حِرَاسَةُ التَّوحِيدِ
የተዋሕዶ ጥበቃ
لِسَمَاحَةِ الشَّيْخِ العَلَّامَةِ
عَبْدِ العَزِيزِ بْنِ عَبْدِ اللهِ بْنِ بَازٍ
رَحِمَهُ اللهُ
ዝግጅት፦ የተከበሩ ሸይኽ
ዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ
بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ
የመጀመሪያው መልዕክት:
ትክክለኛ ዐቂዳ እና ተቃራኒው
ዝግጅት፦ የተከበሩ ሸይኽ
ዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ
ምስጋና ሁሉ ለብቸኛው አላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላትና ሰላም ከእሳቸው በኋላ ነብይ የሌለ በሆኑት ነብይ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸውም ላይ ይስፈን።
በመቀጠል፦ ትክክለኛው ዓቂዳ (እምነት) የእስልምና መሰረት እና የሃይማኖቱም ምሰሶ በመሆኑ፣ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ መነጋገር እንዲሁም እሱን በማብራራትና ግልጽ በማድረግ ላይ መጻፍና ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
ከቁርኣንና ሐዲሥ ሸሪዓዊ ማስረጃዎች መረዳት እንደሚቻለው፤ ተግባራትና ንግግሮች ትክክል የሚሆኑትና ተቀባይነት የሚያገኙት ከትክክለኛ ዐቂዳ (እምነት) ሲመነጩ ነው። ዐቂዳው ትክክለኛ ካልሆነ ግን የእርሷ ቅርንጫፍ የሆኑት ተግባራትና ንግግሮች ውድቅ ይሆናሉ። የበላይ የሆነው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿...وَمَن يَكۡفُرۡ بِٱلۡإِيمَٰنِ فَقَدۡ حَبِطَ عَمَلُهُۥ وَهُوَ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ﴾
{በአላህ ካመነ በኋላ ከእምነቱ ወደ ክህደት የሚመለስ ሁሉ በእርግጥ ስራው ተበላሸ:: በመጨረሻም ቀን ከከሳሪዎች ነው::} [አል ማኢዳህ፥5]
የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَلَقَدۡ أُوحِيَ إِلَيۡكَ وَإِلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكَ لَئِنۡ أَشۡرَكۡتَ لَيَحۡبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ 65﴾
{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብታጋራ ስራህ በእርግጥ ይታበሳል:: በእርግጥም ከከሓዲያን ትሆናለህ በማለት ወደ አንተና እነዚያ ካንተ በፊት ወደ ነበሩት በእርግጥ ተወርዷል::} [አዝ-ዙመር፡ 65]
በዚህ ዙሪያ የመጡ ቁርአናዊ ማስረጃዎች በርካት ናቸው። ግልፅ የሆነው የአላህ መፅሀፍና የታማኙ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን )ሱና እንዳመላከቱት፤ ትክክለኛው እምነት በስድስት ነገሮች ይጠቃለላል። እነርሱም፦ በአላህ፣ በመላዕክቶቹ፣ በመጽህፍቶቹ፣ በመልዕክተኞቹ፣ በመጨረሻው ቀን፣ እና በጥሩውም ይሁን በመጥፎው የአላህ ቅድመ ውሳኔ (በቀደር) ማመን ናቸው። እነኝህ ስድስቱ ነገሮች አላህ መጽሐፍት ያወረደባቸው መልዕክተኛው ሙሐመድንም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የላከበት የትክክለኛው እምነት መሰረቶች ናቸው።
እነዚህን ስድስት መሰረቶች በተመለከተ በቁርኣንና ትክክለኛ በሆነው ሱንና (ሐዲሥ) ላይ በርካታ ማስረጃዎች መጥተዋል። ከነዚህም መካከል ለምሳሌ የሚከተሉት ይገኙበታል፦
አንደኛ: ቁርአናዊ ማስረጃዎች: አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿لَّيۡسَ ٱلۡبِرَّ أَن تُوَلُّواْ وُجُوهَكُمۡ قِبَلَ ٱلۡمَشۡرِقِ وَٱلۡمَغۡرِبِ وَلَٰكِنَّ ٱلۡبِرَّ مَنۡ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ وَٱلۡكِتَٰبِ وَٱلنَّبِيِّـۧنَ...﴾
{መልካም ስራ ፊቶቻችሁን ወደ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞር አይደለም። ግን መልካም ስራ በአላህ፣ በመጨረሻው ቀን፣ በመላዕክት፣ በመጻሕፍት፣ በነብያት ያመነ፤…} [አል-በቀራህ፥177]
ጥራት የተገባውና የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿ءَامَنَ ٱلرَّسُولُ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيۡهِ مِن رَّبِّهِۦ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَۚ كُلٌّ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَكُتُبِهِۦ وَرُسُلِهِۦ لَا نُفَرِّقُ بَيۡنَ أَحَدٖ مِّن رُّسُلِهِ...﴾
{መልዕክተኛው (ሙሐመድ) ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደለት (ቁርኣን) አመነ:: አማኞችም እንደዚሁ አመኑ:: ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱ፣ በመጽሐፍቱና በመልዕክተኞቹ «ከእነርሱ በአንዱም መካከል አንለይም (አንክድም)» የሚሉ ሲሆኑ አመኑ::} [አል-በቀራህ:285]
የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ ءَامِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَٱلۡكِتَٰبِ ٱلَّذِي نَزَّلَ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ وَٱلۡكِتَٰبِ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ مِن قَبۡلُۚ وَمَن يَكۡفُرۡ بِٱللَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَكُتُبِهِۦ وَرُسُلِهِۦ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ فَقَدۡ ضَلَّ ضَلَٰلَۢا بَعِيدًا 136﴾
{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልዕክተኛው በዚያ በመልዕክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍም በዚያም ከበፊቱም ባወረደው መጽሐፍ እመኑ:: በአላህ፣ በመላዕክቱ፣ በመጽሐፍቱ፣ በመልዕክተኞቹና በመጨረሻውም ቀን የካደ ሁሉ ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ።} [አን-ኒሳእ: 136]
የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿أَلَمۡ تَعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا فِي ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِۚ إِنَّ ذَٰلِكَ فِي كِتَٰبٍۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٞ 70﴾
{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ በእርግጥ የሚያውቅ መሆኑን አታውቅምን? ይህ በመጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ እውነት ነው:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነው::} [አል'ሐጅ፡ 70]
ሁለተኛ፦ ሐዲሣዊ ማስረጃዎች፤ ከነዚህም መካከል ሙስሊም በሰሒሕ ኪታባቸው ላይ ከምእመናን መሪ (አሚረል ሙእሚኒን) ዑመር ኢብኑል ኸጣብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የዘገቡትና ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ነቢዩን - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ስለ ኢማን የጠየቀበት የታወቀው ሰሒሕ ሐዲሥ ይገኝበታል፤ በሐዲሡም ጅብሪል ነብዩን - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ስለ ኢማን ሲጠይቃቸው እንዲህ ብለውታል፦
«الإِيمَانُ أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَاليَوْمِ الآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ».
«ኢማን ማለት በአላህ፣ በመላእክቱ፣ በመጻሕፍቱ፣ በመልዕክተኞቹ እና በመጨረሻው ቀን ማመን እና በቀደር መልካምም ይሁን መጥፎው ማመን ነው።»1 ሐዲሥ ቡኻሪ እና ሙስሊም በጥቂት የቃላት ልዩነት ከአቡ ሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ ዘግበውታል።
ማንኛውም ሙስሊም ስለ አላህ፣ ስለ ቂያማ ቀን ጉዳይ እና ከዚህ ውጭ ያሉም የግድ ማመን ያለበት አላህና መልእክተኛው - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የተናገሯቸው ሌሎች የሩቅ ምስጢር ጉዳዮች ሁሉ ከነዚህ ስድስቱ መሰረቶች የሚውጣጣ ነው።
የእነዚህ ስድስቱ መሰረቶች ማብራሪያም እንደሚከተለው ነው፡
የመጀመሪያው መሰረት: የበላይ በሆነው አላህ ማመን
ይህም በርካታ ጉዳዮችን ይዟል፤ ከእነዚህም መካከል፦ የባሮቹ ፈጣሪ፣ በጎ የሚውልላቸው፣ ሲሳይንም የሚለግሳቸው፣ ድብቅም ሆነ ግልፅ ማንነታቸውን ጠንቅቆ የሚያውቅላቸው፤ ከመካከላቸው መልካሞቹን የሚመነዳ ክፉዎቹንም የሚቀጣ በመሆኑ እርሱ እውነተኛ እና ያለ ምንም ተጋሪ በብቸኝነት ሊመለክ የሚገባው አምላክ መሆኑን ማመን ነው።
አላህ ሁለቱን ከባባድ ፍጡሮች (ጂኒን እና ሰውን) የፈጠራቸው ለዚሁ አምልኮ ነው፤ በዚህም አዟቸዋል፤ አላህ እንዲህ ብሏል:-
﴿وَمَا خَلَقۡتُ ٱلۡجِنَّ وَٱلۡإِنسَ إِلَّا لِيَعۡبُدُونِ 56 مَآ أُرِيدُ مِنۡهُم مِّن رِّزۡقٖ وَمَآ أُرِيدُ أَن يُطۡعِمُونِ 57 إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلرَّزَّاقُ ذُو ٱلۡقُوَّةِ ٱلۡمَتِينُ 58﴾
{ጂኒንና ሰዉን ሊገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸዉም::
ከእነርሱም ምንም ሲሳይን አልፈልግም:: እንዲመግቡኝም አልፈልግም::
አላህ እርሱ ሰጪና የብርቱ ሀይል ባለቤት ነውና።} [አዝ-ዛሪያት: 56-58]
የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱعۡبُدُواْ رَبَّكُمُ ٱلَّذِي خَلَقَكُمۡ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ 21 ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَرۡضَ فِرَٰشٗا وَٱلسَّمَآءَ بِنَآءٗ وَأَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَخۡرَجَ بِهِۦ مِنَ ٱلثَّمَرَٰتِ رِزۡقٗا لَّكُمۡۖ فَلَا تَجۡعَلُواْ لِلَّهِ أَندَادٗا وَأَنتُمۡ تَعۡلَمُونَ 22﴾
{እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተንና እነዚያን ከናንተ በፊት የነበሩትንም የፈጠረውን ጌታችሁን (አላህን) በብቸኝነት ተገዙት:: ቅጣትን ልትጠነቀቁ ይከጀላልና።
እርሱ (አላህ) ያ ለእናንተ ምድርን ምንጣፍ፤ ሰማይን ጣራ ያደረገ ጌታ ነው::ከሰማይም (ከዳመና) ውሃን ያወረደና በርሱም (በውሃው) ከፍሬዎች ሁሉ ለእናንተ ሲሳይን ያወጣላችሁ ነው:: እናንተም (ብቸኛ ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትሆኑ ለአላህ (በአምልኮ) ባላንጣዎችን አታድርጉ፡፡} [አል-በቀራህ: 21-22]
ይህንኑ እውነታ እንዲያብራሩ፤ ወደዚህም ጥሪ እንዲያደርጉ፤ ከሚፃረረውም እንዲያስጠነቅቁ የላቀው አላህ መልእክተኞችን ልኮ መጽሐፎችን አውርዷል። ጥራት የተገባውና የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿وَلَقَدۡ بَعَثۡنَا فِي كُلِّ أُمَّةٖ رَّسُولًا أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَٱجۡتَنِبُواْ ٱلطَّٰغُوتَ...﴾
{በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትንም ራቁ በማለት (የሚያስተምሩ) መልዕክተኛን በእርግጥ ልከናል...} [አን-ነሕል፡ 36]
ጥራት የተገባው አላህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَمَآ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِيٓ إِلَيۡهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعۡبُدُونِ 25﴾
{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጂ ከመልዕክተኛ አንድንም አላክንም::} [አል-አንቢያእ፡ 25]
አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿الر كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِنْ لَدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ1 أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ إِنَّنِي لَكُمْ مِنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ2﴾
{አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤. ይህ ቁርኣን አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሀፍ ነው፤ ጥበበኛና ውስጠ አዋቂ ከሆነው (አምላክ) ዘንድ የተወረደ ነው::
(እንዲህ በላቸው): «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ:: እኔ ለእናንተ ከእርሱ ዘንድ የተላኩ አስፈራሪና አብሳሪ ነኝ።» [ሁድ: 1-2]
የዚህ አምልኮ እውነተኛ መገለጫ፡- በዱዓ፣ በፍራቻ፣ በተስፋ፣ በሰላት፣ በፆም፣ በእርድ፣ በስለት እና ከእነዚህ ውጭ ባሉ ሌሎች የአምልኮ ዓይነቶች ሁሉ፣ ለእርሱ በመተናነስ፣ ምንዳውን በመከጀልና ከቅጣቱ በመፍራት እንዲሁም ለእርሱ የተሟላ ውዴታንና ለልቅናው መዋረድን በተላበሰ መልኩ የበላይ የሆነውን አላህን ብቸኛ አድርጎ ማምለክ ነው።
የተከበረውን ቁርኣን ያስተነተነ ሰው አብዛኛው የቁርአን ክፍል በዚህ ታላቅ መሰረት ላይ እንደወረደ ያገኛል፤ ለምሳሌ ከእንከን የጠራውና የላቀው ጌታችን እንዲህ ብሏል፦
﴿إِنَّآ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ فَاعْبُدِ اللَّهَ مُخْلِصًا لَهُ الدِّينَ 2 أَلَا لِلَّهِ الدِّينُ الْخَالِصُ وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَ مَا نَعۡبُدُهُمۡ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَآ إِلَى ٱللَّهِ زُلۡفَىٰٓ إِنَّ ٱللَّهَ يَحۡكُمُ بَيۡنَهُمۡ فِي مَا هُمۡ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي مَنۡ هُوَ كَٰذِبٞ كَفَّارٞ3﴾
{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት የተሞላ ሲሆን አወረድነው:: አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ሆነህ ተገዛው::
ንቁ! ፍጹም ጥሩ የሆነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድረገው የያዙት ሁሉ «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን በማሰብ እንጂ ለሌላ አንገዛቸዉም።» ይላሉ:: አላህ በዚያ እነርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል:: አላህም ውሸታም ከሓዲ የሆነን ሰው አያቀናም::} [አዝ-ዙመር: 2-3]
ጥራት የተገባውና የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّآ إِيَّاهُ...﴾
{ጌታህም እንዲህ ሲል አዘዘ:: እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤…} [አል-ኢስራእ፡ 23]
አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿فَٱدۡعُواْ ٱللَّهَ مُخۡلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡكَٰفِرُونَ14﴾
{አላህንም ከሓዲያን ቢጠሉም (እንኳ) ሃይማኖትን ለእርሱ አጥሪዎች ሆናችሁ ተገዙ::} [ጋፊር: 14]
እንደዚሁም የነብዩን ሐዲሦች ያጤነ ለዚህ ታላቅ መሠረት ትልቅ ትኩረት እንደተሰጠው ይገነዘባል። ከዚህም መካከል በሶሒሕ ቡኻሪና ሙስሊም ከሙዓዝ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በተላለፈ ሐዲሥ ነቢዩ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦
«حَقُّ اللهِ عَلَى العِبَادِ أَن يَعْبُدُوهُ وَلَا يُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا».
"አላህ በባሮቹ ላይ ያለው መብት በእርሱ ላይ ምንንም ሳያጋሩ በብቸኝነት ሊያመልኩት ነው።"(2)2
እንዲሁም በአላህ ማመን ውስጥ ከሚካተቱ ነገሮች መካከል፦ አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ባደረገባቸውና በደነገገላቸው እንደ አምስቱ ግልፅ የእስልምና ማእዘናት ባሉት ሁሉ ማመን አንዱ ነው።
እነሱም፦ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን እና ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መመስከር፣ ሶላትን ደንብና ሥርዓቱን ጠብቆ መስገድ፣ ዘካ መስጠት፣ የረመዳንን ወር መጾም፣ አቅሙ ለቻለ ሰው የተከበረውን የአላህን ቤት ሐጅ ማድረግ እና የጠራው ሸሪዓ በደነገጋቸው ሌሎችም ግዴታዎች ማመን ነው።
ከእነዚህ ማዕዘናት ውስጥ ዋነኛውና ትልቁ፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው ሌላ አምላክ አለመኖሩንና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር ነው። ይህቺም የምስክርነት ቃል የምታስፈርደው፡ አላህን ብቻ መገዛትን እና ሌላ ማንኛውንም ነገር ከመገዛት መቆጠብን ነው። ይህም የ«ላኢላሃ ኢለሏህ» ትርጉም ነው፤ ትርጉሙም - ዑለማዎች አላህ ይዘንላቸውና እንዳሉት፡ «ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም» ማለት ነው። በዚህ ላይ ተመስርቶም፡ ከአላህ ውጭ የሚመለክ ነገር ሁሉ - ሰውም ይሁን መልአክ፣ ጂኒም ሆነ ሌላ - የሚመለከው በውሸት ነው። በእውነት የሚመለከውም አጋር የሌለው አላህ ብቻ ነው። ጥራት የተገባውና የላቀው (አላህ) እንዲህ ብሏል፡-
﴿ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ هُوَ ٱلۡبَٰطِلُ...﴾
{ይህ የሆነው አላህም ፍፁም እውነት በመሆኑ፤ ከርሱም ሌላ የሚገዙት ነገር ፍጹም ውሸት በመሆኑ...} [አል'ሐጅ፡ 62]
ጥራት የተገባው አላህ ሁለቱን ከባባድ ፍጥረታት ለዚሁ ቀዳሚ መርሕ ብሎ የፈጠረ፣ በእርሱም ያዘዛቸው፣ መልዕክተኞቹንም የላከ፣ ኪታቦቹንም ያወረደ መሆኑ ቀደም ብሎ ተብራርቷል። ስለሆነም አንድ ባሪያ ይህንን ቁም ነገር በደንብ ሊያስተውለውና ደጋግሞም ሊያስተነትነው ይገባል፤ ይሄንን ካስታዋለ ብዙሀኑ ሙስሊሞች በዚህ መሰረታዊ ነገር ላይ የወደቁበት ከባድ አላዋቂነት ፍንትው ብሎ ይታየዋል፤ ከአላህ ጋር ሌሎችን እስከማምለክና የእርሱን ብቸኛ መብት ከእርሱ ውጪ ላሉ አካላት እስከመስጠትም ደርሰዋል። አሏሁል ሙስተዓን
ጥራት በተገባው አላህ ከማመን መካከል: አላህ የዓለም ፈጣሪ፣ የጉዳዮቻቸው አስተናባሪ፣ በዕውቀቱም በኃይሉም እንደፍላጎቱ አድርጎ የሚያስተዳድራቸው መሆኑን፤ እንዲሁም እርሱ የዱኒያውም የአኺራውም ባለቤት መሆኑን፤ ከእርሱ ውጭ ፈጣሪ የሌለ ከእርሱም ውጭ ጌታ የሌለ ብቸኛ መሆኑንም ማመን ይገኝበታል። እንዲሁም አላህ ባሮችን ለማረምና፣ በቅርቢቱም (በዱንያ) ሆነ በመጪው ዓለም (በኣኺራ) መዳናቸውና መበጀታቸው (ደህንነታቸው/ስኬታቸው) ወዳለበት ነገር እነርሱን ለመጥራት ሲል፤ መልእክተኞችን እንደላከና መጽሐፍትንም እንዳወረደ (ያምናሉ)።»
ጥራት የተገባውና የላቀው አላህ በዚህ ሁሉ ምንም ተጋሪ የለውም። ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَيۡءٖۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ وَكِيلٞ 62﴾
{አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው::} [አዝ-ዙመር፡ 62]
የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ يُغۡشِي ٱلَّيۡلَ ٱلنَّهَارَ يَطۡلُبُهُۥ حَثِيثٗا وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ وَٱلنُّجُومَ مُسَخَّرَٰتِۭ بِأَمۡرِهِۦٓۗ أَلَا لَهُ ٱلۡخَلۡقُ وَٱلۡأَمۡرُۗ تَبَارَكَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ54﴾
{(ሰዎች ሆይ) ጌታችሁ አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረና ከዚያም በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ ነው። ቀኑንም በሌሊቱ ይሸፍነዋል:: ሁለቱም እርስ በእርስ በፍጥነት ይፈላለጋሉ:: ጸሐይ ጨረቃና ከዋክብት በትዕዛዙ የተገሩ ናቸው። አስተውሉ! መፍጠርም ማዘዝም የእርሱ (የአላህ) ነው:: የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ክብሩ ላቀ::} [አል'አዕራፍ፡ 54]
በላቀው አላህ ማመን ውስጥ ከሚካተት ነገር መካከል፦ በታላቁ ቁርአን ውስጥ በመጡና ከታማኙ መልዕክተኛው በተረጋገጡ የተዋቡ የአላህ ስሞች እና ታላላቅ ባህሪያት፤ ያለ ማዛባት፣ ውድቅ ሳያደርጉ፣ አኳኋኑን ሳይገልፁ እና ከማንም ጋር ሳያመሳስሉ ማመን ነው።
﴿...لَيۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَيۡءٞۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ﴾
{የሚመስለው ምንም ነገር የለም:: እርሱ ሁሉን ነገር ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነው::} [አሽ ሹራ፡ 11]
ልክ በመጣበት መልኩ ‹እንዴት ነው?› ሳይባል (ያለ ከይፍ) እንዲያልፉ ማድረግ ግዴታ ነው። እንዲሁም በመጣበት መልኩ አኳኋኑን ሳይገልፁ መቀበል፣ በሚያመለክቷቸው ታላላቅ ፍቺዎችም -ለሀያሉና የላቀው አላህ መገለጫዎች በሆኑት- ማመን፣ እንዲሁም ማናቸውንም ባህሪያቱ ከፍጡራኑ ጋር ሳያመሳስሉት ለእርሱ በሚገባው መልኩ መግለጽ ግዴታ ነው። ልክ (ከፍ ያለው) አላህ እንደተናገረው።
አሸናፊና ኃያሉ አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿فَلَا تَضۡرِبُواْ لِلَّهِ ٱلۡأَمۡثَالَۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ وَأَنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ74﴾
{ለአላህ አምሳያዎችን አታድርጉ:: አላህ ያውቃል፤ እናንተ ግን አታውቁም::} [አን'ነሕል፡ 74]
ይህች እንግዲህ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ባልደረቦች እና ቅን ተከታዮቻቸው የሆኑት አህለ ሱና ወል-ጀማዓዎች በአላህ ስሞችና ባህሪያት ላይ ያላቸው እምነት ነች። ኢማሙ አቡ አል-ሐሰን አል-አሽዓሪይ አላህ ይዘንላቸውና በ“አልመቃላት” ኪታባቸው ላይ ከአስሓቡል ሐዲሥና ከአህሉ ሱና ያስተላለፉት ሌሎችም የዒልምና የኢማን ሰዎችም ያስተላለፉት አቋም ነች።
አል-አውዛዒይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡- አዝ-ዙህሪይ እና መክሑልም የአላህን ባህሪያት ስለሚገልፁ አንቀጾች ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦ "እንደ አመጣጡ አሳልፉት።"3
አል-አውዛዒይ አላህ ይዘንላቸውና በድጋሚ እንዲህ ብለዋል፦ (በርካታ ታቢዒዮች በነበሩበት ወቅት ጥራት የተገባው አላህ ከዐርሹ በላይ ነው፤ በሓዲሥ በተጠቀሱት የአላህ ባህሪያትም እናምናለን እንል ነበር።)4
አል-ወሊድ ቢን ሙስሊም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህም ብለዋል፦ ማሊክ፣ አል-አውዛዒይ፣ አል-ለይሥ ቢን ሰዕድ እና ሱፍያን አሥ-ሠውሪይ አላህ ይዘንላቸውና የአላህን ባህሪያት የሚገልፁ አንቀፆች በተመለከተ ተጠይቀው ሁሉም በጋራ እንዲህ አሉ፦ "አኳኋኑን ሳትገልፁ ልክ እንደመጣው አፅድቁት።"5
የማሊክ ሸይኽ የሆኑት ረቢዓህ ኢብኑ አቢ ዐብዱረሕማን ሁለቱንም አላህ ይዘንላቸውና ስለ ኢስቲዋእ (ከዐርሽ በላይ ስለመሆኑ) ሲጠየቁ እንዲህ አሉ፡- (አል-ኢስቲዋእ የታወቀ ነው፤ አኳኋኑ በአዕምሮ የሚደረስበት አይደለም፤ መልእክቱ ከአላህ ዘንድ የመጣ ነው፤ መልዕክተኛው የሚጠበቅበት ግልጽ አድርጎ ማድረስ ነው፤ ማመኑ የኛ ፋንታ (ግዴታ) ነው።)6፣ በዚሁ ጉዳይ ኢማሙ ማሊክ አላህ ይዘንላቸውና በተጠየቁ ጊዜም እንዲህ አሉ: (አል-ኢስቲዋእ የታወቀ ነው፤ አኳኋኑ በአዕምሮ የማይደረስበት ነው፤ ማመኑ ግዴታ ነው፤ ስለ ጉዳዩ -በዚህ መልኩ- መጠየቅ ቢድአ (ፈጠራ) ነው።) ከዚያም ጠያቂውን እንዲህ አሉት: ”መጥፎ ሰው (የቢድዓ ሰው) መስለህ ነው የታየኸኝ! “ብለው እንዲወጣላቸው አዘዙ።7 ይኸው መልዕክትም የሙእሚኖች እናት ከሆነችው ከኡሙ ሰለማ - ረዲየሏሁ ዐንሃ - ተላልፏል።8
ኢማም አቡ ዐብዱረሕማን ኢብኑል ሙባረክ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ አሉ፦ (የላቀው ጌታችን አላህ በሰማያት ላይ ከፍጡራኑ ተለይቶ ከዐርሹ በላይ መሆኑን እናውቃለን።)9
የኢስላም ኢማሞች በዚህ ረገድ የተናገሩት ንግግር በጣም ብዙ ነው። በዚህ ጥንቅር ብቻ ለማሰባሰብ አይመችም። በመሆኑም በርእሰ ጉዳዩ የተላለፉ ሃሳቦችን በተሻለ መልኩ መረዳት የሚፈልግ የሱና ሊቃውንት የፃፉትን ይመልከት። ለምሳሌ፦ በዐብደሏህ ቢን ኢማም አሕመድ የተፃፈውን "አስ-ሱና" የሚለውን ኪታብ፤ በታላቁ ኢማም ሙሐመድ ቢን ኹዛይማህ የተፃፈውን “ተውሒድ” የተሰኘውን ኪታብ፤ እንዲሁም በአቡ አል-ቃሲም አል-ላለካኢይ አጥ-ጦባሪይም የተፃፈውን "አስ-ሱና" የተሰኘውን ኪታብ፤ በአቡበክር ቢን አቢ ዓሲም የተፃፈውን “አስ-ሱና” የተሰኘውን ኪታብ እና ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ አላህ ይዘንላቸው ለሐመዊዮች የሰጡትን መልስ ይከልስ። ሸይኹል ኢስላም በመልሱ የአህለ ሱና ዓቂዳን አብራርተው ተቃዋሚዎቻቸው ስለሚያመጡት ሙግት ስህተትነትም ሸሪዓዊ እና አመክንዮአዊ ማስረጃውን የሱና ሰዎችንም ንግግር ትክክለኛነት እና በርእሰ ጉዳዩ የተናገሩትን ብዙ ቃላቶቻቸውንም አስተላልፈዋል።
ልክ እንደዚሁ ተድሙሪያ ብለው በሰየሙት ጽሑፋቸው ላይም፤ የአህለሱና ወልጀማዓን አቋም በሸሪዓዊና አእምሯዊ ማስረጃዎቹ በስፋት አብራርተው፤ ከእውቀት ባለቤቶች መካከል በቅን ልቦናና ሐቅን ለማወቅ ፈልጎ ለተመለከተው ሁሉ እውነትን ግልፅ በሚያደርግና ሃሰትን በሚንድ መልኩ ለተቃዋሚዎችም ምላሽ ሰጥተውበታል። ማጠቃለያውም፡ አህሉስ-ሱንና ወል-ጀማዓ በአላህ ስሞችና ባህሪያት ላይ ያላቸው እምነት ጥራትና ልዕልና የተገባው አላህ በቁርአኑ ለራሱ ያፀደቀውን ወይም መልዕክተኛው ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሱንናቸው ያፀደቁለትን ያለምንም ማመሳሰል ያፀድቃሉ፤ ጥራት የተገባውንም ጌታ ፍጡራኑን ከመምሰልና (ባህሪያቱን) ትርጉም አልባ ከማድረግ የጸዳ በሆነ መልኩ ያጠሩታል። በዚህም ከተቃርኖ ድነዋል። በአላህ እገዛ (ተውፊቅ) ሁሉንም ማስረጃዎችም በተግባር ላይ አዋሉ። ምክንያቱም ጥራት የተገባው አላህ መልዕክተኞቹ ይዘው የመጡትን እውነት አጥብቆ የያዘን፣ ለዚህም የሚችለውን ያህል የጣረን፣ ፍለጋውንም ለእርሱ ብቻ ያደረገን ሰው ወደ እውነት መምራትና ማስረጃውንም ግልጽ ማድረግ የርሱ ፈለግ (ሱንና) ነውና። ልክ የላቀው አላህ እንዲህ እንዳለን ፡-
﴿بَلۡ نَقۡذِفُ بِٱلۡحَقِّ عَلَى ٱلۡبَٰطِلِ فَيَدۡمَغُهُۥ فَإِذَا هُوَ زَاهِقٞ...﴾
{በእርግጥ እውነትን በውሸት ላይ እንጥላለን:: አንጎሉን ያፈርሰዋልም:: ወዲያዉም እርሱ ጠፊ ነው...} [አል'አንቢያእ፡ 18]
የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَلَا يَأۡتُونَكَ بِمَثَلٍ إِلَّا جِئۡنَٰكَ بِٱلۡحَقِّ وَأَحۡسَنَ تَفۡسِيرًا33﴾
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በየትኛዉም ጥያቄ አይመጡብህም እውነተኛውን መልስና መልካም ፍቺውንም የምናመጣልህ ብንሆን እንጅ::} [አል'ፉርቃን፡ 33]
አህሉሱናን በአላህ ስምና ባህርያት ዙርያ ባላቸው አቋም የተቃረኑ በሚያፀድቁትም ሆነ በሚያወግዙት ነገር ሁሉ ግልፅ የሆነ እርስ በርስ መጋጨት ውስጥ ከመግባታቸውም ባሻገር የቁርአንና ሐዲሥንም ሆነ አእምሯዊ ማስረጃዎችን መቃረናቸው አይቀሬ ነው። አል-ሓፊዝ ኢብኑ ከሢር አላህ ይዘንላቸውና በታዋቂው የተፍሲር ኪታባቸው ይህንን የልዕለ ሃያሉን አላህ ቃል ሲያብራሩ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ምርጥ ንግግር አውስተዋል፦
﴿إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ...﴾
{ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረና ከዚያም በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ ነው።…} [አል'አዕራፍ፡ 54]
ካለው ታላቅ ፋይዳ አንፃር እዚህ ላይ እናወሳዋለን፤ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፦
"ሰዎች በዚህ ጉዳይ እጅግ በርከት ያለ አቋም አላቸው። ይህ ቦታ ታዲያ የነሱን አቋም የምናብራራበት አይደለም። ይልቁን እኛ በዚህ ቦታ የምንከተለው የደጋግ ቀደምት ሰለፎች የነ ኢማም ማሊክ፣ የነ አል-አውዛዒን፣ የነ አሥ-ሠውሪይን፣ የነአል-ለይሥ ቢን ሰዕድን፣ የነ አሽሻፊዒይን፣ የነ ኢማም አሕመድ ቢን ሐንበልን፣ የነ ኢስሓቅ ቢን ራህወይህን እንዲሁም ሌሎችም የጥንትም የዘመናችንም የህዝበ ሙስሊሙ ታላላቅ ኢማሞችን ፈለግ ነው። ይኸውም አኳኋኑን ሳንገልፅ፣ ያለ ማመሳሰልና ውድቅም ሳናደርግ እንደመጣው በማፅደቅ ነው። አላህን ከፍጡራኑ ጋር ወደሚያመሳስሉ ሰዎች አእምሮ ከሚመጣው ምስል ሁሉ አላህ የጠራ ነው። ምክንያቱም አላህ ከፍጡራኑ መካከል እርሱን የሚመስለው ምንም ነገር የለምና።
﴿...لَيۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَيۡءٞۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ﴾
{የሚመስለው ምንም ነገር የለም:: እርሱ ሁሉን ነገር ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነው::} (አሽ'ሹራ፡ 11) ከዛም ባሻገር ጉዳዩ እንደነ የቡኻሪይ ሸይኽ ኑዐይም ኢብኑ ሐምማድ አል-ኹዘዒይ እንዳሉት ነው፡ “አላህን ከፍጡራኑ ጋር ያመሳሰለ ከፍሯል፤ አላህ ራሱን የገለፀበትን ባህሪይ ያወገዘም እንዲሁ ከፍሯል።”10 አላህ ራሱን የገለፀበት መገለጫም ይሁን መልዕክተኛው አላህን የገለፁበት መገለጫ ከፍጡራን ጋር ማመሳሰል የሚባል ነገር የለውም። በመሆኑም በግልፅ የቁርአን አንቀፅና ሶሒሕ በሆነ ሓዲሥ ለአላህ የፀኑ መገለጫዎች ለአላህ ተገቢ በሆነ መልኩ ያፀደቀ፤ አላህም ከእንከን የፀዳ መሆኑን ያመነ ቀናውን ጎዳና ተጉዟል11።" የኢብኑ ከሢር - አላህ ይዘንላቸውና - ንግግር ተጠናቀቀ።
በተጨማሪ በአላህ ማመን ውስጥ ከሚካተቱ ነገሮች መካከል: ኢማን ንግግርም ተግባርም መሆኑን፤ ኢማን አላህን በመታዘዝ የሚጨምር አላህን በማመፅም የሚቀንስ መሆኑን፤ ማንኛውም ሙስሊም እንደ ዝሙት፣ ስርቆት፣ ወለድ መብላት፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣት፣ ወላጆችን መጨቆን እና ሌሎች ከሽርክ እና ከኩፍር ያነሱ ወንጀሎችን በመፈፀሙ ብቻ ሐላል ነው ብሎ እስካላለ ድረስ ከእስልምና ወጥቷል ማለት የማይፈቀደ መሆኑን ማመን ነው። ምክንያቱም የላቀውና ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ስላለን፦
﴿إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَغۡفِرُ أَن يُشۡرَكَ بِهِۦ وَيَغۡفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَآءُ...﴾
{አላህ በእርሱ ማጋራትን ፈጽሞ አይምርም:: ከዚህ በታች (ውጭ) ያለውን ኃጢአት ግን ለሚሻው ሁሉ ይምራል...} [አን'ኒሳእ፡ 48] እንዲሁም በሙተዋቲር ሐዲሦች ከአላህ መልዕክተኛ - ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - ከተዘገቡት መካከል እንዲህ ማለታቸው ይገኝበታል፡
«إِنَّ اللهَ يُخْرِجُ مِنَ النَّارِ مَنْ كَانَ فِي قَلْبِهِ مِثْقَالُ حَبَّةٍ مِنْ خَرْدَلٍ مِنْ إِيْمَانٍ».
«በልቡ ውስጥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያክል ኢማን ያለውን አላህ ከእሳት ያወጣዋል።»12
ሁለተኛው መሰረት፦ በመላእክቶች ማመን:
ይህም ሁለት ነገሮችን ያካትታል፡ አንደኛ፦ በመላእክቶች በጥቅሉ ማመን፤ ይህም አላህ ሊታዘዙት ዘንድ የፈጠራቸውና እንዲህ በማለት የገለጻቸው መላእክት እንዳሉት ማመን ነው፦
﴿وَقَالُواْ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَلَدٗاۗ سُبۡحَٰنَهُۥۚ بَلۡ عِبَادٞ مُّكۡرَمُونَ 26 لَا يَسۡبِقُونَهُۥ بِٱلۡقَوۡلِ وَهُم بِأَمۡرِهِۦ يَعۡمَلُونَ27 يَعۡلَمُ مَا بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَمَا خَلۡفَهُمۡ وَلَا يَشۡفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ٱرۡتَضَىٰ وَهُم مِّنۡ خَشۡيَتِهِۦ مُشۡفِقُونَ28﴾
{«አር-ረሕማንም ከመላእክት ልጅን ያዘ።» አሉ። ጥራት ተገባው። አይደለም መላእክት የተከበሩ ባሮች ናቸው።
በንግግር አይቀድሙትም (ያላለውን አይሉም)፤ እነርሱም በትእዛዙ ይሰራሉ።
በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል:: ለወደደውም እንጂ ለሌላው አያማልዱም:: እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው::} [አል-አንቢያእ፡ 26-28]
መላእክቶች ብዙ አይነት ናቸው። ከመካከላቸው የዐርሽ ተሸካሚዎች አሉ፤ ከመካከላቸውም የጀነት እና የጀሀነም በር ጠባቂዎች አሉ፤ ከመካከላቸውም የፍጡራንን ስራ የመመዝገብ የስራ ድርሻ የተሰጣቸው አሉ። ሁለተኛው ጉዳይ፦ በመላእክት በዝርዝር ማመን፤ ይህም ማለት አላህና መልእክተኛው ስማቸውን በጠቀሷቸው ለምሳሌ በወሕይ በተወከለው ጂብሪል፣ በዝናብ በተወከለው ሚካኢል፣ የጀሀነም እሳት ጠባቂ በሆነው ማሊክ እና ቀንዱን በመንፋት በተወከለው ኢስራፊል ማመን ነው። እንዲሁም በሶሒሕ ሐዲሦች በተወሱ የመላእክት ባህሪ ማመን ነው፤ ከእነዚህም መካከል፦ በሶሒሕ ሐዲሥ ከዓኢሻ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተዘገበው ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«خُلِقَتِ الـمَلَائِكَةُ مِن نُورٍ، وَخُلِقَ الجَانُّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ، وَخُلِقَ آدَمُ مِمَّا وُصِفَ لَكُم».
“መላእክት የተፈጠሩት ከብርሃን ነው፤ ጋኔኖችም ከእሳት ከሆነ ነበልባል ተፈጠሩ። አደም ደግሞ ለእናንተ ከተገለፀላችሁ ነው የተፈጠረው።”13 ሙስሊም በሶሒሓቸው ዘግበውታል።
ሦስተኛው መሠረት፦ በመጽሐፍቱ ማመን፣ እርሱም በተመሳሳይ ሁለት ነገሮችን ያጠቃልላል፦
አንደኛው ነገር፦ አላህ ለነቢያቱና ለመልዕክተኞቹ እውነታውን እንዲያብራሩ እና ወደ እርሱም ጥሪ እንዲያደርጉ መጽሐፍትን ያወረደላቸው መሆኑን በጥቅሉ ማመን ነው፤ ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿لَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا رُسُلَنَا بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَأَنزَلۡنَا مَعَهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡمِيزَانَ لِيَقُومَ ٱلنَّاسُ بِٱلۡقِسۡطِ...﴾
{መልዕክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን። ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን።…} [አል'ሐዲድ፡ 25] የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿كَانَ ٱلنَّاسُ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ فَبَعَثَ ٱللَّهُ ٱلنَّبِيِّـۧنَ مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ وَأَنزَلَ مَعَهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ لِيَحۡكُمَ بَيۡنَ ٱلنَّاسِ فِيمَا ٱخۡتَلَفُواْ فِيهِ...﴾
{ሰዎች ሁሉ (አላህን አንድ በማድረግ) አንድ ሕዝብ ነበሩ:: (ተለያዩ) አላህም ነቢያትን አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርጎ ላከ:: ከነርሱም ጋር በሰዎች መካከል በዚያ እነርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ መጽሐፍትን በእውነት አወረደ::…} [አል'በቀራህ፡ 213]
ሁለተኛው ጉዳይ፦ ዝርዘር በሆነ መልኩ ማመን ነው:- ይህም እንደ ተውራት፣ ኢንጂል፣ ዘቡር እና ቁርኣን አላህ ስማቸውን በጠቀሰልን መጽሐፍት ማመን፣ ቁርአን ከመካከላቸው በላጭና የመጨረሻው እንደሆነ እና ከሌሎቹ ሁሉ የበላይ እና አረጋጋጫቸው እንደሆነም እናምናለን። ኡመቱ ባጠቃላይ ከመልዕክተኛው ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ከመጡ ሶሒሕ ሐዲሦች ጋር አጣምረው ሊከተሉትና ሊፋረዱበትም ግዴታቸው ነው። ምክንያቱም ጥራት የተገባው አላህ መልዕክተኛው ሙሐመድን ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለምን ወደ ሰዎችና ጂኖች መልዕክተኛ አድርጎ ልኳቸዋል። በመካከላቸውም እንዲፈርዱበት ይህን ቁርኣን በእርሳቸው ላይ አውርዶታል። ለልቦና ፈውስ፣ ለሁሉም ነገርም ማብራርያ፣ ለሙእሚኖችም መመርያ እና እዝነት አድርጎታል። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَهَٰذَا كِتَٰبٌ أَنزَلۡنَٰهُ مُبَارَكٞ فَٱتَّبِعُوهُ وَٱتَّقُواْ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ155﴾
{ይህ ያወረድነው የሆነ የተባረከ መጽሐፍ ነው:: እናም ተከተሉት፤ ይታዘንላችሁም ዘንድ ከክህደት ተጠንቀቁ።} [አል'አንዓም፡ 155] የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿...وَنَزَّلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ تِبۡيَٰنٗا لِّكُلِّ شَيۡءٖ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٗ وَبُشۡرَىٰ لِلۡمُسۡلِمِينَ﴾
{መጽሐፉንም ለሁሉም ነገር አብራሪ፤ መመሪያ፣ እዝነትና ለሙስሊሞች አብሳሪ ሆኖ ባንተ ላይ አወረድነው::} [አን'ነሕል፡ 89] የበላይ የሆነው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿قُلۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنِّي رَسُولُ ٱللَّهِ إِلَيۡكُمۡ جَمِيعًا ٱلَّذِي لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ يُحۡيِۦ وَيُمِيتُۖ فَـَٔامِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِ ٱلنَّبِيِّ ٱلۡأُمِّيِّ ٱلَّذِي يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَكَلِمَٰتِهِۦ وَٱتَّبِعُوهُ لَعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ158﴾
{(ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደ ሁላችሁም የአላህ መልዕክተኛ ነኝ:: እርሱም ያ የሰማያትና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነ ነው:: እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም:: ህያው ያደርጋል:: ይገድላልም:: በአላህ በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ በሆነው መልዕክተኛውም እመኑ:: ወደ ቅኑ መንገድ ትመሩ ዘንድም ተከተሉት።» በላቸው::} [አልአዕራፍ:158] በዚህ መልኩ የመጡ ቁርአናዊ ማስረጃዎች በርካታ ናቸው።
አራተኛው መሠረት፡ በመልዕክተኞች ማመን
ይህም በተመሳሳይ ለሁለት ይከፈላል፦ አንደኛው ጉዳይ፡ በመልዕክተኞች በጥቅሉ ማመን ነው፤ ይህም ጥራት የተገባውና የላቀው አላህ ወደ ባሮቹ ከመካከላቸው የሆኑ መልዕክተኞችን፤ አብሳሪዎች፣ አስፈራሪዎችና ወደ እውነትም ተጣሪዎች አድርጎ እንደላከ እናምናለን፤ እነርሱን አምኖ የተቀበላቸው በደስታ ስኬትን ይጎናፀፋል፤ የተቃወማቸው ደግሞ ክስረትን ይከናነባል። የመጨረሻቸውና ከመካከላቸው በላጩ ነብያችን ሙሐመድ ቢን ዐብደላህ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ናቸው። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَلَقَدۡ بَعَثۡنَا فِي كُلِّ أُمَّةٖ رَّسُولًا أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَٱجۡتَنِبُواْ ٱلطَّٰغُوتَ...﴾
{በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትን ራቁ በማለት መልዕክተኛን በእርግጥ ልከናል...} [አን-ነሕል፡ 36] የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡
﴿رُّسُلٗا مُّبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَى ٱللَّهِ حُجَّةُۢ بَعۡدَ ٱلرُّسُلِ...﴾
{ከመልዕክተኞች በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ ምንም አስረጂ እንዳይኖራቸው አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርገን መልዕክተኞችን ላክን...} [አን'ኒሳእ፡ 165] የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَآ أَحَدٖ مِّن رِّجَالِكُمۡ وَلَٰكِن رَّسُولَ ٱللَّهِ وَخَاتَمَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ...﴾
{(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንዱም ሰው አባት አይደለም:: ግን የአላህ መልዕክተኛና የነብያት መደምደሚያ ነው...} [አል'አሕዛብ፡ 40]
ሁለተኛው፡ በመልዕክተኞች በዝርዝር ማመን ነው፤ ይህም አላህ ስማቸውን በጠቀሳቸው ወይም የአላህ መልክተኛ ﷺ በተረጋገጠ ዘገባ በጠቀሷቸው መልክተኞች ለይተን በስማቸው ማመን ነው። እንደ ኑሕ፣ ሁድ፣ ሷሊሕ፣ ኢብራሂም እና ሌሎችም፤ የአላህ ሶላትና ሰላም በነሱም፣ በቤተሰቦቻቸውም እንዲሁም በተከታዮቻቸውም ላይ ይስፈን።
አምስተኛው መሰረት፡ በመጨረሻው ቀን ማመን
እርሱም የሚከተሉትን አጠቃሏል:
አላህና መልዕክተኛው -ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም- ከሞት በኋላ እንደሚከሰት በተናገሩት ነገር ሁሉ ማመን፤ ይህም የቀብር ፈተና፣ የቀብር ቅጣትና ፀጋ፣ በእለተ ትንሳኤ የሚሆኑ ከባባድ መጨናነቆችና መከራዎች፣ የሲራጥ ፈተና፣ የስራ መመዘን፣ በስራ መተሳሰብ፣ ምንዳን ማግኘት፣ የስራ መዝገብ ለእያንዳንዱ ሰው መታደል፤ ከዚያም መዝገቡን በቀኙ የሚቀበል፣ በግራ እጁ የሚቀበል፣ ወይም ከጀርባው በኩል የሚቀበል መኖሩን ነው።
በተጨማሪም ነቢያችን ሙሐመድ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በተሰጣቸው "ሐውድ" ማመን፣ በጀነት እና በጀሀነም ማመን፣ ሙእሚኖች የላቀው አላህን የሚመለከቱና አላህም እነርሱን የሚያነጋግራቸው ስለመሆኑ እና ከዚህም ውጭ በተከበረው ቁርአንና ሶሒሕ በሆኑ ከነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በተረጋገጡ ሐዲሦች የመጡ እውነታዎችን ሁሉ ማመንንም የሚያጠቃልል ነው። በመሆኑም በባሪያው ላይ ይህንን ሁሉ እውነት ነው ብሎ መቀበልና አላህና መልዕክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ባብራሩት መልኩ ማመን ግዴታ ነው።
ስድስተኛው መሰረት፡ በቀደር ማመን
በአራት ጉዳዮች ማመንን ያጠቃልላል፡
የመጀመርያው፡ ጥራት የተገባው አላህ የሆነውንም የሚሆነውንም ጠንቅቆ የሚያውቅ እንደሆነ፤ የባሪያዎቹንም ሁኔታ፣ ሲሳያቸውን፣ የህይወት ጊዜያቸውን፣ ስራዎቻቸውን እና ከዚህም ውጭ ያሉ ጉዳዮቻቸውንም ሁሉ እንደሚያውቅ፤ ጥራት ይገባውና ከእርሱ የሚደበቅ አንዳችም ነገር የሌለ መሆኑን ማመን ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿...وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٞ﴾
{አላህ በሁሉ ነገር ላይ አዋቂ መሆኑንም እወቁ::} [አል-በቀራህ፡ 231] የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿...لِتَعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ وَأَنَّ ٱللَّهَ قَدۡ أَحَاطَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عِلۡمَۢا﴾
{አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን አላህም በነገሩ ሁሉ በእውቀት ያካበበ መሆኑን ታውቁ ዘንድ…} [አጥ'ጠላቅ: 12]
ሁለተኛው ጉዳይ፦ አላህ አስቀድሞ የወሰነውንና የፈረደውን ሁሉ እንደጻፈው ማመን ነው። ጥራት የተገባው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿قَدۡ عَلِمۡنَا مَا تَنقُصُ ٱلۡأَرۡضُ مِنۡهُمۡۖ وَعِندَنَا كِتَٰبٌ حَفِيظُۢ 4﴾
{ከእነርሱ አካል ምድር የምታጎድለውን በእርግጥ አውቀናል:: እኛም ዘንድ ጠባቂ መጽሐፍ አለ::} [ቃፍ፡ 4] የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿...وَكُلَّ شَيۡءٍ أَحۡصَيۡنَٰهُ فِيٓ إِمَامٖ مُّبِينٖ﴾
{ሁሉን ነገርም ገላጭና መሪ በሆነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው::} [ሱረቱ ያሲን፡ 12] የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿أَلَمۡ تَعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا فِي ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِۚ إِنَّ ذَٰلِكَ فِي كِتَٰبٍۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٞ70﴾
{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ በእርግጥ የሚያውቅ መሆኑን አታውቅምን? ይህ በመጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ እውነት ነው:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነው::} [አል'ሐጅ፡ 70]
ሦስተኛው ጉዳይ፦ ተፈፃሚ በሆነው የላቀው የአላህ ፈቃድ ማመን ነው፤ በመሆኑም እርሱ የሻው ነገር ይሆናል፤ እርሱ ያልሻው አንዳችም ነገር አይሆንም። ከፍ ያለውና ጥራት የተገባው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿...إِنَّ ٱللَّهَ يَفۡعَلُ مَا يَشَآءُ﴾
{…አላህ የሻውን ይሰራልና} [አል'ሐጅ፡ 18] አሸናፊና ኋያሉ አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿إِنَّمَآ أَمۡرُهُۥٓ إِذَآ أَرَادَ شَيۡـًٔا أَن يَقُولَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ82﴾
{ነገሩ አንዳችን በሻ ጊዜ ሁን ማለት ብቻ ነው:: ወዲያው ይሆናልም::} [ሱረቱ ያሲን፡ 82] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَمَا تَشَآءُونَ إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ29﴾
{(ሰዎች ሆይ!) የዓለማት ጌታ የሆነው አላህ ካልሻ በስተቀር እናንተ አንድም ነገር አትሹም።} [አት'ተክዊር: 29]
አራተኛው ጉዳይ፡- ሁሉንም ግኝቶች የፈጠረው የላቀው አላህ መሆኑን ማመን ነው። ከእርሱ ውጭ ፈጣሪም የለም፤ ከእርሱ ውጭ ጌታም የለም። ጥራት የተገባው አላህ እንዲህ ብሏል፡
﴿ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَيۡءٖۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ وَكِيلٞ62﴾
{አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው::} [አዝ-ዙመር፡ 62] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱذۡكُرُواْ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡۚ هَلۡ مِنۡ خَٰلِقٍ غَيۡرُ ٱللَّهِ يَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِۚ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ فَأَنَّىٰ تُؤۡفَكُونَ3﴾
{እናንተ ሰዎች ሆይ! በእናንተ ላይ (ያለውን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ ከአላህ ሌላ ፈጣሪ አለን? ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አለን? ከእርሱ በስተቀር አምላክ (ሰጪም) የለም፡፡ ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ፡፡} [ፋጢር፡ 3]
ከእነዚህ ከፊሎቹን ካስተባበሉ የቢድዓ ሰዎች በተቃራኒ አህለሱና ወልጀመዓዎች ዘንድ በቀደር ማመን በእነዚህ አራቱም ጉዳዮች ማመንን ያጠቃልላል።
በአህሉ ሱንና ትክክለኛ እምነት ውስጥ ከሚካተቱ አስፈላጊ ጉዳዮች መካከል ለአላህ ብሎ መውደድ፣ ለአላህ ብሎ መጥላት፣ ወዳጅነትንም ጠላትነትንም ለአላህ ብሎ መመስረት ነው። ይህ የ«ወላእና በራእ» ዐቂዳ (እምነት) ሲሆን፤ እርሱም በአላህ ማመን ውስጥ የሚካተት ነው።
ሙእሚን ምእመናንን ይወዳል ይወዳጃቸዋል፤ ከሓዲዎችንም ይጠላል ጠላት አድርጎም ይይዛቸዋል። አህሉ ሱናህ ወልጀማዓዎች ዘንድ እንደፀናውም እዚህ ኡመት ውስጥ የምእመናን ግንባር ቀደም የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶሓቦች ናቸው። እነርሱን ይወዷቸዋል ይወዳጇቸዋል፤ ከነብያት በኋላ ከሰዎች ሁሉ በላጭ እንደሆኑም ያምናሉ። ምክንያቱም ነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ስላሉ፦
«خَيْرُ القُرُونِ قَرْنِي ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُمْ ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُم».
