ﴾
{አላህ በሻ ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ (ከመልክተኞቹ) በኋላ የነበሩት ግልጽ ታምራቶች ከመጡላቸው በኋላ ባልተጋደሉ ነበር፡፡ ግን ተለያዩ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ያመነ ሰው አልለ፡፡ ከነርሱም ውስጥ የካደ ሰው አልለ፡፡ አላህ በሻ ኖሮ ባልተዋጉ (ባልተለያዩ) ነበር፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ይሠራል።}
[አል-በቀራህ፡ 253]
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَلَوۡ شِئۡنَا لَأٓتَيۡنَا كُلَّ نَفۡسٍ هُدَىٰهَا وَلَٰكِنۡ حَقَّ ٱلۡقَوۡلُ مِنِّي لَأَمۡلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ ٱلۡجِنَّةِ وَٱلنَّاسِ أَجۡمَعِينَ 13﴾
{በሻንም ኖሮ ነፍስን ሁሉ ቅንነቷን (እምነቷን) በሰጠናት ነበር፡፡ ግን ገሀነምን ከአጋንንትና ከሰዎች የተሰበሰቡ ሆነው በእርግጥ እሞላለሁ ማለት ቃሉ ከእኔ ተረጋግጧል።}
[አስ-ሰጅዳ: 13]
አዕምሯዊ ማስረጃችን ደሞ፡- ሙሉ አጽናፈ ዓለሙ የአላህ ግዛት ነው፤ የሰው ልጅም የዚህ አጽናፈ አለም አንድ አካል ነው፤ ስለዚህም የሰው ልጅም የልዕለ ኋያሉ አሏህ ግዛት ነው። በጌታው ግዛት ስር ያለ ባሪያ ደሞ በጌታው ግዛት ስር እስከሆነ ድረስ ያለ ጌታው ፈቃድና ፍላጎት ምንም ማድረግ አይችልም።
የኢስላማዊ እምነት አላማዎች
አላማ በቋንቋ ደረጃ የተለያየ ትርጉም ያለው ሲሆን የነገሮች ተፈላጊ ውጤት አንዱ ትርጉሙ ነው።
የኢስላማዊው እምነት ተፈላጊ ውጤቶች ስንል እምነቱን አጥብቀን የመያዛችን ትርፍና መልካም ውጤቶችን ለመግለፅ ነው። እነዚህ ውጤቶች በርከት ያሉና የተለያዩ ናቸው። ከነዚህም መካከል፡
አንደኛ፡ ኒያንና ኢኽላስን ለላቀው አሏህ ብቻ ጥርት ለማድረግ ያግዛል። ምክንያቱም ፈጣሪያችን አሏህ ተጋሪ የሌለው ብቸኛ አምላክ በመሆኑ በአምልኮም ይሁን በኒያ እሱን ብቻ ማሰብ አለብንና።
ሁለተኛ፡ እስላማዊ እምነት ትክክለኛ እምነት የሌላቸው ሰዎችን ከሚገጥማቸው ውዝግብና ግራ መጋባት ነፃ ያወጣቸዋል። ምክንያቱም ይህ ትክክለኛ እምነት የሌለው ልብ ወይ ባዶ እምነት የሆነ ቁስ አምላኪ ነው፤ አለበለዚያም በተሳሳቱ እና ከንቱ በሆኑ እምነቶች መካከል ግራ ተጋብቶ የሚንከራተት ነው።
ሦስተኛ፡- የአዕምሮ ሰላም እና የነፍስ እርካታን ያስገኛል፤ አዕምሮም አይወዛገብም ነፍስም አትጨናነቅም። ምክንያቱም ይህ እምነት ፍጡርን ከፈጣሪ ጋር የሚያቆራኝ በመሆኑ አሏህን በጌትነቱ፣ በፈራጅነቱና በደንጋጊነቱ ወዶ መቀበልን ያድለዋል። በዚህም ልቦናው ቀደርን ወዶ በመቀበል ይደሰታል፤ ከእስልምና ውጭ ሌላ አማራጭ በማይፈልግበት ልክም ለእስልምና ክፍት ይሆናል።
አራተኛ፡- የላቀው አሏህን በማምለክና ፍጡራን ጋር ያለንን መስተጋብር እንዳይበላሽ በማስተካከል ረገድ ኒያንና ተግባርን በንፁህ ቀልብ ለማድረግ ያግዛል። ምክንያቱም ከዚህ እምነት መሰረታዊ መርሆች መካከል አንዱ በሃሳባቸውም ይሁን በተግባራቸው ቅን በሆኑት መልእክተኞች ማመን እና መንገዳቸውንም መከተል ተጠቃሽ ነውና።
አምስተኛ፡ እያንዳንዱን አጋጣሚ ለበጎ ስራ በማዋል ምንዳን ለማግኘት ሲባል በጉዳዮቻችን ላይ ቁርጠኝነትንና አለመቀለድን ያላብሳል። ይህም የኃጢያት ቦታዎችን የአሏህን ቅጣት በመፍራት እንድንርቅ ያደርገናል፤ ምክንያቱም ከዚህ እምነት መሰረቶች መካከል አንዱ በትንሳኤ እና በስራ መመንዳት እንዳለ ማመን ይገኝበታልና።
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَلِكُلّٖ دَرَجَٰتٞ مِّمَّا عَمِلُواْۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَٰفِلٍ عَمَّا يَعۡمَلُونَ 132﴾
{ለሁሉም ከሠሩት ሥራ (የተበላለጡ) ደረጃዎች አልሏቸው፡፡ ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም።} [አል-አንዓም፡ 132]
