PHPWord

 

 

 

فَضْلُ عَشْرِ ذِي الحِجَّةِ

 

የዙል ሒጃ አስሩ ቀናት ትሩፋት

 

 

 

 

 

 

اللَّجْنَةُ العِلْمِيَّةُ

بِرِئَاسَةِ الشُّؤُونِ الدِّينِيَّةِ بِالمَسْجِدِ الحَرَامِ وَالمَسْجِدِ النَّبَوِيِّ

 

በመስጂደል ሐረም እና በመስጂድ አን-ነበዊይ

በሃይማኖት ዘርፍ የዕውቀት ነክ ጉዳዮች

ርዕሰ መስተዳድር ኮሚቴ ያዘጋጀው

 

 


بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ

መግቢያ

ምስጋና ለዓለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላትና ሰላም የዓለማት እዝነት ተደርገው በተላኩት ነቢይ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸውና እስከ እለተ ትንሳኤ ድረስ የርሳቸውን ሱንና (ፈለግ) በተከተሉና በመመሪያቸው በተመሩ ላይ ይስፈን። በመቀጠል:

ይህች መልዕክት ማንኛውም ሙስሊም አስሩን የዙልሒጃ ቀናት ያላቸውን ደረጃ አስመልክቶ ሊያውቃቸው የሚገቡ (ቁም ነገሮችን) አጠር ባለ መልኩ ሰብስባ የያዘች ሲሆን ሁለቱን ቅዱስ ስፍራዎችን ለሚጎበኙ ወንዶችና ሴቶች ዲናቸውን በዕውቀትና በግልፅ መረጃ ላይ ሆነው እንዲይዙ ያዘጋጀናት አጭር ጽሑፍ ነች። ቸርና ለጋስ የሆነው አላህ ጠቃሚ ሊያደርጋት፣ ለርሱ ብቻ የተሰራች በጎ ስራ ያደርግልን ዘንድ እንማፀነዋለን። እነሆ ቢለምኑት ደግ ተስፋ ቢያደርጉበት ቸር እርሱ ነውና።

የተለያዩ ኢስላማዊ ይዘቶች በየቋንቋው አገልግሎት ሰጪ ማህበር የሊቃውንት ኮሚቴ

 

 

 

 

የአስሩ የዙልሒጃ ቀናት ትሩፋት

አስሩ የዙልሒጃ ቀናት ያላቸው ትሩፋት እጅግ የላቀ ነው። (ይህንንም) አላህም በቁርአን ገልፆታል። መልዕክተኛውም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በሐዲሣቸው አብራርተውታል። እነዚህ ቀናት አላህ ቁርአን ላይ እንዲህ ብሎ የማለባቸው ቀናት ናቸው:

﴿وَٱلۡفَجۡرِ 1 وَلَيَالٍ عَشۡرٍ 2﴾

{በጎህ እምላለሁ፡፡* በዐሥር ሌሊቶችም።} [አል‐ፈጅር: 1‐2] ኢብኑ ዐባስ፣ ኢብኑ ዙበይር፣ ሙጃሂድ፣ ኢብኑ ከሢር፣ ኢብኑል ቀይም እና ሌሎችም ቀደምት እንዲሁም ኃለኞችም ዑለሞች እንደገለፁት እነዚህ በዚህ መሃላ የተጠቀሱት አስሩ የዙልሒጃ ቀናት ናቸው።1

እነዚህ ቀናት ካላቸው ደረጃ አንፃር በነዚህ ጊዜያት ውስጥ የሚሰራ ስራ በሌላው ጊዜ ከሚሰራ በአላህ መንገድ ከመታገል እንኳ ሳይቀር በሚበልጥ ልክ በላጭነት ያላቸው ቀናት ናቸው። ይህም ኢብኑ ዐባስ (አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው) ባስተላለፉት ሐዲሥ መሰረት ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል:

«مَا مِنْ أَيَّامٍ الْعَمَلُ الصَّالِحُ فِيهِنَّ أَحَبُّ إِلَى اللَّهِ مِنْ هَذِهِ الْأَيَّامِ الْعَشَرِ»، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللَّهِ! وَلا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ؟ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «وَلا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ، إِلَّا رَجُلٌ خَرَجَ بِنَفْسِهِ وَمَالِهِ فَلَمْ يَرْجِعْ مِنْ ذَلِكَ بِشَيْءٍ».

«በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸም መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም፤ ሰሓቦችም ጠየቁ: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም (ትግልም) ጭምር?” የአላህ መልዕክተኛም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን): “ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም (በአላህ መንገድ መታገልም) ከዚህ አይበልጥም” አሉ።»2

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በአስሩ የዙልሒጃ ቀናት የሚሠሩ በላጭነት ያላቸው ስራዎች

1. ሐጅና ዑምራ ማድረግ: ሁለቱም በነዚህ አስር ቀናት ከሚሰሩ ትላልቅ ስራዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። ምክንያቱም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:

«مَن حَجَّ هَذَا الْبَيْتِ فَلَمْ يَرْفُثْ وَلَمْ يَفْسُقْ رَجَعَ كَيَوْمِ وَلَدَتْهُ أُمُّهُ».

«ሳይባልግ (ከሚስቱ ጋር ግንኙነት ሳይፈጽም) እና ሳያምፅ በዚህ ቤት ሐጅ ያደረገ እናቱ እንደወለደችው ቀን ከወንጀሉ ፀድቶ ይመለሳል።» በሙስሊም ዘገባም:

«مَن أَتَى هَذَا الْبَيْتِ فَلَمْ يَرْفُثْ وَلَمْ يَفْسُقْ؛ رَجَعَ كَيَوْمٍ وَلَدَتْهُ أُمُّهُ».

«ወደዚህ ቤት ሳይባልግ (ከሚስቱ ጋር ግንኙነት ሳይፈትጽም) እና ሳያምፅ ደርሶ የተመለሰ እናቱ እንደወለደችው ቀን ሁኖ ነው የሚመለሰው።»3 "ወደዚህ ቤት ደርሶ የተመለሰ" ሲሉ ለአላህ ምስጋና ይገባውና በተዘዋዋሪ ሐጅንና ዑምራን የሚያጠቃልል ነው። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህም ብለዋል:

«الْعُمْرَةُ إِلَى الْعُمْرَةِ كَفَّارَةٌ لِمَا بَيْنَهُمَا، وَالْحَجُّ الْمَبْرُورُ لَيْسَ لَهُ جَزَاءٌ إِلَّا الْجَنَّةُ».

«ከዑምራ እስከ ዑምራ በመካከላቸው ያለውን ማስሰረዣ ናቸው። የተሟላ ሐጅም ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም።»4

2. (አሟልቶ) ዘጠኙን ቀናት ወይም የተቻለውን ያህል መፆም፤ ይህም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ስላሉ ነው:

«مَا مِنْ أَيَّامٍ الْعَمَلُ الصَّالِحُ فِيهِنَّ أَحَبُّ إِلَى اللَّهِ مِنْ هَذِهِ الْأَيَّامِ الْعَشَرِ».

«በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸም መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም።» ፆም ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ካበረታቷቸው ትላልቅ መልካም ስራዎች መካከል አንዱ ነው። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በፆም ላይ አነሳስተዋልም፤ ለምሳሌ እንዲህ ብለዋል:

«مَا مِنْ عَبْدٍ يَصُومُ يَوْمًا فِي سَبِيلِ اللَّهِ إِلَّا بَاعَدَ اللَّهُ بِذَلِكَ الْيَوْمِ وَجْهَهُ عَنِ النَّارِ سَبْعِينَ خَرِيفًا».

«በአላህ መንገድ ላይ አንዲትን ቀን የሚፆም ባርያ የለም፤ አላህ ፊቱን የሰባ ክረምት ያህል ርቀትን ከእሳት የሚያርቅለት ቢሆን እንጂ።»5

3. በእርዱ ቀንና በአያመ ተሽሪቅ ቀናት ኡዱሒያን ማረድ የተደነገገ ነው። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ማድረጋቸው ተረጋግጧል:

«ضَحَّى بِكَبْشَيْنِ أَمْلَحَيْنِ، أَقْرَنَيْنِ، ذَبَحَهُمَا بِيَدِهِ، وَسَمَّى وَكَبَّرَ وَوَضَعَ رِجْلَهُ عَلَى صِفَاحِهِمَا».

«ሁለት ቡራቡሬና ቀንዳም የሆኑ ሙክቶችን ቢስሚላህ አሏሁ አክበር እያሉ እግራቸውን አንገታቸው ላይ እያደረጉ በእጃቸው አርደዋል።»6

ከእናታችን ዓኢሻ አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና እንደተላለፈው: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:

«مَا عَمِلَ ابْنُ آدَمَ مِنْ عَمَلٍ يَوْمَ النَّحْرِ أَحَبُّ إِلَى اللَّهِ مِنْ إِهْرَاقِ الدَّمِ، وَإِنَّهُ لَيُؤْتَى يَوْمَ الْقِيَامَةِ بِقُرُونِهَا وَأَشْعَارِهَا وَأَظْلافِهَا، وَإِنَّ الدَّمَ لَيَقَعُ مِنَ اللَّهِ بِمَكَانٍ قَبْلَ أَنْ يَقَعَ فِي الْأَرْضِ، فَطَيِّبُوا بِهَا نَفْسًا».