«ከትውልዶች ሁሉ ምርጡ እኔ ያለሁበት ትውልድ ነው። ከዚያም ከነርሱ በኋላ ቀጥለው የሚመጡት፤ ከዚያም ከነርሱ ቀጥለው የሚመጡት ናቸው።»14 በሰሒሕነቱ ላይ ተስማምተውበታል።
አህለ ሱናዎች ከሶሓቦች በላጩ አቡበከር አስ-ሲዲቅ፣ ከዚያም ዑመር አል-ፋሩቅ፣ ከዚያም ዑሥማን ዙን-ኑረይን፣ ከዚያም ዐሊይ አል-ሙርተዷ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - መሆናቸውን፤ ከዛ በኋላ ደግሞ ጀነት ከተመሰከረላቸው ከአስሩ የተቀሩት፤ ከዚያም የተቀሩት ሰሐቦች -አላህ ሁሉንም መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - መሆናቸውን ያምናሉ። በሶሓቦች መካከል በተከሰተው አለመግባባት ዙርያ ከማውራት ይታቀባሉ። ሶሓቦቹ በጉዳዩ ሙጅተሂዶች መኾናቸውንና እውነታውን ላገኘ ድርብ ምንዳዎች ከመካከላቸው ስህተት ላይ የነበረውም አንድ አጅር እንዳለው ያምናሉ።
በረሱል ﷺ ያመኑትን የርሳቸውን ቤተሰቦች (አህሉል በይት) ይወዳሉ፤ ወዳጅ አድርገውም ይይዛሉ። እንዲሁም ‹የምዕመናን እናቶች› የሆኑትን የረሱል ﷺ ሚስቶችንም ባለቤቶች ወዳጅ ያደርጋሉ፤ ለሁሉም አላህ መልካም ሥራቸውን እንዲወድላቸውም ዱዓእ ያደርጋሉ። የአላህ መልእክተኛን ﷺ ባልደረቦች የሚጠሉ፣ የሚዘልፉ፣ በነብዩ ቤተሰቦች ድንበር የሚያልፉና አላህ ከሰጣቸው ደረጃም ከፍ አድርገው ሌላ ደረጃ ላይ የሚያደርጓቸው ከሆኑት የራፊዷዎች አካሄድ ራሳቸውን ያጠራሉ። በተመሳሳይ የነብዩን ቤተሰቦች በንግግርም ሆነ በተግባር ከሚያውኩ ከነዋሲቦችም አካሄድ ራሳቸውን ያጠራሉ።
ይህ የጠቀስነው ሁሉ አላህ መልእክተኛው ሙሐመድን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የላከበት በሆነው ትክክለኛ እምነት ውስጥ የሚካተት ነው። እርሱም ልናምንበት፣ አጥብቀን ልንይዘው፣ በታማኝነት ልንፀናበት እና ከሚፃረረውም ነገር ልንጠነቀቅ የሚገባን ሲሆን፤ የፊርቀቱ ናጂያ አህሉ ሱና ወል-ጀማዓህ ዐቂዳም ነው፤ ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እርሷን አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፦
«لَا تَـزَالُ طَائِفَةٌ مِنْ أُمَّتِي ظَاهِرِينَ عَلَى الحَقِّ، لَا يَضُرُّهُمْ مَنْ خَذَلَهُمْ، حَتَّى يَأْتِيَ أَمْرُ اللهِ وَهُمْ كَذَلِكَ».
«ከኡመቴ መካከል በእውነት ላይ የበላይ የሆኑና ያዋረዳቸው የማይጎዳቸው ጭፍሮች ከመኖር አይወገዱም። የአላህ ትእዛዝ እስኪመጣ ድረስም በዚያው ሁኔታቸው ላይ ይቆያሉ።»15
በሌላ ዘገባ:
«لَا تَزَالُ طَائِفَةٌ مِنْ أُمَّتِي عَلَى الحَقِّ مَنْصُورَةٌ».
«በእውነት ላይ የበላይ የሆነች (ድል የተጎናጸፈች) አንዲት ጭፍራ ከኡመቴ አትወገድም።»16
እንዲህም ብለዋል፦
«افْتَرَقَتِ اليَهُودُ عَلَى إِحْدَى وَسَبْعِينَ فِرْقَةً، وَافْتَرَقَتِ النَّصَارَى عَلَى اثْنَتَيْنِ وَسَبْعِينَ فِرْقَةً، وَسَتَفْتَرِقُ هَذِهِ الأُمَّةُ عَلَى ثَلَاثِ وَسَبْعِينَ فِرْقَةً كُلُّهَا فِي النَّارِ إِلَّا وَاحِدَةً فَقَالَ الصَّحَابَةُ: مَنْ هِيَ يَا رَسُولَ اللهِ؟ قَالَ: مَنْ كَانَ عَلَى مِثْلِ مَا أَنَا عَلَيْهِ وَأَصْحَابِي».
«አይሁዶች ወደ ሰባ አንድ ጭፍሮች ተከፋፍለዋል፤ ክርስቲያኖችም ወደ ሰባ ሁለት ጭፍሮች ተከፋፍለዋል፤ ይህ ሙስሊሙ ኡመት ደግሞ ወደ ሰባ ሦስት ጭፍሮች ይከፋፈላሉ። ሁሉም የእሳት ይሆኑና አንዷ ብቻ ትድናለች። ሱሓቦችም 'የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ይህች (የምትድነዋ) ማን ናት?' ብለው ጠየቁ እርሳቸውም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'እኔና ባልደረቦቼ ባለንበት ሁኔታ የሆኑት ናቸው።' በማለት መለሱ።»17
ትክክለኛውን ዐቂዳ የሚፃረሩ የሆኑ እምነቶች
ከዚህ ዐቂዳ (እምነት) አፈንግጠው በተቃራኒው ጎዳና ላይ የሚጓዙት ብዙ ጭፍሮች ናቸው፤ ከነሱ መካከልም፦ ጣዖታትን፣ ግኡዝ አካላትን፣ መላእክትን፣ ቅዱሳንን፣ አጋንንትን፣ ዛፎችን፣ ድንጋዮችንና ሌሎችንም የሚያመልኩ ይገኙበታል። እነዚህ ቁረይሾችና ሌሎች የዐረብ ጭፍሮች ከነብያችን ሙሐመድ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር እንደነበራቸው መስተጋብር በተመሳሳይ ለረሱል (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዳዕዋ ምላሽ ያልሰጡ እና የተቃረኑ ሰዎች ናቸው። ቁረይሾች አማልክቶቻቸውን ጉዳዮችን እንዲፈፅሙላቸው፣ ህሙማንን እንዲፈውሱላቸው እና በጠላቶች ላይ ድል እንዲያጎናጽፏቸው ይማጸኑ ነበር፤ እርድም ያርዱላቸው፣ ስለትም ይሳሉላቸው ነበር። ረሱል (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ይህንን ድርጊታቸውን ባወገዙባቸውና አምልኮንም ለአላህ ብቻ ጥርት እንዲያደርጉ ባዘዟቸው ጊዜ፣ እንግዳ አድርገው በመደነቅ አስተባበሉ፤ እንዲህም አሉ፦
﴿أَجَعَلَ ٱلۡأٓلِهَةَ إِلَٰهٗا وَٰحِدًاۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيۡءٌ عُجَابٞ5﴾
«አማልክቶችን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው።» [ሷድ፡ 5]
ነቢዩ ﷺ የሚያምነው እስኪያምንላቸውም ድረስ ወደ አላህ ከመጣራትና ከሽርክ ከማስጠንቀቅ፤ የጥሪያቸውን እውነታ ከማብራራትም አልተወገዱም። ከዚያም ሰዎች በቡድን በቡድን እየሆኑ ወደ አላህ ዲን መትመማቸውን ቀጠሉ፤ የአላህ መልክተኛ ﷺ ከዚያም የሶሓቦች -ረዲየሏሁ ዓንሁም- እና እነርሱን በቅንነት የተከተሏቸው ተከታዮቻቸው ያለማቋረጥ ዳዕዋ ካደረጉ በኋላ እና ያላለሰለሰ ትግል ካደረጉ በኋላ የአላህ ዲን በሌሎች ሃይማኖቶች ላይ የበላይነቱን ተቆናጠጠ። ከዚያም ሁኔታዎች ተቀያየሩ፤ በብዙ ሰዎች ዘንድም ጅህልና አመዘነ፤ እናም ብዙዎቹ በነብያቶችና በወልዮች ላይ ድንበር በማለፍ፣ እነርሱን በመማፀንና ድረሱልኝ በማለት እንዲሁም ሌሎች የሽርክ አይነቶችን በመፈፀም ወደ ጃሂሊያው እምነት ተመለሱ። የላ ኢላሃ ኢለሏህንም ትርጉም የዐረብ ሙሽሪኮቹ በተረዱት ያህል እንኳ አልተረዱትም ነበር። አላህ ይርዳንና።
ይኸው ሽርክ አላዋቂነት በማመዘኑ እና ከነብያቶች ዘመን የራቅን በመሆናችን ምክንያት አሁን እስካለንበት ዘመን ድረስ በሰዎች መካከል እየተስፋፋ ያለ ነገር ነው።
የዘመናችን አጋርያን የሚያመጡት ማምታቻ የቀድሞዎቹ አጋርያን ማምታቻን ነው። እርሱም የሚከተለው ነው፦
﴿...هَٰٓؤُلَآءِ شُفَعَٰٓؤُنَا عِندَ ٱللَّهِ...﴾
{…እነዚህ አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው።…} [ዩኑስ፡ 18] እንዲህም ብለዋል:
﴿...مَا نَعۡبُدُهُمۡ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَآ إِلَى ٱللَّهِ زُلۡفَىٰٓ...﴾
{…ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን በማሰብ እንጂ ለሌላ አንገዛቸዉም።…} [አዝ'ዙመር፡ 3] አላህም ይህን ማምታቻ ውድቅ አድርጓል፤ ከእርሱ ሌላን ያመለከ ሰው ማንም ይሁን ማን ሽርክንና ክህደትን እንደፈፀመም ግልፅ አድርጓል። የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿وَيَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمۡ وَلَا يَنفَعُهُمۡ وَيَقُولُونَ هَٰٓؤُلَآءِ شُفَعَٰٓؤُنَا عِندَ ٱللَّهِ...﴾
{አጋሪዎች ከአላህ ሌላ የማይጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውን ይገዛሉ:: «እነዚህ አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው።» ይላሉ…} [ዩኑስ፡ 18] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦
﴿قُلۡ أَتُنَبِّـُٔونَ ٱللَّهَ بِمَا لَا يَعۡلَمُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ18﴾
{አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ እናንተ ትነግሩታላችሁን?» በላቸው:: አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ:: ላቀም::} [ዩኑስ፡ 18]
የላቀው አላህ በዚህ አንቀፅ ከእርሱ ውጭ ነቢይንም ይሁን ወልይን ወይም ሌሎችንም ቢሆን ማምለክ ድርጊቱን የሚፈፅመው ያሻውን ስም ቢሰጠውም ከታላቁ ሽርክ የሚመደብ ወንጀል መሆኑን ግልፅ አደረገ። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿...وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَ مَا نَعۡبُدُهُمۡ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَآ إِلَى ٱللَّهِ زُلۡفَىٰٓ...﴾
{…እነዚያ ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድረገው የያዙት «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን በማሰብ እንጂ ለሌላ አንገዛቸዉም።» (ይላሉ)…} [አዝ'ዙመር፡ 3] ከዚያም ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦
﴿...إِنَّ ٱللَّهَ يَحۡكُمُ بَيۡنَهُمۡ فِي مَا هُمۡ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي مَنۡ هُوَ كَٰذِبٞ كَفَّارٞ﴾
{…አላህ በዚያ እነርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል:: አላህም ውሸታምንና ከሓዲ የሆነን ሰው አያቀናም::} [አዝ'ዙመር፡ 3]
በዚህም ጥራት የተገባው አላህ ሌሎችን መለመን፣ እነርሱን መፍራት፣ ከነርሱ ተስፋ ማድረግና የመሳሰሉት የአምልኮ መገለጫዎችን ለነርሱ መስጠት በእርሱ መካድ መሆኑን ግልፅ አደረገ። ወደ አላህ መቃረብን ያቃርቡናል የሚለው ሙግታቸውንም ውሸትነቱን አጋለጠባቸው።
እንዲሁም መልዕክተኞች (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ይዘውት የመጡትን ትክክለኛ ዐቂዳ (እምነት) የሚቃረኑና የክህደት እምነቶች ከሆኑት መካከል የዘመናችን እምነተ ቢሶች የሚከተሉት የማርክሲዝምና ሌኒኒዝም እምነት ተከታዮች እና ሌሎች የእምነተ ቢስነትና የክህደት ሰባኪዎች ጥሪ ሁሉ ክህደት ነው። ይህንኑ አቋማቸውን ሲፈልጉ ሶሻሊዝም ይበሉት አልያም ኮሚዩኒዝም ከፈለጉም አብዮታዊ ይበሉት ካሻቸውም ሌላ ስም ይስጡት የአቋማቸው ስር መሰረቱ "አምላክ የሚባል ነገር የለም ህይወት የሚባለው ቁሳዊው አለም ብቻ ነው" እስካሉ ድረስ አቋማቸው የክህደት አቋም ነው።
ከአቋማቸው መሰረቶች መካከል ከሞት በኋላ ትንሳኤ መኖሩን መካድ፣ ጀነት እና ጀሀነምን መካድ፣ በሁሉም ሀይማኖቶችም መካድ፣ መጽሐፋቸውን በጥልቅ የመረመረና ያሉበትን ተጨባጭ በሚገባ ያስተዋለ ሰው አቋማቸው ይህ መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ እምነት ደግሞ ሃይማኖቶችን በሙሉ የሚቃረን ለመሆኑ እና ሰዎችንም በዱኒያም በአኺራም ለከፋ ፍፃሜ የሚዳርግ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።
እውነተኛ ዐቂዳን (እምነት) ከሚቃረኑ እምነቶች መካከል አንዳንድ ሱፊዮች ወሊይ የሚሏቸውን ሰዎች በማስተናበሩም ይሁን በአለሙ ክንውን ከአላህ ጋር ተጋሪነት እንዳላቸው የሚያምኑት ነገር ይገኝበታል። እነርሱንም "ቁጥብ"፣ "ዊትድ"፣ "ገውስ" እና ሌሎች ስያሜዎችንም እያፈለቁ አማልክቶቻቸውን የሚጠሩት ነገርም አለ። ይህ በአላህ ጌትነት የሚደረግ ሽርክ ሲሆን፤ በአላህ ከሚደረጉ የሽርክ አይነቶችም እጅግ የከፋው ነው።
የቀድሞዎቹን የጃሂሊያ ሰዎች ሽርክ እና በዘመናችን ሰዎች ዘንድ የተንሰራፋውን ሽርክ አስተውሎ ያነጻጸረ ሰው የዘመናችን ሰዎች ሽርክ ይበልጥ የገዘፈና የከፋ መሆኑን ይገነዘባል። የዚህም ማብራሪያ እንደሚከተለው ነው፡ በድንቁርና ዘመን የነበሩ የዐረብ ከሃዲያን በሁለት ነገሮች ተለይተው ነበር: የመጀመሪያው ጉዳይ፦ በጌትነት ላይ አያጋሩም ነበር፤ ሽርካቸው የነበረው በአምልኮ ላይ ነበር፤ ጌትነት የሀያሉና የላቀው አላህ ብቻ መሆኑን ያምኑ ነበርና፤ ጥራት የተገባው ጌታ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَهُمۡ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُ...﴾
{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ማን እንደ ፈጠራቸው ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይላሉ...} [አዝ'ዙኽሩፍ፡ 87] የላቀው አሏህ እንዲህም ብሏል፡
﴿قُلۡ مَن يَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ أَمَّن يَمۡلِكُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَمَن يُخۡرِجُ ٱلۡحَيَّ مِنَ ٱلۡمَيِّتِ وَيُخۡرِجُ ٱلۡمَيِّتَ مِنَ ٱلۡحَيِّ وَمَن يُدَبِّرُ ٱلۡأَمۡرَۚ فَسَيَقُولُونَ ٱللَّهُۚ فَقُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ31﴾
{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው? መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረላችሁ ማን ነው? ከሙትም ህያውን የሚያወጣ፤ ከህያዉም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው?» በላቸው:: «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል:: «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ? ታዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው።} [ዩኑስ፡ 31] ይህን መሰል መልዕክት ያዘሉ የቁርኣን አንቀጾች በጣም ብዙ ናቸው።
ሁለተኛ፡- በአምልኮ ውስጥ የሚፈፅሙት ሽርካቸው ዘውታሪ ሳይሆን በተድላ ጊዜ ነበር። በችግር ጊዜ ግን አምልኳቸውን ለአላህ ጥርት ያደርጉ ነበር፤ ታላቁ አላህም እንዲህ ብሏል፦
﴿فَإِذَا رَكِبُواْ فِي ٱلۡفُلۡكِ دَعَوُاْ ٱللَّهَ مُخۡلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ فَلَمَّا نَجَّىٰهُمۡ إِلَى ٱلۡبَرِّ إِذَا هُمۡ يُشۡرِكُونَ65﴾
{በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይጠሩታል:: ወደ የብስ በማውጣት ባዳናቸው ጊዜ ግን ወዲያውኑ እነርሱ ጣዖትን ያጋራሉ::} [አል'ዐንከቡት፡ 65]
የዘመናችን ሙሽሪኮች ከቀድሞዎቹ በሁለት መንገድ የባሰባቸው ናቸው፡ አንደኛ፡ አንዳንዶቹ በጌትነት ማጋራታቸው፤ ሁለተኛው ደግሞ፡ በምቾትም በችግርም ጊዜ ሽርክ የሚፈጽሙ መሆናቸው ነው። ይህንንም ከእነርሱ ጋር ተቀላቅሎ ሁኔታቸውን ያጤነና፤ በግብፅ የሑሰይን እና የበደዊይ እና በሌሎችም ቀብር ላይ፣ በኤደን የዓይደሩስ ቀብር ላይ፣ በየመን የሃዲይ ቀብር ላይ፣ በሻም የኢብኑ ዓረቢይ ቀብር ላይ፣ በዒራቅ የሸይኽ ዐብዱልቀድር ጀይላኒይ ቀብር ላይ፣ እንዲሁም ከነዚህም ውጭ በብዙሃኑ ድንበር ያለፉባቸውና በርካታ የላቀውን አላህ ሐቅ አሳልፈው የሰጡባቸውን ታዋቂ ቀብሮች ዘንድ የሚያደርጉትን የተመለከተ ሰው ሁሉ ያውቀዋል። በዛ ላይ ድርጊታቸውን እያወገዘ አላህ ነብዩ ሙሐመድን ﷺ ከእርሳቸው በፊት የነበሩት መልዕክተኞችም -የአላህ ሰላትና ሰላም በሁሉም ላይ ይስፈን- የላከበትን ተውሒድ የሚያብራራላቸው ጥቂቱ ብቻ ነው። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን።
ትክክለኛውን ዐቂዳ ከሚቃረኑ እምነቶች መካከል የአላህ ስምና ባህሪያትን በተመለከተ ቢድዓ ያመጡ እንደ ጀህሚዮች፣ ሙዕተዚላዎች እና የአላህን ባህሪያት በመካድ፣ ጥራት ለተገባው አላህ የተጠቀሱትን የምሉእነት ባህርያት ውድቅ በማድረግ፣ ጥራት የተገባውን አላህ የባዶነት፣ የግኡዛንና ኢ-አእምሯዊ መገለጫ በሆኑ ባህርያት በመግለፅ ፈለጋቸውን የተከተሉ ሰዎች እምነት ይገኝበታል። እነዚህ ሰዎች ከሚሉት ሁሉ ጥራት የተገባው አምላካችን አላህ ላቀ።
እዚህም ውስጥ ከፊል ባህርያቱን እየካዱ ከፊሉንም የሚያፀድቁት የአሽዓሪያዎች እምነት ይካተትበታል። እነዚህም ባፀደቁት ባህርያት የተነሳ የሸሿቸውንም ሆነ የካዷቸውን፣ ትርጉማቸውንም አጣመው የተረጎሟቸውን ባህርያት እንዲያፀድቁ ይገደዳሉ። በዚህ ድርጊታቸውም መለኮታዊውንም አእምሯዊውንም ማስረጃዎች ተቃርነዋል፤ ግልፅ በሆነ መልኩም እርስበርስ ተጋጭተዋል።
አህል ሱና ወል-ጀማዓዎች ግን አላህ ለራሱ ያፀደቀውን እና መልዕክተኛው ሙሐመድ ﷺ ለአላህ ያፀደቁለትን ስምና ባህሪ በተሟላ መልኩ መገለጫው መሆኑን ያፀድቃሉ፤ ፍጡራኑን ከመምሰልም ሆነ ራሱን የገለፀበትን ባህርይ ውድቅ ከማድረግ በመራቅ ከማይገባው ሁሉ እጅግ ጥርት ባለ መልኩ የጠራ መሆኑን ያምናሉ። በዚህም የተባሉትን ሳያዛቡም ውድቅ ሳያደርጉም አምነው፤ ሌሎቹ ካረፉበት እርስ በርስ መጣረስም ድነው የመጡትን ማስረጃዎች ሁሉ ተግባራዊ ማድረግ ቻሉ። ይህንንም ከላይ አብራርተናል።
የመዳኛው መንገድ፣ የዱኒያም የአኺራም ስኬታማነት፣ የዚህች ኡመት ቀደምት መሪዎችና ኢማሞች የተጓዙበት ቀጥተኛው መንገድ ይኸው ነው። የኋለኞቹ የሚስተካከሉበትም የመጀመሪያቸው በተስተካከሉበት ብቻ ነው። ማለትም ቁርኣንና ሱናን በመከተል ቁርአንና ሐዲሥን የሚቃረነውንም በመተው ነው። ጥራትና ልዕልና የተገባው አላህ ኡማውን ወደ ቀናው ጎዳና እንዲመልሰው፣ ቅን ዳዒዎችን እንዲያበዛ፣ መሪዎቹንና ኡለማዎቹንም ሽርክን እንዲታገሉት፣ እንዲያጠፉትና ከመንገዶቹም እንዲያስጠነቅቁ አላህ እንዲረዳቸው እርሱን እንጠይቀዋለን። እርሱ ሰሚው ቅርብ ነውና። ለመልካም የመገጠም ባለቤቱ አላህ ነው፤ እርሱም በቂያችንና መልካም መመኪያ ነው፤ በእርሱም ቢሆን እንጂ ኃይልም ብልሀትም የለም። የአላህ ሰላትና ሰላም በባሪያውና መልዕክተኛው በነብያችን ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ይስፈን።
***
بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ
ሁለተኛው መልዕክት፡
ከነቢዩ ﷺ እርዳታ የመፈለግ ብይን
ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላትና ሰላምም በአላህ መልእክተኛ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው እንዲሁም የእርሳቸውን ቅን ጎዳና በተከተለም ላይ ሁሉ ይስፈን።
ከዚህ በመቀጠል፦ የኩዌት አልሙጅተመዕ ጋዜጣ በቁጥር 15፣ በቀን 19/4/1390 ዓ.ሂ. በወጣው እትሟ «የተከበረው የነብዩ መውሊድ መታሰቢያ» በሚል ርዕስ ስር ግጥሞችን አሳትማለች። እነዚህን ግጥሞች ያፀደቀችውም (አሚና) ብላ እራሷን የጠራች ሴት ናት። እነዚህ ግጥሞች ኡማውን ለማዳን፣ ድል ለማድረግና ኡማው ከወደቀበት መለያየትና ልዩነት ነፃ ለማውጣት ነብዩን ﷺ እርዳታ መለመንንና ድልን ከእርሳቸው መጠየቅን ያካተቱ ነበሩ። ከተጠቀሱትም ግጥሞች መካከል የተወሰነው ይህ ነው፦
የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጦርነትን የሚያቀጣጥልና በነበልባሉ የሚለበለብ ዓለምን ይታደጉ...
የአላህ መልእክተኛ ሆይ፤ በጥርጣሬ ጨለማ ውስጥ መንከራተቷ የረዘመባትን ኡማ አድኗት...
የአላህ መልእክተኛ ሆይ፤ ራእይዋ በኃዘን ጥልፍልፎሽ የጠፋባትን ህዝብ ይታደጉ፤
እንዲህ እስከምትለው ድረስ
እርዳታውን አፋጥን፤ በበድር ቀን ጌታን በጠራህ ጊዜ እንዳፋጠንከው።
ውርደቱም ወደ ግሩም ድል ተለወጠ፤ ለአላህ የማታያቸው ሰራዊቶች አሉትና።
(ይህች ጸሐፊ፣ ድል በአላህ እጅ ብቻ እንጂ በነቢዩ ﷺ እጅም ሆነ በሌሎች ፍጡራን እጅ አለመሆኑን ረስታ -ወይም ሳታውቅ-፣ ድልን እንዲያፋጥኑና ኡማውን እንዲታደጉ በመጠየቅ ጥሪዋንና የእርዳታ ልመናዋን ወደ መልዕክተኛው ﷺ ታቀርባለች፤ አላህ በግልፅ ቁርአኑ ላይ እንዲህ ብሎ ሳለ:-
﴿...وَمَا النَّصْرُ إِلَّا مِنْ عِنْدِ اللَّهِ الْعَزِيزِ الْحَكِيمِ﴾
{... ድልም አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ዘንድ ብቻ እንጂ ከሌላ ከማንም የሚገኝ አይደለም::} [አሊ-ዒምራን 126] ክብሩ የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿إِنْ يَنْصُرْكُمُ اللَّهُ فَلَا غَالِبَ لَكُمْ وَإِنْ يَخْذُلْكُمْ فَمَنْ ذَا الَّذِي يَنْصُرُكُمْ مِنْ بَعْدِهِ...﴾
{አላህ ቢረዳችሁ ለእናንተ አሸናፊ የለም:: እርሱ ካዋረዳቸሁ ደግሞ ከእርሱ ማዋረድ በኋላ የሚረዳችሁ ያ ማን ነው?} [አሊ-ዒምራን፡ 160]
ይህ ዱዓ እና እርዳታን መፈለግ ከአምልኮ አይነቶች አንዱን ከአላህ ውጪ ለሆነ አካል መስጠት ነው። ይህ ነገር እንደማይፈቀድ፣ ጥራት የተገባው አላህ ፍጡራንን የፈጠረው እርሱን እንዲያመልኩት እንደሆነ፣ እንዲሁም ይህንኑ አምልኮ እንዲያብራሩና ወደርሱም ጥሪ እንዲያደርጉ መልዕክተኞችን ልኮ መጻሕፍትን እንዳወረደ በግልፅ መረጃና በዑለማዎች ባጠቃላይ የጋራ ስምምነት ይታወቃል። ጥራት የተገባው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنْسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ56﴾
{ጂኒንና ሰዉንም ሊገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸዉም::} [አዝ-ዛሪያት፡ 56] የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ...﴾
{በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትንም ራቁ በማለት መልዕክተኛን በእርግጥ ልከናል...} [አን-ነሕል፡ 36] የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ 25﴾
{ካንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጂ ከመልዕክተኛ አንድንም አላክንም።} [አል-አንቢያእ፡ 25] ክብሩ የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿الر كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِنْ لَدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ1 أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ إِنَّنِي لَكُمْ مِنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ2﴾
{አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ ይህ ቁርኣን አናቅጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ፤ ጥበበኛና ውስጠ አዋቂ ከሆነው (አምላክ) ዘንድ የተወረደ መጽሐፍ ነው::
(እንዲህ በላቸው) «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ:: እኔ ለእናንተ ከእርሱ ዘንድ የተላኩ አስፈራሪና አብሳሪ ነኝ።» [ሁድ: 1-2]
የላቀው አላህ በእነዚህ ግልፅ አንቀፆች ሰዎችንና ጋኔኖችን የፈጠራቸው ምንም አጋር የሌለውን እርሱን በብቸኝነት እንዲያመልኩት መሆኑን፣ መልዕክተኞቹንም የላከው በዚሁ አምልኮ እንዲያዙና ከተቃራኒው እንዲከለክሉ እንደሆነ፣ እንዲሁም ከእርሱ ውጪ ሌላ አካል እንዳይመለክ የቁርአንን አንቀፆች በማጥራት በዝርዝር እንዳብራራቸውም ግልፅ አድርጓል።
እንደሚታወቀው ዒባዳ (አምልኮ) ማለት፡- አላህን በብቸኝነት ማምለክና ያዘዘውን በመፈጸም እንዲሁም ከከለከለው በመራቅ እርሱን መታዘዝ ነው። አላህም ይህን አስመልክቶ በበርካታ የቁርኣን አንቀጾች ላይ አዟልም ገልጿልም። ከእነዚህም መካከል የሚከተለው የአላህ ንግግር ይገኝበታል፦
﴿وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاءَ...﴾
{ሃይማኖትን ለአላህ ብቻ አጥሪዎችና ቀጥተኞች ሆነው አላህን ሊገዙት እንጂ ያልታዘዙ ሲሆኑ (ተለያዩ)...} [አል-በይናህ፡ 5] አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿وَقَضَى رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ...﴾
{ጌታህ እንዲህ ሲል አዘዘ:: እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤…} [አልኢስራእ: 23] የላቀው አላህ እንዲህም ይላል፦
﴿إِنَّآ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ فَٱعۡبُدِ ٱللَّهَ مُخۡلِصٗا لَّهُ ٱلدِّينَ2 أَلَا لِلَّهِ ٱلدِّينُ ٱلۡخَالِصُۚ وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَ مَا نَعۡبُدُهُمۡ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَآ إِلَى ٱللَّهِ زُلۡفَىٰٓ إِنَّ ٱللَّهَ يَحۡكُمُ بَيۡنَهُمۡ فِي مَا هُمۡ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي مَنۡ هُوَ كَٰذِبٞ كَفَّارٞ3﴾
{እኛ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት የተሞላ ሲሆን አወረድነው:: አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ሆነህ ተገዛው::
ንቁ! ፍጹም ጥሩ የሆነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው:: እነዚያም ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድረገው የያዙት «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን እንጂ ለሌላ አንገዛቸዉም።» ይላሉ:: አላህ በዚያ እነርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል:: አላህም ውሸታም ከሓዲ የሆነን ሰው አያቀናም::} [አዝ-ዙመር: 2-3]
ይህንኑ መልዕክት ይዘው የመጡ አንቀፆች በርካታ ናቸው። ሁሉም የሚያመላክቱት በአምልኮ አላህን ብቻ ነጥለን መገዛታችን እና ከእርሱ ውጭ ያሉ ነቢያትንም ሆኑ ሌሎችን ማምለክን መተው ግዴታ መሆኑን ነው።
ዱዓእ ከታላላቅና ሁሉን አቃፊ ከሆኑ የአምልኮ አይነቶች መካከል አንዱ በመሆኑ ለአላህ ብቻ ጥርት ተደርጎ መፈፀሙ ግዴታ ነው። አሸናፊና የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿فَادْعُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ14﴾
{አላህንም ከሓዲዎች ቢጠሉም (እንኳ) ሃይማኖትን ለእርሱ አጥሪዎች ሆናችሁ ተገዙ::} [ጋፊር፡ 14] የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا18﴾
{ እነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው:: በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ ማለትን ተወረደልኝ::} [አል_ጂን፡ 18] ይህ አላህን በዱዓእ ብቸኛ የማድረግ መመሪያ ነቢያትንም ሆነ ሌሎችን ፍጡራን ሁሉ ያጠቃልላል፤ የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿وَلَا تَدْعُ مِنْ دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَنْفَعُكَ وَلَا يَضُرُّكَ فَإِن فَعَلۡتَ فَإِنَّكَ إِذٗا مِّنَ ٱلظَّٰلِمِينَ106﴾
{«ከአላህም በቀር የማይጠቅምህንና የማይጎዳህን አትገዛ:: ይህን ብትሠራ ያን ጊዜ አንተ ከበደለኞቹ ትሆናለህ» (ተብያለሁ በላቸው)።} [ዩኑስ፡ 106] ይህም ለነቢዩ ﷺ የተላለፈ ንግግር ሲሆን፤ አላህ እርሳቸውን ከሽርክ መጠበቁ የታወቀ ነው። ከዚህ የተፈለገበት ዓላማ ግን እርሳቸውን ሳይሆን ሌሎችን ለማስጠንቀቅ ነው። የላቀው አላህ እንዲህ አለ፡
﴿وَلَا تَدۡعُ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكَ وَلَا يَضُرُّكَ فَإِنْ فَعَلْتَ فَإِنَّكَ إِذًا مِنَ الظَّالِمِينَ106﴾
{«ከአላህ በስተቀር የማይጠቅምህንና የማይጎህዳን አትገዛ:: ይህን ብትሠራ ያን ጊዜ አንተ ከበደለኞቹ ትሆናለህ» (ተብያለሁ በላቸው)።} [ዩኑስ፡ 106] ይህ ለነቢዩ ﷺ የቀረበ ንግግር ሲሆን፥ የተፈለገበትም ከእርሳቸው ውጭ ያሉ ሌሎችን ማስጠንቀቅ ነው፤ ምክንያቱም አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) መልዕክተኛውን ከሽርክ መጠበቁ የታወቀ ነው። ከዚያም አላህ ክልከላውንና ማስጠንቀቂያውን በማጠናከር እንዲህ አለ፦
﴿...فَإِنْ فَعَلْتَ فَإِنَّكَ إِذًا مِنَ الظَّالِمِينَ﴾
{«ይህን ብትሠራ ግን ያን ጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ»…} በደል በደፈናው ሲጠቀስ የሚፈለግበት፡ ትልቁ ሺርክ ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿...وَالْكَافِرُونَ هُمُ الظَّالِمُونَ﴾
{…ከሃዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው።} [አልበቀራህ፡ 254] የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿...إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ﴾
{…ማጋራት ታላቅ በደል ነውና።} [ሉቅማን: 13] የአደም ልጆች ሁሉ አለቃ የሆኑት ﷺ እርሳቸው እንኳ ከአላህ ውጭ ሌላን ቢጣሩ ከበዳዮች የሚመደቡ ከሆኑ ሌላው እንዴት ሊሆን ነው?
ከነዚህና ከሌሎችም አንቀፆች ያወቅነው ነገር ቢኖር ከአላህ ውጭ ያለን አካል — ሙታንን፣ ዛፎችን፣ ጣዖታትንና የመሳሰሉትን — መማፀን በላቀው አላህ ላይ ሽርክ (ማጋራት) እንደሆነ ነው። ይህ ድርጊት አላህ ሰዎችንና ጂኖችን የፈጠረበት፣ መልክተኞችን የላከበትና መጽሐፍትን ያወረደበት አላማ የሆነውን በአምልኮ አላህን መነጠልን (ተውሒድን) የሚፃረርና፤ ከአላህ ውጭ ላለ አካል አምልኮን ውድቅ በማድረግ ለአላህ ብቻ የምታፀድቅ የሆነችውን የ«ላ ኢላሀ ኢለላህ»ን ትርጉምም የሚጋጭ ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ هُوَ ٱلۡبَٰطِلُ وَأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡعَلِيُّ ٱلۡكَبِيرُ62﴾
{ይህ አላህ ፍፁም እውነት በመሆኑ፤ ከርሱም ሌላ የሚገዙት ነገር ፍጹም ውሸት በመሆኑና አላህም የሁሉ በላይ ታላቅ በመሆኑ ነው::} [አል'ሐጅ፡ 62]
ይህም የሃይማኖቱ መሰረት እና የሃይማኖቱም ምሰሶ ነው፤ አምልኮዎችም ትክክል የሚሆኑት ይህ መሰረት ትክክለኛ ከሆነ በኋላ ነው። የበላይ የሆነው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَلَقَدْ أُوحِيَ إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ65﴾
{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብታጋራ ስራህ በእርግጥ ይታበሳል:: በእርግጥም ከከሓዲያን ትሆናለህ በማለት ወደ አንተና እነዚያ ካንተ በፊት ወደ ነበሩት በእርግጥ ተወርዷል::} [አዝ-ዙመር፡ 65] ጥራት የተገባውና የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿...وَلَوْ أَشْرَكُوا لَحَبِطَ عَنْهُمْ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ﴾
{…በአላህ ባጋሩም ኖሮ ይሰሩት የነበሩት መልካም ተግባር ሁሉ ከእነርሱ በታበሰባቸው ነበር::} [አልአንዓም፡ 88]
ቀደም ብለን ካብራራነው የእስልምና ሃይማኖትና ‹ላ ኢላሃ ኢለላህ› የምትለዋ የምስክርነት ቃል ሁለት ታላላቅ መሰረቶች እንዳላቸው እንረዳለን፦
አንደኛው፡ አላህ ብቻውን ሊመለክና በርሱ ላይ ምንም ነገር ላይጋራበት ነው። ስለዚህ ከነብያትም ሆነ ከሌሎች ሙታንን የለመነ፣ ወይም ጣዖታትን፣ ዛፎችን፣ ድንጋዮችን ወይም ሌሎች ፍጡራንን የለመነ፣ ወይም በእነርሱ እርዳታ የጠየቀ፣ ወይም በእርድና በስለት ወደ እነርሱ የተቃረበ፣ ወይም ለነርሱ የሰገደ ሰው በእርግጥ ከአላህ ውጭ ጌቶች አድርጓቸዋል ለእርሱ ባላንጣዎችም አድርጓቸዋል። የላ ኢላሃ ኢለሏህንም ትርጉም ተፃርሯል ውድቅም አድርጓል።
ሁለተኛው: ከፍ ያለው አላህን በመልዕክተኛው ﷺ ሸሪዓ እንጂ በሌላ አለማምለክ ነው። በሃይማኖት ውስጥ አላህ ያልፈቀደውን አዲስ ነገር የፈጠረ ሰው ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ የመሆናቸውን የምስክርነት ቃል ፅንሰ ሃሳብ አላረጋገጠም፤ ስራውም አይጠቅመውም፤ ከእርሱም ተቀባይነት አይኖረውም። ታላቅነትና ክብር የተገባው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَقَدِمْنَا إِلَى مَا عَمِلُوا مِنْ عَمَلٍ فَجَعَلْنَاهُ هَبَاءً مَنْثُورًا23﴾
{ከስራም ወደ ሰሩት እናስባለን:: የተበተነ ትቢያም እናደርገዋለን::} [አልፉርቃን: 23] በአንቀጹ ውስጥ ስራዎች በማለት የተፈለገው በአላህ ላይ በማጋራት የሞተ ሰው ስራዎች ናቸው።
በተጨማሪም አላህ ያልፈቀዳቸው የቢድዓ ስራዎችም እዚህ ውስጥ ይካተታሉ። የቢድዓ ስራዎች ንፁህ ከሆነው የአላህ ሸሪዓ ጋር ባለመግጠማቸው በትንሳኤው ቀን የተበታተነ ትቢያ ይሆናሉ። ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
«مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ مِنْهُ فَهُوَ رَدٌّ».
"በዚህ ሃይማኖታችን ውስጥ ከእርሱ ያልሆነን አዲስ ነገር ያመጣ ይዞት የመጣው አዲስ መጤ ነገር ውድቅ ነው።" ሶሒሕ በመሆኑ ላይ ተስማምተውበታል።
ነገሩን ስናጠቃልልም: ይህች ጸሐፊ የይድረሱልኝ ጥሪዋንና ዱዓዋን ለረሱል ﷺ እንዳቀረበች፤ ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዳቸውም ከእርሱ ውጭ ከማንም እጅ የማይገኝ ከሆነው፣ ድል ሰጪ ከሆነው፣ ጉዳትና ጥቅም በእጁ ከሆነው የዓለማት ጌታ ጀርባዋን መስጠቷ ነው።
ይህ ታላቅና ከባድ በደል መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ከፍ ያለው አላህ እርሱን እንዲለምኑት አዟል፤ የሚለምኑትንም እንደሚቀበላቸው ቃል ገብቷል። ከዚህ የሚኮሩትንም ጀሀነም እንደሚያስገባቸው በዛቻ አስጠንቅቋል፤ ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፡
﴿وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ 60﴾
{ጌታችሁም አለ: «ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነም በእርግጥ ይገባሉ።»} (ጋፊር፡60) ማለትም፡ የተዋረዱና የተናቁ ሆነው ጀሃነም ይገባሉ። ይህች የተከበረች አንቀፅ ዱዓእ አምልኮ መሆኑንና ከእርሱ የሚኮራ ሰው መዳረሻው ጀሀነም መሆኑን ታስረዳለች። አላህን ከመለመን የተኩራራ ሰው ፍፃሜው ይህ ከሆነ፤ አላህ ጥራት የተገባው ቅርብ፣ የሁሉም ነገር ባለቤትና በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ሆኖ ሳለ ከእርሱ ፊቱን አዙሮ ሌላን የለመነ ሰው ሁኔታው እንዴት ሊሆን ነው? ጥራት የተገባው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ 186﴾
{ባሮቼም ስለ እኔ በጠየቁህ ጊዜ እኔ ቅርብ ነኝ:: የለማኝን ጸሎትም በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ:: ስለዚህ ለእኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና። (በላቸው።)} (አል'በቀራህ፡186) ረሱል ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሶሒሕ ሐዲሣቸው ዱዓእ አምልኮ እንደሆነ ተናግረዋል። እንዲሁም ለአጎታቸው ልጅ ለዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁማ እንዲህ ብለዋል፡-
«احْفَظِ اللهَ يَحْفَظْكَ، احْفَظِ اللهَ تَجِدْهُ تُجَاهَكَ، إِذَا سَأَلْتَ فَاسْأَلِ اللهَ، وَإِذَا اسْتَعْنَتَ فَاسْتَعِنْ بِاللهِ».
"የአላህን ትእዛዝና ክልከላ ጠብቅ አላህ ይጠብቅሃል። የአላህን ትእዛዝና ክልከላ ጠብቅ ከፊትህ ታገኘዋለህ። ማንኛውንም ነገር ስትለምን ከአላህ ዘንድ ለምን፤ እርዳታ ከፈለግክም በአላህ ታገዝ።" ቲርሚዚይና ሌሎችም ዘግበውታል።
ነቢዩ ﷺ እንዲህም ብለዋል፡
«مَنْ مَاتَ وَهُوَ يَدْعُو لِلَّهِ نِدًّا؛ دَخَلَ النَّارَ».
«ከአላህ ውጭ ሌላን እየተጣራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።» ቡኻሪ ዘግበውታል። በሶሒሕ ቡኻሪና ሙስሊም እንደተዘገበው ነብዩ ﷺ ‹እጅግ ትልቁ ወንጀል ምንድነው?› ተብለው ተጠይቀው እንዲህ አሉ፦
«أَنْ تَجْعَلَ لِلَّهِ نِدًّا وَهُوَ خَلَقَكَ».
«አላህ ፈጥሮህ ሳለ፤ ለአላህ ቢጤ ማድረግህ ነው፡፡» "ኒድ" ማለት አቻና አምሳያ ማለት ነው። ስለዚህም ነብይንም፣ ወልይንም፣ መልአክንም፣ ጂንንም፣ ጣዖትንም ሆነ ወይም ከዚህ ውጭ ያለን ሌላ ፍጡር ከአላህ ውጭ የተጣራ፣ የድረሱልኝ ጥሪ ያቀረበ፣ ስለት የተሳለለት፣ እርድ ያረደለት ወይም ከነዚህ ውጭ የሆነ ማንኛውንም የአምልኮ አይነት ለእርሱ የፈፀመ ማንም ቢሆን በእርግጥም ይህንን አካል (ለአላህ) ኒድ አድርጎ ይዞታል።
እዚህ ላይ አንድ ሰው እንዲህ የሚል ጥያቄ ሊያነሳ ይችላል፦ በህይወት ያለንና በቦታው ላይ የሚገኝን ሰው ሊያሳካልን የሚችለውን ነገር መጠየቅና አቅሙ የሚፈቅድለትን ህዋሳዊ (ተጨባጭ) ጉዳይ እንዲያግዘን በእርሱ መታገዝስ ብይኑ ምንድን ነው? መልሱም፦ ይህ ከሽርክ የሚመደብ አይደለም፤ ይልቁንም በሙስሊሞች መካከል የተፈቀዱ እና የተለመዱ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል ነው። አላህ ስለ ሙሳ ሲተርክ እንዲህ ብሏል፦
﴿...فَاسْتَغَاثَهُ الَّذِي مِنْ شِيعَتِهِ عَلَى الَّذِي مِنْ عَدُوِّهِ...﴾
{…ያም ከወገኑ የሆነው ሰው በዚያ ከጠላት በሆነው ሰው ላይ እርዳታን ጠየቀው…} [አል-ቀሶስ፡ 15] በተመሳሳይ በሌላ አንቀፅ አላህ ስለ ሙሳ ሲተርክ እንዲህ ብሏል፦
﴿فَخَرَجَ مِنْهَا خَائِفًا يَتَرَقَّبُ...﴾
{የፈራና የሚጠባበቅ ሆኖም ከእርሷ ወጣ...} [አል-ቀሶስ፡ 21] አንድ ሰው እንደ ጦርነትና መሰል ሰዎችን የሚያጋጥሟቸው አደጋዎች ሲከሰቱበት እርስ በርስ ስለሚፈላለጉ ከጓዶቹ እርዳታን መማፀኑ እንደተጨማሪ ምሳሌ ይጠቀሳል።
አላህም ነቢዩን ﷺ ለማንም ሰው ጥቅምና ጉዳት ማምጣት እንደማይችሉ ለኡመታቸው እንዲነግሩ አዟል። አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿قُلْ إِنَّمَا أَدْعُو رَبِّي وَلَا أُشْرِكُ بِهِ أَحَدًا21 قُلْ إِنِّي لَا أَمْلِكُ لَكُمْ ضَرًّا وَلَا رَشَدًا22﴾
{«እኔ የማመልከው ጌታየን ብቻ ነው:: በእርሱም አንድንም አላጋራም» በል።
«እኔ ለእናንተ ጉዳትንም ሆነ ማቅናትን አልችልም» በላቸው።} [አል-ጂን: 20-21] የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿قُلْ لَا أَمْلِكُ لِنَفْسِي نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ وَلَوْ كُنْتُ أَعْلَمُ الْغَيْبَ لَاسْتَكْثَرْتُ مِنَ الْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِيَ السُّوءُ إِنْ أَنَا إِلَّا نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ لِقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ188﴾
{«አላህ የሻዉን በስተቀር ለራሴ ጥቅምንም ሆነ ጉዳት ማምጣት አልችልም:: የሩቅን ሚስጥር የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ሁሉ ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር:: እኔም ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» በላቸው::} [አል'አዕራፍ: 188]
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው ቁርአናዊ ማስረጃዎች በርካታ ናቸው።
እንደሚታወቀው ነቢዩ ﷺ ከጌታቸው በቀር አይማፀኑም ነበር። ከእርሳቸው እንደተረጋገጠውም በበድር ቀን አላህን እርዳታ ጠይቀው ነበር፣ በጠላታቸው ላይ ድልን እንዲያጎናፅፋቸው ይማፀኑት ነበር። አስ-ሲዲቁል አክበር አቡበክር (አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና) «የአላህ መልእክተኛ ሆይ ይበቃዎታል፤ አላህ የገባልህን ቃል ፈጻሚ ነው» እስከሚላቸውም ድረስ «ጌታዬ ሆይ! የገባህልኝን ቃል ሙላልኝ» እያሉ አጥብቀው ይለምኑ ነበር። የላቀው አላህም በዚያን ጊዜ እንዲህ ሲል ንግግሩን አወረደ፦
﴿إِذۡ تَسۡتَغِيثُونَ رَبَّكُمۡ فَٱسۡتَجَابَ لَكُمۡ أَنِّي مُمِدُّكُم بِأَلۡفٖ مِّنَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ مُرۡدِفِينَ9﴾
{ከጌታችሁ እርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ «እኔ በሺህ መላዕክት ተከታታዮች ሲሆኑ እረዳችኋለሁ።» ሲል ለእናንተ የተቀበላችሁን አስታውሱ።} [አል-አንፋል: 9] ጥራት የተገባው ጌታ በእነዚህ አንቀጾች ሙስሊሞች እርዳታን መፈለጋቸውን አስታውሷቸዋል፡፡ ለእነርሱም እንደተቀበላቸውና ድልን ለማበሰርና እርጋታን ለመስጠትም በመላእክት እንደረዳቸው አሳውቋል፡፡ ድሉ ከመላእክት ሳይሆን ከእርሱ ዘንድ ብቻ መሆኑንም አብራርቷል፡፡ ከፍ ያለው ጌታም እንዲህ አለ፡-
﴿وَمَا النَّصْرُ إِلَّا مِنْ عِنْدِ اللَّهِ...﴾
{ድልም ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው...} [አሊ-ዒምራን፡ 126] የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَلَقَدْ نَصَرَكُمُ اللَّهُ بِبَدْرٍ وَأَنْتُمْ أَذِلَّةٌ فَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ123﴾
{በበድርም እናንተ ጥቂቶች ሆናችሁ ሳለ አላህ በእርግጥ ረዳችሁ:: አላህን ታመሰግኑ ዘንድ ፍሩት::} [አሊ-ዒምራን፡ 123] ከፍ ያለው አላህ በበድር ቀን ረዳታቸው እርሱ መሆኑን በዚህች አንቀጽ አብራርቷል፡፡ በዚህም የሰጣቸው የጦር መሣሪያና ኃይል፣ እንዲሁም በመላእክት ያገዛቸውም እገዛ፣ ይህ ሁሉ ለድል፣ ለብስራትና ለልብ እርካታ ሰበቦች ብቻ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ድል ማድረግን የሚሰጡት ግን እነዚህ ሰበቦች አይደሉም፤ ይልቁንም ድል አድራጊነት ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ይህቺ ፀሐፊ ወይም መሰሎቿ፣ የሁሉም ነገር ባለቤትና በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ከሆነው ከዓለማቱ ጌታ ፊታቸውን አዙረው፣ እንዴት ደፍረው ነው የእርዳታ ጥሪያቸውንና የድል ልመናቸውን ወደ ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሚያቀርቡት?