«الْمُؤْمِنُ الْقَوِيُّ خَيْرٌ وَأَحَبُّ إِلَى اللَّهِ مِنَ الْمُؤْمِنِ الضَّعِيفِ، وَفِي كُلٍّ خَيْرٌ، احْرِصْ عَلَى مَا يَنْفَعُكَ، وَاسْتَعِنْ بِاللَّهِ، وَلَا تَعْجِزْ، وَإِنْ أَصَابَكَ شَيْءٌ فَلَا تَقُلْ: لَوْ أَنِّي فَعَلْتُ كَذَا كَانَ كَذَا وَكَذَا، وَلَكِنْ قُلْ: قَدَّرَ اللَّهُ وَمَا شَاءَ فَعَلَ؛ فَإِنَّ (لَوْ) تَفْتَحُ عَمَلَ الشَّيْطَانِ».
ነቢዩም ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲህ በማለት አነሳስተዋል፡ "በሁሉም መልካም ነገር ቢኖርም ጠንካራው ሙእሚን ከደካማው ሙእሚን የተሻለና አሏህ ዘንድም የተወደደ ነው። በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ! በአሏህ ታገዝ! አትስነፍ! ምናልባት አንዳች ነገር የገጠመህ እንደሁ 'እንዲህ እንዲህ ባድረግ ኖሮ እንዲህ ይሆን ነበር' አትበል! ይልቁንም 'አሏህ ወሰነው፤ የሻውንም አደረገ' በል! ምክንያቱም ቢሆን ኖሮ የሚለው አባባል የሸይጧንን በር የሚከፍት ነውና።" (ሙስሊም ዘግበውታል)
ስድስተኛ፡ መንገዱ ላይ የሚመጣበት መሰናክል ምንም ሳይበግረው ውዱንም ይሁን ርካሹን ሁሉ ሃይማኖቱን ለማጠንከርና መሰረቱን ለማፅናት ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ የሆነ ብርቱ ማህበረሰብ ያንፃል። ይህንንም በተመለከተ የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿إِنَّمَا ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ ثُمَّ لَمۡ يَرۡتَابُواْ وَجَٰهَدُواْ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِۚ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلصَّٰدِقُونَ 15﴾
{(እውነተኛዎቹ) ምእምናን እነዚያ በአላህና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፡፡ እነዚያ እነሱ እውነተኞቹ ናቸው።} [አል-ሑጁራት፡ 15]
ሰባተኛ፡ ግለሰብንም ይሁን ማህበረሰብን በማስተካከል ለዱኒያዊም ይሁን ለአኺራዊ ስኬት ያድላል፤ ምንዳንና ክብርንም ያጎናፅፋል። ይህንንም በተመለከተ የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡
﴿مَنۡ عَمِلَ صَٰلِحٗا مِّن ذَكَرٍ أَوۡ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَلَنُحۡيِيَنَّهُۥ حَيَوٰةٗ طَيِّبَةٗۖ وَلَنَجۡزِيَنَّهُمۡ أَجۡرَهُم بِأَحۡسَنِ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ 97﴾
{ ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን።}
[አን-ነሕል፡ 97]
የኢስላማዊው ዓቂዳ አላማዎች በከፊል እነዚህን ይመስላሉ። አሏህ እኛ ላይም ይሁን መላው ሙስሊም ላይ እነዚህን በጎ አላማዎች እውን ያደርግልን ዘንድ እንማፀነዋለን። እነሆ እርሱ ቸርና ለጋስ ነውና። ምስጋና ባጠቃላይ ለአሏህ የተገባ ነው።
የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በነቢያችን ሙሐመድ፣ በተከታዮቻቸውና በባልደረቦቻቸውም ላይ ሁሉ ይስፈን።
ተጠናቀቀ በአዘጋጁ
ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን
***
ማውጫ
መግቢያ 2
የእስልምና ሃይማኖት 4
የኢስላም ማእዘናት 10
የእስልምና እምነት መሰረቶች 15
በላቀው አሏህ ማመን 16
በመላእክቶች ማመን 37
በመጻሕፍቱ ማመን 45
በመልዕክተኞች ማመን 47
በመጨረሻው ቀን ማመን 57
በቀደር ማመን 80
የኢስላማዊ እምነት አላማዎች 94
***
am71v1.0 - 24/06/2026