ይህ ምንም ጥርጥር የሌለው እጅግ አስፀያፊ መሃይምነት ነው፤ ይልቁንም ከባባድ ከሆኑ የሽርክ አይነቶች ነው። በመሆኑም ጸሐፊዋ ወደ አላህ (ሱብሃነሁ) ተጸጽታ በንጹህ ተውበት መመለስ ይኖርባታል። ንጹህ ተውበት የሚባለው ደግሞ በርካታ ጉዳዮችን ያካተተ ሲሆን እነሱም፥ የመጀመሪያው: በፈጸመችው ነገር መጸጸት ነው። ሁለተኛው፡ ከተፈፀመው ወንጀል መላቀቅ ነው። ሶስተኛው: አላህን በማላቅ፣ ለእርሱም ጥርት በማድረግ፣ ትዕዛዙንም በመፈጸምና ከከለከለው ነገር በመጠንቀቅ ወደ ወንጀሉ ላለመመለስ መወሰን ነው፤ እውነተኛ ተውበት (ንስሀ) የሚባለው ይህ ነው። አራተኛው ደግሞ ወንጀሉ ከፍጡራን ሐቅ ጋር የተያያዘ ከሆነ ሐቁን ለባለቤቱ መመለስ ወይም ይቅርታውን መጠየቅ ነው።
አላህ ባሮቹን ተውበት እንዲያደርጉ አዟቸዋል፤ እንደሚቀበላቸውም ቃል ገብቶላቸዋል፤ የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿...وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ﴾
{ምዕመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ በመመለስ ተጸጸቱ::} (አን-ኑር 31) ክርስትያኖችንም አስመልክቶ እንዲህ ብሏል፦
﴿أَفَلَا يَتُوبُونَ إِلَى اللَّهِ وَيَسْتَغْفِرُونَهُ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَحِيمٌ74﴾
{ወደ አላህ አይመለሱምና ምህረትን አይለምኑትምን? አላህም መሀሪና አዛኝ ነው::} [አል-ማኢዳህ: 74] ጥራት ይገባውና እንዲህም ብሏል፡
﴿وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ وَمَنْ يَفْعَلْ ذَلِكَ يَلْقَ أَثَامًا68 يُضَاعَفْ لَهُ الْعَذَابُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَيَخْلُدْ فِيهِ مُهَانًا69 إِلَّا مَنْ تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَالِحًا فَأُولَئِكَ يُبَدِّلُ اللَّهُ سَيِّئَاتِهِمْ حَسَنَاتٍ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَحِيمًا70﴾
{ እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደርጋትን ነፍስ ያለ ህግ የማይገድሉ እና የማያመነዝሩት ናቸው:: ይህንንም የሚፈጽም ሰው ቅጣትን ያገኛል::
በትንሳኤ ቀን ቅጣቱ ይደራረብበታል:: በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ሆኖ ዘላለሙን ይኖራል::
ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ስራ የሰራ ሰው ብቻ ሲቀር እነዚያም አላህ መጥፎ ስራዎቻቸውን በመልካም ስራዎች ይለውጣል:: አላህም እጅግ መሓሪና አዛኝ ነው::} [አል-ፉርቃን፡ 68-70] የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَهُوَ الَّذِي يَقْبَلُ التَّوْبَةَ عَنْ عِبَادِهِ وَيَعْفُو عَنِ السَّيِّئَاتِ وَيَعْلَمُ مَا تَفْعَلُونَ25﴾
{እርሱም ያ ከባሮቹ ንስሓን የሚቀበል፣ ከኃጢአቶችም ይቅር የሚል የምትሰሩትንም ሁሉ የሚያውቅ ነው።} [አሽ-ሹራ: 25]
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ማለታቸውም በሶሒሕ ሐዲሥ ተዘግቧል፡-
«الإِسْلَامُ يَهْدِمُ مَا كَانَ قَبْلَهُ، وَالتَّوْبَةُ تَجُبُّ مَا كَانَ قَبْلَهَا».
«ኢስላም ከእርሱ በፊት የነበረውን (ወንጀል) ያስምራል፤ ንስሐም ከእርሷ በፊት የነበረውን ወንጀል ታስሰርዛለች።»
የሽርክ አደገኝነት ታላቅ በመሆኑ፣ ከወንጀሎችም ሁሉ የከፋ በመሆኑ፣ ከዚህች ፀሐፊ የወጣው ጽሑፍ ሰዎችን እንዳይሸውድ በመስጋት፣ እንዲሁም ለአላህና ለባሮቹ መቆርቆር እና ታማኝ መሆን ግዴታ በመሆኑ፤ ይህችን አጠር ያለች መልዕክት አዘጋጅቻለሁ። ታላቅና የላቀ የሆነውን አላህ በእርሷ ተጠቃሚ እንዲያደርገን፤ የእኛንም ሆነ የመላው ሙስሊሞችን ጉዳይ እንዲያበጅልን፤ ሁላችንንም በዲን ላይ ግንዛቤንና በርሱም ላይ ፅናትን እንዲለግሰን፤ እኛንም ሆነ ሙስሊሞችን ከነፍሶቻችን ክፋትና ከመጥፎ ስራዎቻችን እንዲታደገን እማፀነዋለሁ። እነሆ እርሱ ለዚህ ተማፅኖ የተገባ እውን ሊያደርገው ቻይም ነውና።
የአላህ ሰላት፣ ሰላምና በረከት ባሪያውና መልዕክተኛው በሆኑት በነብያችን ሙሐመድ እንዲሁም በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ይስፈን።
***
بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ
ሦስተኛው መልዕክት:
ጂኒዎችና ሰይጣናትን እርዳታን መለመንና ለእነርሱ ስለት መግባት ያለው ብይን:-
ከዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ ይህንን መልዕክት ለሚያይ ሙስሊም ባጠቃላይ የተላለፈ መልዕክት: አላህ እኔንም እነርሱንም ሃይማኖቱን አጥብቀን ለመያዝና በርሱ ላይ ለመጽናት ይግጠመን! አሚን።
አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ
ከዚህ በመቀጠል፥ አንድ ወንድም አንዳንድ መሃይማን ስለሚፈፅሙት ድርጊት ጠየቀኝ፤ ይኸውም ከአላህ (ሱብሓነሁ) ውጪ ያለን አካል መለመን፣ በአሳሳቢ ጉዳዮች ላይ ከእርሱ እርዳታ መፈለግ፤ ለምሳሌ ጂንን መለመን፣ ከእነርሱ እርዳታን መፈለግ፣ ለእነርሱ ስለት መግባትና ለእነርሱ እርድ ማቅረብ ያሉትን በተመለከተ ነው። ከዚህ ጋርም ተያይዞ የአንዳንዶች እንዲህ የሚል ንግግር ይጠቀሳል፦ «ያ ሰብዓህ (ማለትም ሰባቱ የጂን መሪዎች ሆይ!) ውሰዱት፤ አጥንቱን ስበሩት፤ ደሙን ጠጡ፤ አካሉን አበላሹት፤ እናንተ ሰባቶች ሆይ! እንዲህ እንዲህ አድርጉት።» ወይም አንዳንዶች፡ «የቀትር ጅኖች ሆይ፣ የአስር ጅኖች ሆይ ውሰዱት» የሚለው ንግግር፤ ይህም በአንዳንድ ደቡባዊ አካባቢዎች በብዛት ይገኛል። ነብያትን፣ ደጋጎችንና ሌሎች ሙታንን መለመን፣ እንዲሁም መላኢካዎችን መለመንና ከነርሱ እርዳታ መፈለግም እዚህ ርዕስ ውስጥ ከሚካተቱት መካከል ነው፦ ይህ ሁሉና መሰሎቹ ወደ እስልምና የሚጠጉ ብዙ ሰዎች ባለማወቅና ቀዳሚዎቻቸውን በመከተል የሚፈፅሙት ነው። ምናልባትም አንዳንዶቻቸው በዚህ ጉዳይ ላይ በማቅለል እንዲህ ሲሉ ይሞግታሉ፡- «ይህ በምላስ ላይ እንዲሁ የሚባል ነገር እንጂ የምንፈልገውም ሆነ የምናምንበት አይደለም።»
እነዚህን ስራዎች በመስራት የሚታወቁ ሰዎችን ስለማግባት፣ እርዳቸውን ስለመብላት፣ በነርሱ ጀናዛ ላይ ስለመስገድና ከኋላቸው ተከትሎ ስለመስገድ ስላለው ኢስላማዊ ፍርድ፤ እንዲሁም ከታካሚው ሰውነት ጋር የተነካካን ነገር እንደ ጥምጣም፣ ሱሪ፣ ሻሽ እና መሰል ነገሮችን ብቻ በማየት የበሽታውን አይነትና መንስኤውን እናውቃለን ብለው በሚሞግቱ አጭበርባሪዎችና ሟርተኞች ስለማመንም ጨምሮ ጠይቆኛል።
መልሱም፦ ምስጋና ሁሉ ለብቸኛው አላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላትና ሰላም ከእሳቸው በኋላ ነብይ በሌለ በሆኑት ነብይ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸውም እንዲሁም እስከ ዕለተ ፍርድ ድረስ የእነርሱን ቅን ጎዳና በተከተሉትም ላይ ሁሉ ይስፈን።
ከዚህ በመቀጠል፦ ጥራት የተገባውና ከፍ ያለው አላህ ሰውንና ጋኔኖችን የፈጠረው ከእርሱ ውጪ ያለን ነገር ሁሉ ትተው እርሱን በብቸኝነት እንዲያመልኩት፤ እንዲሁም ዱዓእን፣ እርዳታ መፈለግን፣ እርድን፣ ስለትንና ሌሎች የአምልኮ ዓይነቶችን በሙሉ ለእርሱ ብቻ እንዲያደርጉ ነው። መልዕክተኞችንም የላከውና ያዘዛቸውም ለዚሁ ነው። ታላቁ የሆነውን የተከበረውን ቁርአን ጨምሮ መለኮታዊ መጽሐፍትን ያወረደው ይህንኑ ጉዳይ እንዲያብራሩና ወደርሱም ጥሪ እንዲያደርጉ፣ ሰዎችንም በአላህ ከማጋራትና ከእርሱ ሌላ ያለን አካል ከማምለክ እንዲያስጠነቅቁ ነው። ይህ የመሠረቶች ሁሉ መሠረት እንዲሁም የሃይማኖትና እምነት መሠረት ነው። ይህም የምስክር ቃል የሆነችው የ “ላ ኢላሃ ኢለሏህ” ፅንሰ ሃሳብ ሲሆን “ከአላህ በስተቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው ሌላ አምላክ የለም” የሚለው ማረጋገጫም ነው። ላኢላሃ ኢለሏህ ከአላህ ውጭ ላለ ነገር ተመላኪነትንና አምልኮን ውድቅ ታደርጋለች፤ ይህንኑ አምልኮ ከእርሱ ውጭ ካሉ ፍጥረታት ሁሉ በመነጠል ለአላህ ብቻ መሆኑን ታጸድቃለች። በዚህ ዙሪያ ከቁርአንና ከመልዕክተኛው ﷺ ሱና የተገኙ ማስረጃዎች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። ከእነዚህም መካከል ልዕልናው የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنْسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ56﴾
{ጂኒንና ሰዉንም ሊገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸዉም::} [አዝ-ዛሪያት፡ 56] የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿وَقَضَى رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ...﴾
{ጌታህም እንዲህ ሲል አዘዘ:: እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ።} [አልኢስራእ፡23] አላህ እንዲህም ብሏል:
﴿وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاءَ...﴾
{ሃይማኖትን ለአላህ ብቻ አጥሪዎችና ቀጥተኞች ሆነው አላህን ሊገዙት እንጂ ያልታዘዙ ሲሆኑ (ተለያዩ)} [አል-በይናህ፡ 5] አላህ እንዲህም ብሏል:
﴿وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ60﴾
{ጌታችሁም አለ: «ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነም በእርግጥ ይገባሉ።»} [ጋፊር፡ 60] የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ...﴾
{ባሮቼም ስለ እኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው) እኔ ቅርብ ነኝ:: የለማኝን ጸሎትም በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ...} [አልበቀራህ: 186]
ጥራት የተገባው አምላክ ሰውንና ጋኔንን የፈጠራቸው እርሱን እንዲያመልኩት መሆኑን፣ እንዲሁም በተብራራው ቁርኣኑና በመልዕክተኛውም ﷺ አንደበት አማካኝነት ከጌታቸው በስተቀር ሌላን እንዳያመልኩ በባሮቹ ላይ የደነገገ መሆኑን በእነዚህ አንቀጾች አብራርቷል።
የላቀውና ከፍ ያለው አላህ ዱዓእ ታላቅ አምልኮ መሆኑንና ከእርሱ የኮራ ሰው እሳት እንደሚገባ አብራርቷል። ባርያዎቹንም እርሱን ብቻ እንዲለምኑት አዟል፤ እርሱም ቅርብ መሆኑንና ልመናቸውንም እንደሚቀበል አሳውቋል። በመሆኑም በሁሉም ባርያዎች ላይ ጌታቸውን ብቻ በዱዓእ የመለመን ግዴታ አለባቸው፤ ምክንያቱም (ዱዓእ) ከተፈጠሩበትና ከታዘዙበት የአምልኮ አይነት ነውና። የላቀውና ከፍ ያለው አላህም እንዲህ ብሏል፦
﴿قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ162 لَا شَرِيكَ لَهُ وَبِذَلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُسْلِمِينَ163﴾
{ «ስግደቴ፤ መገዛቴም፣ ሕይወቴም፤ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ነው።
ለእርሱ (ለአላህ) አጋር የለዉም:: በዚህም (አላህን ከተጋሪ በማጥራት) ታዘዝኩ:: እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ።» በል።} [ሱረቱል አንዓም: 162 - 163]
አላህም ለነቢዩ ﷺ ሶላታቸው፣ እርዳቸው፣ ህይወታቸውና ሞታቸውም ተጋሪ ለሌለው የዓለማት ጌታ ለአላህ ብቻ እንደሆነ ለሰዎች እንዲነግሩ አዟቸዋል። በዚህ መሰረት ከአላህ ውጭ ላለ አካል እርድን የሰዋ ልክ ከአላህ ውጭ ላለ አካል ሶላት እንደሰገደው ሁሉ በአላህ ላይ በእርግጥም አጋርቷል። ምክንያቱም የላቀው አላህ ሶላትንና እርድን አጣምሮ ነው የገለፃቸውና፤ ሁለቱም ተጋሪ ለሌለው ለአላህ ብቻ መሆናቸውንም ገልጿል። ለጋኔኖች፣ ለመላእክቶች፣ ለሙታኖች እና ለመሳሰሉት ከአላህ ውጭ ላሉ አካላት ወደነሱ ለመቃረብ በማሰብ እርድ የፈፀመ ሰው ከአላህ ውጭ ላለ አካል ከሰገደ ሰው ጋር ተመሳሳይ ነው። ሶሒሕ በሆነ ሐዲሥም ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«لَعَنَ اللهُ مَنْ ذَبَحَ لِغَيْرِ اللهِ».
«ከአላህ ውጭ ላለ አካል እርድን መስዋእት ያደረገ አላህ ረግሞታል።» ኢማሙ አሕመድም ሐሰን በሆነ ሰነድ ከጧሪቅ ኢብኑ ሺሀብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በዘገቡት ሐዲሥ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
«مرَّ رَجُلَانِ عَلَى قَومٍ لَهُم صَنَمٌ لَا يَجُوزُهُ أَحَدٌ حَتَّى يُقرِّبَ لَهُ شَيئًا، فَقَالُوا لِأَحَدِهِمَا: قَرِّبْ. قَالَ: لَيسَ عِندِي شَيءٌ أَقَرِّبُهُ، قَالُوا: قَرِّبْ وَلَوْ ذَبَابًا، فَقَرَّبَ ذُبَابًا، فَخَلُّوا سَبِيلَهُ، فَدَخَلَ النَّارَ، وَقَالُوا لِلآخَرِ: قَرِّبْ. قَالَ: مَا كُنْتُ لِأُقَرِّبَ لِأَحَدٍ شَيْئًا دُونَ اللهِ جَلَّ جَلَالُهُ، فَضَرَبُوا عُنُقَه، فَدَخَلَ الجَنَّةَ».
«ሁለት ሰዎች ጣኦት አምላኪያን በሆኑ ህዝቦች በኩል አለፉ፤ ለዚያ ጣኦት አንዳች ነገር ሳያቀርብለት ማንም ሰው አያልፍም ነበር። ለአንደኛቸውም፦ ‹አቅርብ› አሉት። እርሱም፦ ‹የማቀርበው ምንም ነገር የለኝም› አለ። እነርሱም፦ ‹ዝንብ እንኳ ቢሆን አቅርብ› አሉት። ዝንብም አቀረበ። መንገዱንም ለቀቁለት፤ እሳትም ገባ። ሌላኛውንም፦ ‹አቅርብ› አሉት። እርሱም፦ ‹ክብሩ ከፍ ካለው አላህ ውጪ ለማንም አንዳችንም ነገር የማቀርብ አይደለሁም› አለ። አንገቱንም ቀሉት፤ ጀነትም ገባ።»
ወደ ጣኦትና መሰል ነገሮች ዝንብን ወይም መሰል ነገር ቁርባን ያቀረበ ሰው ሙሽሪክ (አጋሪ) ከሆነና የእሳት ቅጣት የሚገባው ከሆነ ጂኖችን፣ መላእክቶችንና ወሊዮችን የሚለምን፣ እነርሱ ከጭንቅ እንዲገላግሉት የሚፈልግ፣ ለእነርሱ ስለት የሚሳል፣ በእርድም ወደነርሱ የሚቃረብ ሰው እንዴት ሊታይ ነው? ይህንንም የገንዘቡን መጥጠበቅ፣ የህመምተኛውን መዳን፣ ወይም የእንሰሳዎቹንና የዘሩን ሰላም በመከጀል፣ አልያም የጂኖችን ክፋት በመፍራትና ይህን በመሰለ ምክንያት የሚፈፅምስ ምን ይሆን ቅጣቱ? ይህንንና መሰል ድርጊቶችን የፈፀመ ሰው፤ ያ ዝንብን ለጣኦት መቃረቢያ አድርጎ ካቀረበው ሰውዬ ይልቅ ሙሽሪክ (አጋሪ) ለመሆንና የእሳት ተገቢ ለመሆን ይበልጥ የተገባ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም።
በዚህ ዙሪያ ከመጡ ማስረጃዎች መካከል የሚከተለው የአላህ ንግግር ይገኝበታል፦
﴿إِنَّآ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ فَٱعۡبُدِ ٱللَّهَ مُخۡلِصٗا لَّهُ ٱلدِّينَ2 أَلَا لِلَّهِ ٱلدِّينُ ٱلۡخَالِصُۚ وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَ مَا نَعۡبُدُهُمۡ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَآ إِلَى ٱللَّهِ زُلۡفَىٰٓ إِنَّ ٱللَّهَ يَحۡكُمُ بَيۡنَهُمۡ فِي مَا هُمۡ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي مَنۡ هُوَ كَٰذِبٞ كَفَّارٞ3﴾
{ እኛ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት የተሞላ ሲሆን አወረድነው:: አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ሆነህ ተገዛው::
ንቁ! ፍጹም ጥሩ የሆነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድረገው የያዙት «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን እንጂ ለሌላ አንገዛቸዉም።» ይላሉ:: አላህ በዚያ እነርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል:: አላህም ውሸታም ከሓዲ የሆነን ሰው አያቀናም::} [አዝ'ዙመር፡ 2-3] የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَيَعْبُدُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنْفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِنْدَ اللَّهِ قُلْ أَتُنَبِّئُونَ اللَّهَ بِمَا لَا يَعْلَمُ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى عَمَّا يُشْرِكُونَ18﴾
{ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውን ይገዛሉ:: «እነዚህ አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው።» ይላሉ። «አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ እናንተ ትነግሩታላችሁን?» በላቸው:: አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም::} [ዩኑስ፡ 18]
ጥራት የተገባው አላህ በእነዚህ ሁለት አንቀጾች አጋርያን ከአላህ ውጪ ከፍጡራን መካከል ወዳጆች መያዛቸውን ገልጿል። እነዚያ ወዳጆች ወደ አላህ እንደሚያቃርቧቸውና ከእርሱ ዘንድ እንደሚያማልዷቸው በመሞገት በፍርሃት፣ በተስፋ፣በእርድ፣ በስለት፣ በዱዓና በመሳሰሉት የአምልኮ መገለጫዎች ከአላህ ጋር በማጋራት ያመልኳቸዋል። ከዚያም ጥራት የተገባው አላህ ውሸታምነታቸውን አጋለጠ፤ የሙግታቸውንም ከንቱነት ግልጽ አደረገ። ውሸታሞች፣ ከሓዲዎችና አጋርያን በማለትም ሰየማቸው። ከሽርካቸውም ራሱን አጠራ። አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿...سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى عَمَّا يُشْرِكُونَ﴾
{…አላህ ከማይገባው ሁሉ ጠራ ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ::} [አን-ነሕል: 1] በዚህም አንድ ሰው አላህ ዘንድ እንዲያማልደው ወይም እንዲያቃርበው በመፈለግ አልያም የታመመ እንዲድንለት፣ ንብረቱ እንዲጠበቅለት፣ በሩቅ ያለ ሰው ሰላም እንዲሆንለት እና ይህን መሰል ነገሮች በመከጀል መልአክን፣ ነቢይን፣ ጋኔንን፣ ዛፍን ወይም ድንጋይን ከአላህ ጋር በማጋራት የሚማፀን ከርሱም እርዳታን የሚጠይቅ፣ በስለትና በእርድም ወደርሱ የሚቃረብ ከሆነ አላህ እንዲህ ሲል የተናገረው በሆነው ከባዱ ሽርክ ውስጥና አደገኛ መከራ ውስጥ ወድቋል፦
﴿إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَنْ يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَلِكَ لِمَنْ يَشَاءُ وَمَنْ يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَى إِثْمًا عَظِيمًا48﴾
{አላህ በእርሱ ማጋራትን ፈጽሞ አይምርም:: ከዚህ ውጪ ያለውንም ኃጢአት ለሚሻው ሰው ይምራል:: በአላህ የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኃጢአት በእርግጥ ቀጠፈ::} [አን-ኒሳእ፡ 48] ጥራት ይገባውና እንዲህም ብሏል፡
﴿...إِنَّهُ مَنْ يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنْصَارٍ﴾
{እነሆ በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ:: መኖሪያዉም እሳት ናት:: ለበዳዩችም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም::} [አልማኢዳህ: 72]
የትንሳኤ ቀን ምልጃ ለተውሒድና ኢኽላስ ባለቤቶች እንጂ ለሽርክ ባለቤቶች አትሆንም። ነቢዩ ﷺ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! በርሶ ምልጃ ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛው ማን ነው?" ተብለው ሲጠየቁ:
«مَنْ قَالَ: لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ خَالِصًا مِنْ قَلْبِهِ».
«ከልቡ ጥርት አድርጎ 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ያለ ሰው ነው» በማለት መልሰዋል። ነቢዩ ﷺ እንዲህም ብለዋል:
«لِكُلِّ نَبِيٍّ دَعْوَةٌ مُسْتَجَابَةٌ، فَتَعَجَّلَ كُلُّ نَبِيٍ دَعْوَتَهُ، وَإِنِّي اخْتَـبَأْتُ دَعْوَتِي شَفَاعَةً لِأُمَّتِي يَومَ القِيَامَةِ، فَهِيَ نَائِلَةٌ إِنْ شَاءَ اللهِ مَن مَاتَ مِنْ أُمَّتِي لَا يُشْرِكُ بِاللهِ شَيْئًا».
"እያንዳንዱ ነቢይ ተቀባይነት ያለው አንዲት ልመና አለችው። እያንዳንዱ ነቢይም በልመናው ተቻኩሏል። እኔ ግን ልመናዬን ለህዝቦቼ የትንሳኤ ቀን ምልጃ ትሆን ዘንድ ሸሽጌዋለሁ። እርሷም አላህ ከፈቀደ ከህዝቦቼ መካከል በአላህ ላይ ምንም ነገር ሳያጋራ ለሞተ ሰው ትደርሰዋለች።"
የቀድሞዎቹ ሙሽሪኮች አላህ ጌታቸው፣ ፈጣሪያቸውና ሲሳያቸውን የሚሰጣቸው መሆኑን ያምኑ ነበር። ይልቁንም በነቢያት፣ በወሊዮች፣ በመላእክት፣ በዛፎች፣ በድንጋዮችና በመሰል ነገሮች ላይ ተጣብቀው የቀሩት አላህ ዘንድ የነርሱን ምልጃና ወደርሱ ያቃርቡናል ብለው ይከጅሉ ስለነበር ነው፤ ይህም ከዚህ ቀደም ብሎ በአንቀጾቹ ላይ ተገልጿል። አላህ በዚህ ሰበብ ምህረት አላደረገላቸውም። ይልቁንም አላህ በታላቅ ምጽሐፉ አውግዟቸዋል፤ ካፊሮችና ሙሽሪኮችም ሲል ሰይሟቸዋል። እነዚህ አማልክት ያማልዱናል፤ ወደ አላህም ያቃርቡናል የሚለውን ሙግታቸውንም ውሸትነቱን አጋልጦባቸዋል። የአላህ መልዕክተኛም ﷺ ይህን ሰበባቸውን አልተቀበላቸውም። ይልቁንም ረሱል ﷺ በዚህ ሽርክ ምክንያት አምልኳቸውን ለአላህ ብቻ ጥርት እስኪያደርጉ ድረስ ተፋልመዋቸዋል። ይህም የጥራት ባለቤት የሆነውን ጌታ ቃል ለመተግበር ነው፦
﴿وَقَاتِلُوهُمْ حَتَّى لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ الدِّينُ لِلَّهِ...﴾
{ፈተና (ሁከት) እስከማይኖርና ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስከሚሆን ድረስ ተጋደሏቸው...} [አል-በቀራህ: 193] የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«أُمِرْتُ أَنْ أُقَاتِلَ النَّاسَ حَتَّى يَشْهَدُوا أَنْ لَا إِلهَ إِلَّا اللهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ، وَيُقِيمُوا الصَّلَاةَ، وَيُؤتُوا الزَّكَاةَ، فَإِذَا فَعَلُوا ذَلِكَ عَصَمُوا مِنِّي دِمَاءَهُم وَأَمْوَالَهُمْ إِلَّا بِحَقِّ الإِسْلَامِ، وَحِسَابُهُم عَلَى اللهِ».
"ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ናቸው ብለው እስኪመሰክሩ፣ ሶላትን ቀጥ አድርገው እስኪሰግዱና ዘካን እስኪሰጡ ድረስ ሰዎችን እንድጋደል ታዝዣለሁ። ይህንን ከፈፀሙ በኢስላም ሐቅ ካልሆነ በቀር ደማቸውና ገንዘባቸውን ከኔ ጠብቀዋል። ሒሳባቸውም አላህ ዘንድ ነው።" የሐዲሡ ፍሬ ሃሳብም፦
«حَتَّى يَشْهَدُوا أَن لَا إِلهَ إِلَّا اللهُ».
«ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እስከሚመሰክሩ ድረስ» ማለትም: ከአላህ ውጪ ያሉትን በሙሉ ትተው አላህን በአምልኮ እስኪነጥሉት ድረስ ማለት ነው።
ሙሽሪኮችም ጂንን ይፈሩና በነሱም ይጠበቁ ነበር፤ ይህንንም በተመለከተ የላቀው አሏህ እንዲህ የሚለው ቃሉን አወረደ፡
﴿وَأَنَّهُ كَانَ رِجَالٌ مِنَ الْإِنْسِ يَعُوذُونَ بِرِجَالٍ مِنَ الْجِنِّ فَزَادُوهُمْ رَهَقًا6﴾
{እነሆም ከሰዎች የሆኑ ወንዶች በጋኔን ወንዶች ይጠበቁ ነበር። ኩራትንም (ጥመትን) ጨመሯቸው።} [አል-ጂን: 6] የተፍሲር ሊቃውንቶች ስለዚህች የተከበረች አንቀጽ እንዲህ ብለዋል፦
﴿...فَزَادُوهُمْ رَهَقًا﴾
{…ኩራትንም (ጥመትን) ጨመሯቸው።} ማለትም፡ ፍራቻንና ድንጋጤን፤ ምክንያቱም ጂኖች ሰዎች በነርሱ ሲጠበቁ ባዩ ጊዜ በራሳቸው ስለሚፎክሩና ስለሚኮሩ እነርሱን ማምለክንና ወደነርሱ መጠጋትን እንዲያበዙ ማስፈራራትንና ማስደንገጥን ይጨምሩባቸዋል።
አላህም ሙስሊሞችን ከዚህ ሺርክ ፋንታ ጥራት በተገባው አላህና ፍፁም በሆኑ ቃላቶቹ እንዲጠበቁ አድርጓል፤ በዚህም ላይ እንዲህ ሲል ቃሉን አወረደ፦
﴿وَإِمَّا يَنْزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ200﴾
{የሰይጣን ጉትጎታ ቢያጋጥምህ በአላህ ብቻ ተጠበቅ:: አላህ ሁሉን ሰሚና ሁሉንም አዋቂ ነው::} [አል-አዕራፍ፡ 200] ልቅናው ከፍ ያለው አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ1﴾
{በል፡ -በተፈልቃቂው ጎህ (በአል-ፈለቅ) ጌታ እጠበቃለሁ፤} ነቢዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸውም በሶሒሕ ሐዲሥ ተዘግቧል፦
«مَنْ نَزَلَ مَنْزِلًا فَقَالَ: (أَعُوذُ بِكَلِمَاتِ اللهِ التَّامَّاتِ مِنْ شَرِّ مَا خَلَقَ)؛ لَم يَضُرَّهُ شَيءٌ حَتَّى يَرْتَحِلَ مِنْ مَنْزِلِهِ ذَلِكَ».
"በአንድ ስፍራ ላይ አርፎ ከዚያም ‹አዑዙ ቢከሊማቲላሂ አትታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቀ (ምሉዕ በሆኑ የአላህ ቃላት ከፈጠራቸው ጎጂ ነገሮች እጠበቃለሁ)› ያለ ሰው ከዛ ስፍራ እስኪንቀሳቀስ ድረስ አንዳችም አይጎዳውም።"
ከዚህ ቀደም ከተጠቀሱት የቁርኣን አንቀፆችና ሐዲሦች መዳንን የሚፈልግ፣ ሃይማኖቱን ለመጠበቅ የሚጓጓና ከትንሹም ይሁን ከትልቁ ሺርክ በሰላም መውጣትን የሚሻ ሰው በሙታን፣ በመላእክቶች፣ በጂኖችና በሌሎችም ፍጡራን ላይ ልብን ማንጠልጠል፣ እነርሱንም መማፀን፣ በእነርሱም መጠበቅ እና የመሳሰሉት ነገሮች ሁሉ የጃሂሊያ ዘመን የሆኑ ሙሽሪኮች ስራና እንዲሁም በአላህ ላይ ከሚፈፀም የሽርክ አይነት ሁሉ እጅግ አስቀያሚው መሆኑን ይገነዘባል። በመሆኑም ይህን ድርጊት መተው፣ ከእርሱም መጠንቀቅ፣ ሌሎችም እንዲተዉት መመካከርና በፈፃሚዎቹም ላይ ማውገዝ ግዴታ ነው።
በነዚህ የሽርክ ስራዎች የሚታወቅ ሰው ከዚያ ስራው ወደ አላህ በግልፅ ተውበት አድርጎ ዱዓውንና አምልኮውን ለአላህ ብቻ እስካላደረገ ድረስ ከእርሱ ጋር ጋብቻ መፈፀም፣ ያረደውን መብላት፣ በጀናዛው ላይ ሶላት መስገድም ሆነ ከኋላው ሆኖ መስገድ አይፈቀድም። ዱዓ ራሱ አምልኮ ነው፤ እንደውም የአምልኮ አስኳል (አንኳር) ነው። ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:
«الدُّعَاءُ هُوَ العِبَادَةُ».
"ዱዓእ እርሱ አምልኮ ነው።" በሌላ ዘገባ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፡
«الدُّعَاءُ مُخُّ العِبَادَةِ».
"ዱዓእ የአምልኮ አስኳል (ቁንጮው) ነው።" ሙሽሪኮችን ማግባትን በተመለከተም የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿وَلَا تَنْكِحُوا الْمُشْرِكَاتِ حَتَّى يُؤْمِنَّ وَلَأَمَةٌ مُؤْمِنَةٌ خَيْرٌ مِنْ مُشْرِكَةٍ وَلَوْ أَعْجَبَتْكُمْ وَلَا تُنْكِحُوا الْمُشْرِكِينَ حَتَّى يُؤْمِنُوا وَلَعَبْدٌ مُؤْمِنٌ خَيْرٌ مِنْ مُشْرِكٍ وَلَوْ أَعْجَبَكُمْ أُولَئِكَ يَدْعُونَ إِلَى النَّارِ وَاللَّهُ يَدْعُو إِلَى الْجَنَّةِ وَالْمَغْفِرَةِ بِإِذْنِهِ وَيُبَيِّنُ آيَاتِهِ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ221﴾
{በአላህ አጋሪ የሆኑ ሴቶችን እስከሚያምኑ ድረስ አታግቧቸው:: አጋሪይቱ ነፃ ሴት ምንም ብትስባችሁ እንኳ ያመነችው ባሪያ ሴት በእርግጥ ለእናንተ በላጭ ናት:: ለአጋሪዎቹ እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው:: አጋሪ ወንድ ምንም ቢስባችሁ አማኝ ባሪያዎች ለእናንተ በላጭ ናቸው:: እነዚያ አጋሪዎች ወደ እሳት ይጣራሉ:: አላህም በፈቃዱ ወደ ገነትና ወደ ምህረት ይጠራል:: ህግጋቱንም ለሰዎች ሊገሰጹ ይከጀላልና ይገልጻል፡፡} [አልበቀራህ: 221] እናም ጥራት የተገባው አላህ ሙስሊሞች ጣዖታትን፣ ጂንኖችን፣ መላእክትንና ሌሎችንም ከሚገዙ አጋሪ ሴቶች ጋር አምልኮን ለአላህ ብቻ በማጥራት፣ መልእክተኛውንም ﷺ ባመጡት ነገር በማመንና መንገዳቸውንም በመከተል እስከሚያምኑ ድረስ እንዳይጋቡ ከልክሏል፡፡ ሙስሊም ሴቶችንም ለአጋሪዎች አምልኮን ለአላህ ብቻ በማጥራት፣ መልእክተኛውንም ﷺ በማመንና እርሳቸውንም በመከተል እስከሚያምኑ ድረስ ከመዳር ከልክሏል፡፡
ነፃዋ አጋሪ ሴት ለተመለከታት የምትማርክና ስትናገር የሰማትን የምታስደንቅ ብትሆን እንኳ አማኝ የሆነችው ባሪያ የተሻለች መሆኗን፤ እንዲሁም ነፃው አጋሪ ወንድ ሰሚውንና ተመልካቹን በውበቱ፣ በንግግር ጥበቡ፣ በጀግንነቱና በመሳሰሉት ቢማርክም እንኳን አማኝ የሆነው ባሪያ የተሻለ መሆኑን አሳወቀ። ከዚያም የዚህን ብልጫ ምክንያት እንዲህ በማለት አብራርቷል፦
﴿...أُولَئِكَ يَدْعُونَ إِلَى النَّارِ...﴾
{…እነዚያ አጋሪዎች ወደ እሳት ይጠራሉ…} [አል-በቀራህ፡ 221] አላህ በዚህ አንቀፅ ወደ እሳት ይጠራሉ ማለት የፈለገው አጋሪ ወንዶችንና አጋሪ ሴቶችን ነው፤ እነርሱ በንግግራቸው፣ በሥራቸው፣ በአኗኗራቸውና በባህሪያቸው ወደ እሳት ከሚጠሩት ናቸው። አማኝ ወንዶችና አማኝ ሴቶች ግን በባህሪያቸው፣ በሥራቸውና በአኗኗራቸው ወደ ጀነት ከሚጠሩት ናቸው። ታዲያ እነዚህና እነዚያ እንዴት ይስተካከላሉ?
በአጋሪዎች ጀናዛ ላይ ሶላት መስገድን በተመለከተ: የላቀው አላህ ስለ መናፍቃን እንዲህ ብሏል፦
﴿وَلَا تُصَلِّ عَلَى أَحَدٍ مِنْهُمْ مَاتَ أَبَدًا وَلَا تَقُمْ عَلَى قَبْرِهِ إِنَّهُمْ كَفَرُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَمَاتُوا وَهُمْ فَاسِقُونَ84﴾
{ከእነርሱ መካከል በሞተ በአንዱም ሰው ላይ ቢሆን ፈጽሞ አትስገድ:: በመቃብሩም ላይ አትቁም:: እነርሱ በአላህና በመልዕክተኛው ክደዋልና:: እነርሱም አመጸኞች ሆነው ሞተዋልና::} [አት-ተውባህ፡ 84] ከፍ ያለውና የላቀው አላህ በዚህች በተከበረች አንቀፅ መናፍቅና ከሃዲ በአላህና በመልዕክተኛው በመካዳቸው ምክንያት እንደማይሰገድባቸው ግልፅ አድርጓል። እንደዚሁም ከኋላቸው አይሰገድም፤ ለሙስሊሞችም ኢማሞች አይደረጉም። ይህም በመካዳቸው፣ ታማኝ ባለመሆናቸው፣ በእነርሱና በሙስሊሞች መካከል ባለው ታላቅ ጠላትነት፣ እንዲሁም የሰላትና የአምልኮ ሰዎች ባለመሆናቸው ነው። ምክንያቱም ክህደትና ከሽርክ ጋር ምንም ስራ አይቀርም። አላህን ከዚህ ነገር ደህንነትን እንዲለግሰን እንለምነዋለን። የአጋሪዎችን እርድ መብላትን በተመለከተም ክብሩ የላቀው አላህ የበክትና የአጋሪዎች እርድ ሐራም መሆኑን ሲያብራራ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَلَا تَأْكُلُوا مِمَّا لَمْ يُذْكَرِ اسْمُ اللَّهِ عَلَيْهِ وَإِنَّهُ لَفِسْقٌ وَإِنَّ الشَّيَاطِينَ لَيُوحُونَ إِلَى أَوْلِيَائِهِمْ لِيُجَادِلُوكُمْ وَإِنْ أَطَعْتُمُوهُمْ إِنَّكُمْ لَمُشْرِكُونَ121﴾
{በእርሱ ላይ የአላህ ስም ያልተጠራበትን ነገር አትብሉ:: እርሱም በእርግጥ አመጽ ነው:: ሰይጣናትም ወደ ወዳጆቻቸው በክትን በመብላት ይከራከሯችሁ ዘንድ ያሾከሹካሉ:: ብትታዘዟቸው በእርግጥ አጋሪዎች ናችሁ::} [አል‐አንዓም: 121] ልቅናው የላቀው አላህ ሙስሊሞችን የበከተ ስጋ እና የአጋሪን እርድ ከመብላት ከልክሏል፤ የዚህም ምክንያት አጋሪው የረከሰ ስለሆነ ነው። እርዱም የአላህን ስም ቢያወሳበት እንኳ እንደ በክት ይቆጠራል። ከርሱ የሚወጣው (ቢስሚላህ) ምንም ተጽእኖ የሌለው ከንቱ ነው፤ ምክንያቱም ሲያርዱ ቢስሚላህ ማለት አምልኮ ነው፤ አጋሪው ወደ አላህ ተውበት እስካላደረገ ድረስ አምልኮን ያበላሻል ውድቅም ያደርገዋል። አላህ የመጽሐፍ ሰዎችን ምግብ (ያረዱትን) እንዲህ በሚለው ቃሉ የፈቀደው:
﴿...وَطَعَامُ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ حِلٌّ لَكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّ لَهُمْ...﴾
{...የእነዚያ መጽሐፍን የተሰጡ ሰዎች ምግብም (እርድ) ለእናንተ የተፈቀደ ነው:: ምግባችሁም ለእነርሱ የተፈቀደ ነው...} [አል‐ማኢዳህ: 5] ምክንያቱም ራሳቸውን ወደ መለኮታዊ ኃይማኖት ስለሚያስጠጉ እና በዚህ ጉዳይ ላይ ውሸታሞች ቢሆኑ እንኳ የሙሳና የዒሳ ተከታዮች ነን ብለው ስለሚሞግቱ ነው። አላህ ሙሐመድን ﷺ ለሰው ልጆች ሁሉ በመላክ ኃይማኖታቸውን ሽሮታል፤ ውድቅም አድርጎታል። ነገር ግን አላህ የመጽሐፉን ሰዎች ምግብና ሴቶቻቸውን ለእኛ ፍቁድ አድርጓል፤ ይህም የመፈቀዱ ምክንያት ታላቅ ጥበብና የተጠበቁ ምስጢሮች አሉት። በርግጥም የዕውቀት ባለቤቶች ጥበቡን አብራርተውታል። ይህ ግን ነብያትን፣ ወሊዮችንና የመሳሰሉትን ሙታንንና ጣዖታትን የሚያመልኩ አጋሪዎችን አይመለከትም። ምክንያቱም ኃይማኖታቸው መሰረትም ሆነ ምንም ዓይነት ማምታቻ የሌለው ነው፤ ይልቁንም ከመሰረቱ ውድቅ ነው። ስለሆነም የእነሱ እርድ በክት ነው፤ መብላቱም አይፈቀድም።
አንድ ሰው ለሚያናግረው ሰው፡- ‹ጂኒ አግኝቶሃል›፣ ‹ጂኒ ይዞሃል›፣ ‹ሸይጧን ዞሮብሃል› እና የመሳሰሉትን መናገር በተመለከተ ይህ ከስድብና ዘለፋ የሚመደብ ነው። ይህም ልክ እንደሌሎች የስድብና የዘለፋ አይነቶች ሁሉ በሙስሊሞች መካከል አይፈቀድም። ይህ ግን ከሽርክ የሚመደብ አይደለም፤ ተናጋሪው ጂኖች ያለ አላህ ፈቃድና ውሳኔ በሰዎች ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድሩ እምነት ካለው ግን ሺርክ ይሆናል። ጅኖችም ሆኑ ሌሎች ፍጡራን ያለ አላህ ፈቃድ ተፅእኖ ያሳድራሉ የሚል እምነት የያዘ ሰው በዚህ እምነቱ ከሀዲ ነው፤ ምክንያቱም ጥራት የተገባው አላህ የሁሉም ነገር ገዥ፣ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ፣ የሚጠቅመውም የሚጎዳውም እርሱ ብቻ ነውና። ያለ አላህ ፈቃድ፣ መሻትና ውሳኔ የሚሆን አንዳችም ነገር የለም። ግርማው ከፍ ያለው አላህ ነቢዩን ﷺ ይህን ታላቅ መሠረት ለሰዎች እንዲነግሩ ሲያዝ እንዲህ ብሏል፦
﴿قُلْ لَا أَمْلِكُ لِنَفْسِي نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ وَلَوْ كُنْتُ أَعْلَمُ الْغَيْبَ لَاسْتَكْثَرْتُ مِنَ الْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِيَ السُّوءُ إِنْ أَنَا إِلَّا نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ لِقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ188﴾
{«አላህ የሻዉን በስተቀር ለራሴ ጥቅምንም ሆነ ጉዳት ማምጣት አልችልም:: የሩቅን ሚስጥር የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ሁሉ ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር:: እኔም ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም።» በላቸው::} [አል-አዕራፍ፡ 188] የፍጡራን አይነታና ከሁሉም በላጭ የሆኑት ነቢይ ﷺ አላህ ከሻላቸው በቀር ለራሳቸው ጥቅም ማምጣትም ሆነ ጉዳት መከላከል የማይችሉ ከሆኑ ታዲያ ከእርሳቸው ውጭ ያሉ ሌሎች ፍጡራንስ እንዴት ሊሆኑ ይችላሉ?! በዚህ ዙሪያ የተወሱ የቁርኣን አንቀጾች እጅግ በርካታ ናቸው።
የሩቅ ምስጢራትን እናውቃለን ብለው የሚሞግቱ ሟርተኞችን፣ አጭበርባሪዎችን፣ ኮከብ ቆጣሪዎችንና መሰሎቻቸውን መጠየቅ የማይፈቀድ የተወገዘ ድርጊት ነው። የሚሉትን አምኖ መቀበል ደግሞ ይበልጥ የከፋና የተወገዘ ነው። ይልቁንም ከክህደት ዘርፎች መካከል አንዱ ነው፤ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«مَنْ أَتَى عَرَّافًا فَسَأَلَهُ عَنْ شَيءٍ؛ لَمْ تُقْبَلْ لَهُ صَلَاةٌ أَرْبَعِينَ يَومًا».
"ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለ አንዳች ነገር የጠየቀ የአርባ ቀናት ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።" ሙስሊም በሶሒሓቸው ዘግበውታል። ሙስሊም በሶሒሕ መጽሐፋቸው ላይ ከሙዓዊያህ ቢን አል'ሐከም አስ'ሱለሚይ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንዳስተላለፉት፦
«أَنَّ النَّبيَّ ﷺ نَهَى عَنْ إِتْيَانِ الكُهَّانِ وَسُؤَالِهِم».
"ነቢዩ ﷺ ወደ ጠንቋዮች ከመሄድና እነርሱንም ከመጠየቅ ከልክለዋል።"
በሱነኖች ውስጥ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፦
«مَنْ أَتَى كَاهِنًا، فَصَدَّقَهُ بِمَا يَقُولُ؛ فَقَدْ كَفَرَ بِمَا أُنْزِلَ عَلَى مُحَمَّدٍ ﷺ».
"ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ጠንቋዩ የተናገረውን ያመነ ሰው ሙሐመድ ﷺ ላይ በወረደው ክዷል።" ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው ሐዲሦች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። በመሆኑም የሙስሊሞች ግዴታ በህክምናም ይሁን በሌላ ስም ስለ ሩቅ ምስጢራት በማውራትና ሙስሊሞችን በማወዛገብ ላይ የተሰማሩ ጠንቋዮችን፣ ሟርተኞችንና ሌሎች አጭበርባሪዎችን ከመጠየቅ መጠንቀቅ ነው። ይህም ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰው ነቢዩ ﷺ ከዚህ ነገር በመከልከላቸውና በማስጠንቀቃቸው ነው። እዚህ ውስጥ ከሚካተቱ ነገሮች መካከል: አንዳንድ ሰዎች በሕክምና ስም የሩቅ ምስጢራዊ ጉዳዮችን እንደሚያውቁ መሞገታቸው ነው፤ የታመመውን ሰው ጥምጣም ወይም የታመመችዋን ሴት ሻሽ እና መሰል ነገሮችን በማሽተት “ይህ ህመምተኛ ወይም ይህች ህመምተኛ እንዲህ እንዲህ አድርጓል፤ እንዲህ እንዲህ ሰርቷል” በማለት በህመምተኛው ጥምጣም እና በመሰል ነገሮች ውስጥ ምንም አይነት ማመላከቻ የሌለውን የሩቅ ምስጢራዊ ጉዳዮችን ይናገራሉ። የዚህም አላማ ተራውን ህዝብ ማወናበድ ብቻ ነው፤ ይህም ሰዎች፡- “እርሱ ህክምናን፣ የህመም አይነቶችንና ምክንያቶቻቸውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ነው” እንዲሉ ነው። ምናልባትም አንዳንድ መድኃኒቶችን ይሰጣቸውና በአላህ ፈቃድ ከፈውሱ ጋር ሊገጣጠም ይችላል፤ በመሆኑም ሰዎች ፈውሱ የተገኘው በእርሱ መድኃኒት ሰበብ እንደሆነ ያስባሉ። አንዳንዴም ህመሙ ሀኪም ነኝ ባዩን በሚያገለግሉ አንዳንድ ጂኒዎችና ሰይጣናት ሰበብ ሊከሰት ይችላል። እነርሱም ስለሚያውቋቸው አንዳንድ የሩቅ ሚስጥራት ይነግሩትና በዚህ ላይ ይተማመናል። ጂኒዎችንና ሰይጣናትንም ለእነርሱ በሚስማማቸው የአምልኮ አይነት ያስደስታቸዋል። በዚህም ምክንያት ከህመምተኛው ላይ ይነሳሉ፤ ተጣብቀውበት የነበረውንም ጥቃት ይተዉለታል። ይህም ስለ ጂኒዎችና ሰይጣናት እንዲሁም ይህን ስልት ስለሚጠቀሙ ሰዎች ያጤነ ሰው የሚያውቀው ነገር ነው።
በሙስሊሞችም ላይ ያለባቸው ግዴታ ከዚህ ነገር መጠንቀቅ፣ ሙስሊሞች እንዲተዉት መተዋወስ፣ በሁሉም ጉዳዮች ላይ ጥራት በተገባው አላህ ላይ መደገፍና በእርሱ ላይ መመካት ነው። ሸሪዓዊ በሆኑ ሩቃዎችና በተፈቀዱ መድኃኒቶች መጠቀም እንዲሁም በሽተኛውን በቤተ-ሙከራ በመመርመር በሽታውን በማረጋገጥ በሚያክሙ ሐኪሞች ዘንድ መታከም ችግር የለውም። ከነቢዩም ﷺ በትክክል እንደተዘገበው እንዲህ ብለዋል፦
«مَا أَنْزَلَ اللهُ دَاءً إِلَّا أَنْزَلَ لَهُ شِفَاءً، عَلِمَهُ مَنْ علِمه، وَجَهِلَهُ مَنْ جَهِلَهُ».
"አላህ ምንም አይነት በሽታን አላወረደም ለርሱ ፈውሱንም ያወረደ ቢሆን እንጂ፤ የሚያውቅ ያውቀዋል ያላወቀ አያውቀውም።" ነቢዩ ﷺ እንዲህም ብለዋል፡
«لِكُلِّ دَاءٍ دَوَاءٌ، فإِذَا أُصِيبَ دَوَاءٌ الدَّاءَ بََرَأَ بِإِذْنِ اللهِ».
«ለእያንዳንዱ በሽታ መድኃኒት አለው፤ መድኃኒቱ በሽታውን ካገኘው በአላህ ፈቃድ ይድናል።» ነቢዩ ﷺ እንዲህም ብለዋል፡
«عِبَادَ اللهِ، تَدَاوَوا وَلَا تَدَاوَوا بِحَرَامٍ».
"የአላህ ባሪያዎች ሆይ፤ ተካከሙ በሓራም ነገር ግን አትተካከሙ።" ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው ሐዲሦች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው።
ልቅናው የላቀ የሆነው አላህ የሙስሊሞችን ሁሉ ሁኔታ እንዲያስተካክልልን፣ ልባቸውንም ሆነ አካላቸውን ከክፉ ነገር ሁሉ እንዲፈውስ፣ በቅን መንገድ ላይ እንዲሰበስባቸው፣ እኛንም ሆነ እነርሱንም ከአጥማሚ ፈተናዎችና ለሰይጣንና ለወዳጆቹ ከመታዘዝ እንዲጠብቀን እንለምነዋለን። እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና። ብልሃትም ሆነ ኃይል በታላቁና ልቅናው ከፍ ባለዉ በአላህ ቢሆን እንጂ የለም።
የአላህ ሰላት፣ ሰላምና በረከት በባሪያውና በመልዕክተኛው በነቢያችን ሙሐመድ እንዲሁም በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ይስፈን።
***
بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ
አራተኛው መልዕክት፡
በቢድዓዊና ሽርካዊ አውራዶች አላህን መገዛት ያለው ብይን:
ከዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ ለተከበረው ወንድም (.........) አላህ ለመልካም ነገር ሁሉ ይግጠመው፤ አሚን።
የአላህ ሰላም፣ እዝነትና በረከት በናንተ ላይ ይሁን።
ከዚህ በመቀጠል፦ አላህ በቀናው ጎዳና ይምራዎትና በሀገራችሁ ላይ አላህ ምንም ማስረጃ ያላወረደባቸውን አውራዶች አጥብቀው የያዙ ሰዎች መኖራቸውን፣ ከእነዚህም ውስጥ የቢድዓም የሽርክም ስራዎች እንደሚገኙበት፣ እንዲሁም ይህንን ተግባር የምእመናን መሪ ወደ ሆኑት ዐሊይ ኢብን አቢ ጧሊብ (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እና ወደ ሌሎችም እንደሚያስጠጉ የሚገልጸው ክቡር ደብዳቤዎ ደርሶኛል። እነዚህንም አውራዶች በዚክር መድረኮች ወይም ከመግሪብ ሶላት በኋላ በመስጂዶች ውስጥ ወደ አላህ የሚያቃርብ ነው ብለው እየሞገቱ ይላሉ፤ ለምሳሌም እንደ «ቢሐቂላህ፣ ሪጃለላህ፣ አዒኑና ቢዐውኒላህ፣ ወኩኑ ዐውነና ቢላህ» ማለታቸው። እንዲህም ይላሉ፡ «እናንተ አቅጧቦችም፣ ጌቶችም፣ በኛም ውስጥ ያላችሁ የእርዳታ ባለቤቶችም ሆይ! (ጥሪያችንን) ተቀበሉን፤ አላህ ዘንድም አማልዱን፡፡ ይህ ባሪያችሁ በደጃፋችሁ ቆሟል፤ በበራችሁም ላይ ተወስኗል፡፡ ከጉድለቱም የተነሳ ፈሪ ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ ሆይ! ድረስልን፡፡ ከእናንተ ሌላ የምሄድበት የለኝም፡፡ ፍላጎትም የሚገኘው ከእናንተ ዘንድ ነው፡፡ እናንተም የአላህ ቅርብ ሰዎች ናችሁ፡፡ የሰማዕታት አለቃ በኾነው በሐምዛ እንዲሁም ከእናንተ ውስጥ ለኛ ረዳት በኾኑት እንማጸናችኋለን፡፡ የአላህ መልክተኛ ሆይ! ድረስልን፡፡» እንዲህም ይላሉ: «አላህ ሆይ! የሃይልህ ምስጢሮች መገለጥና ለእዝነታዊ ብርሃኖችህ መፍለቅ ሰበብ ላደረከው፤ ለአምላካዊ ስፍራህ ምትክና ለዛታዊ ምስጢሮችህ ምትክ በሆነውም ላይ ሶላትህን አውርድ።»
ቢድዓና ሽርክ ምን እንደሆኑ እንዲሁም ይህን ዱዓ በሚያደርግ ኢማም ኋላ የሚሰገድ ሶላት ይፈቀድ እንደሆነ እንዲብራራላችሁ የነበራችሁ ፍላጎት ከጥያቄያችሁ አውድ ይታወቅ ነበር?
መልሱም፦ ምስጋና ሁሉ ለብቸኛው አላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላትና ሰላም ከእሳቸው በኋላ ነብይ የሌለ በሆኑት ነብይ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸውም እንዲሁም እስከ ዕለተ ፍርድ ድረስ በእርሳቸው መመሪያ በተመሩትም ላይ ሁሉ ይስፈን።
በመቀጠል:- አላህ መልካሙን ይግጠምህና - አላህ ፍጡራንን የፈጠረውና መልክተኞችንም (ዐለይሂሙ ሰላቱ ወሰላም) የላከው ምንም ተጋሪ ሳይኖረው እርሱ በብቸኝነት እንዲመለክ እንደሆነ እወቅ! ከፍ ያለው አላህም እንዲህ ብሏል፦
﴿وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنْسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ56﴾
{ጂኒንን እና ሰዉን ሊገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸዉም::} [አዝ-ዛሪያት፡ 56]
አምልኮ ማለት -ከዚህ በፊት እንደተብራራው- አላህና መልክተኛው ያዘዙትን በመፈጸምና የከለከሉትን በመተው፣ በአላህና በመልክተኛው በማመን፣ ሥራን ለአላህ ብቻ ጥርት በማድረግ፣ ለአላህም ከፍ ያለ ውዴታን እንዲሁም ከርሱ ውጭ ለማንም ሳይሆን ለእርሱ ብቻ ሙሉ መተናነስን በመላበስ ጥራት የተገባውን አላህንና መልክተኛውን ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መታዘዝ ነው፤ የበላይ የሆነው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
﴿وَقَضَى رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ...﴾
{ጌታህም እንዲህ ሲል አዘዘ:: እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤} [አል-ኢስራእ፡ 23] ማለትም፦ እርሱ በብቸኝነት እንዲመለክ አዘዘ፤ አደራም አለ ማለት ነው። ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ2 الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ3 مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ4 إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ5﴾
{{ምስጋና ሁሉ የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአሏህ የተገባ ነው።
እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ ለሆነው፤
የፍርዱ ቀን ባለቤት ለሆነው (ለአላህ ብቻ የተገባ ነው)::
አንተን ብቻ እንግገዛለን:: አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን (በሉ)።} [አል-ፋቲሓ፡ 2-5] በመሆኑም ከፍ ያለው አላህ በነዚህ አንቀፆች በብቸኝነት ሊመለክና እርዳታ ሊጠየቅበት የሚገባው እርሱ ብቻ መሆኑን ግልፅ አድርጓል። ልቅናው ከፍ ያለው አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿إِنَّآ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ فَٱعۡبُدِ ٱللَّهَ مُخۡلِصٗا لَّهُ ٱلدِّينَ2 أَلَا لِلَّهِ ٱلدِّينُ ٱلۡخَالِصُۚ...﴾
{ እኛ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት የተሞላ ሲሆን አወረድነው:: አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ሆነህ ተገዛው::
አስተውሉ ፍጹም ጥሩ የሆነው ሃይማኖት ለአላህ ብቻ ነው::…} [አዝ-ዙመር፡ 2-3] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿فَادْعُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ14﴾
{አላህንም ከሓዲያን ቢጠሉም እንኳ ሃይማኖትን ለእርሱ አጥሪዎች ሆናችሁ ተገዙት}:: [ጋፊር፡ 14] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا18﴾
{እነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው:: እናም በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ ማለትም ተወረደልኝ::} [አል_ጂን፡ 18] በዚህ መልኩ የመጡ ቁርአናዊ ማስረጃዎች በርካታ ሲሆኑ ሁሉም የሚያመለክቱት አላህን በአምልኮ መነጠል ግዴታ መሆኑን ነው።
የዱዓእ አይነቶች ባጠቃላይ አምልኮ እንደሆኑ የታወቀ ነው። በመሆኑም በእነዚህ የተከበሩ አንቀፆችና ተመሳሳይ ሃሳብ ይዘው የመጡትን ማስረጃዎች መሰረት በማድረግ ዱዓእ ማድረግ፣ እገዛን መሻትና የድረሱልኝ ጥሪ ማቅረብ ከአላህ በቀር ከማንም መጠየቅ አይፈቀድም። ይህ ግን ህያውና በቅርብ የሚገኝ ፍጡር ሊፈፅማቸው የሚችላቸው የተለመዱና ተጨባጭ የሆኑ ጉዳዮችን አያካትትም፤ ምክንያቱም እነኚህ ከአምልኮ አይመደቡምና። ይልቁንም አንድ ሰው አቅሙ በሚፈቅድላቸው የተለመዱ ጉዳዮች ላይ ህያው ከሆነና ማድረግ ከሚችል ሌላ ሰው እርዳታን መከጀሉ በግልፅ መረጃና በዑለማዎች ስምምነት የተፈቀደ ነው። ለምሳሌ ልጁ፣ አገልጋዩ ወይም ውሻው እና የመሳሰሉት የሚያደርሱበትን ጉዳት ለመከላከል ባለቤቱን እርዳታ ቢጠይቅ ወይም የድረስልኝ ጥሪ ቢጣራ ችግር የለውም። ለምሳሌ አንድ ሰው ህያው በሆነ በአካል ቀርቦ በሚገኝና አቅም ባለው ወይም ደግሞ ሩቅ በሆነ ሰው እንደ መጻጻፍና በመሳሰሉት ተጨባጭ መንገዶች አማካኝነት ቤቱን በመገንባት፣ መኪናውን በማሰራት ወይም ይህን በመሰሉ ጉዳዮች ላይ መታገዙ ይፈቀዳል። ከዚህም ውስጥ አንድ ሰው በጂሀድና በጦርነት እንዲሁም በመሳሰሉት አጋጣሚዎች ከባልደረቦቹ እገዛን መሻቱ ይገኝበታል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከፍ ያለው አላህ በነብዩሏህ ሙሳ ዓለይሂ ሰላም ታሪክ ላይ እንዲህ ብሏል፦
﴿...فَاسْتَغَاثَهُ الَّذِي مِنْ شِيعَتِهِ عَلَى الَّذِي مِنْ عَدُوِّهِ...﴾
{ያም ከወገኑ የሆነው ሰው በዚያ ከጠላት በሆነው ሰው ላይ እርዳታን ጠየቀው።} [አልቀሶስ፡ 15]
በሙታን፣ በጂኖች፣ በመልአኮች፣ በዛፎችና በድንጋዮች እርዳታን መፈለግ ከትልቁ ሽርክ ነው። ይህም የቀድሞዎቹ ሙሽሪኮች እንደ አል-ዑዛና አል-ላት ከመሳሰሉ አማልክቶቻቸው ጋር ይፈፅሙት ከነበረው ተግባር ጋር ተመሳሳይ ነው። በተመሳሳይ መልኩ ወሊይነት አላቸው ተብለው ከሚታመኑ ህያዋን ህሙማንን መፈወስ፣ ልቦችን መምራት፣ ጀነት ማስገባት፣ ከእሳት ማዳን እና በመሳሰሉት አላህ እንጂ ሌላ አካል ሊፈፅመው በማይችለው ጉዳይ ላይ እርዳታን መፈለግና መከጀልም ከዚሁ የሚመደብ ነው።
ከላይ የተጠቀሱት አንቀፆችና ይህንኑ ትርጉም ይዘው የመጡ ሌሎች አንቀፆችም ሆኑ ሐዲሶች ሁሉ የሚያመለክቱት በሁሉም ጉዳዮች ላይ ልብን ወደ አላህ ማዞርና አምልኮንም ለእርሱ ብቻ ጥርት አድርጎ መፈፀም ግዴታ መሆኑን ነው፤ ምክንያቱም ቀደም ብሎ በተጠቀሱ አንቀጾች ላይ እንደሰፈረው የአላህ ባሮች የተፈጠሩት ለዚህ ነው፤ የታዘዙትም በዚሁ ነው። ጥራት የተገባው ጌታችንም እንዲህ ብሏል፡-
﴿وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا...﴾
{አላህን ተገዙ:: በእርሱ ምንንም አታጋሩ።…} [አን-ኒሳእ: 36] የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ...﴾
{ሃይማኖትን ለአላህ ብቻ አጥሪዎችና ቀጥተኞች ሆነው አላህን ሊገዙት እንጂ ያልታዘዙ ሲሆኑ (ተለያዩ)} [አል-በይናህ፡ 5] ነቢዩም ﷺ በሙዓዝ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሓዲሥ እንዲህ ብለዋል፦
«حَقُّ اللهِ عَلَى العِبَادِ أَنْ يَعْبُدُوهُ وَلَا يُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا».
"አላህ በባሮቹ ላይ ያለው መብት በእርሱ ምንንም ሳያጋሩ በብቸኝነት ሊያመልኩት ነው።" ሶሒሕ በመሆኑ ላይ ተስማምተውበታል። ነቢዩም ﷺ ከኢብኑ መስዑድ -ረዲየሏሁ ዐንሁ- በተላለፈ ሐዲስ እንዲህ ብለዋል፦
«مَنْ مَاتَ وَهُوَ يَدْعُو لِلَّهِ نِدًّا؛ دَخَلَ النَّارَ».
«ከአላህ ውጭ ሌላን ሲማፀን የሞተ ሰው እሳት ገባ።» ቡኻሪ ዘግበውታል። በሶሒሕ ቡኻሪና ሙስሊም ከኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - በተላለፈ ሓዲሥ ነብዩ ﷺ ሙዓዝን ወደ የመን በላኩት ጊዜ እንዲህ ብለውታል፦
«إِنَّكَ تَأْتِي قَومًا أَهْلَ كِتَابٍ، فَلْيَكُنْ أَوَّلَ مَا تَدْعُوهُم إِلَيهِ شَهَادَةِ أَنْ لَا إِلهَ إِلَّا اللهُ».
"አንተ የምትሄድባቸው ሰዎች ከመጽሐፉ ባለቤት የሆኑ ህዝቦች ናቸው፤ በመሆኑም የመጀመሪያው ጥሪህ ወደ "ላ ኢላሃ ኢለሏህ" ምስክርነት ይሁን።" በሌላ ዘገባ:
«اُدْعُهُمْ إِلَى شَهَادَةِ أَنْ لَا إِلهَ إِلَّا اللهُ وَأَنِّي رَسُولُ اللهِ».
«ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና እኔም የአላህ መልዕክተኛ መሆኔን እንዲመሰክሩ ጥራቸው»። በቡኻሪ ዘገባ:
«فَلْيَكُنْ أَوَّلَ مَا تَدْعُوهُم إِلَى أَنْ يُوَحِّدُوا اللهَ».
«በቅድሚያ ልትጠሯቸው የሚገባው አላህን በአምልኮ ወደ መነጠል ይሁን!» በሶሒሕ ሙስሊምም ከጧሪቅ ቢን አሽየም አልአሽጀዒይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
«مَنْ قَالَ: لَا إِلهَ إِلَّا اللهُ، وَكَفَرَ بِمَا يُعْبَدُ مِن دُونِ اللهِ؛ حَرُمَ مَالُهُ وَدَمُهُ، وَحِسَابُهُ عَلَى اللهِ جَلَّ جَلَالُهُ».
«ላኢላሃ ኢለሏህ ብሎ ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ነገሮች የካደ ሰው፤ ገንዘቡም ደሙም እርም ይሆናል። ሂሳቡ ያለው አላህ ላይ ነው።» ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው ሐዲሦች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው።
ይህ ተውሒድ የእስልምና ሃይማኖት መሰረትና አስኳል፣ የነገሩ ሁሉ ቁንጮና ከግዴታዎችም ሁሉ ታላቁ ነው። ሰውንና ጋኔንን የመፍጠሩም ሆነ መልዕክተኞችን ሁሉ (በእነርሱ ላይ የአላህ ሰላም ይሁን) የመላኩ ጥበብም ይኸው ነው። ለዚህም ማስረጃ የሚሆኑ አንቀፆች ከዚህ በፊት አልፈዋል። ከእነዚህም መካከል የላቀው ጌታችን እንዲህ ብሏል፦
﴿وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنْسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ56﴾
{ጂኒንና ሰዉን ሊገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸዉም::} [አዝ-ዛሪያት፡ 56] ለዚህም ሌላኛው ማስረጃው ተከታዩ ክብሩ የላቀው የአላህ ንግግር ነው፦
﴿وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ...﴾
{በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትን ራቁ በማለት የሚያስተምር መልዕክተኛን ልከናል...} [አን-ነሕል፡ 36] ጥራት የተገባውና የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ25﴾
{ካንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጂ ከመልዕክተኛ አንድንም አላክንም::} [አል-አንቢያእ፡ 25] ታላቅና የላቀው አላህም ኑሕ፣ ሁድ፣ ሷሊህና ሹዐይብ (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በእነርሱ ላይ ይስፈንና) ለህዝቦቻቸው እንዲህ ማለታቸውን ነግሮናል፦
﴿...اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُمْ مِنْ إِلَهٍ غَيْرُهُ...﴾
{አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም::…} [አልአዕራፍ 59] ይህች ከዚህ በፊት የነበሩት ሁለት አንቀፆች እንዳመለከቱት የሁሉም መልክተኞች ጥሪ ናት። የመልክተኞቹ ጠላቶችም እንኳ መልክተኞቹ አላህን በአምልኮ እንዲነጥሉና ከእርሱ ሌላ የሚመለኩ አማልክትን እንዲተዉ እንዳዘዟቸው አምነዋል። ልክ ክብሩ የላቀው አላህ በዓድ ህዝቦች ታሪክ ውስጥ እንደገለጸው፤ እነርሱም ለሁድ - የአላህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁንና - እንዲህ ብለውታል፦
﴿...أَجِئْتَنَا لِنَعْبُدَ اللَّهَ وَحْدَهُ وَنَذَرَ مَا كَانَ يَعْبُدُ آبَاؤُنَا...﴾
{አላህን አንድ አድርገን ብቻውን እንድንገዛውና አባቶቻችን ይገዟቸው የነበሩትን አማልክት እንድንተው መጣህብን?...} [አል-አዕራፍ፡ 70] ነብያችን ሙሐመድ ﷺ ቁረይሾችን አላህን በብቸኝነት ወደ ማምለክና ከእርሱ ሌላ የሚያመልኳቸውን መላእክትን፣ ወሊዮችን፣ ጣዖታትን፣ ዛፎችንና ሌሎችንም ነገሮች ወደ መተው በጠሯቸው ጊዜ ስለነርሱ መልስ አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿أَجَعَلَ الْالِهَةَ إِلَهًا وَاحِدًا إِنَّ هَذَا لَشَيْءٌ عُجَابٌ5﴾
{«አማልዕክቶችን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው።»} [ሷድ፡ 5] ጥራት ይገባውና የላቀው አላህ ስለ መካ አጋርያን እንዲህ ብሏል፦
﴿إِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ35 وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُوٓاْ ءَالِهَتِنَا لِشَاعِرٖ مَّجۡنُونِۭ36﴾
{ እነርሱ «ከአላህ ሌላ እውነተኛ አምላክ የለም» በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ።
«እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን እንዴ?» ይሉ ነበር።} [አስ-ሷፋት፡ 35-36] ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው የቁርኣን አንቀጾች በርካታ ናቸው።
አላህ እኔንም አንተንም በዲኑ ላይ ጥልቅ ግንዛቤንና የዓለማቱን ጌታ እውነት በተመለከተም አስተዋይነትን ይግጠመንና በጠቀስናቸው አንቀፆችና ሐዲሦች መሰረት በጥያቄህ ላይ ያብራራሃቸው እነዚህ ዱዓዎችና የእርዳታ ፍለጋ አይነቶች ሁሉም ከትልቁ ሺርክ አይነቶች የሚመደቡ መሆናቸው ግልጽ ይሆንልሃል። ምክንያቱም ከአላህ ውጭ ላለ አካል የሚደረግ አምልኮና ከእርሱ ውጭ ማንም ሊያደርጋቸው የማይችላቸውን ነገሮች ከሙታንና ሩቅ ካሉ አካላት መጠየቅ ናቸውና። ይህ ደግሞ ከቀድሞዎቹ ሰዎች ሺርክ የከፋ ነው። ምክንያቱም የቀድሞዎቹ ሰዎች የሚያጋሩት በድሎት ጊዜ ብቻ ነው። በችግር ጊዜ ግን አምልኮን ለአላህ ጥርት ያደርጋሉ። ምክንያቱም ከችግር ሊያላቅቃቸው የሚችለው እርሱ ብቻ መሆኑን ያውቃሉና። አላህም ግልፅ በሆነው መጽሐፉ ላይ ስለነዚያ አጋሪዎች እንዲህ ብሏል፦
﴿فَإِذَا رَكِبُواْ فِي ٱلۡفُلۡكِ دَعَوُاْ ٱللَّهَ مُخۡلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ فَلَمَّا نَجَّىٰهُمۡ إِلَى ٱلۡبَرِّ إِذَا هُمۡ يُشۡرِكُونَ65﴾
{በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይጠሩታል:: ወደ የብስ በማውጣት ባዳናቸው ጊዜ ግን ወዲያውኑ እነርሱ ጣዖትን ያጋራሉ::} [አል'ዓንከቡት፡ 65] ጥራት ይገባውና የላቀው አላህ በሌላ አንቀጽ ሲያናግራቸው እንዲህ ብሏል፦
﴿وَإِذَا مَسَّكُمُ ٱلضُّرُّ فِي ٱلۡبَحۡرِ ضَلَّ مَن تَدۡعُونَ إِلَّآ إِيَّاهُۖ فَلَمَّا نَجَّىٰكُمۡ إِلَى ٱلۡبَرِّ أَعۡرَضۡتُمۡۚ وَكَانَ ٱلۡإِنسَٰنُ كَفُورًا67﴾
{በባህሩ ውስጥ ጉዳት በደረሰባችሁ ጊዜ የምትጠሯቸው አማልክት ሁሉ ይጠፉባችሁና እርሱ አላህ ብቻ ይቀራል። ወደ የብስም በማድረስ ባዳናችሁ ጊዜ እምነትን ትተዋላችሁ:: ሰውም በጣም ከሓዲ ነው::} [አል-ኢስራእ: 67]
ከእነዚህ በዘመናችን ካሉ አጋሪዎች አንዱ እንዲህ ቢል፡- «እኛ እነዚያ በራሳቸው እንደሚጠቅሙ፣ በሽተኞቻችንንም በራሳቸው እንደሚፈውሱ፣ ወይም በራሳቸው እንደሚጠቅሙን ወይም በራሳቸው እንደሚጎዱን አናስብም፡፡ ይልቁንስ የምንፈልገው በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ አላህ የሚያቃርቡበትን ምልጃቸውን ነው፡፡»
መልሱም፦ ይህ የቀድሞዎቹ ከሃዲያን አላማና ፍላጎት ነበር። ፍላጎታቸው አማልክቶቻቸው ይፈጥራሉ ወይም ሲሳይ ይሰጣሉ፣ አልያም በራሳቸው ጥቅም ማምጣትም ይሁን ጉዳትን ማስወገድ ይችላሉ የሚል አልነበረም። ይህን አላህ በቁርኣን ውስጥ ስለነርሱ የጠቀሰው ነገር ውድቅ ያደርገዋል። ይልቁንም እነርሱ የፈለጉት የእነዚያን አማልክት ምልጃና ክብር እንዲሁም ወደ አላህ ያቃርቡናል የሚለውን ነበር። ጥራት የተገባው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَيَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمۡ وَلَا يَنفَعُهُمۡ وَيَقُولُونَ هَٰٓؤُلَآءِ شُفَعَٰٓؤُنَا عِندَ ٱللَّهِ...﴾
{አጋሪዎች ከአላህ ሌላ የማይጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውን ይገዛሉ:: «እነዚህ አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው።…» [ዩኑስ፡ 18] አላህም እንዲህ በማለት መለሰላቸው፦
﴿...قُلۡ أَتُنَبِّـُٔونَ ٱللَّهَ بِمَا لَا يَعۡلَمُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ﴾
{…«አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ እናንተ ትነግሩታላችሁን?» በላቸው:: አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም::} [ዩኑስ፡ 18] ከእንከን የጠራው ጌታችን በሰማያትም ሆነ በምድር አጋሪዎቹ በሚፈልጉት መልኩ እርሱ ዘንድ አማላጅ እንደሌለ ግልጽ አድርጓል፡፡ አላህ መኖሩን የማያውቀው ነገር ህልውና የለውም፤ ምክንያቱም ከርሱ ምንም ነገር አይሰወርምና፡፡ የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿تَنزِيلُ ٱلۡكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَكِيمِ 1 إِنَّآ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ فَٱعۡبُدِ ٱللَّهَ مُخۡلِصٗا لَّهُ ٱلدِّينَ2 أَلَا لِلَّهِ ٱلدِّينُ ٱلۡخَالِصُۚ وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَ مَا نَعۡبُدُهُمۡ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَآ إِلَى ٱللَّهِ زُلۡفَىٰٓ إِنَّ ٱللَّهَ يَحۡكُمُ بَيۡنَهُمۡ فِي مَا هُمۡ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي مَنۡ هُوَ كَٰذِبٞ كَفَّارٞ3﴾
{ የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ነው::
እኛ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት የተሞላ ሲሆን አወረድነው:: አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ሆነህ ተገዛው::
ንቁ! ፍጹም ጥሩ የሆነው ሃይማኖት ለአላህ ብቻ ነው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድረገው የያዙት «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን በማሰብ እንጂ ለሌላ አንገዛቸዉም።» ይላሉ:: አላህ በዚያ እነርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል:: አላህም ውሸታም ከሓዲ የሆነን ሰው አያቀናም::} [አዝ-ዙመር: 1-3]
እዚህ አንቀጽ ላይ ሃይማኖት በማለት የተፈለገው አምልኮ ነው። ይህም -ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው- አላህንና መልዕክተኛውን ﷺ መታዘዝ ነው። በውስጡም የሚከተሉት ይካተታሉ፦ ዱዓእ፣ እገዛን መጠየቅ፣ ፍራቻ፣ ተስፋ ማድረግ፣ እርድ፣ ስለት፣ ሶላት፣ ፆምና ሌሎችም አላህና መልዕክተኛው ያዘዙባቸው ነገሮች ሁሉ ይካተቱበታል። ጥራት የተገባው ጌታችንም አምልኮ ለእርሱ ብቻ እንደሆነና ባሮቹም ለታላቁ ጌታ በኢኽላስ ሊፈጽሙት ግዴታ መሆኑን አብራርቷል። ምክንያቱም አላህ ለነቢዩ ﷺ አምልኮን በኢኽላስ እንዲፈጽሙ ማዘዙ ለኡመታቸውም ሁሉ የተሰጠ ትዕዛዝ ነውና።
ከዚያም የላቀው አላህ ስለ ከሓዲዎች እንዲህ በማለት ገለፀ፦
﴿...وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَ مَا نَعۡبُدُهُمۡ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَآ إِلَى ٱللَّهِ زُلۡفَىٰٓ...﴾
{እነዚያ ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድረገው የያዙት ሁሉ «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን በማሰብ እንጂ ለሌላ አንገዛቸዉም።»ይላሉ።} [አዝ-ዙመር: 3] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦
﴿...إِنَّ ٱللَّهَ يَحۡكُمُ بَيۡنَهُمۡ فِي مَا هُمۡ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي مَنۡ هُوَ كَٰذِبٞ كَفَّارٞ﴾
{አላህ በዚያ እነርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል:: አላህም ውሸታም ከሓዲ የሆነን ሰው አያቀናም::} [አዝ'ዙመር፡ 3] ጥራት የተገባው አላህ በዚህች በተከበረች አንቀፅ ከሃዲዎች ከእርሱ ሌላ ያሉ ወሊዮችን ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቀርቧቸው እንጅ ለሌላ እንዳልተገዟቸው ተናግሯል። ይህም የጥንቶቹም የዘመኑም ከሃዲዎች ዓላማ ነው። አላህም ይህንን በሚከተለው ቃሉ ውድቅ አድርጎታል፦
﴿...إِنَّ ٱللَّهَ يَحۡكُمُ بَيۡنَهُمۡ فِي مَا هُمۡ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي مَنۡ هُوَ كَٰذِبٞ كَفَّارٞ﴾
{…አላህ በዚያ እነርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል:: አላህም ውሸታም ከሓዲ የሆነን ሰው አያቀናም::} [አዝ-ዙመር: 3] አማልክቶቻቸው ወደ አላህ መቃረብን ያቃርቧቸዋል የሚለው ሙግታቸው ውሸት መሆኑንና ለእነርሱ ያዋሉት አምልኮም ክህደት መሆኑን አላህ ግልፅ አድርጓል። በዚህም አነስተኛ ማስተዋል ያለው ማንኛውም ሰው የቀድሞዎቹ ከሓዲዎች ክህደት ነቢያትን፣ ወሊዮችን፣ ዛፎችን፣ ድንጋዮችን እና ሌሎች ፍጡራንን በእነርሱና በአላህ መካከል አማላጅ አድርገው በመያዛቸው የመጣ መሆኑን ይገነዘባል። ልክ ሚኒስትሮች በነገሥታት ዘንድ እንደሚያማልዱት ሁሉ እነርሱም አማላጆቻቸው ያለ እርሱ ፈቃድና ውዴታ ጉዳዮቻቸውን እንደሚፈጽሙላቸው በማመን ከጉድለት ሁሉ የጠራውንና ግርማው የላቀውን አላህ ከነገሥታትና ከመሪዎች ጋር አመሳሰሉት። እንዲህም አሉ፦ ‹‹አንድ ሰው ንጉሥ ወይም አንድ መሪ ዘንድ ጉዳይ ሲኖረው በቅርብ ሰዎቹና በአማካሪዎቹ አማላጅ እንደሚያስይዝ ሁሉ እኛም እንደዚሁ ነብያቱንና ወልዮቹን በማምለክ ወደ አላህ እንቃረባለን።›› ይህ እጅግ በጣም ከንቱ ሙግት ነው፤ ምክንያቱም አላህ አምሳያ የለውም፣ ከፍጡራኑም ጋር አይነፃፀርም፣ በእርሱ ዘንድም እርሱ ለማማለድ ካልፈቀደለት በቀር ማንም አያማልድም፤ ፈቃዱንም የሚሰጠው ለተውሒድ ሰዎች እንጂ ለሌላ አይደለም፤ እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው፤ ሁሉንም ነገርም አዋቂ ነው፤ እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው፤ ማንንም አይፈራም፤ አይሰጋምም፤ ምክንያቱም አላህ ከባሮቹ ሁሉ የበላይ የሆነ ኃያል ነውና፤ በእነርሱም ላይ እንደሻው የሚወስን ነው። ንጉሶችና መሪዎች ግን በተቃራኒ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ አይደሉም። ስለዚህም ሊያቅታቸው በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ከሚንስትሮቻቸው፣ ከአማካሪዎቻቸውና ከወታደሮቻቸው የሚያግዟቸው ያስፈልጓቸዋል። እንዲሁም ፍላጎቱን የማያውቁለትን ሰው ጉዳይ የሚያደርስላቸው ያስፈልጋቸዋል፤ ስለሆነም ከሚኒስትሮቻቸውና ከአማካሪዎቻቸው እዝነት የሚከቱባቸውና ውዴታቸውን የሚጠይቁላቸው ያስፈልጓቸዋል። የላቀውና ከፍ ያለው ጌታ አላህ ግን ከፍጡራኑ ሁሉ የተብቃቃ ነው፤ እርሱም ለነርሱ ከእናቶቻቸው የበለጠ አዛኝ፣ ፍትሐዊ ፈራጅ፣ ነገራትን በጥበቡ፣ በዕውቀቱና በችሎታው መሠረት በየስፍራቸው የሚያስቀምጥ ነው። ከፍጡራኑ ጋር በምንም መልኩ ሊነፃፀር ፈፅሞ አይገባውም። ለዚህም አጋርያን አላህ ፈጣሪ፣ ሲሳይ ሰጪና አስተናባሪ፣ የተቸገረን ሰው ጥሪ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያነሳ፣ ህያው የሚያደርግና የሚገድል መሆኑንና ከዚህ ውጭ ያሉትን ሌሎች የእርሱን ድርጊቶች ጭምር እንደሚያምኑ ጥራት የተገባው አላህ በመጽሐፉ ውስጥ ግልጽ አድርጓል። በእርግጥም በሙሽሪኮችና በመልእክተኞች መካከል የነበረው ሙግት አምልኮን ለአላህ በብቸኝነት በማጥራት ዙሪያ ነበር። ክብሩ የላቀው እንዲህ ብሏል፦
﴿وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَهُمۡ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُ...﴾
{ማን እንደ ፈጠራቸው ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይላሉ...} [አዝ-ዙኽሩፍ፡ 87] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿قُلۡ مَن يَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ أَمَّن يَمۡلِكُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَمَن يُخۡرِجُ ٱلۡحَيَّ مِنَ ٱلۡمَيِّتِ وَيُخۡرِجُ ٱلۡمَيِّتَ مِنَ ٱلۡحَيِّ وَمَن يُدَبِّرُ ٱلۡأَمۡرَۚ فَسَيَقُولُونَ ٱللَّهُۚ فَقُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ31﴾
{«ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው? መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረላችሁ ማን ነው? ከሙትም ህያውን የሚያወጣ፤ ከህያዉም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው?» በላቸው:: «በእርግጥ አላህ ነው።» ይሉሃል:: «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ? ታዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው።} [ዩኑስ፡ 31] በዚህ ዙሪያ የመጡ ቁርአናዊ ማስረጃዎች በርካታ ናቸው።
ቀደም ብሎ እንደተገለፀው በመልዕክተኞችና በሕዝቦቻቸው መካከል የነበረው ሙግት ዋናው ነጥብ አላህን በብቸኝነት ማምለክ እንደሆነ የሚያመላክቱ አንቀፆች ተጠቅሰዋል። ጥራት የተገባው አምላክ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَلَقَدۡ بَعَثۡنَا فِي كُلِّ أُمَّةٖ رَّسُولًا أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَٱجۡتَنِبُواْ ٱلطَّٰغُوتَ...﴾
{በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልዕክተኛን በእርግጥ ልከናል...} [አን-ነሕል፡ 36] ተመሳሳይ መልዕክት ያላቸው የቁርአን አንቀፆች በርካታ ናቸው: ከጉድለት የጠራው አላህ በታላቁ መጽሐፍ ውስጥ በበርካታ ቦታዎች የምልጃን ጉዳይ አብራርቷል። ከፍ ያለው አላህ እንዲህም ብሏል፦
﴿...مَن ذَا ٱلَّذِي يَشۡفَعُ عِندَهُۥٓ إِلَّا بِإِذۡنِهِ...﴾
{…ያ እርሱ ዘንድ በፍቃዱ ቢሆን እንጂ የሚያማልድ ማን ነው?…} [አል-በቀራህ፡ 255] የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَكَم مِّن مَّلَكٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ لَا تُغۡنِي شَفَٰعَتُهُمۡ شَيۡـًٔا إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ أَن يَأۡذَنَ ٱللَّهُ لِمَن يَشَآءُ وَيَرۡضَىٰٓ26﴾
{በሰማያት ውስጥ ካሉ መላዕክት ብዙዎች አላህ እንዲያማልዱ ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ያማልዱ ዘንድ ከፈቀደላቸው በኋላ እንጂ ምልጃቸው የማይፈይድ አያሌዎች ናቸው::} [አን-ነጅም፡ 26]
መላእክትንም ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፡
﴿...وَلَا يَشۡفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ٱرۡتَضَىٰ وَهُم مِّنۡ خَشۡيَتِهِۦ مُشۡفِقُونَ﴾
{…ለወደደውም እንጂ ለሌላው አያማልዱም:: እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው::} [አል'አንቢያእ፡ 28]
ክብሩ የላቀው አላህ ባሪያዎቹ ክህደትን ሲፈፅሙ እንደማይወድ፤ ይልቁንም የሚወድላቸው ምስጋናን እንደሆነ አሳውቋል። ምስጋና ማለት ደግሞ እርሱን መነጠልና ትእዛዙን መፈፀም ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿إِن تَكۡفُرُواْ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَنِيٌّ عَنكُمۡۖ وَلَا يَرۡضَىٰ لِعِبَادِهِ ٱلۡكُفۡرَۖ وَإِن تَشۡكُرُواْ يَرۡضَهُ لَكُمۡ...﴾
{ብትክዱ አላህ ከናንተ የተብቃቃ ነው:: ለባሪያዎቹም ክህደትን አይወድም፤ ብታመሰግኑም እርሱን ይወድላችኋል...} [አዝ-ዙመር: 7]
ቡኻሪ በሰሒሓቸው እንደዘገቡት አቡ ሁረይራ አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልእክተኛ ሆይ! በርሶ ምልጃ ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛው ማን ነው?»
«مَنْ قَالَ: لَا إِلهَ إِلَّا اللهُ خَالِصًا مِنْ قَلْبِهِ».
እርሳቸውም እንዲህ በማለት መለሱ: "ከልቡ አጥርቶ 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ያለ ሰው ነው።" ወይም እንዲህ ብለዋል፡
«مِنْ نَفْسِهِ».
«ከነፍሱ አጥርቶ»።
በሶሒሕ ዘገባ አነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
«لِكُلِّ نَبِيٍّ دَعْوَةٌ مُسْتَجَابَةٌ، فَتَعَجَّلَ كُلُّ نَبِيٍّ دَعْوَتَهُ، وَإِنِّي اخْتَبَأْتُ دَعْوَتِي شَفَاعَةً لِأُمَّتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ، فَهِيَ نَائِلَةٌ إِنْ شَاءَ اللَّهُ مَنْ مَاتَ مِنْ أُمَّتِي لَا يُشْرِكُ بِاللَّهِ شَيْئًا».
"ለእያንዳንዱ ነቢይ ተቀባይነት ያላት ልመና አለው። እያንዳንዱ ነቢይም በልመናው ተቻኩሏል። እኔ ግን ልመናዬን ለህዝቦቼ የትንሳኤ ቀን ምልጃ ትሆን ዘንድ ሸሽጌያታለሁ። እርሷም አላህ ከፈቀደ ከህዝቦቼ በአላህ ላይ አንዳችንም ነገር ሳያጋራ የሞተን ሰው ታገኛለች።" ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው ሐዲሦች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው።
የጠቀስናቸው አንቀፆችና ሐዲሶች ባጠቃላይ የሚያመላክቱት አምልኮ የአላህ ብቻ ሐቅ መሆኑን፣ ከርሷም አንዳችንም ነገር ለነቢያትም ሆነ ለሌሎች ከአላህ ውጪ መስጠት እንደማይፈቀድ፣ እንዲሁም ምልጃ የዚያ ክብሩ ከፍ ያለው የአላህ ብቻ መሆኑን ነው። ክብሩ የጠራው (ጌታ) እንዲህ ብሏል፦
﴿قُل لِّلَّهِ ٱلشَّفَٰعَةُ جَمِيعٗا...﴾
{«ምልጃ ሁሉም የአላህ ብቻ ነው...»} [አዝ-ዙመር፡ 44] አላህ ለአማላጁ ከፈቀደለትና የሚማለደውንም ሰው ከወደደው በኋላ ካልሆነ በቀር አንድም ሰው ምልጃ አይገባውም። ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰው አላህ ከተውሒድ በቀር አይወድም። በዚህም መሰረት፦ ሙሽሪኮች ከምልጃ ምንም ድርሻ የላቸውም። ይህንንም አላህ በላቀው ቃሉ እንዲህ በማለት አብራርቷል፦
﴿فَمَا تَنفَعُهُمۡ شَفَٰعَةُ ٱلشَّٰفِعِينَ 48﴾
{የአማላጆችም (ሁሉ) ምልጃ አትጠቅማቸዉም።} [አል-ሙደሢር፡ 48] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿...مَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنۡ حَمِيمٖ وَلَا شَفِيعٖ يُطَاعُ﴾
{…ለበዳዮች ምንም ወዳጅና ተሰሚ አማላጅ የላቸዉም::} [ጋፊር: 18]
በደል ተብሎ በጥቅሉ ሲጠቀስ በአላህ ማጋራት መሆኑ የሚታወቅ ነው፤ የላቀው አላህም እንዲህ ብሏል፦
﴿...وَٱلۡكَٰفِرُونَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ﴾
{…ከሓዲዎችም በዳዮች እነርሱ ናቸው::} [አል-በቀራህ: 254] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿...إِنَّ ٱلشِّرۡكَ لَظُلۡمٌ عَظِيمٞ﴾
{…ማጋራት ታላቅ በደል ነውና።} [ሉቅማን: 13]
በጥያቄው ላይ የጠቀስከውን በተመለከተ፤ አንዳንድ ሱፊያዎች በመስጂዶችና በሌሎችም ቦታዎች ከሚሉት ንግግር ውስጥ፦ «አላህ ሆይ! የኃያልነትህ ምስጢሮች እንዲሰነጠቁና የእዝነታዊ ብርሃኖችህ እንዲፈልቁ ሰበብ ባደረከው፣ የመለኮታዊ ስፍራህ ተወካይና የዛታዊ ምስጢሮችህ ምትክ በሆነው ላይ ሶላት አውርድ፤ … ወዘተ።»
መልሱ፡ ይህ ንግግርና መሰሎቹ ከአቅም በላይ እና ወሰን ባለፈ መልኩ ራስን መጫን ውስጥ የሚመደብ ነው፤ ነቢያችን ሙሐመድም ﷺ ሙስሊም በሶሒሐቸው ከዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- በዘገቡት ሐዲሥ ከዚህ ነገር አስጠንቅቀዋል። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡
«هَلَكَ المُتَنَطِّعُونَ» قَالَهَا ثَلَاثًا.
{ወሰን አላፊዎች ጠፉ!' ሶስት ጊዜ ደጋገሟት።}
አልኢማም አል-ኸጧቢይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡ አል‐ሙተነጢዕ፡ በአንድ ነገር ውስጥ በጥልቀት የሚገባ፣ እርሱን ለመመራመር ከአቅሙ በላይ የሚጣጣር፤ በማይመለከታቸውና አዕምሮአቸው በማይደርስበት ጉዳይ ውስጥ ሰምጠው በሚገቡት የአህሉል ከላም ሰዎች መንገድ የሚጓዝ ነው።
አቡ አስ-ሰዓዳት ኢብኑል-አሢር እንዲህ ብለዋል፦ እነርሱ በንግግራቸው ከመጠን በላይ የሚጨነቁና ወሰን የሚያልፉ፤ በጉሮሯቸው መጨረሻ የሚናገሩ ናቸው። ቃሉ የተወሰደው ‹አን-ነጥዕ› ከሚለው ሲሆን እርሱም የአፍ የላይኛው ዋሻ ነው። ከዚያም በንግግርም ሆነ በተግባር ወሰን ለሚያልፉ ሁሉ መጠቀሚያ ሆነ።
እነዚህ ሁለት የቋንቋ ሊቃውንት በጠቀሱት መሰረት ለአንተም ሆነ አነስተኛ ግንዛቤ ላለው ማንኛውም አካል ግልፅ እንደሚሆነው፤ በነቢያችንና በአይነታችን በአላህ መልእክተኛ ﷺ ላይ የሚደረገው ይህ የሶላትና ሰላም አፈፃፀም ከተከለከለው ራስን ከማስጨ ከአጉል ጥልቀት ውስጥ ይመደባል። በዚህ ዙሪያ ለሙስሊሙ የተደነገገው፤ በአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላይ ሶላትና ሰላም በሚያወርድበት አፈጻጸም ላይ ከሳቸው የተረጋገጠውን መጠበቁ ነው፤ ይህም ከሌላው ነገር ሁሉ ያብቃቃል።
ከነዚህም መካከል ቡኻሪና ሙስሊም በሰሒሓቸው ከከዕብ ቢን ዑጅራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንደዘገቡት ሶሓቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አላህ በርሶ ላይ ሶላት እንድናወርድ አዞናል፤ በርሶ ላይ ሶላት የምናወርደውስ እንዴት ነው?» እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦
«قُولُوا: اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، وَبَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ».
«በሉ፦ አላህ ሆይ! በኢብራሂምና በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ሰላት እንዳወረድክ ሁሉ በሙሐመድና በሙሐመድ ቤተሰቦች ላይም ሰላት አውርድ፡፡ አንተ ምስጉንና የላቅክ ነህና፡፡ አላህ ሆይ! በኢብራሂምና በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ እንደባረክክ ሁሉ በሙሐመድና በሙሐመድ ቤተሰቦች ላይም ባርክ፡፡ አንተ ምስጉንና የላቅክ ነህና፡፡»
በሶሒሕ ቡኻሪና ሙስሊም ከአቡ ሑመይድ አስ-ሳዒዲይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውው - እንደተዘገበው፤ (ሶሐቦች) እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርሶ ላይ ሶላት የምናወርደው እንዴት ነው?» እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦
«قُولُوا: اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى أَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى آلِ إِبرَاهِيمَ، وَبَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى أَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إِبرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ».
በሉ፡ “«አልላሁመ ሰሊ ዐላ ሙሐመድ ወዐላ አዝዋጂሂ ወዙርሪያቲሂ ከማ ሰለይተ ዐላ ኣሊ ኢብራሂም፣ ወባሪክ ዐላ ሙሐመድ ወዐላ አዝዋጂሂ ወዙርሪያቲሂ ከማ ባረክተ ዐላ ኣሊ ኢብራሂም፣ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ።»” (ትርጉሙም፡ አላህ ሆይ! በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ውዳሴህን እንዳወረድክ ሁሉ በሙሐመድ፣ በሚስቶቻቸውና በዝርዮቻቸው ላይም ውዳሴህን አውርድ፤ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ በረከትህን እንዳሰፈንክ ሁሉ በሙሐመድ፣ በሚስቶቻቸውና በዝርዮቻቸው ላይም በረከትህን አውርድ። አንተ ምስጉንና የላቅክ ነህና።) ማለት ነው።
በሶሒሕ ሙስሊም ከአቢ መስዑድ አል-አንሷሪ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፡ በሺር ኢብኑ ሰዕድ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህ በርሶ ላይ ሶላት እንድናወርድ አዞናል። በርሶ ላይ ሶላት የምናወርደውስ እንዴት ነው?» አላቸው። እርሳቸውም ዝም አሉና ከዚያም እንዲህ አሉ፡
«قُولُوا: اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ؛ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى آلِ إِبرَاهِيمَ، وَبَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ؛ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إِبرَاهِيمَ فِي العَالَمِينَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، وَالسَّلَامُ كَمَا عَلِمتُم».
«በሉ፡ “አልላሁመ ሰሊ ዐላ ሙሐመድ ወዐላ ኣሊ ሙሐመድ፤ ከማ ሰለይተ ዐላ ኣሊ ኢብራሂም፣ ወባሪክ ዐላ ሙሐመድ ወዐላ ኣሊ ሙሐመድ፤ ከማ ባረክተ ዐላ ኣሊ ኢብራሂም ፊል ዓለሚን፣ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ።” (ትርጉሙም፡ አላህ ሆይ! በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ውዳሴህን እንዳወረድክ ሁሉ በሙሐመድና በቤተሰቦቻቸው ላይም ውዳሴህን አውርድ፤ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ በአለማት ውስጥ በረከትህን እንዳሰፈንክ ሁሉ በሙሐመድና በቤተሰቦቻቸው ላይም በረከትህን አውርድ፤ አንተ ምስጉንና የላቅክ ነህና።) ሰላምታውም እንዳወቃችሁት ነው።»
እነዚህ እና መሰል ከነቢዩ ﷺ የተረጋገጡ ቃላቶች አንድ ሙስሊም በአላህ መልዕክተኛ ﷺ ላይ ሰላትና ሰላም ሲያወርድ ሊጠቀምባቸው የሚገቡ ናቸው፤ ምክንያቱም የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ለእርሳቸው ክብር የሚገባውን ነገር ከሰዎች ሁሉ የበለጠ የሚያውቁ ናቸውና። እንዲሁም ለጌታቸው ውዳሴም ሊውሉ የሚገቡ ቃላትንም ከሰዎች ሁሉ የበለጠ የሚያውቁ ናቸው።
ከአቅም በላይ የተጣጣሩባቸውና አዲስ የተፈጠሩ ቃላቶች፣ እንዲሁም ትክክል ያልሆነ ትርጉም ሊይዙ የሚችሉ ቃላቶችን ለምሳሌ በጥያቄው ላይ እንደተጠቀሱት ያሉትን መጠቀም ተገቢ አይደለም። ምክንያቱም በውስጣቸው ከአቅም በላይ መጣጣርን ስለያዙ፣ ውድቅ በሆኑ ትርጉሞችም ሊተረጎሙ ስለሚችሉ፣ እንዲሁም የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከመረጧቸውና ኡመታቸውንም ወደ እነርሱ ከጠቆሙባቸው ቃላቶች ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው ነው። እርሳቸው ከፍጡራን ሁሉ የበለጠ አዋቂ፣ ለእነርሱም የበለጠ መካሪና ከአቅም በላይ ከመጣጣርም የበለጠ የራቁ ናቸው። የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን።
በዚህም የተውሒድን ምንነትና የሽርክን ምንነት፣ በፊተኞቹና በኋለኞቹ ሙሽሪኮች መካከል በዚህ ጉዳይ ላይ የነበረውን ልዩነት፣ እንዲሁም በአላህ መልእክተኛ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ላይ ስለሚደረገው ትክክለኛ የሰላት አፈጻጸም ለማብራራት የጠቀስናቸው ማስረጃዎች ለሐቅ ፈላጊ በቂና አሳማኝ እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ። እውነትን ለማወቅ ፍላጎት የሌለው ሰው ግን ስሜቱን ተከታይ ነው፤ ልቅናው ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿فَإِن لَّمۡ يَسۡتَجِيبُواْ لَكَ فَٱعۡلَمۡ أَنَّمَا يَتَّبِعُونَ أَهۡوَآءَهُمۡۚ وَمَنۡ أَضَلُّ مِمَّنِ ٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ بِغَيۡرِ هُدٗى مِّنَ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ50﴾
{እሺ ባይሉህም የሚከተሉት ዝንባሌዎቻቸውን ብቻ መሆኑን ዕወቅ፤ ከአላህም የሆነ መመሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ብቻ ከተከተለ ሰው ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም፤ አላህ በደለኞች ህዝቦችን አይመራምና::} [አልቀሶስ፡ 50]
አላህ በዚህች በተከበረች አንቀፅ ሰዎች አላህ ነቢዩ ሙሐመድን ﷺ ከላከበት ቅን መመሪያና እውነተኛ ሀይማኖት አንፃር ለሁለት እንደሚከፈሉ ገለፀ፦
አንደኛው፡ ለአላህና ለመልክተኛው ታዛዥ ነው።
ሁለተኛውም፡ የስሜቱ ተከታይ ነው፤ ቀጥሎም ከአላህ መመሪያ ውጭ ስሜቱን ከተከተለ ሰው የበለጠ የጠመመ እንደሌለ ተናገረ።
ታላቅና የላቀ የሆነውን አላህ ስሜትን ከመከተል እንዲጠብቀን፣ እኛንም ሆነ እናንተንም እንዲሁም ሌሎችንም ወንድሞቻችንን ለአላህና ለመልእክተኛው ﷺ ጥሪ ምላሽ ከሚሰጡት፣ ሸሪዓውን ከሚያልቁት፣ ሸሪዓውንም ከሚቃረኑ ቢድዓዎችና ስሜታዊ ዝንባሌዎች ሁሉ ከሚያስጠነቅቁት እንዲያደርገን እንማፀነዋለን። እርሱ ቸርና ለጋስ ነውና።
የአላህ ሰላትና ሰላም በባሪያውና መልዕክተኛው በነብያችን ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸው እና እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ በመልካም በተከተሏቸው ላይ ሁሉ ይስፈን።
***
بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ
አምስተኛው መልዕክት፡
የነብዩን ﷺ መውሊድና ሌሎች መውሊዶችን የማክበር ብይን
ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላትና ሰላም በአላህ መልእክተኛ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው እንዲሁም የእርሳቸውን ቅን ጎዳና በተከተለም ላይ ሁሉ ይስፈን።
ከዚህ በመቀጠል፡- የነብዩን ﷺ ልደት (መውሊድ) ስለማክበር፣ በዝግጅቱ ላይ ለርሳቸው መቆም፣ በርሳቸው ላይ ሰላምታ ማቅረብ እና በመውሊዶች ላይ የሚፈፀሙ ሌሎች መሰል ድርጊቶች ብይንን በተመለከተ ከብዙዎች ዘንድ ጥያቄ ተደጋግሞ ቀርቧል።
መልሱም እንዲህ የሚል ነው፡ የመልክተኛውን ﷺ ልደት (መውሊድ) ማክበርም ሆነ የሌላን ማክበር አይፈቀድም፤ ምክንያቱም ይህ በዲን ውስጥ አዲስ መጤ (ቢድዓ) ነውና፤ መልክተኛው ﷺ እና ቅን የሆኑ ኸሊፋዎቻቸው፣ ሌሎችም ሶሓቦች (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንዲሁም በበላጭ ክፍለ ዘመናት ውስጥ በመልካም የተከተሏቸው ታቢዒዮችም አልሰሩትም። እነርሱም ከነሱ በኋላ ከመጡት ሰዎች ይልቅ ሱናን በበለጠ የሚያውቁ፣ ለመልክተኛው (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያላቸው ፍቅርም የተሟላ እንዲሁም ሸሪዓውን በመከተል የላቁ ነበሩ። ጥራት ይገባውና የላቀው አላህ ግልፅ በሆነው ቁርኣን ውስጥ እንዲህ ብሏል፦
﴿...وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمۡ عَنۡهُ فَٱنتَهُواْ...﴾
{…መልዕክተኛው የሰጣችሁን ማንኛዉንም ነገር ያዙት፤ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ሁሉም ተከልከሉ።…}
[አል-ሐሽር፡ 7] ግርማው የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿...فَلۡيَحۡذَرِ ٱلَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنۡ أَمۡرِهِۦٓ أَن تُصِيبَهُمۡ فِتۡنَةٌ أَوۡ يُصِيبَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٌ﴾
{…እነዚያም ትእዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ::} [አን-ኑር፡ 63] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿لَّقَدۡ كَانَ لَكُمۡ فِي رَسُولِ ٱللَّهِ أُسۡوَةٌ حَسَنَةٞ لِّمَن كَانَ يَرۡجُواْ ٱللَّهَ وَٱلۡيَوۡمَ ٱلۡأٓخِرَ وَذَكَرَ ٱللَّهَ كَثِيرٗا21﴾
{ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ::} [አልአሕዛብ፡ 21] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَٱلسَّٰبِقُونَ ٱلۡأَوَّلُونَ مِنَ ٱلۡمُهَٰجِرِينَ وَٱلۡأَنصَارِ وَٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُم بِإِحۡسَٰنٖ رَّضِيَ ٱللَّهُ عَنۡهُمۡ وَرَضُواْ عَنۡهُ وَأَعَدَّ لَهُمۡ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي تَحۡتَهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۚ ذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ100﴾
{ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል:: ከእርሱም ወደዋል:: በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸዉም ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲሆኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል:: ይህ ታላቅ እድል ነው::} [አት-ተውባህ: 100] የላቀው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿...ٱلۡيَوۡمَ أَكۡمَلۡتُ لَكُمۡ دِينَكُمۡ وَأَتۡمَمۡتُ عَلَيۡكُمۡ نِعۡمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلۡإِسۡلَٰمَ دِينٗا...﴾
{…ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ:: ጸጋየንም በእናንተ ላይ ፈጸምኩ:: ለእናንተም በሃይማኖትነት ኢስላምን ወደድኩላችሁ::…} [አል‐ማኢዳህ: 3] በዚህ ዙሪያ የመጡ ቁርአናዊ ማስረጃዎች በርካታ ናቸው። ነቢዩም ﷺ እንዲህ ማለታቸው ተረጋግጧል፦
«مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ مِنهُ فَهُوَ رَدٌّ».
"በዚህ ሃይማኖታችን ውስጥ ከእርሱ ያልሆነን አዲስ ነገር ያመጣ ሰው እርሱ ውድቅ ነው።" ማለትም፦ በእርሱ ላይ ተመላሽ ነው። በሌላ ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል:
«عَلَيكُم بِسُنَّتِي وَسُنَّةِ الخُلَفَاءِ الرَّاشِدِينَ المَهْدِيَّينَ مِنْ بَعدِي، تَمَسَّكُوا بِهَا، وَعَضُّوا عَلَيهَا بِالنَّوَاجِذِ، وَإِيَّاكُمْ وَمُحْدَثَاتِ الأُمُورِ، فَإِنَّ كُلَّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلَّ بِدْعَةٍ ضَلَالةٌ».
«በኔ እና ከኔ በኋላ ባሉት የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን! እርሷን አጥብቃችሁ ያዟት፤ በመንጋጋ ጥርሳችሁም ነክሳችሁ ያዟት። አደራችሁን አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ! አዲስ መጤ ነገር ሁሉ ቢድዓ ነውና፤ ሁሉም ቢድዓ ደግሞ ጥመት ነው።» እናም በነዚህ ሁለት ሐዲሦች ውስጥ ቢድዓዎችን ከመፈብረክና ቢድዓን በመስራት ላይ ብርቱ ማስጠንቀቂያ አለ።
እንዲህ አይነት መውሊዶችን መፈብረካቸው "ኋላ ላይ ዘግይተው የመጡ ሰዎች ይህንን አላህ ያልፈቀደውን የአላህ ድንጋጌ ወደ አላህ ያቃርበናል በሚል ሙግት እስኪፈበርኩ ድረስ አላህ ለዚህ ህዝብ ሃይማኖቱን ሙሉ አላደረገም፣ መልክተኛውም (ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ኡመታቸው ሊሰራበት የሚገባውን ነገር አላደረሱም" ማለታቸውን ያስይዛል። ይህም ያለጥርጥር ታላቅ አደጋና በላቀው አላህ እንዲሁም በመልዕክተኛው ﷺ ላይ መቃወም ነው። የላቀው አላህ ለባሮቹ ሃይማኖቱን አሟልቶላቸዋል፤ ፀጋውንም በእነርሱ ላይ ሙሉ አድርጓል። መልዕክተኛውም ﷺ ግልፅ የሆነውን መልእክት አድርሰዋል። ወደ ጀነት የሚያደርስና ከእሳት የሚያርቅ የትኛውንም መንገድ ለህዝባቸው ግልፅ አድርገው እንጂ አልተዉም። ከዐብደላህ ኢብኑ ዐምር (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) በተዘገበ ሶሒሕ ሐዲስ ላይ እንደተረጋገጠው እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«مَا بَعَثَ اللهُ مِن نَبِيٍ إِلَّا كَانَ حَقًّا عَلَيهِ أَن يَدُلَّ أُمَّتَهُ عَلَى خَيرِ مَا يَعْلَمُهُ لَهُم، وَيُنْذِرَهُمْ شَرَّ مَا يَعْلَمُهُ لَهُمْ».
«አላህ አንድንም ነቢይ ሕዝቡን ወደሚያውቅላቸው መልካም ነገር እንዲመራቸውና ከሚያውቅላቸው ክፉ ነገር እንዲያስጠነቅቃቸው ግዴታው ተደርጎ እንጂ አልላከም፡፡» ሙስሊም በሰሒሓቸው ዘግበውታል።
እንደሚታወቀው ነቢያችን ﷺ ከነቢያት ሁሉ በላጭና መደምደሚያቸውም ናቸው፤ መልእክትን በማድረስና ህዝባቸውን በመምከርም ከማንም በላይ የተሟሉ ናቸው። መውሊድን ማክበር አላህ ከሚወደው ዲን ቢሆን ኖሮ፤ መልእክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ለህዝባቸው በገለፁት ነበር፤ ወይም እርሳቸው በህይወታቸው በሰሩት ነበር፤ ወይም ሰሓቦቻቸው (ረዲየላሁ ዐንሁም) በሰሩት ነበር። ከዚህ መካከል አንዳቸውም ነገር ስላልተከሰተ ይህ ከእስልምና ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ይታወቃል። ይልቁንም መልእክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ህዝባቸውን ካስጠነቀቁባቸው መጤ ነገሮች (ቢድዓ) ውስጥ የሚካተት ነው። ይህም ቀደም ብሎ በሐዲሶች ላይ እንደተገለፀው ነው። በዚህ ዙሪያ የመጡ የቁርኣን አንቀጾችና ሐዲሶች በርካታ ናቸው።
በርካታ ዑለማዎች የተጠቀሱትንና ሌሎችንም ማስረጃዎች መሰረት በማድረግ መውሊድን አውግዘዋል፤ ከእርሱም አስጠንቅቀዋል። ኋላ ላይ የመጡት ከፊሎች ግን በተቃራኒ የአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላይ ድንበር ማለፍ፣ የሴቶችና የወንዶች መቀላቀል፣ የመዝናኛ መሳርያዎችን መጠቀም እና የመሳሰሉ ንጹሑ ሸሪዓ የሚያወግዛቸውን መጥፎ ነገሮች እስካላካተተ ድረስ ይፈቀዳል ብለዋል። ከመልካም ቢድዓዎች መካከል እንደሆነም አስበዋል።
ሸሪዓዊው መርህ ሰዎች የሚከራከሩበትን ነገር ወደ አላህ ኪታብና ወደ መልዕክተኛው ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሱና መመለስ ነው፤ ታላቅና ከፍ ያለው አላህም እንዲህ ብሏል፦
﴿يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُواْ ٱلرَّسُولَ وَأُوْلِي ٱلۡأَمۡرِ مِنكُمۡۖ فَإِن تَنَٰزَعۡتُمۡ فِي شَيۡءٖ فَرُدُّوهُ إِلَى ٱللَّهِ وَٱلرَّسُولِ إِن كُنتُمۡ تُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِۚ ذَٰلِكَ خَيۡرٞ وَأَحۡسَنُ تَأۡوِيلًا59﴾
{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ታዘዙ:: መልዕክተኛውን እና ከመካከላችሁም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ:: በማንኛዉም ነገር ብትከራከሩም በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ከሆናችሁ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው መልሱት:: ይህ የተሻለ እና መጨረሻዉም ያማረ ነው::} [አን-ኒሳእ፡ 59] ጥራት ይገባውና እንዲህም ብሏል፡
﴿وَمَا ٱخۡتَلَفۡتُمۡ فِيهِ مِن شَيۡءٖ فَحُكۡمُهُۥٓ إِلَى ٱللَّهِ ...﴾
{«ያ የተለያያችሁበት ነገር ሁሉ ፍርዱ ወደ አላህ ብቻ ነው...»} [አሽ ሹራ፡ 10]
ይህንን የመውሊድ ክብረ በዓልን የማክበር ጉዳይ ጥራት ወደተገባው የአላህ መጽሐፍ መልሰነዋል፤ መጽሐፉም ረሱልን (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይዘውት በመጡት ነገር እንድንከተል ሲያዘንና ከከለከሉን ነገርም ሲያስጠነቅቀን፣ እንዲሁም ጥራት የተገባው አላህ ለዚህች ህዝብ ሀይማኖቷን እንዳሟላላት ሲነግረን አግኝተነዋል። ይህ ክብረ በዓል ረሱል (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይዘውት ከመጡት ነገሮች አይደለም፤ ስለሆነም አላህ ለኛ ካሟላልንና መልክተኛውንም እንድንከተልበት ካዘዘን ሀይማኖት ውስጥ የሚካተት አይደለም።
ይህንን ጉዳይ ወደ መልእክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሱና ስንመልሰው፤ እርሳቸው የሰሩትም ሆነ ያዘዙበት፣ እንዲሁም ሶሓቦቻቸው የሰሩት ሆኖ አላገኘንም። በዚህም ከዲን አለመሆኑን፤ ይልቁንም አዲስ መጤ ፈጠራ እና በበዓላቶቻቸው ከየሁዶችና ከክርስቲያኖች ጋር መመሳሰል መሆኑን አውቀናል።
በዚህም አነስተኛ ግንዛቤ ላለው፣ እውነትን ለሚከጅልና በፍለጋውም ሚዛናዊ ለሆነ ማንኛውም ሰው፤ መውሊድን ማክበር ከእስልምና ዲን እንዳልሆነ፣ ይልቁንም አላህ እና መልዕክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ልንተዋቸውና ልንጠነቀቃቸው ካዘዙን አዲስ መጤ ቢድዓዎች መካከል መሆኑ ግልፅ ይሆንለታል። አእምሮ ያለው ሰው በተለያዩ ሀገራት አንድን ድርጊት በሚፈፅሙ ሰዎች ብዛት ሊታለል አይገባውም። እውነት የሚታወቀው በፈፃሚዎቹ ብዛት ሳይሆን በሸሪዓዊ ማስረጃዎች ነውና። የላቀው አላህ ስለ አይሁዶችና ነሷራዎች እንዲህ ብሏል፦
﴿وَقَالُواْ لَن يَدۡخُلَ ٱلۡجَنَّةَ إِلَّا مَن كَانَ هُودًا أَوۡ نَصَٰرَىٰۗ تِلۡكَ أَمَانِيُّهُمۡۗ قُلۡ هَاتُواْ بُرۡهَٰنَكُمۡ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ111﴾
{«ጀነትን አይሁድ ወይም ክርስቲያኖች የሆነ እንጂ ሌላ አይገባትም።» አሉ:: «ይህች ከንቱ ምኞታቸው ናት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነተኞች እንደሆናችሁ እስቲ ማስረጃችሁን አምጡ።» በላቸው።} [አል-በቀራህ፡ 111] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَإِنْ تُطِعْ أَكْثَرَ مَنْ فِي الْأَرْضِ يُضِلُّوكَ عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ...﴾
{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በምድር ካሉት መካከል አብዛኞቹን ብትከተል የአላህን መንገድ ያሳስቱሀል::} [አል‐አንዓም: 116]
ከዚያም አብዛኛዎቹ እነዚህ የመውሊድ ክብረ በዓላት ቢድዓ ከመሆናቸውም ጋር ሌሎች ውግዝ ተግባራትን ከመያዝ የጸዱ አይደሉም፤ እንደ የሴቶችና የወንዶች መቀላቀል፣ የዘፈንና የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጠቀም፣ አስካሪ መጠጦችንና አደንዛዥ እፆችን መጠቀም እና ሌሎችም መሰል መጥፎ ተግባሮችን አካተዋል። ከዚህም የባሰ ነገር ሊከሰት ይችላል፤ እርሱም ትልቁ ሺርክ ነው። ይህም በአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወይም ከእርሳቸው ውጭ ባሉ ወልዮች ላይ ድንበር በማለፍ፣ እነርሱን በመማጸን፣ በእነርሱ እገዛን በመጠየቅ፣ ረድኤትን ከእነርሱ በመፈለግ፣ የተሰወረውን ነገር ያውቃሉ ብሎ በማመን እና የመሳሰሉትን የክህደት ተግባራት መፈጸም ነው። ብዙ ሰዎች እነዚህን የክህደት ተግባራት የሚፈፅሙት የነብዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) የልደት በዓል (መውሊድ) ወይም ‘ወልዮች’ ብለው የሚጠሯቸውን ሲያከብሩ ነው። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ማለታቸው ተረጋግጧል፦
«إِيَّاكُم وَالغُلُوُّ فِي الدِّينِ، فَإِنَّمَا أَهْلَكَ مَن كَانَ قَبْلَكُم الغُلُوَّ فِي الدِّينِ».
"በሃይማኖት ላይ ወሰን ከማለፍ ተጠንቀቁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ያጠፋቸው በሃይማኖት ላይ ወሰን ማለፍ ነውና።" እንዲህም ብለዋል፦
«لَا تُطْرُونِي كَمَا أَطْرَتِ النَّصَارَى ابْنَ مَرْيَمَ، إِنَّمَا أَنَا عَبدٌ، فَقُولُوا: عَبدُ اللهِ وَرَسُولُه».
“ክርስቲያኖች የመርየም ልጅን እንዳጋነኑት እኔን አታጋንኑኝ፤ እኔ ባሪያ ብቻ ነኝ። ስለዚህ ‘የአላህ ባሪያና መልክተኛው’ በሉኝ።” ቡኻሪይ በሶሒሐቸው ላይ ከዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ዘግበውታል።
ከሚያስደንቁና ከሚያስገርሙ ጉዳዮች መካከል ብዙ ሰዎች በእነዚህ የተፈበረኩ የቢድዓ ዝግጅቶች ላይ ለመገኘት ሲነቃቁና ሲተጉ እንዲሁም ሲከላከሉላቸው፤ በሌላ በኩል ግን አላህ ግዴታ ካደረገባቸው ከጁሙዓና ከጀመዓ ሰላቶች ይቀራሉ። ለዚህም ምንም ትኩረት አይሰጡትም፤ ታላቅ የሆነን የተወገዘ ድርጊት እንደፈፀሙም አድርገው አያዩትም። ይህ ደግሞ የኢማን ድክመት፣ የማስተዋል ማነስ እና በልቦቻቸው ላይ ከተደራረቡት የተለያዩ ወንጀሎችና ኃጢአቶች ብዛት የመነጨ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። አላህን ለእኛም ሆነ ለመላው ሙስሊሞች ዐፊያ እንዲሰጠን እንለምነዋለን።
ከዚህም ውስጥ ከፊሎቹ የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) በመውሊድ ላይ እንደሚገኙ ማሰባቸው ነው። ለዚህም ነው ሰላምታ እያቀረቡና እንኳን ደህና መጡ እያሉ ለእርሳቸው የሚቆሙት። ይህ ደግሞ ከታላላቅ ውድቅ ነገሮች እና እጅግ አስቀያሚ ድንቁርና ነው። ምክንያቱም መልዕክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ከትንሳኤ ቀን በፊት ከቀብራቸው አይወጡም። ከየትኛውም ሰው ጋር ግንኙነት አይፈጥሩም፤ በስብሰባዎቻቸው ላይም አይገኙም። ይልቁንም እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ በቀብራቸው ውስጥ የጸኑ ናቸው። ነፍሳቸው ደግሞ ከጌታቸው ዘንድ በክብር አገር በአዕላ ዒልዪን ውስጥ ናት። የላቀው አላህ እንዲህ እንዳለው፦
﴿ثُمَّ إِنَّكُمْ بَعْدَ ذَلِكَ لَمَيِّتُونَ15 ثُمَّ إِنَّكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ تُبْعَثُونَ16﴾
{(ሰዎች ሆይ!) ከዚያም እናንተ ከዚህ በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ::
ከዚያም እናንተ በትንሳኤ ዕለት ትቀሰቀሳላችሁ::} [አል-ሙእሚኑን፡ 15-16]
ነብዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
«أَنَا أَوَّلُ مَنْ يَنْشَقُّ عَنْهُ القَبْرُ يَومَ القِيَامَةِ، وَأَنَا أَوَّلُ شَافِعٍ، وَأَوَّلُ مُشَفَّعٍ».
«እኔ የትንሳኤ ቀን ቀብሩ የሚሰነጠቅለት የመጀመሪያው ነኝ፤ እኔም የመጀመሪያው አማላጅና የመጀመሪያውም አማላጅ ተደራጊ ነኝ።» የጌታችን በላጩ ሰላምና እዝነት በርሳቸው ላይ ይስፈን።
እነዚህ ሁለት የተከበሩ አንቀጾች፣ የተከበረው ሐዲስ፣ እንዲሁም በይዘታቸው ተመሳሳይ የሆኑ ሌሎች አንቀጾችና ሐዲሶች ሁሉም የሚያመለክቱት ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እና ሌሎችም ሙታን ከመቃብራቸው የሚወጡት በትንሳኤው ቀን መሆኑን ነው። ይህም በሙስሊም ሊቃውንት መካከል ስምምነት የተደረሰበትና በመካከላቸውም ምንም አይነት ውዝግብ የሌለበት ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ሙስሊም እነዚህን ጉዳዮች ሊገነዘብ፣ እንዲሁም ጃሂሎችና መሰሎቻቸው ካመጧቸውና አላህ በርሷ ላይ ምንም ማስረጃ ካላወረደባቸው ፈጠራዎችና ኹራፋቶች ሊጠነቀቅ ይገባል። አላህ እርዳታው የሚከጀል ነው። መመካትም በርሱው ላይ ነው። ከአላህ በስተቀር ብልሃትም ሀይልም የለም።
በአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ሶለዋትና ሰላምን ማውረድማ በላጭ ከሆኑ መቃረቢያዎችና ከመልካም ስራዎችም ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِيِّۚ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ صَلُّواْ عَلَيۡهِ وَسَلِّمُواْ تَسۡلِيمًا56﴾
{አላህና መላዕክቱ በነቢዩ (ሙሐመድ) ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ:: እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ:: የማክበርን ሰላምታንም ሰላም በሉ::} [አል-አሕዛብ: 56] ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
«مَنْ صَلَّى عَلَيَّ وَاحِدَةً؛ صَلَّى اللهُ عَلَيهِ بِهَا عَشْرًا».
«በኔ ላይ አንዲትን ሶላት ያወረደ፤ አላህ በርሱ ላይ አስር ሶለዋት ያወርድለታል።» እርሷም በሁሉም ወቅቶች የተደነገገች ስትሆን፣ በእያንዳንዱ ሶላት መጨረሻ ላይ ደግሞ ጠንከር ያለች ናት። ይልቁንም በከፊል ዑለማዎች ዘንድ በእያንዳንዱ ሶላት የመጨረሻው ተሸሁድ ላይ ግዴታ ትሆናለች። ሱና መሆኗ በበርካታ ቦታዎች ላይ አፅንዖት ይሰጠዋል። ከእነዚህም ውስጥ ከአዛን በኋላ፣ እርሳቸው (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሚወሱበት ጊዜ፣ በጁምዓ ቀንና በሌሊቷም ላይ ሲሆን፤ ይህንንም በርካታ ሐዲሶች ጠቁመዋል።
አላህ እኛንም ሆነ መላ ሙስሊሞችን ሃይማኖቱን በአግባቡ ለመገንዘብና በእርሱ ላይ ለመፅናት እንዲያድለን፣ በሁሉም ላይም ሱናን አጥብቆ መያዝንና ከቢድዐ መጠንቀቅን እንዲለግስልን እንማፀነዋለን። እርሱ ቸርና ለጋስ ነውና።
የአላህ ሰላትና ሰላም በነቢያችን ሙሐመድ ላይ እንዲሁም በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ይስፈን።
***
بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ
ስድስተኛው መልእክት፡
የኢስራእ እና ሚዕራጅን ሌሊት የማክበር ህግ
ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላትና ሰላም በአላህ መልእክተኛ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ይስፈን።
ከዚህ በመቀጠል፡ ኢስራእና ሚዕራጅ ያለምንም ጥርጥር የመልዕክተኛውን የሙሐመድን ﷺ እውነተኛነትና ልቅናው የላቀው አላህ ዘንድ ያላቸውን ታላቅ ደረጃ ከሚያመላክቱ የአላህ ታላላቅ ተአምራት መካከል ነው። እንዲሁም የአላህን አስደናቂ ችሎታና ከፍጡራኑ ሁሉ በላይ ያለውን ልቅና ከሚያሳዩ ማስረጃዎችም አንዱ ነው። ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ እንዲህ ብሏል፡
﴿سُبۡحَٰنَ ٱلَّذِيٓ أَسۡرَىٰ بِعَبۡدِهِۦ لَيۡلٗا مِّنَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ إِلَى ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡأَقۡصَا ٱلَّذِي بَٰرَكۡنَا حَوۡلَهُۥ لِنُرِيَهُۥ مِنۡ ءَايَٰتِنَآۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ1﴾
{ያ ባሪያውን (ሙሐመድን) ከተከበረው የሐረም መስጊድ ወደ እዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ሩቁ (አል አቅሷ) መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኬደው (ጌታ) ጥራት ይገባው:: ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው (አስኬድነው):: እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚዉና ተመልካቹ ነው::} [አል-ኢስራእ: 1]
ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በተዋቱር (በሰፊና በተረጋገጠ ዘገባ) እንደተላለፈው እርሳቸው ወደ ሰማያት አርገዋል፤ በሮቿም ተከፍተውላቸው ሰባተኛውን ሰማይ አልፈዋል። ጌታቸውም (አላህ) በፈለገው መልኩ አናግሯቸዋል፤ አምስቱንም ሶላቶች ግዴታ አድርጎባቸዋል። አላህ መጀመሪያ ላይ ግዴታ ያደረገው ሀምሳ ሶላቶችን ነበር። ነብያችን ሙሐመድም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲቀነስላቸው በተደጋጋሚ እየተመለሱ ይጠይቁት ነበርና በመጨረሻም አምስት አደረገላቸው። በመሆኑም በግዴታነት አምስት ሲሆኑ በምንዳ ግን ሀምሳ ናቸው፤ ምክንያቱም አንዲት መልካም ስራ በአስር እጥፍ ትመነዳለችና። ለአላህም በሁሉም ፀጋዎቹ ላይ ምስጋና ተገባው።
ይህች ኢስራእ እና ሚዕራጅ የተከናወነባት ሌሊት፣ በረጀብ ወርም ሆነ በሌላ ወር ውስጥ መሆኗን በትክክለኛ ሐዲሶች ላይ አልተገለጸም። ስለ እርሷ መለያም የተዘገቡ ሁሉ በሐዲስ ሊቃውንቶች ዘንድ ከነቢዩ ﷺ ያልጸደቁ ናቸው። አላህም ሰዎች እንዲረሷት በማድረግ ላይ ፍጹም ጥበብ አለው። ሌሊቷ የምትውልበት ቀን በትክክል ቢረጋገጥ ኖሮ ሙስሊሞች በተለየ የአምልኮ አይነት እንዲለዩዋትም ሆነ እንዲያከብሯት አይፈቀድላቸውም ነበር፤ ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ እና ባልደረቦቻቸው (አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና) አላከበሯትም፤ በምንም ነገርም አልለዩዋትምና። እርሷን ማክበር የተደነገገ ጉዳይ ቢሆን ኖሮ ረሱሉ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለኡመታቸው በንግግራቸውም ሆነ በተግባራቸው ያብራሩት ነበር። ከዚህ መካከል አንዱ እንኳ ተከስቶ ቢሆን ኖሮ በታወቀና በገነነ ነበር፤ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና ሶሓቦችም ለእኛ ባስተላለፉልን ነበር። ነቢያቸው (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ኡመታቸው የሚፈልገውን ነገር ሁሉ አስተላልፈዋልና፤ ከዲንም አንዱንም ነገር አላጓደሉም፤ ይልቁንም ወደ መልካም ነገር ሁሉ ቀዳሚ ናቸው። ይህችን ሌሊት ማክበር የተደነገገ ቢሆን ኖሮ ወደ እርሱ ከሰዎች ሁሉ የቀደሙ በሆኑ ነበር። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከሰዎች ሁሉ ለሰዎች የበለጠ መካሪ ናቸው። መልእክቱንም በሚገባ አድርሰዋል፤ አደራውንም ተወጥተዋል። ይህችን ሌሊት ማላቅና በሷ ማክበር ከአላህ ዲን ቢሆን ኖሮ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አይዘነጉትም እንዲሁም አይደብቁትም ነበር። ከዚህ ውስጥ አንዳቸውም አለመከሰቱ፤ በሷ ማክበርና እሷን ማላቅ ከእስልምና በምንም መልኩ አለመሆኑን ያሳያል። አላህ ለዚህ ህዝብ ዲኑን ሞልቶለታል፤ ፀጋውንም በእርሷ ላይ ሙሉ አድርጓል። አላህ ያልፈቀደውን በዲን ውስጥ የደነገገን ሰውም አውግዟል። አላህ ግልፅ በሆነው መጽሐ ላይ እንዲህ ብሏል፦
﴿...ٱلۡيَوۡمَ أَكۡمَلۡتُ لَكُمۡ دِينَكُمۡ وَأَتۡمَمۡتُ عَلَيۡكُمۡ نِعۡمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلۡإِسۡلَٰمَ دِينٗا...﴾
{…ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ:: ጸጋየንም በእናንተ ላይ ፈጸምኩ:: ለእናንተም በሃይማኖትነት ኢስላምን ወደድኩላችሁ::…} [አል‐ማኢዳህ: 3] ክብሩ የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿أَمۡ لَهُمۡ شُرَكَٰٓؤُاْ شَرَعُواْ لَهُم مِّنَ ٱلدِّينِ مَا لَمۡ يَأۡذَنۢ بِهِ ٱللَّهُۚ وَلَوۡلَا كَلِمَةُ ٱلۡفَصۡلِ لَقُضِيَ بَيۡنَهُمۡۗ وَإِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ21﴾
{ከሓዲያን ከአላህ ያልተፈቀደውን ሃይማኖት የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን? የፍርዱ ቃል ባልነበረ ኖሮ በመካከላቸው ወዲያውኑ በተፈረደ ነበር:: በደለኞችም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ አለባቸው::} [አሽ-ሹራ: 21]
ከቢድዐዎች ማስጠንቀቅና ጥመት መሆኗንም በግልፅ መግለፅ ከአላህ መልዕክተኛ ‐የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን‐ በሰሒሕ ሐዲሶች ተረጋግጧል፤ ይህም ኡማውን ስለከፍተኛ አደገኛነቷ ለማንቃትና እንዳይፈጽሟትም ለማራቅ ነው። ከዚህም ውስጥ በሰሒሐይን ከእናታችን ዓኢሻ ‐ረዲየላሁ ዐንሃ‐ የተረጋገጠው፤ ነቢዩ ‐የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና‐ እንዲህ ማለታቸው ነው፡-
«مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ مِنْهُ؛ فَهُوَ رَدٌّ».
""በዚህ ሃይማኖታችን ጉዳይ ከእርሱ ያልሆነን አዲስ ነገር ያመጣ ይዞት የመጣው አዲስ ፈሊጥ ውድቅ ነው።"" በሙስሊም ዘገባም፡
«مَنْ عَمِلَ عَمَلًا لَيْسَ عَلَيهِ أَمْرَنَا؛ فَهُوَ رَدٌّ».
""በርሱ ላይ የኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ነገር የሰራ ሰዉ ስራው ወደርሱ ተመላሽ ነዉ።"" በሶሒሕ ሙስሊም ከጃቢር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተዘገበው፤ የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በጁሙዓ ቀን ኹጥባቸው ላይ እንዲህ ይሉ ነበር፦
«أَمَا بَعْدَ، فَإِنَّ خَيرَ الحَدِيثِ كِتَابُ اللهِ، وَخَيرَ الهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ ﷺ، وَشَرَّ الأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا، وَكُلَّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ».
«ከዚህ በመቀጠል፤ በላጩ ንግግር የአላህ ኪታብ ነው፤ በላጩ መመሪያ ደግሞ የሙሐመድ ‐ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ‐ መመሪያ ነው፤ ከጉዳዮች ሁሉ ክፉ ደግሞ አዲስ መጤ ነገሮች ናቸው፤ ፈጠራም በሙሉ ጥመት ነው።» ነሳኢይ ጥሩ በሆነ ሰነድ የሚከተለውን ጨምረዋል፡
«وَكُلَّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ».
""ሁሉም ጥመት በእሳት ውስጥ ነዉ።"" በሱነን መጽሐፍት ውስጥ ከዒርባድ ቢን ሳሪየህ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ልቦናዎች የራዱበትና አይኖች ያነቡበትን ጥግ የደረሰ ምክር መከሩን። እኛም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምክሮት ልክ የተሰናባችን ምክር ይመስላል። ምከሩን!" አልናቸው። እርሳቸውም:
«أُوصِيكُم بِتَقْوَى اللهِ وَالسَّمعِ وَالطَّاعَةِ وَإِنْ تَأَمَّرَ عَلَيكُم عَبدٌ، فَإِنَّهُ مَنْ يَعِشْ مِنْكُم فَسَيَرَى اخْتِلَافًا كَثِيرًا، فَعَلَيكُم بِسُنَّتِي وَسُنَّةِ الخلُفَاءِ الرَّاشِدِينَ المَهْدِيِّينَ مِنْ بَعْدِي، تَمَسَّكُوا بِهَا وَعَضُّوا عَلَيْهَا بِالنَّوَاجِذِ، وَإِيَّاكُم وَمُحْدَثَاتِ الأُمُورِ، فَإِنَّ كُلَّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٍ وَكُلَّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ».
«አላህን በመፍራት፤ ባሪያ እንኳ ቢሾምባችሁ እንድትሰሙና እንድትታዘዙ አደራ እላችኋለሁ። እነሆ! ከናንተ መካከል የሚኖር ሰው ብዙ ልዩነትን ማየቱ አይቀርም፤ ስለሆነም በኔ ሱናና ከኔ በኋላ ባሉት የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን! እርሷን አጥብቃችሁ ያዙ፤ በማኘኪያ ጥርሳችሁም ነክሳችሁ ያዟት። አደራችሁን አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ! አዲስ መጤ ነገር ሁሉ ቢድዓ ነው፤ ቢድዓም ሁሉ ጥመት ነውና።» ይህንን መልዕክት ይዘው የመጡ ሐዲሦች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው።
ከአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶሐቦች፣ እንዲሁም ከእነሱ በኋላ ከመጡት ደጋግ ሰለፎች ከቢድዓዎች (ፈጠራዎች) ማስጠንቀቅና ከእርሷም ማስፈራራት ተረጋግጧል፤ ይህም የሆነው እርሷ (ቢድዓ) በዲን ላይ ጭማሪ፣ አላህ ያልፈቀደው ድንጋጌ፣ እንዲሁም በሃይማኖታቸው ላይ በመጨመርና አላህ ያልፈቀደውንም በውስጡ በመፍጠር የአላህ ጠላቶች የሆኑትን አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን መመሳሰል በመሆኗ ነው፡፡ በተጨማሪም አስገዳጅ ውጤቷ የእስልምናን ሃይማኖት ማጉደልና ፍፁም አይደለም ብሎ መወንጀል ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ያለው ታላቅ ጥፋት፣ አስከፊ ክፋት እና ልዕልናው የላቀው ከሆነው ከሚከተለው የአላህ ቃል ጋር መጋጨትም የታወቀ ነው፡
﴿...ٱلۡيَوۡمَ أَكۡمَلۡتُ لَكُمۡ دِينَكُمۡ...﴾
{…ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ…} [አል‐ማኢዳህ: 3] ከቢድዐ የሚያስጠነቅቁና ከእርሷም የሚያርቁ የመልዕክተኛውን የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈን ሐዲሶች በግልፅ መቃረንም ነው።
እስካሁን የጠቀስናቸው ማስረጃዎች ይህችን ቢድዓ —ማለትም የኢስራእና ሚዕራጅን ሌሊት የማክበርን ፈጠራ— ውድቅ ለማድረግና ከእርሷም ለማስጠንቀቅ፤ እንዲሁም ከኢስላም ዲን ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌላት ለመገንዘብ ለሐቅ ፈላጊ በቂና አሳማኝ እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ።
አላህ ለሙስሊሞች መመካከርን (መቆርቆር) እና ከዲንም የደነገለላቸውን ነገር ማብራራትን ግዴታ ከማድረጉ እንዲሁም እውቀትን መደበቅ ክልክል ከመሆኑ አንፃር፤ በብዙ ሀገራት ተሰራጭታ አንዳንድ ሰዎችም ከዲን እስከሚቆጥሯት የደረሱትን ይህችን ቢድዓ አስመልክቶ ሙስሊም ወንድሞቼን ማንቃት ወደድኩ።
አላህን የሙስሊሞችን ሁኔታ በሙሉ እንዲያስተካክልልን፣ የሃይማኖት ግንዛቤን እንዲለግሳቸው፣ እኛንም ሆነ እነርሱን እውነትን አጥብቆ መያዝንና በርሱ ላይ መፅናትን፣ የሚፃረረውንም መተው እንዲገጥመን እንጠይቀዋለን። እርሱ ለዚህ ባለቤትም ቻይም ነውና።
የአላህ ሰላትና ሰላም በረከቱም በባሪያውና በመልዕክተኛው በነብያችን ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ይስፈን።
***
بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ
ሰባተኛው መልእክት፡
የሸዕባን ወር አጋማሽ ሌሊትን የማክበር ህግ
ምስጋና ለዚያ ሃይማኖትን ላሟላልን፣ ፀጋውንም በእኛ ላይ ለሞላልን አላህ የተገባ ነው። የአላህ ሶላትና ሰላምም የንስሃና የእዝነት ነብይ በሆኑት በነብዩና በመልእክተኛው ሙሐመድ ላይ ይስፈን።
በመቀጠልም፦ የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿...ٱلۡيَوۡمَ أَكۡمَلۡتُ لَكُمۡ دِينَكُمۡ وَأَتۡمَمۡتُ عَلَيۡكُمۡ نِعۡمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلۡإِسۡلَٰمَ دِينٗا...﴾
{…ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ:: ጸጋየንም በእናንተ ላይ ፈጸምኩ:: ለእናንተም በሃይማኖትነት ኢስላምን ወደድኩላችሁ::…} [አል‐ማኢዳህ: 3] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿أَمۡ لَهُمۡ شُرَكَٰٓؤُاْ شَرَعُواْ لَهُم مِّنَ ٱلدِّينِ مَا لَمۡ يَأۡذَنۢ بِهِ ٱللَّهُ...﴾
{ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን?…} [አሽ ሹራ፡ 21] በሁለቱ ሶሒሖችም ውስጥ ከእናታችን ዓኢሻ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
«مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ مِنْهُ؛ فَهُوَ رَدٌّ».
""በዚህ ጉዳያችን ከእርሱ ያልሆነን አዲስ ፈሊጥ ያመጣ፤ ይዞት የመጣው ፈሊጥ ውድቅ ነው።"" በሶሒሕ ሙስሊም ከጃቢር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተዘገበው፤ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በጁሙዓ ኹጥባቸው እንዲህ ይሉ ነበር፡
«أَمَّا بَعْدُ: فَإِنَّ خَيرَ الحَدِيثِ كِتَابُ اللهِ، وَخَيرَ الهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ صَلَّى اللهُ عَلَيهِ وَسَلَّمَ، وَشَرَّ الأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا، وَكُلَّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ».
«ከዚህ በመቀጠል፥ በላጩ ንግግር የአላህ ኪታብ ነው፤ በላጩ መንገድም የሙሐመድ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መንገድ ነው፤ ከጉዳዮች ሁሉ ክፉው አዲስ መጤዎቹ ናቸው፤ ፈጠራ በሙሉ ጥመት ነው፡፡» በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያሉ አንቀጾችና ሐዲሶች በርካታ ሲሆኑ እነዚህም የላቀው አላህ ለዚህ ህዝብ (ኡማ) ዲኑን እንዳሟላለትና ጸጋውንም በእርሱ ላይ ሙሉ እንዳደረገ በግልጽ ያመላክታሉ። ነብዩንም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ግልጽ የሆነውን መልዕክት ካደረሱና ለህዝቡም አላህ የደነገገላቸውን የንግግርና የተግባር ድንጋጌዎች በሙሉ ካብራሩ በኋላ ቢሆን እንጂ አላሳረፋቸውም። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከእርሳቸው በኋላ ሰዎች የሚፈጥሩትና ወደ ኢስላም ሃይማኖት የሚያስጠጉት ማንኛውም ንግግርም ሆነ ተግባር፤ ሐሳቡ መልካም ቢሆንም እንኳ በፈጠረው ሰው ላይ ተመላሽ የሆነ ቢድዓ መሆኑን አብራርተዋል። ይህንንም ጉዳይ የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶሐቦች እንዲሁም ከእነርሱ በኋላ የመጡ የኢስላም ሊቃውንት አውቀውታል። በመሆኑም ቢድዓዎችን አውግዘው ከእርሷም አስጠንቅቀዋል። ይህንንም ሱናን ስለማላቅና ቢድዓን ስለማውገዝ የጻፉ ሁሉ እንደ ኢብኑ ወዷሕ፣ አጥ-ጡርጡሺ፣ አቡ ሻማና ሌሎችም ጠቅሰውታል፡፡
አንዳንድ ሰዎች ከፈጠሯቸው ቢድዓዎች መካከል፡ የሻዕባንን ወር የአስራ አምስተኛዋን ሌሊት ማክበርና ቀኗን በጾም መነጠል ይገኝበታል። ለዚህም ሊመረኮዙበት የሚፈቀድ ምንም አይነት ማስረጃ የለም። ስለ ትሩፋቷ የተዘገቡ ደካማ ሐዲሶች ቢኖሩም፤ ሊደገፉባቸው ግን አይፈቀድም።
በእርሷ ውስጥ ስለሚሰገደው ሶላት ትሩፋት የተዘገበው ዘገባማ በርካታ ሊቃውንት እንዳስጠነቀቁበት ሁሉም የተቀጠፈ ነው። አላህ ከፈቀደ ከንግግራቸውም የተወሰነው ወደፊት ይወሳል።
እንዲሁም በዚህች ላይ ከሻም ሰዎችና ከሌሎችም ከሆኑት ከተወሰኑ ቀደምት አበዎች አሰሮች መጥተዋል።
በአብዛኞቹ ዑለሞች ዘንድ ስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ ይህንን በዓል ማክበር ቢድዓ መሆኑ እና ስለ ትሩፋቱም የተዘገቡት ሐዲሦች በሙሉ ያልተረጋገጡ (ዶዒፎች) ሲሆኑ ከፊሎቹ ደግሞ የተቀጠፉ (መውዱዕ) መሆናቸው ነው። ይህንንም ካስጠነቀቁት መካከል ሓፊዝ ኢብኑ ረጀብ (ለጧኢፉል መዓሪፍ) በተሰኘው ኪታባቸው እና ሌሎችም ይገኙበታል። እንደሚታወቀው ደግሞ ያልተረጋገጡ (ዶዒፍ) ሐዲሦች ስራ ላይ የሚውሉት መሰረታቸው በትክክለኛ ማስረጃዎች በተረጋገጡ ዒባዳዎች ላይ ነው። የሸዕባንን ወር አስራ አምስተኛ ሌሊት ማክበርን በተመለከተ በደካማ ሐዲሶች እንኳ የሚጠናከርለት ትክክለኛ መሰረት የለውም። ይህችንም ታላቅ መመሪያ ኢማሙ አቡል ዐባስ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ አላህ ይዘንላቸውና ጠቅሰዋታል።
ውድ አንባቢ ሆይ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ ግንዛቤ እንዲኖርህ አንዳንድ ዐሊሞች የተናገሩትን እጠቅስልሃለሁ።
ዑለማዎች (አላህ ይዘንላቸውና) ሰዎች በሚወዛገቡባቸው ጉዳዮች ላይ ወደ ታላቁ አላህ ኪታብና ወደ መልዕክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሱና መመለስ ግዴታ በመሆኑ ላይ በሙሉ ድምፅ ተስማምተዋል። ሁለቱም ወይም አንዳቸው የፈረዱበት ነገር ሊከተሉት የሚገባ ሸሪዓ ሲሆን ሁለቱንም የሚፃረር ነገር ደግሞ መጣል ግዴታ ነው። በሁለቱም ውስጥ ያልተጠቀሰ የዒባዳ አይነት ቢድዓ ነው፤ መስራቱ አይፈቀድም፤ ወደ እርሱ መጣራትና እንዲወደድ ማድረግ ይቅርና አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሏል፦
﴿يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُواْ ٱلرَّسُولَ وَأُوْلِي ٱلۡأَمۡرِ مِنكُمۡۖ فَإِن تَنَٰزَعۡتُمۡ فِي شَيۡءٖ فَرُدُّوهُ إِلَى ٱللَّهِ وَٱلرَّسُولِ إِن كُنتُمۡ تُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِۚ ذَٰلِكَ خَيۡرٞ وَأَحۡسَنُ تَأۡوِيلًا59﴾
{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ታዘዙ:: መልዕክተኛውን እና ከመካከላችሁም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ:: በማንኛዉም ነገር ብትከራከሩም በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ከሆናችሁ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው መልሱት:: ይህ የተሻለ እና መጨረሻዉም ያማረ ነው::} [አን-ኒሳእ፡ 59] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿وَمَا ٱخۡتَلَفۡتُمۡ فِيهِ مِن شَيۡءٖ فَحُكۡمُهُۥٓ إِلَى ٱللَّهِ...﴾
«ያ የተለያያችሁበት ነገር ሁሉ ፍርዱ ወደ አላህ ብቻ ነው...» [አሽ ሹራ፡ 10] ጥራት የተገባው አላህ እንዲህም ብሏል፡
﴿قُلۡ إِن كُنتُمۡ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِي يُحۡبِبۡكُمُ ٱللَّهُ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡ ذُنُوبَكُمۡ...﴾
{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ እኔን ተከተሉኝ:: አላህም ይወዳችኋል፤ ኃጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና...» በላቸው።} [አሊ ዒምራን: 31] የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤۡمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيۡنَهُمۡ ثُمَّ لَا يَجِدُواْ فِيٓ أَنفُسِهِمۡ حَرَجٗا مِّمَّا قَضَيۡتَ وَيُسَلِّمُواْ تَسۡلِيمٗا65﴾
{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጉዳዩ እነርሱ እንዳሉት አይደለም:: በጌታህ እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ የሚያስፈርዱህ ሆነው ከዚያ ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አማኝ አይሆኑም::} [አንኒሳእ፡ 65] የዚህን ዓይነት መልዕክት ያዘሉ አንቀጾች በርካታ ናቸው። እነሱም የልዩነት ጉዳዮችን ወደ ቁርኣንና ሱና መመለስ ግዴታ መሆኑን፣ ፍርዳቸውንም በውዴታ መቀበል ግዴታ መሆኑን፣ ይህም የኢማን መስፈርት እንደሆነ፣ ለባሮችም በቅርቢቱም ሆነ በኋለኛው ዓለም መልካም እንደሆነና በፍጻሜውም እጅግ የተሻለ መሆኑን በግልጽ የሚያስረዱ ናቸው።
አል-ሐፊዝ ኢብኑ ረጀብ ـ አላህ ይዘንላቸውና ـ "(ለጣኢፉ-ል-መዓሪፍ)" በተሰኘው ኪታባቸው ላይ፣ ከዚህ ቀደም ካብራሩት በመቀጠል ይህችን ነጥብ አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፦
«የሻዕባን ወር አጋማሽ ሌሊትን፤ ከሻም ሰዎች የሆኑት ታቢዒዮች፤ እንደ ኻሊድ ኢብኑ መዕዳን፣ መክሑል፣ ሉቅማን ኢብኑ ዓሚር እና ሌሎችም፣ ያከብሯትና በዒባዳ ላይ ይጥሩባት ነበር። ሰዎችም ትሩፋቷንና ማክበሯን የወሰዱት ከእነርሱ ነው። በዚህ ጉዳይ የኢስራኢሊያህ ዘገባዎች እንደደረሷቸው ተዘግቧል። ይህ ነገራቸው በየሀገራቱ ሲታወቅም ሰዎች በጉዳዩ ላይ ያላቸው አቋም ተለያይቷል፤ አንዳንዶቹ ከእነሱ ተቀብለውት እርሷንም በማላቅ ገጥመዋቸዋል፤ ከእነዚህም መካከል የበስራ ዒባዳ አብዢዎች እና ሌሎችም ይገኙበታል። አብዛኞቹ የሒጃዝ ዑለማዎች ይህንን ተቃውመዋል፤ ከእነሱም መካከል አጧእ እና ኢብኑ አቢ ሙለይካህ ይገኙበታል። ዐብዱ'ር-ረሕማን ኢብኑ ዘይድ ኢብኑ አስለምም ከመዲና ሊቃውንት ዘግበውታል፤ ይህም የማሊክ ተከታዮችና የሌሎችም አቋም ሲሆን ይህ ሁሉ ቢድዐ ነውም ብለዋል።
የሻም ዑለማዎቸ በአፈፃፀሙ ሁኔታ ላይ በሁለት ሀሳብ ተለያይተዋል:
አንደኛው፡ "እሷን (ሌሊቷን) በመስጂዶች ውስጥ በጀመዓ በዒባዳ ማሳለፍ ይወደዳል" የሚል ነው። ኻሊድ ኢብኑ መዕዳንና ሉቅማን ኢብኑ ዓሚር እንዲሁም ሌሎችም ምርጥ ልብሳቸውን ይለብሱ፣ ይታጠኑ እንዲሁም ይኳሉ ነበር፤ ያቺንም ሌሊት በመስጂድ (በዒባዳ) ሲቆሙ ያሳልፏት ነበር። ኢስሓቅ ኢብኑ ራሀወይህም በዚህ ላይ ተስማምቶባቸዋል። በመስጂዶች ውስጥ በጀመዓ ስለመስገዷም «ይህ ቢድዐ አይደለም» ብለዋል፤ ይህንንም ሐርብ አል-ኪርማኒ በመሳኢላቸው ላይ ዘግበውታል።
ሁለተኛው፦ በመስጂዶች ውስጥ ለሶላት፣ ለቂሷና ለዱዓ መሰብሰብ የተጠላ ነው። አንድ ሰው ለብቻው ቢሰግድበት ግን አይጠላም። ይህ የሻም አገር ኢማም፣ ፈቂህና ዐሊም የሆኑት የአውዛዒይ አቋም ሲሆን፤ ኢንሻአላህ (በአላህ ፈቃድ) ይበልጥ ትክክለኛውም ይኸው ነው።» …እንዲህም ብለዋል፦ «ለኢማም አህመድ የሸዕባን ወር አጋማሽ ሌሊትን በተመለከተ የተናገሩት ነገር አይታወቅም። በዚህች ሌሊት መስገድ መወደድን በተመለከተ ከርሳቸው የተገኙት ሁለት ሪዋያዎች ከሁለቱ የኢድ ሌሊቶች መስገድን አስመልክቶ ከርሳቸው ከተዘገቡት ሁለት ሪዋያዎች የሚወሰዱ ናቸው። እርሳቸው (በአንደኛው ሪዋያ) በጀመዓ መስገድን አልወደዱትም፤ ምክንያቱም ከነብዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) እና ከባልደረቦቻቸው አልተዘገበምና።» ሙስተሐብ (የተወደደ) መሆኑም (በአንድ ዘገባ) ተጠቅሷል፤ ይህም ከታቢዒዮች አንዱ የሆነው ዐብዱራሕማን ኢብኑ የዚድ ኢብኑል አስወድ ይህንኑ በመፈፀሙ ነው። ልክ እንደዚሁ የ(ሻዕባን) አጋማሽ ሌሊት ስግደትን በተመለከተ ከነቢዩ ﷺ ሆነ ከባልደረቦቻቸው ምንም የተረጋገጠ ነገር የለም። ከሻም አገር ታላላቅ የፊቅህ ሊቃውንት ከሆኑት ታቢዒዮች መካከል ግን መፈፀሙ ተረጋግጧል።»
ከሐፊዝ ኢብኑ ረጀብ (አላህ ይዘንላቸው) ንግግር የተወሰደው ዋና ሀሳብ፣ በሸዕባን አጋማሽ ሌሊት ላይ ከነብዩም ﷺ ሆነ ከሶሐቦቻቸው (አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው) የተረጋገጠ ምንም ነገር እንደሌለ በግልጽ የሚናገር መሆኑ ነው።
አል-አውዛዒይ -አላህ ይዘንላቸውና- በግል መስገድ የተወደደ መሆኑን መምረጣቸው እና ሓፊዝ ኢብኑ ረጀብም ይህንን አቋም መምረጣቸው እንግዳና ደካማ ነው። ምክንያቱም በሸሪዐዊ ማስረጃዎች የተደነገገ መሆኑ ያልተረጋገጠን ማንኛውንም ነገር አንድ ሙስሊም በአላህ ዲን ውስጥ ሊፈጥረው አይፈቀድለትምና፤ በግልም ሆነ በጀመዓ፣ በስውርም ሆነ በይፋ ቢፈጽመው የነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ንግግር ይህን ሁሉ የሚያጠቃልል በመሆኑ ነው፦
«مَنْ عَمِلَ عَمَلًا لَيْسَ عَلَيهِ أَمْرُنَا؛ فَهُوَ رَدٌّ».
"በርሱ ላይ የኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ነገር የሰራ ሰዉ ስራው ወደርሱ ተመላሽ ነዉ።" ይህ ሐዲሥ እና ሌሎችም ቢድዐን የሚያወግዙና ከእርሷ የሚያስጠነቅቁ ማስረጃዎች ይህን ይጠቁማሉ።
አልኢማም አቡ በክር አጥ-ጦርጡሺይ ـ አላህ ይዘንላቸውና ـ «አል-ሐዋዲስ ወል-ቢደዕ» በተሰኘው ኪታባቸው እንዲህ ብለዋል፡-
«ኢብኑ ወዳሕ ከዘይድ ኢብኑ አስለም እንደዘገቡት እንዲህ ብለዋል፦ ከመሻኢኾቻችንም ሆነ ከፉቀሃዎቻችን ለሸዕባን አጋማሽ ትኩረት ሲሰጡ፣ የመክሑልንም ሐዲስ ሲመለከቱ፣ እንዲሁም ከሌሎች (ሌሊቶች) የተለየ ብልጫ እንዳላት ሲያምኑ አንድንም አላገኘንም ነበር።»
ለኢብኑ አቢ ሙለይካህም ዚያድ አን-ኑመይሪ እንዲህ እንደሚል ተነገራቸው፦ «የሻዕባን አጋማሽን ሌሊት ምንዳ እንደ ለይለቱል ቀድር ምንዳ ነው» እንዲህም አሉ: «እንዲህ ሲል ስሰማው በእጄ ዱላ ቢኖር ኖሮ እመታው ነበር።» ዚያድ የተባለውም ተራኪ ነበር፣ ማስተላለፍ የተፈለገው መልዕክት እዚህ ላይ አበቃ።
አል-ዐላማህ አሽ-ሸውካኒ ـ አላህ ይዘንላቸውና ـ «አል-ፈዋኢዱ-ል-መጅሙዓህ» በተሰኘው ኪታባቸው እንዲህ ብለዋል፡-
«“አንተ ዐልይ ሆይ፥ በሸዕባን ወር አጋማሽ ሌሊት በእያንዳንዱ ረከዓ ላይ ፋቲሐቱል ኪታብን እና ‘ቁል ሁወላሁ አሐድ’ን አስር ጊዜ እየቀራ መቶ ረከዓዎችን ለሰገደ ሰው አላህ ጉዳዩን ሁሉ ይፈጽምለታል።” እስከመጨረሻው » የሚለው ሐዲሥ የተፈበረከ ነው፤ በቃላቶቹ ውስጥ ፈፃሚው ስለሚያገኘው ምንዳ በግልፅ የተጠቀሰው ነገር የማገናዘብ ችሎታ ያለው ሰው በመፈብረኩ ላይ እንዳይጠራጠር ያደርገዋል፤ ዘጋቢዎቹም የማይታወቁ ናቸው፤ እንዲሁም ሁሉም የተፈበረኩና ዘጋቢዎቻቸውም የማይታወቁ በሆኑ በሁለተኛና በሶስተኛ ሰነዶች ተዘግቧል። በ«ሙኽተሶር» ላይ እንዲህ ብለዋል፡- «የሻዕባን አጋማሽ ሶላት ሀዲስ መሰረተ-ቢስ ነው።» ኢብኑ ሒባን ከዐሊይ በዘገቡትም «የሻዕባን አጋማሽ ሌሊት ሲሆን ሌሊቱን በሶላት አሳልፉ፤ ቀኑንም ጹሙ» የሚለው ሀዲስ ደካማ ነው። በ«አል-ለኣሊእ» ላይ እንዲህ ብለዋል፦ «"በሸዕባን አጋማሽ መቶ ረከዓዎችን በኢኽላስ አስር ጊዜያት (የመስገድ)" ሐዲሥ፣ ትሩፋቱ በሰፊው ቢተረክም በደይለሚይ እና በሌሎችም የተዘገበ ቢሆንም የተቀጠፈ (መውዱዕ) ነው። በሶስቱም የዘገባ ሰንሰለቶች ውስጥ ያሉ አብዛኞቹ ዘጋቢዎቹም ተለይተው የማይታወቁ (መጅሁሎች) እና ደካሞች (ዶዒፎች) ናቸው።» እንዲህም ብለዋል: «አስራ ሁለት ረከዓ በኢኽላስ ሰላሳ ጊዜ» የሚለው ሐዲሥ የተቀጠፈ ነው፤ «አስራ አራት ረከዓ» የሚለውም የተቀጠፈ ነው።
በዚህ ሐዲስ ከፊቅህ ሊቃውንት የተወሰኑት፤ እንደ (ኢሕያ) ባለቤትና ሌሎችም እንዲሁም ከሙፈሲሮችም ጭምር ተሸውደዋል፤ የዚህች ሌሊት ሶላት — ማለቴም የሻዕባን አጋማሽ ሌሊት — በተለያዩ መንገዶች የተዘገበ ሲሆን ሁሉም ውድቅና የተቀጠፉ ናቸው። ይህም ቲርሚዚ ዓኢሻ (አላህ ስራዋን ይውደድላትና) ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ በቂዕ መሄዳቸውን፣ ጌታ በወሩ አጋማሽ ሌሊት ወደ ቅርቢቱ ሰማይ መውረዱን እና ከከልብ ነገድ በግ ፀጉር ብዛት ለሚበልጡ ሰዎች እንደሚምር ከዘገበችው ሐዲሥ ጋር አይቃረንም፤ ምክንያቱም እያወራን ያለነው በዚህች ሌሊት ላይ ስለተቀጠፈችው ሶላት ብቻ ነውና። «ይህ የዓኢሻ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- ሐዲሥ ድክመትና መቆራረጥ አለበት። ልክ እንደዚሁም ቀደም ብሎ የሌሊት ሶላቷን አስመልክቶ የተጠቀሰው የዓሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ሐዲሥ እኛ እንደጠቀስነው በራሱ ላይ ድክመት ቢኖርበትም እንኳ ይህቺ ሶላት የተቀጠፈች መሆኗን አይቃረንም።» ከንግግሩ የተፈለገው እዚህ ላይ ያበቃል።
አል-ሐፊዝ አል-ዒራቂይ እንዲህ ብለዋል: «የኒስፍ (የወሩ አጋማሽ) ሌሊት ሶላት ሐዲሥ በአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ላይ የተቀጠፈና ውሸት ነው።» ኢማም ነወዊይ (አልመጅሙዕ) በተሰኘው መጽሐፋቸው እንዲህ ብለዋል፦ “'ሶላተ አር-ረጋኢብ' በመባል የምትታወቀውና በረጀብ ወር የመጀመሪያ ጁሙዓ ሌሊት በመግሪብና ዒሻ መካከል የምትሰገድ አስራ ሁለት ረከዓ ሶላት እንዲሁም የሸዕባን ወር አጋማሽ ሌሊት የምትሰገደው የመቶ ረከዓ ሶላት፤ እነዚህ ሁለቱ ሶላቶች የተወገዙ ቢድዓዎች ናቸው። (ቁቱል ቁሉብ) እና (ኢሕያኡ ዑሉሚዲን) በተባሉ መጽሐፍት ውስጥ በመጠቀሳቸውና በውስጣቸውም በተወሳው ሐዲሥ ማንም አይሸወድ፤ ይህ ሁሉ ውድቅ ነውና። አንዳንድ ሊቃውንት ፍርዱ ስለተመሳሰለባቸው ተወዳጅ መሆኑን የሚገልጹ ጽሑፎችን በማዘጋጀታቸውም ማንም አይሸወድ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ተሳስተዋልና።”
ሸይኽ ኢማም አቡ ሙሐመድ ዐብዱረሕማን ኢብኑ ኢስማዒል አል-መቅዲሲ የሁለቱን ጉዳዮች ውድቅነት በማስመልከት እጅግ ጠቃሚ የሆነ ኪታብ አዘጋጅተዋል፤ በኪታባቸውም ላይ እጅግ አሳምረውበታል። በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ የሊቃውንት ንግግር በጣም ብዙ ነው። በጉዳዩ ላይ ያገኘናቸውን ንግግሮች ሁሉ ለማስተላለፍ ብንሞክር ኖሮ ሐተታው ይረዝምብን ነበር። ምናልባት እኛ የጠቀስነው ሐቅን ለሚፈልግ ሰው በቂና አሳማኝ ይሆናል።
ከዚህ ቀደም ከቀረቡት የቁርኣን አንቀፆች፣ ሐዲሶች እና የእውቀት ባለቤቶች ንግግሮች በመነሳት እውነትን ለሚፈልግ ሰው የሸዕባንን ወር አጋማሽ ሌሊት በሶላት ወይም በሌላ ነገር መለየት፣ እንዲሁም ቀኑን ለፆም መነጠል፤ በአብዛኛዎቹ የእውቀት ባለቤቶች ዘንድ የተወገዘ ፈጠራ (ቢድዓ) መሆኑ ግልፅ ይሆንለታል። በጠራው ሸሪዓ ላይ ምንም መሰረት የለውም፤ ይልቁንም ከሰሃባዎች (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) ዘመን በኋላ በእስልምና ውስጥ የተከሰተ ነው። በዚህም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ላይ እውነትን ለሚፈልግ ሰው ክብሩ ከፍ ያለው የአላህ ቃል በቂው ነው፡
﴿...ٱلۡيَوۡمَ أَكۡمَلۡتُ لَكُمۡ دِينَكُمۡ...﴾
{…ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ…} [አል‐ማኢዳህ: 3] በተመሳሳይ ሃሳብ የመጡ የቁርአን አንቀፆችና፣ ነቢዩም ﷺ እንዲህ ማለታቸው፦
«مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ مِنْهُ فَهُوَ رَدٌّ».
"በዚህ ጉዳያችን ከእርሱ ያልሆነን አዲስ ነገር ያመጣ ይዞት የመጣው አዲስ ፈሊጥ ውድቅ ነው።" ይህንኑ መልዕክት ይዘው ከመጡ ሐዲሶችም መካከል።
በሶሒሕ ሙስሊምም አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«لَا تَخُصُّوا لَيْلَةَ الْجُمُعَةِ بِقِيَامٍ مِنْ بَيْنِ اللَّيَالِي، وَلَا تَخُصُّوا يَوْمَهَا بِالصِّيَامِ مِنْ بَيْنِ الْأَيَّامِ، إِلَّا أَنْ يَكُونَ فِي صَوْمٍ يَصُومُهُ أَحَدُكُمْ».
"ከሌሊቶች መካከል የጁሙዓን ሌሊት በቂያም አትለዩ፤ ከቀናትም መካከል ቀኑን በጾም አትልዩት፤ አንዳችሁ ከሚፆመው ፆም ጋር የሚገጥም ቢሆን እንጂ።" ከሌሊቶች መካከል አንዷን በሆነ የዒባዳ አይነት መለየት የተፈቀደ ቢሆን ኖሮ፣ የጁሙዓ ሌሊት ከሌሎች የበለጠ ተገቢ ትሆን ነበር፤ ምክንያቱም ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በተገኙ ትክክለኛ ሐዲሶች በግልፅ እንደተነገረው ቀኗ ፀሐይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን ነውና። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንዷን ሌሊት ከሌሎች ሌሊቶች መካከል ለይቶ በቂያም ልዩ ከማድረግ ማስጠንቀቃቸው ይህ የሚያመላክተው ከእርሷ ውጪ ያሉ ሌሎች ሌሊቶችም በበለጠ መልኩ ልዩ ስለመደረጋቸው የሚያመላክት ትክክለኛ ማስረጃ ካልተገኘ በቀር በአንዳችም የአምልኮ አይነት ልዩ ማድረግ እንደማይፈቀድ ነው።
ለይለተል ቀድርና የረመዷን ሌሊቶች በሶላት ሊቆሙባቸውና በዒባዳ ሊተጋባቸው የተደነገገ በመሆኑ ዙሪያ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በዚህ ላይ አሳስበዋል። ኡማውንም እንዲቆሟቸው አነሳስተዋል። ይህንንም በራሳቸው ፈፅመውታል። በሁለቱ ሶሒሕ መዛግብት ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንደተዘገበው እንዲህ ብለዋል፦
«مَنْ قَامَ رَمَضَانَ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا، غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ، وَمَنْ قَامَ لَيْلَةَ الْقَدْرِ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا، غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ».
"ረመዷንን አምኖበትና (ምንዳ እንደሚያገኝበት) አስቦ (በሶላት) የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል። ለይለቱል ቀደርንም አምኖበትና (ምንዳ እንደሚያገኝበት) አስቦ (በሶላት) የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።" የሸዕባን ወር አጋማሽ ሌሊት፣ ወይም የረጀብ ወር የመጀመሪያው ጁሙዓ ሌሊት ወይም የኢስራእ እና የሚዕራጅ ሌሊት በበዓል ወይም በሆነ የአምልኮ አይነት መለየቱ የተደነገገ ቢሆን ኖሮ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ህዝባቸውን ወደርሱ ባመላከቱ ወይም እራሳቸው በሰሩት ነበር። ከዚህ አይነቱ አንዱም ነገር ተከስቶ ቢሆን ኖሮ ሶሓቦች (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) ለህዝቡ ባስተላለፉት ነበር፤ ከነርሱም አይደብቁትም ነበር። እነርሱ ከነቢያት (ዐለይሂሙ ሰላም) በኋላ ከሰዎች ሁሉ በላጭና ለሰዎች ሁሉ በበለጠ መካሪዎች ናቸውና። አላህም ከአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባልደረቦች ስራቸውን ይውደድላቸው፤ እነሱንም ደስ ያሰኛቸው።
ከዚህ ቀደም ከሊቃውንት ንግግር እንደታወቀው የረጀብ ወር የመጀመሪያ ጁሙዓ ሌሊትንም ሆነ የሸዕባን ወር አጋማሽ ሌሊትን ብልጫ አስመልክቶ ከነቢዩም ﷺ ሆነ ከሶሓቦቻቸው ረዲየላሁ ዐንሁም ምንም የጸደቀ ነገር የለም። በመሆኑም በነዚህ በሁለቱ (ሌሊቶች) ማክበር በእስልምና ውስጥ አዲስ መጤ ፈጠራ መሆኑ ይታወቃል። በተመሳሳይም በሆነ አምልኮ ነጥሎ መለየት የተወገዘ ፈጠራ (ቢድዓ) ነው። እንደዚሁም አንዳንድ ሰዎች የኢስራእና የሚዕራጅ ሌሊት ናት ብለው የሚያምኗት የረጀብ ወር ሃያ ሰባተኛዋ ሌሊት ቀደም ሲል በተጠቀሱት ማስረጃዎች መሰረት በምንም አይነት አምልኮ መለየትም ሆነ እርሷን ማክበር አይፈቀድም። ይህ እኮ ሌሊቷ የምትታወቅ ናት ካልን ነው፤ ታዲያ ከዑለማዎች ንግግሮች ትክክለኛው አቋም ሌሊቷ የማትታወቅ መሆኗ ሆኖ ሳለ እንዴት ሊሆን ይችላል? እርሷ የረጀብ ወር ሃያ ሰባተኛዋ ሌሊት ናት የሚለው ንግግር በትክክለኛ ሐዲሶች መሠረት የሌለው ውድቅ የሆነ አባባል ነው። እንዲህ ያለውም ሰው መልካም ተናግሯል፦
ከጉዳዮች ሁሉ በላጩ በቅኑ መንገድ ላይ የነበሩት የቀደሙት ሲሆኑ ከጉዳዮች ሁሉ ክፉው ደግሞ አዲስ መጤ ፈጠራዎች ናቸው።
አላህን እኛንም ሆነ መላ ሙስሊሞችን ሱናን አጥብቆ መያዝንና በእርሷ ላይ መፅናትን፣ ከሚቃረናት ነገርም መጠንቀቅን እንዲገጥመን እንጠይቀዋለን። እርሱ ቸርና ለጋስ ነውና።
የአላህ ሰላትና ሰላም በባሪያውና መልዕክተኛው በነብያችን ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ሁሉ ላይ ይስፈን።
***
بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ
ስምንተኛው መልዕክት፡
በውሸት ስለተነገረው ኑዛዜ የተሰጠ አስፈላጊ ማሳሰቢያ
ለሐረመ ነበዊ አሸሪፍ አገልጋይ ሸይኽ አሕመድ
ከዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ ይህንን መልዕክት ለሚያገኘው ሙስሊም ባጠቃላይ የተላለፈ መልዕክት፦ አላህ በእስልምና ይጠብቃቸው፤ እኛንም እነርሱንም ከመሃይማንና ከብኩኖች (ከመናኛ) የቅጥፈት ክፋት ይጠብቀን። አሚን።
የአላህ ሰላም እዝነትና በረከቱ በናንተ ላይ ይስፈን
ከዚህ በመቀጠል፡ በተከበረው የነብዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሐረም አገልጋይ በሆኑት በሸይኽ አሕመድ ስም የተላለፈችንና «ይህች ከመዲነቱል ሙነወራ፤ ከተከበረው የነብዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሐረም አገልጋይ ከሸይኽ አሕመድ የተላለፈች ምክር ናት» የሚል ርዕስ ያላትን አንድ መልእክት ተመልክቻለሁ፤ በውስጧም እንዲህ ብሏል፡-
«የጁሙዓን ሌሊት ሳልተኛ ክቡር ቁርኣንን እቀራ ነበር። የአላህን መልካም ስሞችም ከቀራሁ በኋላ ለመተኛት ተዘጋጀሁ። በዚያም አንፀባራቂ ገፅታ ባለቤት የሆኑትን፣ የቁርኣን አንቀፆችንና የተከበሩ ህግጋትን ይዘው የመጡትን፣ ለዓለማት እዝነት የሆኑትን መሪያችንን ሙሐመድን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በህልሜ አየኋቸው። እንዲህም አሉኝ፦ ‹ሸይኽ አሕመድ ሆይ!› እኔም አልኩኝ፦ ‹አቤት! የአላህ መልክተኛ ሆይ! የፍጡራን ሁሉ በላጭ ሆይ!›» እንዲህም አሉኝ፦ "በሰዎች አስቀያሚ ድርጊት አፍሬያለሁ፤ ጌታዬንም ሆነ መላኢካዎችን መገናኘት አልቻልኩም፤ ምክንያቱም ከጁምዓ እስከ ጁምዓ መቶ ስልሳ ሺህ ሰዎች በእስልምና ዲን ላይ ሳይሆኑ ሞተዋል።" ከዚያም ሰዎች ከወደቁባቸው ኃጢኣቶች መካከል ከፊሉን ጠቀሰ፤ ከዚያም «ይህች ምክር አሸናፊና ሃያል ከሆነው (ጌታ) ዘንድ ለነርሱ የተደረገች እዝነት ናት።» አሉ፡፡ ከዚያም የተወሰኑ የትንሳኤ ምልክቶችን አውስተው እንዲህ አሉ፦ «አንተ ሸይኽ አሕመድ ሆይ ይህችን ኑዛዜ ንገራቸው፤ ምክንያቱም እሷ ከለውሐል መሕፉዝ በቀደር ብዕር የተወሰደች ናትና፤ የሚጽፋትና ከሀገር ወደ ሀገር፣ እንዲሁም ከቦታ ወደ ቦታ የሚልካት ሰው በጀነት ውስጥ ቤተ-መንግስት ይገነባለታል፤ ያልጻፋትና ያልላካት ሰው ደግሞ የትንሳኤው ቀን ሸፋዓዬ በርሱ ላይ እርም ትሆንበታለች።» የጻፋትም ሰው ድሃ ቢሆን አላህ ባለፀጋ ያደርገዋል፤ እዳ ያለበትም ቢሆን አላህ እዳውን ይከፍልለታል፤ ወይም ወንጀል ያለበት ቢሆን በዚህች ኑዛዜ በረከት አላህ ለእርሱም ለወላጆቹም ይምርላቸዋል። ከአላህ ባሮችም ውስጥ ያልጻፋት፤ ፊቱ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ይጠቁራል። እንዲህም አለ፡ «በታላቁ አላህ ሶስት ጊዜ እምላለሁ፤ ይህ እውነት ነው። እኔ ውሸታም ከሆንኩ ከእስልምና ውጪ ሆኜ ከዱንያ ልውጣ። በርሷ ያመነ ከእሳት ቅጣት ይድናል፤ በርሷ ያስተባበለ ደግሞ ከፍሯል።»
ይህ በአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ የተቀጠፈው የኑዛዜው ማጠቃለያ ነው። ይህንኑ የተቀጠፈ ኑዛዜ ከበርካታ ዓመታት ወዲህ ብዙ ጊዜ ሰምተነዋል፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ በሰዎች መካከል እየተሰራጨና በብዙሃኑ ተራው ህዝብም ዘንድ እየተስፋፋ ይገኛል። በአገላለጾቹም ላይ ልዩነቶች አሉት። ይህም ቀጣፊ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በህልሙ እንዳያቸውና ይህችንም አደራ እንደሰጡት ይናገራል። አንባቢ ሆይ ላንተ በጠቀስናት በዚህች የመጨረሻዋ ጽሑፍ ላይም፣ ቀጣፊው ለመተኛት በተዘጋጀ ጊዜ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዳያቸው ይሞግታል፤ ይህ ማለት ደግሞ፡ በውናቸው አይቷቸዋል ማለት ነው።
ይህ ቀጣፊ በዚህ ኑዛዜው ውስጥ እጅግ ግልጽ ውሸት እና ፍጹም ከንቱ የሆኑ ብዙ ነገሮችን ሞግቷል፤ ኢንሻ አላህ በዚሁ ጽሑፍ ውስጥ በቅርቡ እጠቁምሃለሁ። በእርግጥም ባለፉት ዓመታት ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አስጠንቅቄያለሁ፤ ለሰዎችም እጅግ ግልጽ ውሸት እና ፍጹም ከንቱ ነገር መሆኑን አብራርቻለሁ። ይህን የመጨረሻውን ህትመት ባየሁ ጊዜ፤ ከንቱነቱ ግልጽ በመሆኑና ቀጣፊው በውሸት ላይ ያለው ከፍተኛ ድፍረት የተነሳ ስለ ጉዳዩ ከመጻፍ አመንትቼ ነበር። ይህ ከንቱ ነገር ትንሽ እንኳን ማስተዋል ወይም ጤናማ ተፈጥሮ ባለው ሰው ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል ብዬ ፈጽሞ አላሰብኩም ነበር። ነገር ግን ብዙ ወንድሞች በብዙ ሰዎች ዘንድ እንደተሰራጨች፣ በመካከላቸውም እንደሚቀባበሏትና ከፊሎቻቸውም እውነት መሆኗን እንዳመኑ ስለነገሩኝ፣ ሀሰትነቷንና በአላህ መልዕክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን- ላይ የተቀጠፈች መሆኗን በመግለፅ ማንም እንዳይታለልባት በእኔ አምሳያዎች ላይ መፃፍ እንደሚገባ አየሁ። ከእውቀትና ከእምነት ባለቤቶች፣ ወይም ከንጹሕ ተፈጥሮና ከትክክለኛ አእምሮ ባለቤቶች የሆነ ሰው እርሷን ቢያስተነትናት፤ በብዙ መንገዶች ውሸትና ቅጥፈት መሆኗን ያውቃል፡፡
በእርግጥም ይህች ቅጥፈት የምትጠጋባቸውን የሸኽ አሕመድን አንዳንድ ዘመዶች ስለዚች ኑዛዜ ጠይቄአቸው ነበር፤ የመለሱልኝም መልስ፦ ኑዛዜዋ በሸኽ አሕመድ ላይ የተቀጠፈች መሆኗንና እርሳቸውም በፍፁም አለማለታቸውን ነው። እናም ጽሁፉ ላይ የተጠቀሱት ሼኽ አሕመድ ከሞቱ ቆይተዋል። የተጠቀሱት ሼኽ አሕመድ ወይም ከእርሳቸው የበለጠ ትልቅ ሰው ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በህልምም ሆነ በእውን እንዳያቸውና ይህንንም አደራ እንደሰጡት ቢሞግት እንኳ በእርግጠኝነት ውሸታም መሆኑን ወይም ይህን ያለው አካል መልእክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሳይሆን ሰይጣን መሆኑን እናውቅ ነበር፤ ይህም ለበርካታ ምክንያቶች ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ፡
በመጀመሪያ: መልእክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ከሞቱ በኋላ በእውን አይታዩም። ከሱፊያ ጃሂሎች ውስጥ ነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) በእውን እንደሚያይ፣ ወይም በመውሊድ ላይ እንደሚገኙ፣ ወይም ይህን የመሳሰለውን ነገር የሚሞግት ሰው፤ በእርግጥም እጅግ አስቀያሚ የሆነን ስህተት ተሳስቷል፤ በከፍተኛ ሁኔታም ነገሩ ተመሳስሎበታል፤ በታላቅ ስህተትም ውስጥ ወድቋል፤ ቁርአንን፣ ሱናንና የእውቀት ባለቤቶችን ስምምነትም ተፃርሯል። ምክንያቱም ሙታን ከቀብራቸው የሚወጡት በትንሳኤ ቀን እንጂ በዱንያ አይደለምና። ከዚህ በተቃራኒ የተናገረ ሰው፤ እርሱ ደጋግ ቀደምቶች ያወቁትንና የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ሶሓቦችና እነርሱን በበጎ የተከተሏቸው የተጓዙበትን እውነት ያላወቀ ግልጽ ውሸታም፣ ወይም የተሳሳተና ነገሩ የተምታታበት ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿ثُمَّ إِنَّكُم بَعۡدَ ذَٰلِكَ لَمَيِّتُونَ15 ثُمَّ إِنَّكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ تُبْعَثُونَ16﴾
{ ከዚያም እናንተ ከዚህ በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ:: ከዚያም እናንተ በትንሳኤ ዕለት ትቀሰቀሳላችሁ::}
«أَنَا أَوَّلُ مَنْ تَنْشَقُّ عَنْهُ الْأَرْضُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، وَأَنَا أَوَّلُ شَافِعٍ وَأَوَّلُ مُشَفَّعٍ».
«እኔ የትንሳኤ ቀን ምድር መጀመሪያ የምትሰነጠቅለት ነኝ፤ የመጀመሪያው አማላጅም የመጀመሪያውም ምልጃ ተቀባይ የሆነ ነኝ።» ይህንን መልዕክት ያዘሉ የቁርኣን አንቀጾችና ሐዲሦች በርካታ ናቸው።
ሁለተኛው: መልክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በህይወታቸውም ሆነ በሞታቸው ከሐቅ ውጭ የሆነን ነገር አይናገሩም፤ ይህ ኑዛዜ ሸሪዐቸውን በግልፅ ይፃረራል፤ ይህም -በኋላ ላይ እንደሚብራራው- በብዙ መልኩ ነው። እርሳቸው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በህልም ይታያሉ። በህልሙ በተከበረው ቁመናቸው ያያቸው ሰው በእርግጥም እርሳቸውን አይቷል፤ ምክንያቱም ሸይጧን በእርሳቸው ቁመና ሊመሰል አይችልምና፤ ትክክለኛ በሆነው በተከበረው ሐዲስ እንደመጣው። ነገር ግን ዋናው ጉዳይ ያለው ህልም ባየው ሰው ኢማን፣ እውነተኝነት፣ ፍትሐዊነት፣ ጥንቁቅነት፣ ሃይማኖተኝነትና ታማኝነት ላይ ነው፤ እናም ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያያቸው በእውነተኛ ቁመናቸው ነው ወይስ በሌላ? የሚለው ነው።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሕይወት ዘመናቸው የተናገሩት ሐዲሥ ቢመጣ እንኳን፤ ታማኝ፣ ፍትሐዊና ጠንካራ የማስታወስ ችሎታ ባላቸው ዘጋቢዎች መንገድ ካልሆነ ተቀባይነት አይኖረውም፤ ማስረጃም አይሆንም። ወይም ታማኝና ጠንካራ የማስታወስ ችሎታ ባላቸው ዘጋቢዎች መንገድ ቢመጣ ነገር ግን ከእነርሱ የበለጠ ጠንካራ የማስታወስ ችሎታ ያላቸውንና ይበልጥ ታማኝ የሆኑትን ዘገባ ሁለቱን ማስታረቅ በማይቻልበት ሁኔታ የሚፃረር ከሆነ፤ ይህ መስፈርቶቹን ባሟላ ሁኔታ የሚቻል ከሆነ፤ አንደኛው ሥራ ላይ የማይውል ‘መንሱኽ’ (የተሻረ) ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ሥራ ላይ የሚውል ‘ናሲኽ’ (ሻሪ) ይሆናል። ማስታረቅም ሆነ መሻር የማይቻል ከሆነ ደግሞ፤ የማስታወስ ችሎታው አነስተኛና ፍትሐዊነቱም ዝቅተኛ የሆነውን ዘጋቢ ዘገባ ውድቅ ማድረግ ግዴታ ይሆናል። ዘገባውም ሥራ ላይ የማይውል “ሻዝ” (ብቸኛና ደካማ ዘገባ) ተብሎ ይፈረድበታል።
ታዲያ ከአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስተላለፈው ባለቤቱም ሆነ ታማኝነቱና ፍትሃዊነቱ የማይታወቅ ኑዛዜ እንዴት [ተቀባይነት ይኖረዋል]! ይህ ኑዛዜ በዚህ ሁኔታው በውስጡ ሸሪዓን የሚፃረር ነገር ባይኖርበትም እንኳ ሊጣልና ትኩረት ሊነፈገው የተገባ ነው። ታዲያ ኑዛዜው ሐሰት መሆኑን የሚያመላክቱ በርካታ ጉዳዮችን ያካተተ፣ በአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ የተቀጠፈ እና አላህ ያልፈቀደውን ዲን የሚደነግግ ከሆነማ እንዴት ሊሆን ነው?
ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
«مَنْ قَالَ عَلَيَّ مَا لَمْ أَقُلْ؛ فَلْيَتَـبَوَّأْ مَقْعَدَهُ مِنَ النَّارِ».
"በኔ ላይ ያላልኩትን የተናገረ ሰው ከእሳት የሆነ መቀመጫውን ያዘጋጅ።" በእርግጥ ይህንን ኑዛዜ በአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ የቀጠፈው ሰው እርሳቸው ያላሉትን ተናግሯል፤ ግልፅና አደገኛ የሆነ ውሸትንም በርሳቸው ላይ ዋሽቷል። ወደ ተውበት (ንሰሀ) ለመመለስ ካልተጣደፈና ይህ ኑዛዜ በአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ የተቀጠፈ ውሸት መሆኑን ለሰዎች ይፋ ካላደረገ ለዚህ ታላቅ ዛቻ የተገባ ይሆናል። ምክንያቱም በሰዎች መካከል ባጢልን (ውድቅን) ያሰራጨና ወደ ዲንም ያስጠጋ ሰው፤ ሰዎች ከውሸቱ መመለሱንና ራሱንም ማስተባበሉን እንዲያውቁ በይፋ በማወጅና ግልፅ በማድረግ ካልሆነ በስተቀር ከዚህ ወንጀሉ ተውበቱ ተቀባይነት አይኖረውም። ክብሩና ጥራቱ የላቀው አላህ እንዲህ ብሏልና፦
﴿إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكۡتُمُونَ مَآ أَنزَلۡنَا مِنَ ٱلۡبَيِّنَٰتِ وَٱلۡهُدَىٰ مِنۢ بَعۡدِ مَا بَيَّنَّٰهُ لِلنَّاسِ فِي ٱلۡكِتَٰبِ أُوْلَٰٓئِكَ يَلۡعَنُهُمُ ٱللَّهُ وَيَلۡعَنُهُمُ ٱللَّٰعِنُونَ159 إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُواْ وَأَصۡلَحُواْ وَبَيَّنُواْ فَأُوْلَٰٓئِكَ أَتُوبُ عَلَيۡهِمۡ وَأَنَا ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ160﴾
{ እነዚያ ከአንቀጾችና ከቅን መምሪያ ያወረድነውን ለሰዎች በመጽሐፉ ከገለጽነው በኋላ የሚደብቁትን አላህ ይረግማቸዋል:: ረጋሚዎችም ሁሉ ይረግሟቸዋል::
እነዚያ የተጸጸቱ፤ (ያበላሹትን) ያስተካከሉና (የደበቁትንም) የገለጹ ሲቀሩ:: የእነርሱን ጸጸትንማ እቀበላለሁ:: እኔም ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነኝ::} [አል-በቀራህ 159-160] የላቀው አላህ በዚህች በተከበረች አንቀጽ ላይ ከእውነት አንዳች ነገር የደበቀ ሰው፤ ካስተካከለና ግልፅ ካደረገ በኋላ ካልሆነ በቀር ንስሃው ትክክል እንደማይሆን አብራርቷል። የላቀው አላህ ለባሮቹ ሃይማኖትን አሟልቷል፤ መልዕክተኛውን ሙሐመድን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) በመላክና ወደ እርሳቸውም ካወረደው የተሟላ ሸሪዓ ጋር ፀጋውንም በነርሱ ላይ ሙሉ አድርጓል። እርሳቸውንም ከማሟላትና ግልፅ ከማድረግ በኋላ እንጂ ወደ ራሱ አልወሰዳቸውም፤ የላቀው እንዲህ እንዳለው፦
﴿...ٱلۡيَوۡمَ أَكۡمَلۡتُ لَكُمۡ دِينَكُمۡ وَأَتۡمَمۡتُ عَلَيۡكُمۡ نِعۡمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلۡإِسۡلَٰمَ دِينٗا...﴾
{…ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ፤ ጸጋየንም በእናንተ ላይ ፈጸምኩ፤ ለእናንተም በሃይማኖትነት ኢስላምን ወደድኩላችሁ።…} [አል‐ማኢዳህ: 3]
የዚህ ወሲያ ቀጣፊ በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን የመጣ ሲሆን፣ ድንጋጌውን ለተቀበለ ጀነት እንዲገባና ላልተቀበለው ደግሞ ከጀነት ተከልክሎ እሳት እንዲገባ የሚያደርግ አዲስ ዲን በሰዎች ላይ ሊያምታታባቸው ይፈልጋል። ይህችን የቀጠፋትን ኑዛዜ ከቁርኣን የበለጠችና የላቀች ሊያደርጋት ይፈልጋል። በውስጧም እንዲህ ሲል ቀጥፏል፦ «ይህችን የጻፈና ከአገር ወደ አገር ወይም ከቦታ ወደ ቦታ የላካት ሰው፤ በጀነት ቤተ መንግስት ይገነባለታል። ያልጻፋትና ያልላካት ደግሞ የቂያማ ቀን የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ምልጃ ይከለከላል።» ይህ ከውሸቶች ሁሉ እጅግ የከፋው ሲሆን የዚህንም ኑዛዜ ውሸትነት፣ የቀጣፊውንም የሐፍረት ማጣትና በውሸት ላይ ያለውን ታላቅ ድፍረት ከሚያሳዩ ግልጽ ማስረጃዎች መካከል አንዱ ነው። ምክንያቱም የተከበረውን ቁርኣን ጽፎ ከአገር ወደ አገር ወይም ከቦታ ወደ ቦታ የላከ ሰው እንኳ በተከበረው ቁርኣን ካልሠራበት ይህን ትሩፋት አያገኝም። ታዲያ ይህን ቅጥፈት ለጻፈውና ከአገር ወደ አገር ላስተላለፈው እንዴት ሊገኝለት ይችላል? ቁርኣንን ያልጻፈና ከአገር ወደ አገር ያልላከ ሰው በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያመነና ሸሪዓቸውን የሚከተል ከሆነ የርሳቸውን ሸፋዓ አይከለከልም። በዚህ ኑዛዜ ውስጥ ያለችው ይህቺ አንዲት ቅጥፈት ብቻዋን፣ የኑዛዜውን ውድቅነት፣ የአሰራጩን ውሸታምነት፣ ድፍረቱን፣ ጅልነቱንና መልእክተኛው ﷺ ይዘውት ከመጡት ቅን መንገድ ያለውን ርቀት ለማመላከት በቂ ናት።
በዚህ ኑዛዜ ውስጥ — ከተጠቀሰው በተጨማሪ — ውድቅና ውሸት መሆኑን የሚያመለክቱ ሌሎች ጉዳዮች ይገኙበታል። ቀጣፊው ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ ሺህ ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ ቢምልም፣ እውነተኛ መሆኑን ለማሳየት በራሱ ላይ ታላቁን ቅጣትና የከፋውን መከራ ቢለምንም (ቀጣፊው) እውነተኛ ሊሆን አይችልም፤ ኑዛዜውም ትክክል አይሆንም። ይልቁንም በአላህም ከዚያም በድጋሚ በአላህም (እምላለሁ)፤ ከባጢሎች ሁሉ እጅግ የከፋና አስቀያሚ ነው። እኛም አላህን (ሱብሓነሁ) እና ከእኛ ጋር የተገኙትን መላኢኮች እናስመሰክራለን! ይህ ጽሑፍ ከደረሳቸው ሙስሊሞች ዘንድ የምንመሰክረው ምስክርነት — እርሱም ጌታችን ጀለ ጀላሉሁ ፊት የምንቀርብበት ነው — ይህ ኑዛዜ በአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ የተፈጠረ ውሸትና ቅጥፈት መሆኑን ነው። ይህን የቀጠፈውን አላህ ያዋርደው፤ የሚገባውንም ፍርዱን ይስጠው።
ከዚህ ቀደም ከተጠቀሰው በተጨማሪ የዚህችን ኑዛዜ ውሸት መሆኗንና መበላሸቷን ከተጠቀሰው ጽሑፍ የሚጠቁሙ በርካታ ነገሮች አሉ። ከነሱም መካከል፡
አንደኛው ነጥብ፡ በውስጡ የተጠቀሰው «ከጁሙዓ እስከ ጁሙዓ አንድ መቶ ስልሳ ሺህ ሰዎች ከእስልምና ውጭ በሆነ ሃይማኖት ላይ ሆነው ሞተዋል» የሚለው ንግግር ነው። ምክንያቱም ይህ የሩቅ ምስጢር እውቀት ነውና። መልዕክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ከሕልፈታቸው በኋላ ወሕይ ተቋርጦባቸዋል። እርሳቸው በህይወት እያሉ ሩቅ ምስጢርን የማያውቁ ከነበሩ ከሕልፈታቸው በኋላ እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ? ልዕልናው የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡
﴿قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمۡ عِندِي خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعۡلَمُ ٱلۡغَيۡبَ...﴾
{«የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልላችሁም:: ሩቅ ሚስጥርንም አላውቅም...» በላቸው።} [አል'አንዓም: 50] አላህ እንዲህም ብሏል:
﴿قُل لَّا يَعۡلَمُ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ ٱلۡغَيۡبَ إِلَّا ٱللَّهُ...﴾
{«በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም:: አላህ ግን ያውቀዋል...» በላቸው።} [አንነምል፡ 65] ሶሒሕ በሆነ ሐዲሥም ነቢዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል፡-
«يُذَادُ رِجَالٌ عَنْ حَوْضِي يَوْمَ القِيَامَةِ، فَأَقُولُ: يَا رَبِّ! أَصْحَابِي أَصْحَابِي، فَيُقَالُ لِي: إِنَّكَ لَا تَدْرِي مَا أَحْدَثُوا بَعْدَكَ، فَأَقُولُ كَمَا قَالَ العَبْدُ الصَّالِحُ: ﴿وَكُنتُ عَلَيۡهِمۡ شَهِيدٗا مَّا دُمۡتُ فِيهِمۡۖ فَلَمَّا تَوَفَّيۡتَنِي كُنتَ أَنتَ ٱلرَّقِيبَ عَلَيۡهِمۡۚ وَأَنتَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٌ﴾ [المائدة: 117]».
«በትንሳኤው ቀን ሰዎች ከሐውዴ ይከለከላሉ፤ እኔም፡- “ጌታዬ ሆይ! ባልደረቦቼ፤ ባልደረቦቼ” እላለሁ። ለኔም፡- “ከአንተ በኋላ ምን አዲስ ነገር እንደፈጠሩ አታውቅም” እባላለሁኝ። እኔም መልካሙ ባሪያ እንዳለው እላለሁ፡-{በውስጣቸውም እስካለሁ ድረስ በነርሱ ላይ ተጣባበቂ ነበርኩ፡፡ በተሞላኸኝም ጊዜ (ባነሳኸኝ ጊዜ) አንተ በነሱ ላይ ተጠባባቂ ነበርክ፡፡ አንተም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነህ።} [አል-ማኢዳህ፡ 117]»
ሁለተኛው ጉዳይ፦ -ይህ ኑዛዜ ውድቅና ሐሰት መሆኑን ከሚያመላክቱት መካከል-፤ በውስጡ የተጠቀሰው ቃል እንዲህ የሚል ነው፦ «ይህን የጻፈ ሰው ድሃ ቢሆን አላህ ባለጸጋ ያደርገዋል፤ ባለዕዳ ከሆነ አላህ እዳውን ይከፍልለታል፤ ወንጀል ያለበት እንደሆነም በዚሁ ኑዛዜ በረከት አላህ ለርሱም ለወላጆቹም ይምርለታል» ወዘተ። ይህ ደግሞ ከባድ ውሸትና የቀጣፊውንም ውሸታምነት እንዲሁም ከአላህና ከባሮቹ ሐያእ ማጣቱን የሚያሳይ ግልፅ ማስረጃ ነው። ምክንያቱም እነዚህ ሦስቱ ነገሮች የተከበረውን ቁርኣን በመጻፍ ብቻ አይገኙምና። ታዲያ ይህችን ውድቅ ኑዛዜ ለጻፈው ሰው እንዴት ሊገኙለት ይችላሉ? የዚህ ውዳቂ ፍላጎቱ ሰዎችን ማወናበድና በዚህ ኑዛዜ እንዲቆራኙ ማድረግ ነው፤ ይህም ኑዛዜውን እንዲፅፉትና በዚህ ሀሰተኛ ትሩፋት እንዲንጠለጠሉ፣ እንዲሁም አላህ ለባሮቹ የደነገጋቸውንና ወደ ሲሳይ፣ እዳን መክፈልና የወንጀል ምህረት የሚያደርሱ ሰበቦችን እንዲተዉ ነው። ከውርደት ሰበቦች፣ ስሜትን ከመከተልና ከሸይጧንም በአላህ እንጠበቃለን።
ሦስተኛው ጉዳይ፡ —ይህ ኑዛዜ ውድቅ መሆኑን ከሚያመላክቱ ጉዳዮች መካከል— በውስጡ “ከአላህ ባሪያዎች መካከል ይህችን ያልጻፈ፤ ፊቱ በዱንያም በአኼራም ይጠቁራል።” ማለቱ ነው። ይህ ደግሞ እጅግ አስቀያሚ ከሆኑ የውሸት አይነቶችና ይህ ኑዛዜ ፍፁም ውድቅ መሆኑን እንዲሁም ቀጣፊውም ውሸታም እንደሆነ ከሚያመላክቱ ግልፅ ማስረጃዎች መካከል ነው። ለነገሩ እንዴት ሆኖ ነው አንድ አዕምሮ ያለው ሰው በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ላይ ቀጥፎ ይዞት መጣ የተባለውንና «ይህን ኑዛዜ ያልፃፈ ሰው ፊቱ በዱንያም በአኺራም ይጠቁራል፤ የጻፈው ደግሞ ከድህነት በኋላ ሃብታም ይሆናል፤ ከተደራረበበት እዳም ነፃ ይወጣል፤ ለሰራውም ወንጀል ሁሉ ምህረት ያገኛል!!» የሚለውን ኑዛዜ ሊቀበለው የሚችለው?
ሱብሐነሏህ፤ ይህ ታላቅ ቅጥፈት ነው!! ማስረጃዎችና ነባራዊው ሁኔታም የዚህን ቀጣፊ ውሸታምነት፣ በአላህ ላይ ያለውን የድፍረቱን ታላቅነት፣ ከአላህና ከሰዎችም ያለውን የሐፍረት ማነስ ይመሰክራሉ፡፡ እነሆ ብዙ ሕዝቦች አልጻፏትም፤ ፊቶቻቸውም አልጠቆሩም፡፡ እዚህም ጋር ቁጥራቸውን አላህ እንጂ ሌላ የማያውቃቸው እጅግ በርካታ ሕዝቦች ብዙ ጊዜ ጽፈዋታል፡፡ ዕዳቸውም አልተከፈለም፤ ድህነታቸውም አልተወገደም፡፡ ከቀልቦች ጥመትና ከወንጀሎች ዝገትም በአላህ እንጠበቃለን፡፡ እነዚህማ የተከበረው ሸሪዓ ከመጽሐፍት ሁሉ በላጩንና ታላቁን የሆነውን የተከበረውን ቁርኣን ለጻፈ ሰው እንኳን ያልደነገጋቸው ባህሪያትና ቅጣቶች ናቸው። ታዲያ የተለያዩ የባጢል (የውሸት) አይነቶችንና በርካታ የክህደት ንግግሮችን የያዘችን የሐሰት ኑዛዜ ለጻፈ ሰው እንዴት ትገኛለች? አላህ ጥራት ይገባው! በእርሱ ላይ በመዋሸት ድፍረት በፈጸሙት ላይ ምንኛ ታጋሽ ነው!
አራተኛው፦ ይህ ኑዛዜ ፍፁም ውድቅና ግልፅ ውሸት መሆኑን ከሚያመለክቱት መካከል፤ በውስጡ «በእርሷ ያመነ ከጀሀነም ቅጣት ይድናል፤ የካዳትም ከፍሯል» የሚለው ንግግሩ ነው። ይህም ደግሞ በውሸት ላይ ከሚደረግ ከባባድ ድፍረት እና ከእጅግ አስቀያሚ ውሸትም ነው። ይህ ቀጣፊ ሰዎችን ሁሉ በቅጥፈቱ እንዲያምኑ ይጣራል፤ በዚህም ከጀሀነም ቅጣት እንደሚድኑና በርሱ ያስተባበለ ደግሞ እንደሚከፍር ይሞግታል። በአላህ ይሁንብኝ! ይህ ውሸታም በአላህ ላይ ታላቅ ቅጥፈትን በእርግጥ ቀጥፏል፤ ከእውነት የራቀንም ነገር ተናግሯል። ያስተባበላት ሳይሆን በእርሷ ያመነ ሰው ነው ከሓዲ ሊሆን የሚገባው፤ ምክንያቱም እርሷ ምንም ዓይነት የእውነት መሠረት የሌላት ቅጥፈት፣ ከንቱና ውሸት ናትና። እኛም እርሷ ውሸት መሆኗንና ቀጣፊዋም ውሸታም መሆኑን አላህን እናስመሰክራለን። አላህ ያልፈቀደውን ለሰዎች ሊደነግግና ከእርሱ ያልሆነውንም በዲናቸው ውስጥ ሊያስገባ ይፈልጋል። አላህ ግን ከዚህች ቅጥፈት በአሥራ አራት ክፍለ ዘመናት በፊት ለዚህ ኡማ ዲኑን ሙሉ አድርጎና አሟልቶታል። እናንተ አንባቢያንና ወንድሞች ሆይ አስተውሉ፤ እንዲህ አይነት የተቀጠፉ ውሸቶችን ከማመንና በመካከላችሁ እንዲሰራጩ ከማድረግ ተጠንቀቁ፡፡ እውነት ብርሃን ስላለው በፈላጊው ላይ አሻሚ አይሆንምና። ስለዚህ እውነትን በማስረጃው ፈልጉ፤ አሻሚ የሆነባችሁንም ነገር የዕውቀት ባለቤቶችን ጠይቁ፡፡ በውሸታሞች መሐላም አትሸወዱ፤ የተረገመው ኢብሊስ ለወላጆቻችሁ ለአደም እና ሐዋ እርሱ ለነርሱ ከመካሪዎች እንደሆነ ምሎላቸዋልና። እርሱ ግን ከከሐዲዎች ሁሉ ታላቁና ከውሸታሞችም ሁሉ የበለጠ ውሸታም ነው፡፡ አላህ ስለ እርሱ ይህን ሲተርክ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَقَاسَمَهُمَآ إِنِّي لَكُمَا لَمِنَ ٱلنَّٰصِحِينَ21﴾
{«እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሯችሁ ነኝ።» ሲልም ማለላቸው።} [አል-አዕራፍ፡ 21] እርሱንና ቀጣፊ ተከታዮቹንም ተጠንቀቁ። እርሱም ሆኑ እነርሱ፣ ለማሳሳትና ለማጥመም ስንትና ስንት የውሸት መሐላዎች፣ ቃል አፍራሽ ኪዳኖችና ያጌጡ ንግግሮች አሏቸውና! ይህ ቀጣፊ ስለ ውግዝ ተግባራት መበራከት የጠቀሰው ነገር እውን የሆነ ጉዳይ ነው። ክቡር ቁርኣንና የጠራችው ሱናም ከእርሷ በብርቱ አስጠንቅቀዋል። በሁለቱም ውስጥ መመራትና በቂነት አለ።
የሰዓቲቱን ምልክቶች በተመለከተ ለተጠቀሰው ነገርማ፤ የነቢያዊ ሐዲሦች ከሰዓቲቱ ምልክቶች መካከል የሚሆኑትን አብራርተዋል። ክቡር ቁርኣንም ከፊሉን አመላክቷል። ይህንን ማወቅ የፈለገ ሰው ከሱና መጽሐፍትና ከዕውቀትና ከእምነት ባለቤቶች ድርሳናት ውስጥ በቦታው ያገኘዋል። ሰዎች የዚህ አይነቱን ቀጣፊ ማብራሪያና ማደናገር፣ እንዲሁም እውነትን ከሐሰት ጋር መቀላቀሉን አያስፈልጋቸውም። አላህ እኔንም ሆነ እናንተን እንዲሁም መላውን ሙስሊሞች ከሰይጣኖች ክፋት፣ ከአሳሳቾች ፈተና፣ ከጠማሞች ጥመት፣ እንዲሁም የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋትና በሰዎች ላይ ሃይማኖታቸውን ለማደባለቅ ከሚፈልጉ ሀቅን በውሸት ከሚለውጡ የአላህ ጠላቶች ማታለል ይጠብቀን። አላህ ግን ጠላቶቹ የሆኑት ሰይጣናትና ተከታዮቻቸው ከሀዲያንና አምላክ የለም ባዮች ቢጠሉትም እንኳ ብርሃኑን ሙሉ አድራጊ፤ ሃይማኖቱንም አሸናፊ የሚያደርግ ነው። አላህን የሙስሊሞችን ሁኔታ እንዲያስተካክል፣ እውነትን እንዲከተሉ፣ በርሱም ላይ እንዲጸኑ እንዲሁም ከኃጢአት ሁሉ ወደ እርሱ (ጥራት የተገባው) እንዲመለሱ እንዲያድላቸው እንጠይቀዋለን። እርሱ ጸጸትን ተቀባይ፣ አዛኝና በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና። አላህም መመኪያችንና በቂያችን ነው፤ ሁሉን ቻይ ታላቅ በሆነው አምላክ በቀር ምንም ኃይል እና ዘዴ የለም።
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው አላህ ይገባው። የአላህ ሶለዋትና ሰላም እውነተኛና ታማኝ በሆኑት በባሪያውና በመልእክተኛው ላይ፣ በቤተሰቦቻቸው ላይ፣ በባልደረቦቻቸው ላይ እና እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ በመልካም በተከተሏቸውም ላይ ይስፈን።
***
بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ
ዘጠነኛው መልዕክት፦
የድግምት እና የጥንቆላ ብይን እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች18
ምስጋና ሁሉ ለብቸኛው አላህ የተገባ ነው። የአላህ ሶላትና ሰላም ከእሳቸው በኋላ ነብይ የሌለ በሆኑት ነብይ ላይ ይስፈን። በመቀጠል:
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በህክምና ሰበብ ጥንቆላንና ድግምትን ተግባራዊ የሚያደርጉ ሟርተኞች ቁጥራቸው ከመብዛቱና በአንዳንድ ሀገሮችም ከመሰራጨታቸው እንዲሁም ከማህበረሰቡ መካከል አላዋቂነቱ የጠናበትን ተላላ መጠቀሚያ ከማድረጋቸው አንፃር ለአላህና ለባርያዎቹ በመቆርቆር ጉዳዩ ከአላህ ውጭ ባለ አካል መንጠልጠልና ለአላህና ለመልዕክተኛው ﷺ መመሪያ መጣስ በመሆኑ ለሙስሊሙም ይሁን ለኢስላም ያለውን አደገኝነት ግልፅ ማድረግን ወደድኩ።
ስለዚህም በአላህ በመታገዝ የሚከተለውን እላለሁ። መታከም የተፈቀደ ስለመሆኑ ሙሉ ስምምነት ያለበት ጉዳይ በመሆኑ ሙስሊሞች ለውስጥ ህመም፣ ለቀዶ ጥገና፣ ለነርቭም ይሁን ለመሳሰሉት ህመሞች ሁሉ ወደ ህክምና ሄዶ ሀኪሙም በህክምና ሳይንስ በሚያውቀው መሰረት በሽታውን መርምሮ ሐላል በሆኑ መድሃኒቶች በሚስማማው መሰረት መታከም ይቻላል። ምክንያቱም ይህ የተለመደውን ሰበብ ማድረስ በሚል ርዕስ ስር የሚታይ እንጂ በአላህ ላይ ያለ ተወኩል ጋር የሚቃረን አይደለም። ጥራት የተገባው የላቀው አላህ ደግሞ የሚያውቅ አውቆት ያላወቀ አላወቀውም እንጅ በሽታን እንዳወረደው ሁሉ መድኃኒቱንም አውርዷል። ጥራት ይገባውና የበሽታ መድሀኒቶችንም በሐራም ነገሮች አላደረገም።
በመሆኑም የትኛውም ህመምተኛ ህመሙን እንዲያውቁለት በሚልም ቢሆን የሩቅ ምስጢር እናውቃለን ባይ ብለው ወደሚሞግቱ ጠንቋዮች ሊሄድ አይፈቀድለትም። ልክ እንደዚሁ የሚሞግቱትንም ነገር ማመን አይፈቀድለትም። ምክንያቱም የጥንቆላ ንግግራቸውን የሚናገሩት ወይ በግምት አለበለዚያም ለፍላጎታቸው ጂኒዎች ሊያግዟቸው ዘንድ ጂኒዎችን በማሳተፍ ነውና። እነዚህም የሩቅ ምስጢር እናውቃለን ብለው የሚሞግቱ እስከሆኑ ድረስ ክህደትና ጥመት ላይ ናቸው።
ሙስሊም ነቢዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸውን ዘግበዋል፦
«مَنْ أَتَى عَرَّافًا فَسَأَلَهُ عَنْ شَيْءٍ، لَمْ تُقْبَلْ لَهُ صَلَاةٌ أَرْبَعِينَ يَوْمًا».
«ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለ አንዳች ነገር የጠየቀ ለአርባ ቀናት ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።»
አቡ ሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ ባስተላለፉት ሐዲሥ ደግሞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
«مَنْ أَتَى كَاهِنًا فَصَدَّقَهُ بِمَا يَقُولُ، فَقَدْ كَفَرَ بِمَا أُنْزِلَ عَلَى مُحَمَّدٍ ﷺ».
"ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ሟርተኛው የተናገረውን ያመነ ሰው ወደ ሙሐመድ ﷺ በወረደው ክዷል።" አቡ ዳውድ ዘግበውታል፤ እንዲሁም አራቱ የሱነን ባለቤቶችም መልዕክቱን የዘገቡት ሲሆን አል-ሐኪም በተከታዩ ቃል ከነብዩ ﷺ ሶሒሕ ሆኖ መምጣቱን አረጋግጠዋል፡-
«مَنْ أَتَى عَرَّافًا أَوْ كَاهِنًا فَصَدَّقَهُ بِمَا يَقُولُ، فَقَدْ كَفَرَ بِمَا أُنْزِلَ عَلَى مُحَمَّدٍ ﷺ».
«ሟርተኛ ወይም ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ የተናገረውን ያመነ፣ ወደ ሙሐመድ ﷺ በወረደው ክዷል።»
ዒምራን ቢን ሑሰይን (ረዲየሏሁ ዓንሁ) የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፈዋል፡-
«لَيْسَ مِنَّا مَنْ تَطَيَّرَ أَوْ تُطُيِّرَ لَهُ، أَوْ تَكَهَّنَ أَوْ تُكُهِّنَ لَهُ، أَوْ سَحَرَ أَوْ سُحِرَ لَهُ، وَمَنْ أَتَى كَاهِنًا فَصَدَّقَهُ بِمَا يَقُولُ، فَقَدْ كَفَرَ بِمَا أُنْزِلَ عَلَى مُحَمَّدٍ ﷺ».
«የገድ ተግባርን የፈፀመ ወይም ለሱ የተፈፀመለት፣ ወይም የጠነቆለ ወይም ያስጠነቆለ፣ ወይም የደገመ ወይም ያስደገመ ከኛ አይደለም። ጠንቋይ ዘንድ የሄደና የሚናገረውን ነገር አምኖ የተቀበለ በሙሐመድ ﷺ ላይ በወረደው ነገር በእርግጥ ክዷል።» አል-በዛር በጥሩ ሰነድ ዘግበውታል።
በእነዚህ የተከበሩ ሐዲሦች ውስጥ ወደ ጠንቋዮች፣ ሟርተኞች፣ ደጋሚዎችና መሰሎቻቸው ዘንድ መሄድ፣ እነርሱን መጠየቅና የሚናገሩትን ማመን የተከለከለ ሲሆን በዚህ ላይ ዛቻም እንዳለበት ተገልጿል።
በአንዳንድ አጋጣሚዎች ላይ ትክክል ሆነው በመገኘታቸውም ይሁን ወደነርሱ በሚመጡ አላዋቂ ሰዎች ብዛት መታለል አይገባም። ምክንያቱም የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ወደ እነርሱ መሄድን፣ መጠየቅንና በተናገሩት ማመንን ከልክለዋልና ነው። የከለከሉትም ከሚያስከትለው ከባድ መዘዝ፣ አደገኛ ክፋት እና አስከፊ ፍፃሜ አንፃር እንዲሁም እነርሱ ክፉ ውሸታሞች በመሆናቸውም ነው።
ልክ እንደዚሁ በእነዚህ ሐዲሦች ውስጥ ጠንቋይና ድግምተኛ መሆናቸውን የሚጠቁም ማስረጃም አለ። ምክንያቱም ጠንቋይና ድግምተኛ የሩቅ ዕውቀት የሚሞግቱ በመሆናቸውና ግባቸው ላይ ሊደርሱ የሚችሉትም በጂኖች በመታገዝ በመሆኑ በጂኖች መታገዝ የሚችሉት ደግሞ እነርሱን በማስተናገድና ከአላህ ውጭ እነርሱን በማምለክ ስለሆነ ነው። ይህ ደግሞ ጥራት ይገባውና በአላህ ላይ መካድና በእርሱም ማጋራት ነው። የሚሞግቱትን የሩቅ ዓዋቂነትን አምኖ የሚቀበል የነርሱ አምሳያ ነው። እነዚህን ጉዳዮች ከሚያከናውኑ ሰዎች ጋር የተሳተፈ ደግሞ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከእንዲህ ዓይነቱ የጠሩ ናቸው።
በተመሳሳይም ማንኛውም ሙስሊም በመድሀኒት ሰበብ ለሚያነበንቡት መተትም ይሁን ለሚያስተምሩት ሌላ አጉል እምነት ተገዥ ሊሆን አይፈቀድለትም። ምክንያቱም ይህ ሟርትና ሰዎችን ማምታታት በመሆኑ ይህንንም ወዶ የተቀበለ ሰው በውሸታቸውና በክህደታቸው ላይ እየተባበራቸው ነው።
እንዲሁም ከሙስሊሞች መካከል የትኛውም ሰው ወደ እነርሱ ሄዶ ልጁን ወይም ሌላ ዘመዱን ለማን ማጋባት እንዳለበት፣ ወይም በትዳር አጋሮች እና በቤተሰቦቻቸው መካከል ያለባቸውን የፍቅር፣ የመተማመን፣ የጥላቻና የመለያየት ሁኔታዎችን እና የመሳሰሉትን በተመለከተ ለመጠየቅ ብሎ መሄድ በፍፁም የተከለከለ ነው። ምክንያቱም ይህ ጥራት ከተገባው አላህ በቀር ማንም የማያውቀው የሩቅ ምስጢር ውስጥ የሚካተት ነው።
በመሆኑም ባለስልጣናትና አቅምና ችሎታው ያላቸው የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ወደ ጠንቋዮች እና ሟርተኞች ዘንድ የሚሄዱ ሰዎችን ማውገዝና በእንዲህ አይነቱ ድርጊት ላይ በግብይትም ይሁን በሌላ መስክ የሚሳተፉ አካላትን እንዲሁም ወደነርሱ የሚሄዱ ሰዎችን በደንብ ሊያወግዟቸው ይገባል።
ድግምትም ተመሳሳይ ብይን ነው ያለው፤ ድግምት በክህደት ደረጃ እርም ከተደረጉ ሐራም ነገሮች መካከል የሚመደብ ነው፤ ልዕለ ኃያሉ አላህም ሁለቱን መላእክቶችን በተመለከተ እንዲህ ብሏል፦
﴿...وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنۡ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَآ إِنَّمَا نَحۡنُ فِتۡنَةٞ فَلَا تَكۡفُرۡۖ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنۡهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِۦ بَيۡنَ ٱلۡمَرۡءِ وَزَوۡجِهِۦۚ وَمَا هُم بِضَآرِّينَ بِهِۦ مِنۡ أَحَدٍ إِلَّا بِإِذۡنِ ٱللَّهِۚ وَيَتَعَلَّمُونَ مَا يَضُرُّهُمۡ وَلَا يَنفَعُهُمۡۚ وَلَقَدۡ عَلِمُواْ لَمَنِ ٱشۡتَرَىٰهُ مَا لَهُۥ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ مِنۡ خَلَٰقٖۚ وَلَبِئۡسَ مَا شَرَوۡاْ بِهِۦٓ أَنفُسَهُمۡۚ لَوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ﴾
{... (ሀሩትና ማሩት) «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉ ድረስ አንድንም አያስተምሩም:: ከእነርሱም በሰውዬውና በሚስቱ መካከል በርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ:: እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልሆነ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም:: የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውን ይማራሉ:: የገዛውም ሰው ለርሱ በመጨረሻይቱ አገር ምንም ዕድል የሌለው መሆኑን በእርግጥ አወቁ:: ነፍሶቻቸውንም በርሱ የሸጡበት ዋጋ ከፋ! የሚያውቁ በሆኑ ኑሮ (ይህን ተግባር ባልሰሩት ነበር::)} [አል-በቀራህ፡ 102]
እነዚህ የተከበሩ ጥቅሶች ድግምት ክህደት መሆኑን እና ደጋሚዎች በአንድ ወንድና በሚስቱ መካከል መለያየትንም የሚፈጥሩ መሆናቸውን ያመለክታሉ። ከዚያም ባሻገር ድግምት ተፅእኖ ሊያሳድር የሚችለው በራሱ እንዳልሆነ ይልቁን ጥቅምም ሆነ ጉዳትን ሊያስከትል የሚችለው የአላህን ይሁንታዊ ፈቃድ እና ፍርድ ተከትሎ እንደሆነም ያመለክታል። ምክንያቱም ጥራት የተገባው የላቀው አላህ መልካሙንም እና ክፉውንም የፈጠረው እርሱ ነውና።
እነዚህ የተከበሩት አንቀጾች ድግምት የሚማሩ ሰዎች እየተማሩ ያሉት የማይጠቅማቸውን ብሎም የሚጎዳቸውን እንደሆነም ግልፅ አድርገዋል። አላህ ዘንድ ምንም አይነት ድርሻ እንደሌላቸው ማለትም፡ እድለኝነት እና መልካም ምንዳ የሌላቸው መሆኑንም አስረድተዋል። ይህ ደግሞ በዱኒያም በአኺራም የሚገጥማቸው ክስረት አደገኛ መሆኑን የሚጠቁም ከባድ ዛቻ ነው። ራሳቸውንም በዝቅተኛ ዋጋ የሸጡ በመሆናቸው ልዕለ ኃያሉ አላህ እንዲህ ሲል ኮንኗቸዋል፦
﴿...وَلَبِئۡسَ مَا شَرَوۡاْ بِهِۦٓ أَنفُسَهُمۡۚ لَوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ﴾
{…ነፍሶቻቸውን የሸጡበት ዋጋ ከፋ! የሚያውቁ በሆኑ ኑሮ (ይህን ተግባር ባልሰሩት ነበር::)} [አል-በቀራህ፡ 102] እዚህ አንቀጽ ውስጥ መግዛት የተባለው ራሳቸውን መሸጣቸው ለማለት ነው።
ይህንን ዕውቀት ከሙሽሪኮች በወረሱና ደካማ አዕምሮ ያላቸውንም ሰዎች ባደናገሩ በእነዚህ ቀጣፊዎች ምክንያት ከባድ ጉዳት ደርሷል፤ ንግግሩም አፅንዖት ባለው መልኩ ሆኗል። እኛም የአላህ ነን፤ ወደርሱም ተመላሾች ነን። አላህም በቂያችን ነው፤ ምንኛ ያማረ መመኪያ ነው።
ከጠንቋዮች፣ ከሟርተኞችና እና ሌሎችም አጭበርባሪዎች ክፋት አላህ ይጠብቀን ዘንድ እንማፀነዋለን። ጥራት የተገባው አላህ ሙስሊሞችን ከክፋት እንዲጠብቃቸው፣ የሙስሊም መሪዎችንም እንዲጠነቀቋቸው፣ የአላህ ባርያዎች ከክፋታቸውም ከመጥፎ ስራዎቻቸውም ሰላም ሊሆኑ ዘንድ የአላህን ፍርድ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አላህ ይወፍቃቸው ዘንድ እንማፀነዋለን።
ጥራት የተገባው አምላካችን አላህ ድግምት ከመከሰቱ በፊት ከድግምቱ መጠንቀቅ የሚቻልበትን መንገዶች ለባሮቹ ደነግጎላቸዋል። ጥራት ይገባውና ለእነርሱ ካለው እዝነትና ከእነርሱ አንፃር ከተከሰተ በኋላ መታከም የሚቻልበትንም መንገድ ግልፅ አድርጎላቸዋል።
የድግምትን አደጋ ከመከሰቱ በፊት መጠንቀቅ የሚቻልባቸውንም ይሁን ከተከሰተ በኋላ መታከም የሚቻልባቸውን መንገዶች በሸሪዓም ከተፈቀዱት መካከል ማብራሪያቸው እንደሚከተለው ነው፡
አንደኛ፡ ድግምት ከመከሰቱ በፊት ከሚያስከትለው አደጋ መከላከያ፤ ከእነዚህም እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚው፦ በሸሪዓዊ ዚክሮች፣ በዱዓዎች እና ከነብዩ በተገኙ የክፋት መጠበቂያ ውዳሴዎችን በመጠቀም መከላከል ነው። ከእነዚህም መካከል፦ ከእያንዳንዱ የግዴታ ሶላት በኋላ ካሰላመቱ በኋላ አየተል ኩርሲይን መቅራት ነው፤ እርሱም በቅዱስ ቁርአን ውስጥ እጅግ ታላቅ አንቀፅ ሲሆን እርሱም የሚከተለው የአላህ ንግግር ነው፦
﴿ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلۡحَيُّ ٱلۡقَيُّومُۚ لَا تَأۡخُذُهُۥ سِنَةٞ وَلَا نَوۡمٞۚ لَّهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۗ مَن ذَا ٱلَّذِي يَشۡفَعُ عِندَهُۥٓ إِلَّا بِإِذۡنِهِۦۚ يَعۡلَمُ مَا بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَمَا خَلۡفَهُمۡۖ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَيۡءٖ مِّنۡ عِلۡمِهِۦٓ إِلَّا بِمَا شَآءَۚ وَسِعَ كُرۡسِيُّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَۖ وَلَا يَـُٔودُهُۥ حِفۡظُهُمَاۚ وَهُوَ ٱلۡعَلِيُّ ٱلۡعَظِيمُ255﴾
{አላህ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: አላህ ሕያው፤ በራሱ የተብቃቃ ነው:: ማንገላጀትም ሆነ እንቅልፍ አትይዘዉም:: በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: ያ እርሱ ዘንድ በፍቃዱ ቢሆን እንጂ የሚያማልድ ማን ነው? (ከፍጡራን) ሁሉ በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል:: በሻውም ነገር እንጂ ከእውቀቱ (ፍጡራን) በምንም ነገር አያካብቡም:: መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ:: ጥበቃቸዉም አያቅተዉም:: እርሱ የሁሉ በላይ ታላቅ ነው::} [አል-በቀራህ፡ 255] ልክ እንደዚሁ በእንቅልፍ ወቅትም ይቀራል፤ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ማለታቸው በሶሒሕ ሐዲሥ ተረጋግጧል፦
«مَنْ قَرَأَ آيَةَ الْكُرْسِيِّ فِي لَيْلَةٍ، لَمْ يَزَلْ عَلَيْهِ مِنَ اللَّهِ حَافِظٌ، وَلَا يَقْرَبُهُ شَيْطَانٌ حَتَّى يُصْبِحَ».
«በምሽቱ ክፍለጊዜ አየተል ኩርሲይን የቀራ ሰው እስኪነጋ ድረስ የአላህ ከለላ አይለየውም፤ ሸይጧንም አይቀርበውም።»
ከነዚህም መካከል የሚከተለውን ማንበብ ይገኝበታል፦
﴿قُلۡ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ1﴾
{ በል፡ -እርሱ አላህ አንድ ብቻ ነው::}
﴿قُلۡ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلۡفَلَقِ1﴾
{በል፡ -በተፈልቃቂው ጎህ (በአል-ፈለቅ) ጌታ እጠበቃለሁ፤}
﴿قُلۡ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلنَّاسِ1﴾
{በል፡ -የሰዎች ሁሉ ፈጣሪ በሆነው ጌታ እጠበቃለሁ፤} [አን-ናስ: 1] እስከመጨረሻው። ከእያንዳንዱ ግዴታ ሶላት በኋላ እነኝህን ሶስት ሱራዎች በቀኑ መጀመሪያ ከፈጅር ሶላት በኋላ እና በሌሊቱ መጀመሪያ ከመግሪብ ሶላት በኋላ ሶስት ሶስት ጊዜ መቅራት።
ከእነዚህም መካከል፦ የሱረቱል በቀራህ የመጨረሻዎቹን ሁለት አንቀፆች በመጀመርያው የሌሊቱ ክፍል መቅራት። እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦
﴿ءَامَنَ ٱلرَّسُولُ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيۡهِ مِن رَّبِّهِۦ وَٱلۡمُؤۡمِنُونَۚ كُلٌّ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَكُتُبِهِۦ وَرُسُلِهِۦ لَا نُفَرِّقُ بَيۡنَ أَحَدٖ مِّن رُّسُلِهِۦۚ وَقَالُواْ سَمِعۡنَا وَأَطَعۡنَاۖ غُفۡرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيۡكَ ٱلۡمَصِيرُ285﴾
{መልክተኛው ከጌታው ወደርሱ በተወረደው አመነ:: አማኞችም እንደዚሁ አመኑ:: ሁሉም በአላህ፣ በመላእክቱም፣ በመጻህፍቱም፣ በመልክተኞቹም ከመልክተኞቹ «በአንዱም መካከል አንለይም (አንክድም)» የሚሉ ሲሆኑ አመኑ:: «ሰማን ታዘዝንም። ጌታችን ሆይ! ምህረትህን እንሻለን :: መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው።» አሉም::} እስከ ምዕራፉ መጨረሻ ድረስ አንብብ!
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸው በሶሒሕ ሐዲሥ ተዘግቧል፦
«مَنْ قَرَأَ الآيَتَيْنِ مِنْ آخِرِ سُورَةِ البَقَرَةِ فِي لَيْلَةٍ كَفَتَاهُ».
"በምሽት ውስጥ የመጨረሻዎቹን የበቀራህ ምእራፍ ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው ይበቁታል።" ትርጉሙ፡- ከክፋት ነገር ሁሉ ይጠብቁታል ማለት ነው። ሌላው የአላህን ጥበቃ እናገኝባቸው ዘንድ በሸሪዓው የተደነገጉ (ፍፁም የሆኑ ከፍጡራኑ ክፋት የምንጠበቅባቸው) ውዳሴዎችን ሌትም ቀንም፣ በቤት ውስጥም ይሁን በበረሃ በአየርም ይሁን በባህር የአላህን ጥበቃ የሚያስገኙልን የተደነገጉ አዝካሮችን ማብዛት ነው። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ እንዲህ በማለታቸው ነው፡-
«مَن نَزَلَ مَنْزِلًا فَقالَ: أَعُوذُ بِكَلِمَاتِ اللهِ التَّامَّاتِ مِن شَرِّ ما خَلَقَ، لَمْ يَضُرَّهُ شَيءٌ حتَّى يَرْتَحِلَ مِن مَنْزِلِهِ ذَلِكَ».
"በአንድ ስፍራ ላይ አርፎ ከዚያም ‹አዑዙ ቢከሊማቲላሂ አትታማቲ ሚን ሸሪ ማ ኸለቀ (ምሉዕ በሆኑ የአላህ ቃላት ከፈጠራቸው ጎጂ ነገሮች እጠበቃለሁ)› ያለ ሰው ከዛ ስፍራ እስኪንቀሳቀስ ድረስ አንዳችም አይጎዳውም።"
እንዲሁም አንድ ሙስሊም በቀኑ መጀመሪያ እና በሌሊቱ መጀመሪያ ላይ ሶስት ጊዜ ተከታዩን ማለት፦
«بِسْمِ اللهِ الَّذِي لَا يَضُرُّ مَعَ اسْمِهِ شَيءٌ فِي الأَرْضِ وَلَا فِي السَّمَاءِ، وَهُوَ السَّمِيعُ العَلِيمُ».
«ቢስሚላሂ ለዚ ላ የዹሩ መዐ_ስሚሂ ሸይኡን ፊል አርዺ ወላ ፊ ስሰማኢ ወሁወ አስ'ሰሚዑል ዐሊም።» (በዚያ ከስሙ ጋር በምድርም ይሁን በሰማይ ምንም ነገር የማይጎዳ በሆነው እንዲሁም ሰሚና ዐዋቂ በሆነው አላህ ስም።)
ይህንን የሚያበረታቱ ሶሒሕ ሐዲሦች ከነብዩ ﷺ በመዘገባቸው እነዚህ አዝካሮች ከክፋት ሁሉ ለመጠበቅ ሰበብ ናቸው።
ሁለተኛ፡ ድግምት ከተከሰተ በኋላ የሚታከምባቸው መንገዶች፤ ይህም በበርካታ መንገዶች ነው:-
የመጀመሪያው: ወደ አላህ መዋደቅን ማብዛት፣ እንዲሁም ጉዳትን እንዲያነሳና መከራንም እንዲያስወግድ እርሱን መጠየቅ ነው።
ሁለተኛው: ድግምትን ለማከም ከሚረዱ ፋይዳቸው ከጎሉ ዘዴዎች መካከል አንዱ ድግምቱ የተቀበረበትን ቦታ በመሬት ላይም ይሁን በተራራ አልያም በሌላ ቦታ ለይቶ ለማወቅ መጣጣር ነው። ምክንያቱም ድግምቱ ያለበት ቦታ ከታወቀ አውጥተው ቢበታትኑት ድግምቱ ይከሽፋልና ነው።
ሶስተኛው፦ በሸሪዓዊ ዚክሮች እና አውራዶች ሩቃ ማድረግ፤ እነርሱም ብዙ ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል፦
በአላህ መልዕክተኛ ﷺ ንግግር እንደተረጋገጠው፦
«اللَّهُمَّ رَبَّ النَّاسِ، أَذْهِبِ الْبَأْسَ، وَاشْفِ أَنْتَ الشَّافِي، لَا شِفَاءَ إِلَّا شِفَاؤُكَ، شِفَاءً لَا يُغَادِرُ سَقَمًا».
("አሏሁምመ ረበ‐ን‐ናስ፣ አዝሂቢል በእሰ፣ ወሽፊ አንተ‐ሽ‐ሻፊ፣ ላ ሺፋአ ኢላ ሺፋኡክ፣ ሺፋአን ላ ዩጋዲሩ ሰቀማ" ትርጉሙም፦ የሰዎች ጌታ የሆንከው አላህ ሆይ! በሽታውን አስወግድ፤ ፈዋሹም አንተ ነህና ፈውስ፤ ምንም አይነት በሽታ የማያስቀር ከሆነው ከአንተ ፈውስ በቀር ሌላ ፈውስ የለም።") ይህንንም ሶስት ጊዜ ይለዋል:
ከእነዚህም መካከል ጂብሪል ዓለይሂ ሰላም ነቢዩን ﷺ ሩቃ ያደረገበት ዚክር ይገኝበታል፤ ይኸውም፦
«بِسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ، مِنْ كُلِّ شَيْءٍ يُؤْذِيكَ، وَمِنْ شَرِّ كُلِّ نَفْسٍ أَوْ عَيْنِ حَاسِدٍ، اللَّهُ يَشْفِيكَ، بِسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ».
(“በስሚላሂ አርቂከ ሚን ኩሊ ሸይኢን ዩእዚከ ወሚን ሸሪ ኩሊ ነፍሲን አው ዓይኒን ሐሢድ፥ አሏሁ የሽፊከ ቢስሚላሂ አርቂከ” ትርጉሙ፦ «በአላህ ስም ሩቅያ አደርግልሃለሁ (አክምሀለሁ)፤ ከሚጎዳህ ነገር ሁሉ፣ ከነፍስ ሁሉ (ክፋት) እና ከምቀኛ ዓይን (ክፋት)፤ አላህ ይፈውስህ፤ በአላህ ስም ሩቅያ አደርግልሃለሁ።» ይህንንም ሦስት ጊዜ ደጋግሞ ይበለው!
ከነዚህም መካከል -በተለይ ከባለቤቱ ጋር ግንኙነት ለመፈፀም ለተቸገረ ሰው ጠቃሚ ፈውስ ነው-፡ ሰባት አረንጓዴ የቁርቁራ ቅጠል ወስዶ በድንጋይ ወይም በመሳሰሉት ፈጭቶ፣ በአንዳች እቃ አድርጎ ለትጥበት የሚበቃውን ያህል በውሀ በመዘፍዘፍ ላዩ ላይ ይቀራበታል፡
አያቱል ኩርሲይን እና
﴿قُلۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡكَٰفِرُونَ1﴾
{(ለካሓዲያን እንዲህ) በላቸው፡- እናንተ ከሓዲያን ሆይ!} [አል-ካፊሩን፡ 1] እስከመጨረሻው። እንዲሁም
﴿قُلۡ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ1﴾
{ በል፡ -እርሱ አላህ አንድ ብቻ ነው::} "[አል-ኢኽላስ፡ 1] እስከመጨረሻው። እንዲሁም
﴿قُلۡ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلۡفَلَقِ1﴾
{ በል፡ -በተፈልቃቂው ጎህ (በአል-ፈለቅ) ጌታ እጠበቃለሁ፤} [አል-ፈለቅ: 1] እስከመጨረሻው። እንዲሁም
﴿قُلۡ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلنَّاسِ1﴾
{በል፡ -የሰዎች ሁሉ ፈጣሪ በሆነው ጌታ እጠበቃለሁ፤} [አን-ናስ: 1] እስከመጨረሻው።
በሱረቱል አዕራፍ ውስጥ ያሉ ለድግምት የሚቀሩ አንቀጾች ማለትም ተከታዮቹ አንቀጾች፦
﴿وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنۡ أَلۡقِ عَصَاكَۖ فَإِذَا هِيَ تَلۡقَفُ مَا يَأۡفِكُونَ117 فَوَقَعَ ٱلۡحَقُّ وَبَطَلَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ118 فَغُلِبُواْ هُنَالِكَ وَٱنقَلَبُواْ صَٰغِرِينَ119﴾
{ ወደ ሙሳም «ዘንግህን ጣል» ስንል ላክንበት (ጣላትም) ወዲውኑም የሚቀጣጥፉትን ማታለያ መዋጥ ጀመረች::
እውነቱም ተገለጸ:: ይሠሩት የነበሩት ድግምትም ተበላሸ::
እዚያ ላይ ተሸነፉና ወራዶች ሆነው ተመለሱ።} [አል-አዕራፍ 117-119]
በሱረቱ ዩኑስ ውስጥ ያሉ አንቀጾች ማለትም ተከታዮቹ አንቀጾች፦
﴿وَقَالَ فِرۡعَوۡنُ ٱئۡتُونِي بِكُلِّ سَٰحِرٍ عَلِيمٖ79 فَلَمَّا جَآءَ ٱلسَّحَرَةُ قَالَ لَهُم مُّوسَىٰٓ أَلۡقُواْ مَآ أَنتُم مُّلۡقُونَ80 فَلَمَّآ أَلۡقَوۡاْ قَالَ مُوسَىٰ مَا جِئۡتُم بِهِ ٱلسِّحۡرُۖ إِنَّ ٱللَّهَ سَيُبۡطِلُهُۥٓ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُصۡلِحُ عَمَلَ ٱلۡمُفۡسِدِينَ81 وَيُحِقُّ ٱللَّهُ ٱلۡحَقَّ بِكَلِمَٰتِهِۦ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡمُجۡرِمُونَ82﴾
{ ፈርዖን፡- «አዋቂ ድግምተኛን ሁሉ አምጡልኝ።» አለ::
ድግምተኞቹ በመጡ ጊዜም ሙሳ ለእነርሱ፡- «እናንተ የምትጥሉትን ነገር ጣሉ።» አላቸው::
በጣሉም ጊዜ ሙሳ፡- «ያ በእርሱ የመጣችሁበት ነገር ድግምት ነው:: አላህ በእርግጥ ያፈርሰዋል:: አላህ የአጥፊዎችን ሥራ ፈጽሞ አያበጅምና።» አለ::
አላህም ከሓዲያን ቢጠሉም እውነትን በቃላቱ ያረጋግጣል።} [ዩኑስ: 79-82]
በሱረቱ ጣሃ ውስጥም ያሉት አንቀጾች፡-
﴿قَالُواْ يَٰمُوسَىٰٓ إِمَّآ أَن تُلۡقِيَ وَإِمَّآ أَن نَّكُونَ أَوَّلَ مَنۡ أَلۡقَىٰ65 قَالَ بَلۡ أَلۡقُواْۖ فَإِذَا حِبَالُهُمۡ وَعِصِيُّهُمۡ يُخَيَّلُ إِلَيۡهِ مِن سِحۡرِهِمۡ أَنَّهَا تَسۡعَىٰ66 فَأَوۡجَسَ فِي نَفۡسِهِۦ خِيفَةٗ مُّوسَىٰ67 قُلۡنَا لَا تَخَفۡ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡأَعۡلَىٰ68 وَأَلۡقِ مَا فِي يَمِينِكَ تَلۡقَفۡ مَا صَنَعُوٓاْۖ إِنَّمَا صَنَعُواْ كَيۡدُ سَٰحِرٖۖ وَلَا يُفۡلِحُ ٱلسَّاحِرُ حَيۡثُ أَتَىٰ69﴾
{ «ሙሳ ሆይ! በመጀመሪያ ትጥላለህ ወይስ እኛ እንጣል? (ምረጥ)» አሉ።
ሙሳም «እናንተ መጀመሪያ ጣሉ።» አላቸው። ጣሉም:: ወዲያዉም ገመዶቻቸውና ዘንጎቻቸው ከድግምታቸው የተነሳ የሚሮጡ እባቦች ሆነው (መስለው) ወደ እርሱ ተመሰሉበት።
ሙሳም በውስጡ ፍርሃት አደረበት::
አልነውም: «አትፍራ። የበላዩ አንተ ነህና።»
«በቀኝ እጅህ ያለችውን ብትር ጣል:: ያንን የሰሩትን ትውጣለችና። የሰሩት የድግምተኛ ተንኮል ብቻ ነውና:: ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናዉም::»} [ጧሀ: 65-69]
ከላይ የተጠቀሱትን በውሃ ላይ ከቀራበት በኋላ ሶስት እፍኝ ይጠጣበትና በቀሪው ይታጠብ። በዚህም የአላህ ፈቃድ ታክሎበት በሽታው ይወገዳል። ሁለቴ እና ከዛ በላይ መደጋገሙ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ደግሞ በሽታው እስኪወገድ ድረስ ቢደጋገምም ችግር የለውም።
እነዚህ ውዳሴዎች፣ መጠበቂያ ዚክሮች እና መንገዶች በቅንነት፣ በእምነት፣ በአላህ ላይ በመተማመንና በእርሱም ላይ በመደገፍ ለሚሰጡት መልዕክትም በአፅንኦት ልቡን ከፍቶ ለሚከታተላቸው የድግምትም የሌላውንም ክፋት ለመመከት ከታላላቅ ሰበቦች ከመሆናቸውም ባሻገር ድግምቱ ከተከሰተ በኋላ ለማስወገድም ታላቅ መሳሪያ ናቸው።
ድግምትን መጠንቀቅና ማከም የሚቻልባቸው ዘዴዎችን በተመለከተ አላህ ያገራልን ይህን ይመስላል። አላህ ተውፊቁን ይግጠመን።
እዚህ ላይ አንድ ወሳኝ ጉዳይ ይነሳል። ይህም ድግምትን በድግምተኞች ስራ ማከሙ ማለትም በመስዋእት ወይም በሌላ አምልኮ ወደ አጋንንት መቃረቡ በፍፁም አይፈቀድም፤ ምክንያቱም ከሰይጣን ስራ እና ከዛም አልፎ ከባዱ ሽርክ ነውና። ልክ እንደዚሁ ጠንቋዮችን፣ ሟርተኞችንና አጭበርባሪዎችን እየጠየቁ መተካከሙና የሚሉትንም ተግባራዊ ማድረጉም አይፈቀድም። ምክንያቱም እምነተቢሶችና ቀጣፊ ሟርተኛ ጋጠወጦች በመሆናቸው ነው። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እነኝህ ሰዎች ዘንድ ከመሄድ፣ እነርሱን ከመጠየቅና የሚሉትን አምኖ ከመቀበል አስጠንቅቀዋል። ይህም ቀደም ብለን በዚህ ጽሑፍ መጀመሪያ ላይ ገልፀነዋል። ከዚህ ነገር መጠንቀቅ ግዴታ ሲሆን የአላህ መልዕክተኛም ﷺ ድግምትን በድግምት ስለማክሸፍ ተጠይቀው እንዲህ ማለታቸው በሶሒሕ ሐዲሥ ተረጋግጧል፡-
«هِيَ مِنْ عَمَلِ الشَّيْطَانِ».
«እርሱ የሸይጧን ስራ ነው።» ኢማሙ አሕመድ እና አቡ ዳውድ በጥሩ ሰነድ ዘግበውታል።
“ኑሽራ” ማለት ድግምትን በድግምት ማክሸፍ ማለት ሲሆን እሳቸው እንዲህ ሲሉ የፈለጉበት: “የጃሂሊያ ሰዎች ይጠቀሙበት የነበረውን የማክሸፊያ አይነት ማለትም ድግምትን ደጋሚ እንዲያከሽፈው አልያም ድግምቱን በአምሳያው ድግምት ማክሸፍን ማውገዛቸው ነው።
ሩቃ በማድረግ፣ በሸሪዓው የተደነገጉ በሆኑ ዱዓዎች እና በተፈቀዱ ፈውሶች ድግምትን ማክሸፉ ግን ቀደም ብለንም እንዳሳለፍነው ምንም ችግር የለውም። ይህም ታላቁ ሊቅ ኢብኑል ቀይም እና ሸይኽ ዐብዱረሕማን ኢብኑ ሐሰን ፈትሑል መጂድ በተሰኘው ኪታባቸው አላህ ይዘንላቸውና እንዲሁም ሌሎችም ሊቃውንት ያብራሩት ጉዳይ ነው።
አላህ ሙስሊሞችን በሙሉ ከመጥፎ ነገር ሁሉ እንዲታደጋቸው፣ ሃይማኖታቸውንም ለእነርሱ እንዲጠብቅላቸው፣ መገንዘቡንም እንዲለግሳቸው፣ የእርሳቸውን ድንጋጌ ከመጣስም እንዲያድናቸው አላህን እንማፀነዋለን።
የአላህ ሰላትና ሰላም ባሪያውና መልክተኛው በሆኑት በሙሐመድ፣ እንዲሁም በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ይስፈን።
***
بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ
አስረኛው መልዕክት፦
መቃብሮች ላይ መስጂዶችን ከመገንባት ማስጠንቀቅ
በአላህ ስም፤ ምስጋናም ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላትና ሰላምም በአላህ መልእክተኛ ላይ ይስፈን።
ከዚህ በመቀጠል፡ በራቢጠቱል ኡሉም አል-ኢስላሚያ መጽሔት ሶስተኛ እትም ‹‹የወሩ የሙስሊሞች ዜና›› በሚለው ክፍል ውስጥ፤ በጆርዳን ሃሺማዊት ንጉሳዊ ግዛት የሚገኘው ራቢጠቱል ኡሉም አል-ኢስላሚያ፣ አር-ሩሐይብ በምትባል መንደር በቅርቡ በተገኘው ዋሻ ላይ መስጊድ ለመገንባት ማሰቡን የሚገልጽ ጽሑፍ ተመልክቻለሁ። ይህ ዋሻም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ የተጠቀሱት የዋሻው ሰዎች (አህለል-ከህፍ) ያንቀላፉበት ነው ተብሎ የሚነገርለት ነው፤ አበቃ።
ለአላህና ለባሮቹ ተቆርቋሪ መሆን ግዴታ መሆኑን ከግምት በማስገባት፤ በዚሁ መጽሔት ላይ በሃሺማዊቷ የጆርዳን መንግስት ለሚገኘው የኢስላማዊ ምርምር ማህበር አንድ ቃል ለማቅረብ አሰብኩ፤ ይዘቱም ማህበሩ በተጠቀሰው ዋሻ ላይ መስጂድ ለመገንባት የነበረውን ሀሳብ እንዳይተገብረው መምከር ነው፤ ይህም የሆነበት ምክንያት፣ በነቢያቶችና በሷሊሖች መቃብር እንዲሁም በቅሪቶቻቸው ላይ መስጂዶችን መገንባት ወደ ሺርክ ከሚያደርሱና በነቢያቶችና በሷሊሖች ድንበር ከማለፍ መንገዶች አንዱ ስለሆነ ፍፁም የሆነው ኢስላማዊ ሸሪዓ የከለከለው፣ ያስጠነቀቀበት እንዲሁም ፈፃሚውን የረገመበት በመሆኑ ነው። ተጨባጩ ሸሪዓው ይዞት የመጣው ነገር እውነት ለመሆኑ ምስክር ነው፣ ክብሩ የላቀ ከሆነው ከአላህ ዘንድ ለመሆኑ ማስረጃ ነው፣ እንዲሁም የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከአላህ ዘንድ ይዘውት በመጡትና ለህዝባቸው ባደረሱት ነገር ላይ እውነተኛ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ፍንትው ያለ ማስረጃና የማያዳግም ማረጋገጫም ነው። የሙስሊሙን ዓለም ሁኔታዎችና በውስጡም በዶሪሖች ላይ መስጂዶችን በመገንባት፣ እነርሱንም በማላቅ፣ ለነርሱ ምንጣፍ በማንጠፍና በማስዋብ እንዲሁም አገልጋዮችን በመመደብ ምክንያት የተከሰተውን ሽርክና ድንበር ማለፍ በጥሞና የተመለከተ ማንኛውም ሰው ይህ ድርጊት ወደ ሽርክ ከሚያዳርሱ መንገዶች መካከል መሆኑንና፤ የእስልምና ሸሪዓም ካሉት መልካም ገፅታዎች መካከል ይህንን እንደሚከለክልና ከመገንባቱም እንደሚያስጠነቅቅ በእርግጠኝነት ይገነዘባል።
በዚህ ዙሪያ ከተዘገቡት መካከል ቡኻሪና ሙስሊም (አላህ ይዘንላቸውና) በዘገቡት ሐዲሥ: እናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንዲህ ብላለች: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:"
«لَعَنَ اللَّهُ الْيَهُودَ وَالنَّصَارَى، اتَّخَذُوا قُبُورَ أَنْبِيَائِهِمْ مَسَاجِدَ، قالَتْ عَائِشَةُ: يُحَذِّرُ مَا صَنَعُوا، قالَتْ: وَلَوْلَا ذَلِكَ لَأُبْرِزَ قَبْرُهُ، غَيْرَ أَنَّهُ خُشِيَ أَنْ يُتَّخَذَ مَسْجِدًا».
"«አላህ አይሁድና ክርስቲያኖችን ረገመ፤ የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስጂድ አድርገው ያዙ።» ዓኢሻም እንዲህ አለች: "ከሰሩት ሥራ እያስጠነቀቁ ነው። ይህ ባልነበረ ኖሮ ቀብራቸው ይፋ ይሆን ነበር። ነገር ግን መስጂድ ተደርጎ እንዳይያዝ ተፈራ።" እንዲሁም በቡኻሪ እና ሙስሊም እንደተዘገበው «ኡሙ ሰላማ እና ኡሙ ሀቢባ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በሀበሻ ምድር ስላዩት ቤተ ክርስቲያን እና በውስጡ ስለነበሩት ምስሎች ለአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነገሯቸው። የአላህ መልዕክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦»
«أُولَئِكَ إِذَا مَاتَ فِيهِمُ الرَّجُلُ الصَّالِحُ؛ بَنَوْا عَلَى قَبْرِهِ مَسْجِدًا، وَصَوَّرُوا فِيهِ تِلْكَ الصُّوَرَ، أُولَئِكَ شِرَارُ الْخَلْقِ عِنْدَ اللَّهِ».
«እነዚህ በመካከላቸው ደግ ሰው ሲሞት፤ በቀብሩ ላይ መስጂድ ይገነቡና በውስጡም እነዚያን ስእሎች ይስላሉ፤ እነዚህ አላህ ዘንድ እጅግ ክፉ ፍጡራን ናቸው።»
በሶሒሕ ሙስሊምም ከጁንዱብ ቢን ዐብዲላህ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተዘገበው እንዲህ ብሏል: «የአላህ መልዕክተኛን ﷺ ከመሞታቸው አምስት ቀናት በፊት እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦»
«إِنِّي أَبْرَأُ إِلَى اللَّهِ أَنْ يَكُونَ لِي مِنْكُمْ خَلِيلٌ، فَإِنَّ اللَّهَ قَدِ اتَّخَذَنِي خَلِيلًا، كَمَا اتَّخَذَ إِبْرَاهِيمَ خَلِيلًا، وَلَوْ كُنْتُ مُتَّخِذًا مِنْ أُمَّتِي خَلِيلًا، لَاتَّخَذْتُ أَبَا بَكْرٍ خَلِيلًا، أَلَا وَإِنَّ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ كَانُوا يَتَّخِذُونَ قُبُورَ أَنْبِيَائِهِمْ وَصَالِحِيهِمْ مَسَاجِدَ، أَلَا فَلَا تَتَّخِذُوا الْقُبُورَ مَسَاجِدَ، فَإِنِّي أَنْهَاكُمْ عَنْ ذَلِكَ».
«እኔ ከናንተ መካከል ፍፁም ወዳጅ ከመያዝ ወደ አላህ እጥራራለሁ። ምክንያቱም አሏህ ኢብራሂምን ፍፁም ወዳጅ አድርጎ እንደያዘው ሁሉ እኔንም ፍፁም ወዳጅ አድርጎ ይዞኛልና። ከኡመቴ መካከል ፍፁም ወዳጅ (ኸሊል) አድርጌ የምይዝ ብሆን ኖሮ አቡበከርን ነበር ፍፁም ወዳጅ አድርጌ የምይዘው። አዋጅ! እነዚያ ከናንተ በፊት የነበሩት የነብያቶቻቸውንና የፃድቃኖቻቸውን መቃብር መስገጃ ስፍራ አድርገው ይይዙ ነበር። አዋጅ! መቃብርን መስገጃ ስፍራ አድርጋችሁ አትያዙ! እኔ እየከለከልኳችሁ ነው።» በዚህ ዙሪያ የመጡ ሐዲሦች በርካታ ናቸው።
በእርግጥም ከአራቱ መዝሀቦችና ከሌሎችም የሆኑ የሙስሊም ሊቃውንት እና ኢማሞች፤ የመልዕክተኛውን ﷺ ሱና በመከተል፣ ለህዝበ ሙስሊሙ በመቆርቆርና ኡመቱ ከእነርሱ በፊት የነበሩት የአይሁዶችና የክርስቲያኖች ድንበር አላፊዎች እንዲሁም ከዚህ ኡመት የጠመሙ አምሳያዎቻቸው በወደቁበት ላይ እንዳይወድቁ ለማስጠንቀቅ፤ በመቃብር ላይ መስጊዶችን መገንባት ክልክል መሆኑን በግልፅ አስቀምጠዋል፤ ከዚህም አስጠንቅቀዋል።
በዮርዳኖስ በሚገኘው የእስልምና እውቀት ማህበር እና በሌሎችም ሙስሊሞች ላይ ግዴታው፤ ሱናን መያዝ፣ የኢማሞችን ፈለግ መከተል እንዲሁም አላህና መልዕክተኛው ካስጠነቀቁት ነገር መጠንቀቅ ነው። በዚህ ውስጥ የባሪያዎች መስተካከል፣ ደስታቸውና በዱንያም ሆነ በአኺራ መዳናቸው ይገኛልና። በዚህ ጉዳይ ላይም አንዳንድ ሰዎች፤ የዋሻው ባለቤቶችን ታሪክ አስመልክቶ አላህ የተናገረውን እንደማስረጃ ተጠቅመዋል ፡
﴿...قَالَ ٱلَّذِينَ غَلَبُواْ عَلَىٰٓ أَمۡرِهِمۡ لَنَتَّخِذَنَّ عَلَيۡهِم مَّسۡجِدٗا﴾
{እነዚያ በነገራቸው ላይ ያሸነፉት ግን «በእነርሱ ላይ በእርግጥ መስጊድን እንሰራለን።» አሉ።} [አልከህፍ:21]
ለዚህም ምላሹ፦ አላህ በዚያ ዘመን የነበሩትን መሪዎችና የሥልጣን ባለቤቶች ይህንን ንግግር ማለታቸውን የጠቀሰው እነርሱን በመውደድና በማጽደቅ ሳይሆን፤ ይልቁንም እነርሱን ለመኮነን፣ ለማነወርና ከድርጊታቸው ለማሸሽ ነው። ለዚህም ማሳያው ይህ አንቀጽ የወረደላቸውና ፍቺውንም ከሰዎች ሁሉ በላይ የሚያውቁት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ህዝባቸውን መቃብርን መስገጃ አድርገው ከመያዝ መከልከላቸው፣ ከዚህም ድርጊት ማስጠንቀቃቸው፣ እንዲሁም ይህን የፈጸመን ሰው መርገማቸውና ማውገዛቸው ነው።
ይህ ነገር የተፈቀደ ቢሆን ኖሮ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ በብርቱ አያጠብቁም፣ ከዚህም አልፈው ፈጻሚውን አይረግሙም፣ ከፍ ያለውና የተከበረው አላህ ዘንድም ከፍጡራን ሁሉ ክፉ መሆኑን አይናገሩም ነበር። ይህም ለሀቅ ፈላጊ በቂና አሳማኝ ነው። በቀብር ላይ መስጊድ መገንባት ከእኛ በፊት ለነበሩት ህዝቦች የተፈቀደ ነበር ብለን ብንገምት እንኳን፤ በዚህ ተግባር እነርሱን መከተል ለኛ አይፈቀድልንም፤ ምክንያቱም የእኛ ሸሪዓ ከእኛ በፊት የነበሩ ሸሪዓዎችን የሚሽር ነውና። መልክተኛችንም ﷺ የመጨረሻው መልክተኛ ሲሆኑ ሸሪዓቸውም ሙሉና ሁሉን አቀፍ ነው። እርሳቸውም በቀብር ላይ መስጊድ ከመገንባት ከልክለውናል፤ ስለሆነም ትእዛዛቸውን መቃረን አይፈቀድልንም። በኛ ላይ ግዴታ የሚሆነው እርሳቸውን መከተል፣ ይዘውት የመጡትን አጥብቆ መያዝና ይህን የሚቃረኑ የቆዩ ሸሪዓዎችንና በሰሪዎቻቸው ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ ልማዶችን መተው ነው። ምክንያቱም ከአላህ ሸሪዓ የበለጠ ሙሉ ሸሪዓ የለምና፤ ከአላህ መልክተኛም (ﷺ) መመሪያ የተሻለ መመሪያ የለም።
አላህ እኛንም ሆነ መላ ሙስሊሞችን በሃይማኖቱ ላይ ፅናትንና የመልዕክተኛውን የሙሐመድን ﷺ ሸሪዓ አጥብቀን መያዝን፤ በንግግራችንም ሆነ በተግባራችን፣ በግልጽም ሆነ በስውር እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮቻችን ላይ ሁሉ፣ የላቀውን አላህ እስክንገናኝ ድረስ እንዲገጥመን እንለምነዋለን። እርሱ ሰሚና ቅርብ ነውና።
የአላህ ሰላትና ሰላም ባሪያውና መልክተኛው በሆኑት በሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸው እና እስከ ቂያማ ቀን ድረስ በቅን መንገዱ በተመሩት ላይ ሁሉ ይስፈን።
***
بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ
አስራ አንደኛ መልዕክት:
ሙታንን በመስጂዶች ውስጥ መቅበር
በአላህ ስም፤ ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላትና ሰላም በአላህ መልእክተኛ፣ በቤተሰቦቻቸውና እንዲሁም የእርሳቸውን ቅን ጎዳና በተከተለም ላይ ሁሉ ይስፈን። በመቀጠል፦
በ 17/4/1415 ዓ.ሂ የወጣችውን «አል-ኸርጡም» ጋዜጣ ተመልክቼ ነበር፤ በውስጧም አስ-ሰይድ ሙሐመድ አል-ሐሰን አል-ኢድሪሲ በኡምዱርማን ከተማ በሚገኘው መስጊዳቸው ከአባታቸው ጎን ስለመቀበራቸው …… የወጣ መግለጫ ታትሞ አግኝቻለሁ።
አላህ ለሙስሊሞች መካሪ መሆንን፣ መጥፎን ነገር መከልከልን እና ግልፅ ማድረግን ግዴታ ስላደረገ፤ በመስጂዶች ውስጥ መቅበር የማይፈቀድ ነገርና ይልቁንም ወደ ሺርክ ከሚያዳርሱ ነገሮች መካከል መሆኑን ለማስታወስ ወደድኩ። እንዲሁም አላህ በእርሱ የወቀሳቸውና የአላህ መልዕክተኛም ﷺ የረገሟቸው ከሆኑት ከአይሁዶችና ከክርስቲያኖች ተግባራትም ነው። በቡኻሪና ሙስሊም ከእናታችን ዓኢሻ (አላህ ስራዋን ይውደድላትና) እንደተዘገበው ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«لَعَنَ اللَّهُ الْيَهُودَ وَالنَّصَارَى، اتَّخَذُوا قُبُورَ أَنْبِيَائِهِمْ مَسَاجِدَ».
"አላህ አይሁድና ክርስቲያኖችን ረገመ። የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስጂድ አድርገው ያዙ።" በሶሒሕ ሙስሊምም ጁንዱብ ቢን ዐብዲላህ እንዳስተላለፉት ነብዩ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን - እንዲህ ብለዋል:
«أَلَا وَإِنَّ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ كَانُوا يَتَّخِذُونَ قُبُورَ أَنْبِيَائِهِمْ وَصَالِحِيهِمْ مَسَاجِدَ، أَلَا فَلَا تَتَّخِذُوا الْقُبُورَ مَسَاجِدَ؛ فَإِنِّي أَنْهَاكُمْ عَنْ ذَلِكَ».
"ንቁ! ከእናንተ በፊት የነበሩት የነቢያቶቻቸውንና የደጋጎቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው ይይዙ ነበር፤ ንቁ! መቃብሮችን መስገጃ አድርጋችሁ አትያዙ፤ እኔ ከዚህ ነገር እከለክላችኋለሁና።" ይህንን መልዕክት ይዘው የመጡ ሐዲሦች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው።
በመሆኑም በየትኛውም ቦታ በሚገኙ ሙስሊሞች ላይ - መንግስታትም ሆኑ ህዝቦች - አላህን መፍራት፣ እርሱ ከከለከለው ነገር መጠንቀቅና ነቢዩ ﷺ እና ባልደረቦቻቸው (አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና) እና እነርሱን በመልካም የተከተሉት ሟቾችን ከመስጂዶች ውጭ ይቀብሩ እንደነበረው ሁሉ ሟቾቻቸውን ከመስጂዶች ውጭ መቅበር ግዴታ ነው።
የነብዩ ﷺ እና የሁለቱ ባልደረቦቻቸው የአቡበክርና የዑመር (አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና) ቀብር በእርሳቸው መስጂድ ውስጥ መገኘቱ ሙታንን በመስጂዶች ውስጥ ለመቅበር ማስረጃ አይሆንም። ምክንያቱም እርሳቸው ﷺ የተቀበሩት በቤታቸው - በአዒሻ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ቤት ውስጥ - ነውና። ከዚያም ሁለቱ ባልደረቦቻቸው ከእርሳቸው ጋር ተቀበሩ። ወሊድ ኢብን ዐብዱልመሊክ ከሂጅራ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ መስጂዱን ሲያሰፋ ክፍሉን ከመስጂዱ ጋር አካተተው። የእውቀት ሰዎችም ይህን ድርጊቱ አውግዘውበት ነበር። ነገር ግን እርሱ ይህ መስጂዱን ከማስፋፋት እንደማይከለክልና ጉዳዩም ግልፅና የማያሻማ እንደሆነ አስቧል።
በዚህም ለእያንዳንዱ ሙስሊም ግልፅ የሚሆነው፤ እርሳቸው ﷺ እና ሁለቱ ባልደረቦቻቸው (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) መስጂድ ውስጥ አለመቀበራቸው ነው። በመስጂዱ የማስፋፊያ ስራ ምክንያት ወደ መስጂዱ ግዛት ውስጥ መካተታቸው በመስጂዶች ውስጥ መቅበር እንደሚፈቀድ ማስረጃ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም እነርሱ የተቀበሩት መስጂድ ውስጥ ሳይሆን በሳቸው ﷺ ቤት ውስጥ ነውና። እንዲሁም የወሊድ ስራ በዚህ ጉዳይ ላይ ለማንም ሰው ማስረጃ ሊሆን አይችልም። ይልቁንም ማስረጃው ቁርአን እና ሐዲሥ እንዲሁም የኡማው ቀደምት ሰለፎች ስምምነት (ኢጅማዕ) ነው። አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እኛንም በበጎ መልኩ ከተከታዮቻቸው ያድርገን።
ምክርን ለመለገስና ኃላፊነትን ለመወጣት ሲባል በ14/5/1415 ሂ. ተጻፈ (ተዘጋጀ)።
ለመልካም የመገጠም ባለቤቱ አላህ ነው። የአላህ ሶላትና ሰላም በነቢያችን ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና ባልደረቦቻቸው እንዲሁም በመልካም በተከተሏቸው ላይ ሁሉ ይስፈን።
***
بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ
አስራ ሁለተኛው መልእክት:
ከነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ሸሪዓ መውጣት ይፈቀዳል ብሎ የሚሞግት ሰው እንደካደ እና እንደጠመመ ማብራሪያ:
ምስጋና ሁሉ የዓለማት ጌታ ለሆነው አላህ የተገባ ነው። ሶላትና ሰላም በነቢያትና መልክተኞች መደምደሚያ በሆኑት ነብያችን ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸውም ላይ ሁሉ ይስፈን።
በመቀጠል፦ በአሽ-ሸርቅ አል-አውሰጥ ጋዜጣ በቀን 5/6/1415 ዓ.ሂ በወጣው ቁጥር (5824) እትሙ ላይ፣ ራሱን ዐብዱልፈታሕ አል-ሓይክ ብሎ በሰየመው ሰው “የተሳሳተ ግንዛቤ” በሚል ርዕስ የተጻፈውን ጽሑፍ ተመልክቼዋለሁ።
የጽሑፉ ማጠቃለያ፡ በእስልምና ሃይማኖት በግልፅ መረጃና በዑለማዎች ባጠቃላይ የጋራ ስምምነት ሙስሊም በመሆን ብቻ የግዴታ የሚታወቅን ጉዳይ ማውገዙ ነው። ይኸውም የሙሐመድ ﷺ ተልዕኮ ለሁሉም ሰዎች አጠቃላይ መሆኑን በማስተባበል ሙሐመድን ﷺ ያልተከተለና ያልታዘዛቸው፣ ይልቁንም አይሁድ ወይም ክርስቲያን ሆኖ የቀረ ሰው በትክክለኛ ሃይማኖት ላይ ነው ብሎ መሞገቱ ነው፤ ከዛም አልፎ ከሓዲዎችንና ዓመፀኞችን በመቅጣት ባለው የዓለማት ጌታ (ጥራት ይገባውና) ጥበብ ላይ ድንበር ማለፉና ይህንንም ከንቱ ድርጊት እና ጨዋታ አድርጎ መቁጠሩ ነው።
ይህ ግለሰብ ሸሪዓዊ ማስረጃዎችን አጣምሞ አቅርቧል፣ ከአውዳቸውም ውጭ አስቀምጧቸዋል፤ ስሜቱ በሚያዘውም መልኩ ተርጉሟቸዋል። የሙሐመድ ﷺ መልዕክት ሁሉን አቀፍ መሆኑን፣ ስለ እርሳቸው ሰምቶ ያልተከተለ ሰው ካፊር መሆኑን፣ አላህም ከእስልምና ውጭ ሌላ ሃይማኖትን እንደማይቀበልና የመሳሰሉትን የሚያመለክቱ ግልፅ የሆኑ ሸሪዓዊ ማስረጃዎችንና ጽሑፎችን ቸል ብሏል፤ ይህም መሃይማኖች በንግግሩ እንዲታለሉ ነው። ይህ የፈጸመው ድርጊት ግልጽ ክህደት፣ ከእስልምና መውጣት፣ እንዲሁም ከጉድለት የጠራውንና ከፍ ያለውን አላህንና መልእክተኛውን ﷺ ማስተባበል ነው፤ ይህንንም ከእውቀትና ከኢማን ባለቤቶች ውስጥ ጽሑፉን ያነበበ ሰው ሁሉ ያውቀዋል።
የአገሪቱ ገዢ ያለበት ግዴታ ተውበት እንዲያደርግ እንዲጠየቅና በንፁሁ ሸሪዓ በተደነገገው መሰረት እንዲፈረድበትም ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ ነው።
የላቀው አላህም የሙሐመድ ﷺ መልእክተኝነት አጠቃላይ መሆኑን፣ እርሳቸውን መከተል ለሰውና ለጋኔን ባጠቃላይ ግዴታ መሆኑን በእርግጥ ገልጿል። ይህንንም ከሙስሊሞች መካከል ትንሽም ቢሆን እውቀት ያለው ሰው አይሰወርበትም።
የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿قُلۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنِّي رَسُولُ ٱللَّهِ إِلَيۡكُمۡ جَمِيعًا ٱلَّذِي لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ يُحۡيِۦ وَيُمِيتُۖ فَـَٔامِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِ ٱلنَّبِيِّ ٱلۡأُمِّيِّ ٱلَّذِي يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَكَلِمَٰتِهِۦ وَٱتَّبِعُوهُ لَعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ158﴾
{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደ ሁላችሁም የአላህ መልዕክተኛ ነኝ:: እርሱም ያ የሰማያትና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነ ነው:: እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም:: ህያው ያደርጋል:: ይገድላልም:: በአላህ በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ ነቢይ በሆነው መልዕክተኛውም እመኑ:: ወደ ቅኑ መንገድ ትመሩ ዘንድም ተከተሉት።» በላቸው::} [አል‐አዕራፍ: 158] የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿...وَأُوحِيَ إِلَيَّ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانُ لِأُنذِرَكُم بِهِۦ وَمَنۢ بَلَغَ...﴾
{…ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውን ሰው ሁሉ በርሱ ላስፈራራበት ወደኔ ተወረደ።…} [አልአንዓም፡ 19] የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿قُلۡ إِن كُنتُمۡ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِي يُحۡبِبۡكُمُ ٱللَّهُ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡ ذُنُوبَكُمۡۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ31﴾
{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)፡- «አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ እኔን ተከተሉኝ:: አላህም ይወዳችኋል፤ ኃጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።» በላቸው።} [አሊ ዒምራን: 31] የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿وَمَن يَبۡتَغِ غَيۡرَ ٱلۡإِسۡلَٰمِ دِينٗا فَلَن يُقۡبَلَ مِنۡهُ وَهُوَ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ85﴾
{ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይነት የለዉም:: እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው::} [አሊ-ዒምራን፡ 85] የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿وَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ إِلَّا كَآفَّةٗ لِّلنَّاسِ بَشِيرٗا وَنَذِيرٗا...﴾
{አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አልላክንህም...} [ሰበእ፡ 28] የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿وَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ إِلَّا رَحۡمَةٗ لِّلۡعَٰلَمِينَ107﴾
{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማት እዝነት አድርገን እንጂ አልላክንህም::} [አል-አንቢያእ: 107] የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿...وَقُل لِّلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡأُمِّيِّـۧنَ ءَأَسۡلَمۡتُمۡۚ فَإِنۡ أَسۡلَمُواْ فَقَدِ ٱهۡتَدَواْۖ وَّإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنَّمَا عَلَيۡكَ ٱلۡبَلَٰغُۗ وَٱللَّهُ بَصِيرُۢ بِٱلۡعِبَادِ﴾
{ለእነዚያም መጽሐፉን ለተሰጡት ሰዎችና ለመሐይሞቹ፡- «ሰለማችሁን?» በላቸው:: ቢሰልሙም በእርግጥ (ወደቀናው መንገድ) ተመሩ:: እምቢ ቢሉ ግን ባንተ ላይ ያለብህ ማድረስ ብቻ ነው:: አላህም ባሮቹን ተመልካች ነው።} [አሊ-ዒምራን: 20] የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿تَبَارَكَ ٱلَّذِي نَزَّلَ ٱلۡفُرۡقَانَ عَلَىٰ عَبۡدِهِۦ لِيَكُونَ لِلۡعَٰلَمِينَ نَذِيرًا1﴾
{ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይሆን ዘንድ ያወረደው (አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው።} [አል-ፉርቃን: 1]
ቡኻሪና ሙስሊምም ከጃቢር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደዘገቡት ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«أُعْطِيتُ خَمْسًا لَمْ يُعْطَهُنَّ أَحَدٌ قَبْلِي: نُصِرْتُ بِالرُّعْبِ مَسِيرَةَ شَهْرٍ، وَجُعِلَتْ لِيَ الْأَرْضُ مَسْجِدًا وَطَهُورًا، فَأَيُّمَا رَجُلٍ مِنْ أُمَّتِي أَدْرَكَتْهُ الصَّلَاةُ، فَلْيُصَلّ، وَأُحِلَّتْ لِيَ الْمَغَانِمُ، وَلَمْ تُحَلَّ لِأَحَدٍ قَبْلِي، وَأُعْطِيتُ الشَّفَاعَةَ، وَكَانَ النَّبِيُّ يُبْعَثُ إِلَى قَوْمِهِ خَاصَّةً، وَبُعِثْتُ إِلَى النَّاسِ عَامَّةً».
"ከኔ በፊት አንድም አካል ያልተሰጠው አምስት ነገሮችን ለኔ ተሰጥተውኛል፤ የወር መንገድ ሲቀር (ጠላቶች ውስጥ) ፍርሃት በመክተት ተረድቻለሁ፤ ምድር ለኔ መስገጃም ንፅህና መጠበቂያም ተደርጋልኛለች፤ ስለዚህ ከኡመቴ ማንኛውም ሰው ሶላት ከደረሰችበት ይስገድ። ምርኮ ለኔ ተፈቅዷል፤ ከኔ በፊት ለአንድም አካል አልተፈቀደችም። ምልጃ ተሰጥቶኛል። ነቢይ የሚላከው ወደ ህዝቦቹ ብቻ ነበር። እኔ ግን ወደ ሰው ባጠቃላይ ተልኬያለሁ።"
ይህም የነቢያችን ሙሐመድ ﷺ መልክተኝነት ለሰው ልጆች ሁሉ አጠቃላይና ሁሉን አቀፍ መሆኑን፣ የቀድሞ ድንጋጌዎችን በሙሉ መሻሩንና እርሳቸውን ያልተከተለና ያልታዘዘ ሰውም ከሃዲና አመጸኛ በመሆኑ ቅጣቱ የሚገባው መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿...وَمَن يَكۡفُرۡ بِهِۦ مِنَ ٱلۡأَحۡزَابِ فَٱلنَّارُ مَوۡعِدُهُۥ...﴾
{…ከአህዛቦቹ በእርሱ የሚክድ ሰው መመለሻው እሳት ናት…} [ሁድ፡ 17] የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿...فَلۡيَحۡذَرِ ٱلَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنۡ أَمۡرِهِۦٓ أَن تُصِيبَهُمۡ فِتۡنَةٌ أَوۡ يُصِيبَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٌ﴾
{…እነዚያም ትእዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ::} [አን-ኑር፡ 63] የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿وَمَن يَعۡصِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَيَتَعَدَّ حُدُودَهُۥ يُدۡخِلۡهُ نَارًا خَٰلِدٗا فِيهَا وَلَهُۥ عَذَابٞ مُّهِينٞ14﴾
{አላህንና መልዕክተኛውንም የሚያምጽ ወሰኖቹንም የሚተላለፍ በውስጧ ዘውታሪ ሲሆን እሳት ያስገባዋል:: ለእርሱም አዋራጅ ቅጣት አለበት።} [አንኒሳእ፡ 14] የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿...وَمَن يَتَبَدَّلِ ٱلۡكُفۡرَ بِٱلۡإِيمَٰنِ فَقَدۡ ضَلَّ سَوَآءَ ٱلسَّبِيلِ﴾
{…በእምነት ክህደትን የሚለውጥ ሰው በእርግጥ ትክክለኛውን መንገድ ስቷል፡፡} [አል-በቀራ፡ 108] በዚህ ዙሪያ የመጡ ቁርአናዊ ማስረጃዎች በርካታ ናቸው።
ጥራት የተገባው አላህ መልዕክተኛውን ﷺ መታዘዝ ከራሱ መታዘዝ ጋር አቆራኝቷል፤ እንዲሁም ከኢስላም ሌላን ሃይማኖት አድርጎ የያዘ ሰው ከሳሪ መሆኑንና ከእርሱ ምንም ዓይነት ግዴታም ትርፍ አምልኮዎቹን እንደማይቀበል አብራርቷል። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَمَنْ يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَنْ يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ 85﴾
{ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለዉም:: እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው::} [አሊ-ዒምራን፡ 85] ጥራት ይገባውና እንዲህም ብሏል፡
﴿مَنْ يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ...﴾
{መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ በእርግጥ አላህን ታዘዘ::} [አን-ኒሳእ፡ 80] የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿قُلْ أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ فَإِنْ تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا عَلَيْهِ مَا حُمِّلَ وَعَلَيْكُمْ مَا حُمِّلْتُمْ وَإِنْ تُطِيعُوهُ تَهْتَدُوا...﴾
{«አላህን ታዘዙ፤ መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: ብትሸሹም አትጎዱትም:: በእርሱ ላይ ያለበት የተገደደውን ማድረስ ብቻ ነው:: በእናንተም ላይ ያለባችሁ የተገደዳችሁትን መታዘዝ ብቻ ነው:: ብትታዘዙትም ትመራላችሁ።» በላቸው።} [አን-ኑር፡ 54] የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:
﴿إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَالْمُشْرِكِينَ فِي نَارِ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا أُولَئِكَ هُمْ شَرُّ الْبَرِيَّةِ 6﴾
{እነዚያ ከመጽሐፉ ሰዎች የካዱት፣ አጋሪዎቹም በገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው:: በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ መጥፎዎቹ እነርሱ ናቸው::} [አል-በይናህ፡ 6]
ሙስሊም በሶሒሓቸው እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ؛ لَا يَسْمَعُ بِي أَحَدٌ مِنْ هَذِهِ الْأُمَّةِ، يَهُودِيٌّ وَلَا نَصْرَانِيٌّ، ثُمَّ يَمُوتُ وَلَمْ يُؤْمِنْ بِالَّذِي أُرْسِلْتُ بِهِ؛ إِلَّا كَانَ مِنْ أَهْلِ النَّارِ».
"ያ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ ኡመት ውስጥ አንድም አይሁድ ይሁን ክርስቲያን ስለኔ ሰምቶ ከዚያም በዛ በተላኩበት ሳያምን የሚሞት የለም፤ ከእሳት ሰዎች መካከል ቢሆን እንጂ።"
የአላህ መልዕክተኛም ﷺ ወደ እስልምና እምነት ያልገባን ሰው ሃይማኖት ውድቅ መሆኑን በተግባራቸውና በንግግራቸው ገልፀዋል። ከክርስቲያኖችና አይሁዶች ውጪ ያሉ ከሃዲያንን እንደተዋጉ ሁሉ አይሁዶችንና ክርስቲያኖችንም ተዋግቷል። ከነርሱ መካከል ጂዝያ የሰጡትነ ተቀብለዋል። ይህም የሆነው ጥሪው (ዳዕዋው) ወደ ቀሪዎቹ ህዝቦቻቸው ከመድረስ እንዳይከለክሉና እንዲሁም ከነርሱ መካከል ወደ እስልምና መግባት የፈለገ ሰው ህዝቦቹ ያቅቡኛል፣ ይከለክሉኛል ወይም ይገድሉኛል ብሎ ሳይፈራ ወደ እስልምና እንዲገባ ነው።
ቡኻሪና ሙስሊም ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንደዘገቡት እንዲህ ብለዋል፦ «እኛ መስጂድ ውስጥ ሳለን የአላህ መልክተኛ ﷺ በመውጣት እንዲህ አሉ፦»
«انْطَلِقُوا إِلَى يَهُودَ، فَخَرَجْنَا مَعَهُ حَتَّى جِئْنَا بَيْتَ الْمِدْرَاسِ، فَقَامَ النَّبِيُّ ﷺ، فَنَادَاهُمْ فَقَالَ :يَا مَعْشَرَ يَهُودَ، أَسْلِمُوا تَسْلَمُوا، فَقَالُوا: قَدْ بَلَّغْتَ يَا أَبَا الْقَاسِمِ، فَقَالَ لَهُمْ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ: ذَلِكَ أُرِيدُ، أَسْلِمُوا تَسْلَمُوا، فَقَالُوا: قَدْ بَلَّغْتَ يَا أَبَا الْقَاسِمِ، فَقَالَ لَهُمْ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ: ذَلِكَ أُرِيدُ، ثُمَّ قَالَهَا الثَّالِثَةَ...».
«"ወደ አይሁዶች ተጓዙ።" እናም ከእርሳቸው ጋር ወጥተን ቤተ አምልኳቸው ደረስን። ነቢዩም ﷺ ቆመው ጠሯቸውና እንዲህ አሉ፦ «እናንተ አይሁዶች ሆይ! ስለሙ፤ ትድናላችሁ።» እነርሱም፦ «አቡል ቃሲም ሆይ! በእርግጥ አድርሰሃል» አሉ። የአላህ መልክተኛም ﷺ፦ «የምፈልገው ይህንኑ ነው። ስለሙ፤ ትድናላችሁ» አሏቸው። እነርሱም፦ «አቡል ቃሲም ሆይ! በእርግጥ አድርሰሃል» አሉ። የአላህ መልክተኛም ﷺ፦ «የምፈልገው ይህንኑ ነው» አሉ፤ ከዚያም ለሶስተኛ ጊዜ ይህንኑ ደገሙት...» ሐዲሥ።
ዋናው የሐዲሡ ፍሬ ሃሳብ፡ እርሳቸው ﷺ የአይሁዶች የሃይማኖት ሰዎች ዘንድ ትምህርት ቤታቸው ድረስ ሄደው ወደ እስልምና ጠሯቸው፤ እንዲህም አሏቸው፡ «ስለሙ፤ ትድናላችሁ»። ይህንንም ደጋግመው ነገሯቸው።
በተመሳሳይም ወደ ሒረቅል ደብዳቤ ልከው ወደ እስልምና ጠሩት፤ እምቢተኛ ከሆነም እርሱ እምቢተኛ በመሆኑ ምክንያት ከእስልምና የታቀቡትን ሰዎች ኃጢአት እንደሚሸከም አሳወቁት። ቡኻሪና ሙስሊም እንደዘገቡት፤ ሒረቅል የአላህ መልዕክተኛን ﷺ ደብዳቤ አስጠርቶ አነበበው፤ በውስጡም እንዲህ የሚል ነበር፦
«بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ، مِنْ مُحَمَّدٍ رَسُولِ اللَّهِ إِلَى هِرَقْلَ عَظِيمِ الرُّومِ، سَلَامٌ عَلَى مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَى، أَمَّا بَعْدُ: فَإِنِّي أَدْعُوكَ بِدِعَايَةِ الْإِسْلَامِ، أَسْلِمْ تَسْلَمْ، وَأَسْلِمْ يُؤْتِكَ اللَّهُ أَجْرَكَ مَرَّتَيْنِ، فَإِنْ تَوَلَّيْتَ، فَإِنَّ عَلَيْكَ إِثْمَ الْأَرِيسِيِّينَ وَ
"በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። ከአላህ መልዕክተኛ ሙሐመድ የሮም ታላቅ ለሆነው ሂረቅል፤ ቅኑን መንገድ በተከተለ ላይ ሰላም ይስፈን። ከዚህ በመቀጠል፡ የእስልምናን ጥሪ አቀርብልሃለሁ። ስለም፤ ሰላም ታገኛለህ፤ እስልምናን ብትቀበል አላህ ምንዳህን ሁለት ጊዜ ይሰጥሃል። ከዚህ ጀርባህን ብትሰጥ ግን፣ የተከታዮችህ ኃጢያት ባንተ ላይ ይሆናል።"
﴿يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ تَعَالَوۡاْ إِلَىٰ كَلِمَةٖ سَوَآءِۭ بَيۡنَنَا وَبَيۡنَكُمۡ أَلَّا نَعۡبُدَ إِلَّا ٱللَّهَ وَلَا نُشۡرِكَ بِهِۦ شَيۡـٔٗا وَلَا يَتَّخِذَ بَعۡضُنَا بَعۡضًا أَرۡبَابٗا مِّن دُونِ ٱللَّهِۚ فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَقُولُواْ ٱشۡهَدُواْ بِأَنَّا مُسۡلِمُونَ64﴾
{የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ሆነችው ቃል ኑ። (እርሷም) ‹አላህን ብቻ እንጂ ሌላን ላንገዛ፤ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፤ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይዝ› ነው።» በላቸው። እምቢ ካሉም «እኛ ሙስሊሞች መሆናችንን መስክሩ።» በሏቸው።} [አሊ-ዒምራን፡ 64]»
ከዚያም ፊታቸውን አዙረው ወደ እስልምና ለመግባት እምቢ ባሉ ጊዜ፤ እርሳቸው ﷺ እና ሶሓቦቻቸው - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - ተዋጓቸው፤ ጂዝያንም በላያቸው ላይ ጣሉባቸው።
እነርሱ በጥመት ላይ መሆናቸውንና ሃይማኖታቸውም በነብዩ ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሃይማኖት ከተሻረ በኋላ የሐሰት መሆኑን ለማረጋገጥ፤ አላህ አንድ ሙስሊም በየቀኑ፣ በየሰላቱ እና በየረከዓው ትክክለኛና ተቀባይነት ወዳለው ወደ ቀጥተኛው መንገድ እንዲመራው እንዲጠይቀው አዟል፤ እሱም እስልምና ነው። እንዲሁም በጥመት ላይ መሆናቸውን እያወቁ በርሱ ላይ የሚፀኑ ከሆኑት አይሁዶችና መሰሎቻቸው አላህ ከተቆጣባቸው ሰዎች መንገድ እንዲያርቀው እንዲጠይቀው አዟል፤ ከነዚያ ያለ ዕውቀት ከሚገዙት፤ እነርሱ በመሳሳት መንገድ ላይ ሆነው ሳለ በቅን መንገድ ላይ እንደሆኑ ከሚሞግቱት የተሳሳቱ ሰዎች መንገድ እንዲያርቀው እንዲጠይቀው አዟል። እነርሱም፡ ክርስቲያኖችና ከሌሎች ህዝቦችም ሆነው በመሳሳትና ባለማወቅ እየተገዙ እነርሱን የሚመሳሰሉ ሁሉ ናቸው። ይህም ሁሉ ሙስሊም ከእስልምና ውጭ ያለ ማንኛውም ሃይማኖት ውድቅ መሆኑን እና ከእስልምና ውጭ በሆነ መንገድ አላህን የሚያመልክ ሁሉ የጠመመ መሆኑን በእርግጠኝነት እንዲያውቅ ነው። ይህን ያላመነ ሰው ከሙስሊሞች አይደለም። በዚህ ርዕስ ዙሪያ ከቁርኣንና ከሐዲሥ የመጡ ማስረጃዎች በርካታ ናቸው።
በመሆኑም በጽሑፉ ባለቤት -በአብዱል ፈታህ- ላይ ግዴታው፦ ወደ ንፁህ ተውበት መቻኮል እና ተውባውን የሚገልጽበትን ጽሑፍ መጻፍ ነው። ወደ አላህ እውነተኛ ተውበት በማድረግ የተመለሰ ሰው አላህ ጸጸቱን ይቀበለዋል፤ ጥራት የተገባው አላህ እንዲህ ብሏልና፦
﴿...وَتُوبُوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ لَعَلَّكُمۡ تُفۡلِحُونَ﴾
{…ምዕመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ ተጸጸቱ::} (አን-ኑር 31) የላቀው አላህ እንዲህም ይላል፦
﴿وَٱلَّذِينَ لَا يَدۡعُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ وَلَا يَقۡتُلُونَ ٱلنَّفۡسَ ٱلَّتِي حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلۡحَقِّ وَلَا يَزۡنُونَۚ وَمَن يَفۡعَلۡ ذَٰلِكَ يَلۡقَ أَثَامٗا68 يُضَٰعَفۡ لَهُ ٱلۡعَذَابُ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَيَخۡلُدۡ فِيهِۦ مُهَانًا69 إِلَّا مَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ عَمَلٗا صَٰلِحٗا فَأُوْلَٰٓئِكَ يُبَدِّلُ ٱللَّهُ سَيِّـَٔاتِهِمۡ حَسَنَٰتٖۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمٗا70﴾
{[እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደርጋትን ነፍስ ያለ ህግ የማይገድሉ እና የማያመነዝሩት ናቸው:: ይህንንም የሚሰራ ሰው ቅጣት ያገኛል::
በትንሳኤ ቀን ቅጣት ይደራረብበታል:: በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ሆኖ ይኖራል::
ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ስራ የሰራ ሰው ብቻ ሲቀር እነዚያም አላህ መጥፎ ስራዎቻቸውን በመልካም ስራዎች ይለውጣል:: አላህም እጅግ መሓሪና አዛኝ ነው::} [አል-ፉርቃን: 68-70] ነቢዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«الإِسْلَامُ يَهْدِمُ مَا كَانَ قَبْلَهُ، وَالتَّوبَةُ تَهْدِمُ مَا كَانَ قَبْلَهَا».
"እስልምና ከእርሱ በፊት የነበረውን (ወንጀል) ያፈርሳል፤ ተውበትም ከእርሱ በፊት የነበረውን ታፈርሳለች።" ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«التَّائِبُ مِنَ الذَّنْبَ كَمَنْ لَا ذَنْبَ لَهُ».
«ከወንጀል ተመላሽ ወንጀል እንደሌለው ሰው ነው።»
ይህንን መልዕክት ይዘው የመጡ የቁርኣን አንቀጾችና ሐዲሦች በርካታ ናቸው።
ከፍ ያለውና የጠራው አላህ ሐቅን ሐቅ መሆኑን እንዲያሳየንና መከተሉንም እንዲወፍቀን፤ ጥመትንም ጥመት መሆኑን እንዲያሳየንና መራቁንም እንዲወፍቀን፤ በእኛም ላይ፣ በጸሐፊው ዐብዱልፈታሕም ላይ እንዲሁም በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ንፁህ የሆነችውን ተውባ እንዲለግሰን፤ ሁላችንንም ከአሳሳች ፈተናዎች እንዲሁም ስሜትንና ሸይጧንን ከመከተል እንዲጠብቀን እማፀነዋለሁ። እነሆ እርሱ ለዚህ ተማፅኖ የተገባ እውን ሊያደርገው ቻይም እርሱ ነውና።
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያችን ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸው እና እስከ ቂያማ ቀን ድረስ በመልካም በተከተሏቸው ላይ ሁሉ ይስፈን።
***
ማውጫ
ትክክለኛ ዐቂዳ እና ተቃራኒው 2
የመጀመሪያው መሰረት: የበላይ በሆነው አላህ ማመን 6
ሁለተኛው መሰረት፦ በመላእክቶች ማመን: 22
ሦስተኛው መሠረት፦ በመጽሐፍቱ ማመን፣ እርሱም በተመሳሳይ ሁለት ነገሮችን ያጠቃልላል፦ 24
አራተኛው መሠረት፡ በመልዕክተኞች ማመን 27
አምስተኛው መሰረት፡ በመጨረሻው ቀን ማመን 28
ስድስተኛው መሰረት፡ በቀደር ማመን 29
ትክክለኛውን ዐቂዳ የሚፃረሩ የሆኑ እምነቶች 36
ሁለተኛው መልዕክት፡ ከነቢዩ ﷺ እርዳታ የመፈለግ ብይን 46
ሦስተኛው መልዕክት: 65
ጂኒዎችና ሰይጣናትን እርዳታን መለመንና ለእነርሱ ስለት መግባት ያለው ብይን:- 65
አራተኛው መልዕክት፡ 88
በቢድዓዊና ሽርካዊ አውራዶች አላህን መገዛት ያለው ብይን: 88
አምስተኛው መልዕክት፡ 117
የነብዩን ﷺ መውሊድና ሌሎች መውሊዶችን የማክበር ብይን 117
ስድስተኛው መልእክት፡ 130
የኢስራእ እና ሚዕራጅን ሌሊት የማክበር ህግ 130
ሰባተኛው መልእክት፡ 138
የሸዕባን ወር አጋማሽ ሌሊትን የማክበር ህግ 138
ስምንተኛው መልዕክት፡ 155
በውሸት ስለተነገረው ኑዛዜ የተሰጠ አስፈላጊ ማሳሰቢያ 155
ለሐረመ ነበዊ አሸሪፍ አገልጋይ ሸይኽ አሕመድ 155
ዘጠነኛው መልዕክት፦ የድግምት እና የጥንቆላ ብይን እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች 172
አስረኛው መልዕክት፦ መቃብሮች ላይ መስጂዶችን ከመገንባት ማስጠንቀቅ 191
አስራ አንደኛ መልዕክት: ሙታንን በመስጂዶች ውስጥ መቅበር 198
አስራ ሁለተኛው መልእክት: ከነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ሸሪዓ መውጣት ይፈቀዳል ብሎ የሚሞግት ሰው እንደካደ እና እንደጠመመ ማብራሪያ: 202
***
am397v4.0 - 21/04/2026
ቡኻሪ በቁጥር (2856) እና ሙስሊም በቁጥር (30) ዘግበውታል።
አል-ላለካኢይ በሸርሕ ኡሱል አል-ኢዕቲቃድ (735) ዘግበውታል፤ ኢብኑ ዐብዱልበርም በጃሚዕ አል-ዒልም ወፈድሊሂ (1801) ዘግበውታል፤ የኢብኑ ዐብዱልበር ዘገባ ግን “አያት አስ-ሲፋት” ከሚለው ይልቅ “አል-አሓዲሥ” በሚል ቃል ነው፤ ቃሉም፡ "እነዚህን ሓዲሦች እንደመጡት ዘግቧቸው፤ በእነርሱም ላይ አትከራከሩባቸው።"
አል-በይሀቂይ በአል-አስማእ ወስ-ሲፋት (865) ዘግበውታል፤ ኢብኑ ተይሚያህ በአል-ሐመዊያህ (269) ሰነዱን ሶሒሕ ብለውታል፤ ዘሀቢም በአል-ዐርድ (2/223) “ዘጋቢዎቹ ታማኝ ኢማሞች ናቸው።” ብለዋል።
አል-ላለካኢ በ "ሸርህ ኡሱል አል-ኢዕቲቃድ" (930)፣ በይሀቂይም በ "አል-አስማእ ወስ-ሲፋት" (955) ዘግበውታል።
አል-ላለካኢይ በ “ሸርሕ ኡሱል አል-ኢዕቲቃድ” (665) ዘግበውታል፤ አል-በይሀቂም በ “አል-አስማእ ወስ-ሲፋት” (868) ዘግበውታል።
አል-ላለካኢ በ"ሸርሕ ኡሱል አል-ኢዕቲቃድ" (664) ላይ ዘግበውታል፤ አቡ ኑዐይም በ"ሒልየቱል አውሊያእ" (325/6) ላይ ዘግበውታል፤ አል-በይሀቂም በ"አል-አስማእ ወስ-ሲፋት" (867) ላይ ዘግበውታል።
አል-ሙዘኪይ በአል-ሙዘኪያት (29)፣ ኢብኑ በጦህ በአል-ኢባናህ (120) እና አል-ላለካኢይ በሸርሕ ኡሱል አል-ኢዕቲቃድ (663) ላይ ዘግበውታል።
ዳሪሚይ በአር-ረድ ዐለል ጀህሚየህ (67) እንዲሁም በይሀቂይ በአል-አስማእ ወስ-ሲፋት (903) ዘግበውታል።
ዘሀቢ በ "አል-ዑሉው" (464) የዘገቡት ሲሆን አልባኒም በ "ሙኽተሶር አል-ዑሉው" (ገጽ: 184) ላይ “ይህ ሰነድ ሶሒሕ ነው፤ ዘጋቢዎቹ ታማኝና የሚታወቁ ናቸው።” ብለዋል።
ተፍሲር ኢብኑ ከሢር (3/426 እና 427)
ቡኻሪይ በቁጥር (22) ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ ረዲየላሁ ዐንሁ ዘግበውታል።
ሙስሊም(2996) ከዓኢሻ አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና ዘግቦታል።
ቡኻሪይ በቁጥር (3651) እና ሙስሊም በቁጥር (2533) ከዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ ዘግበውታል።
ሙስሊም (1920) ከሠውባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ሐዲስ ዘግበውታል።
ኢብኑ ማጃህ (3952) ከሠውባን ረዲየላሁ ዐንሁ ሐዲስ ዘግበውታል፤ ኢብኑ ሒባንም (6714) ሐኪምም (8653) ሶሒሕ ብለውታል።
ቲርሚዚይ (2641) ከዐብደላህ ኢብኑ ዐምር ረዲየላሁ ዐንሁ ዘግበውታል። ሙናዊይም በ “ፈይዱል ቀዲር” (5/347) ላይ “በሰነዱ ውስጥ ዐብዱራሕማን ኢብኑ ዚያድ አል-ኢፍሪቂ አለ፤ ዘሀቢይ ‘ዶዒፍ ብለውታል’ ብሏል” ብለዋል። አልባኒይም በ “ሶሒሑል ጃሚዕ” (5343) ሶሒሕ ብለውታል።
ይህች መልዕክት (ወሲያ) በ1402 ዓ.ሂ ከዕውቀታዊ ምርምር፣ ፈትዋ፣ ዳዕዋና ኢርሻድ ጠቅላይ መምሪያ አማካኝነት በቁጥር 17 ኩራሳ (ቡክሌት) ታትማ ወጥታለች።
ሙስሊም በቁጥር (8) ዘግበውታል።