«የትኛውም ሰው በእርዱ ቀን የሚያከናውነው ምርጡ ስራ እርዱን መፈፀም ነው። በእለተ ትንሳኤ ከቀንዶቹ፣ ከፀጉሩ፣ ከሸኮናው ጋር ሁኖ ይመጣለታል። ደሙ ፈሶ መሬት ላይ ከማረፉ በፊት አላህ ዘንድ ተቀባይነትን ያገኛልና ደስ ይበላችሁ።»7

እርድን ማከናወን የፈለገ ሰው አስሩ የዙልሒጃ ቀናት ሲገቡ ፀጉሩንም ይሁን ሌላ ሰውነቱን ከመንካት ይታቀብ። ይህም ኡሙ ሰለማ አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ማለታቸውን ስላስተላለፈች ነው:

«إِذَا رَأَيْتُمْ هِلَالَ ذِي الْحِجَّةِ وَأَرَادَ أَحَدُكُمْ أَنْ يُضَحِّيَ؛ فَلْيُمْسِكْ عَنْ شَعْرِهِ وَأَظْفَارِهِ».

«ከናንተ መካከል እርድን ማከናወን የሚፈልግ ሰው የዙልሒጃ ጨረቃ ከታየች በኃላ ፀጉሩንም ይሁን ጥፍሩን ከመንካት ይታቀብ።» በሌላ ዘገባም፡

«... فَلَا يَأْخُذَنَّ مِنْ شَعْرِهِ وَلَا مِنْ أَظْفَارِهِ شَيْئًا حَتَّى يُضَحِّيَ».

«… እርዱን እስከሚያከናውን ድረስ ከፀጉሩም ይሁን ከጥፍሩ ቅንጣት ታክል እንኳ አይንካ።»8

4. በነዚህ አስርት ቀናት ሆነ በአያመ ተሽሪቅ (የዙልሒጃ አስራ አንደኛው፣ አስራ ሁለተኛውና አስራ ሶስተኛው) ቀናት ተክቢራ ማድረግ፣ ላ ኢላሃ ኢለላህ ማለት፣ አላህን ማውሳት (ዚክር)፤ ይህም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ስላሉ ነው:

«مَا مِنْ أَيَّامٍ أَعْظَمَ عِندَ اللَّهِ وَلَا أَحَبُّ إِلَيْهِ مِنَ الْعَمَلِ فِيهِنَّ مِنْ هَذِهِ الْأَيَّامِ الْعَشَرِ، فَأَكْثِرُوا فِيهِنَّ: مِنَ التَّهْلِيلِ، وَالتَّكْبِيرِ، وَالتَّحْمِيدِ».

«ከእነዚህ አስር ቀናት በበለጠ አላህ ዘንድ ታላቅ የሆኑና መልካም ስራ እጅግ የተወደደባቸው ቀናት የሉም፤ ስለዚህ ተህሊል (ላ ኢላሃ ኢለሏህ ማለት)፣ ተክቢር እና ተሕሚድ አብዙ።»9

ተክቢራ እንደሚከተለው ሁለት ዓይነት ነው:

የመጀመርያው አይነት: ልቅ የሆነው ተክቢራ ሲሆን ከሶላት ጋር ምንም የተቆራኘ ገደብ ሳይኖረው በየትኛውም ወቅት የሚባል ነው።

ይህ ልቅ የሆነው ተክቢራ በዒድ አል‐አድሓ፤ ከአስሩ የዙልሒጃ ቀናት በመጀመርያው ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው የአያመ ተሽሪቅ ቀናት ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን በየትኛውም ጊዜና ቦታ በሌሊትም፣ በቀንም፣ በመንገድም፣ በገበያም፣ በመስጅድም፣ በመኖርያም በየትኛውም አላህ ሊወሳበት በሚችል ቦታ ሁሉ የሚባል ነው።

ሁለተኛው አይነት: በወቅት የተገደበው ተክቢራ ሲሆን በዒድ አል‐አድሓ በተለይም ከሶላት በኃላ ጊዜውና ሁኔታውም በሚከተለው መልኩ የተወሰነ ነው:

አንደኛ: በወቅት የተገደበው ተክቢራ በዐረፋ ቀን ከፈጅር ሶላት በኃላ ጀምሮ ከአያመ ተሽሪቅ ቀናት በሶስተኛው ቀን ሶላተል ዐስር ላይ ይጠናቀቃል። ይህ ሐጅ ለማያከናውን ሰው ሲሆን ሐጅን የሚያከናውን ለሆነ ሰው በወቅት የተገደበው ተክቢራ የሚጀምረው በእርዱ ቀን ዙህር ላይ ነው።

ሁለተኛ: የተክቢራ አባባሉም፡ (አላሁ አክበር፤ አላሁ አክበር፤ ላ ኢላሃ ኢለላህ ወላሁ አክበር፤ አላሁ አክበር፤ ወሊላሂል ሐምድ) (ትርጉሙም: አላህ ታላቅ ነው፤ አላህ ታላቅ ነው፤ ከአላህ በቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው አንድም የለም፤ አላህ ታላቅ ነው፤ አላህ ታላቅ ነው፤ ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባው ነው።)10

5. ሐጅ የማያደርግ ሰው የዒድ ሶላትን ለማከናወን መጣር፣ ወደ ሶላቱም ቀድሞ መሄድ፣ ኹጥባውን ማዳመጥ አለበት። ምክንያቱም የዒድ ሶላት ካለው ትልቅ ደረጃ አንፃር የወር አበባ ላይ ያሉም ይሁኑ ልጃገረድ ሴቶችም ጭምር እንዲወጡ የታዘዘበት የሆነ ከኢስላም ታላላቅ መገለጫዎች አንዱ ነው። ከኡሙ ዐጢያህ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች:

«كُنَّا نُؤْمَرُ أَنْ نَخْرُجَ يَوْمَ الْعِيدِ حَتَّى نُخْرِجَ الْبِكْرَ مِنْ خِدْرِهَا، حَتَّى نُخْرِجَ الْحُيَّضَ فَيَكُنَّ خَلْفَ النَّاسِ، فَيُكَبِّرْنَ بِتَكْبِيرِهِمْ، وَيَدْعُونَ بِدَعَائِهِمْ، وَيَرْجُونَ بَرَكَةَ ذَٰلِكَ الْيَوْمِ وَطَهَارَتِهِ».

«በዒድ ቀን ልጃገረድን ከክፍሏ እንድትወጣ እስከማድረግና፤ በወር አበባ ላይ ያለችን ሴት እንኳ መጥታ ከሰጋጆች ኃላ ሁና እንድትገኝ እስከማድረግ ደረጃ ‐እነሱም መጥተው ከሌላው ጋር ተክቢራቸውን እንዲሉ፤ ዱዓቸውንም እንዲያደርጉና የቀኑን በረካና ንፅህናን እነሱም እንዲቋደሱ ‐ (ሁላችንም) ለዒድ እንድንወጣ እንታዘዝ ነበር።» በሌለ ዘገባም፡

«وَأَمَرَ الْحُيَّضَ أَنْ يَعْتَزِلْنَ مُصَلَّىٰ الْمُسْلِمِينَ».

«በወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶችም የመስገጃ ስፍራውን ርቀው እንዲቀመጡ ታዘዋል።»11

6. ተጨማሪ አምልኮ የሆኑ በጎ ስራዎችን ማብዛት: እንደ ሶላት፣ ሶደቃ፣ የተከበረውን ቁርአን መቅራት፣ በመልካም ማዘዝ፣ ከመጥፎ መከልከል፣ ለጎረቤት በጎ መዋል፣ ዝምድና መቀጠል እና ሌሎችም በጎ ስራዎችን ማብዛት ይገባል። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ከተናገሩት ጥቅል ቃል አንፃር ነው:

«مَا مِنْ أَيَّامٍ الْعَمَلُ الصَّالِحُ فِيهِنَّ أَحَبُّ إِلَى اللَّهِ مِنْ هَذِهِ الْأَيَّامِ الْعَشَرِ»، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللَّهِ! وَلَا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ؟ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «وَلَا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ، إِلَّا رَجُلٌ خَرَجَ بِنَفْسِهِ وَمَالِهِ فَلَمْ يَرْجِعْ مِنْ ذَلِكَ بِشَيْءٍ».

«በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸም መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም፤ ሰሓቦችም ጠየቁ: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም (ትግልም) ጭምር?” የአላህ መልዕክተኛም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን): “ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም (በአላህ መንገድ መታገልም) ከዚህ አይበልጥም” አሉ።»12

ባሳወቀን እንዲጠቅመንና የሚጠቅመንን እንዲያሳውቀን የምንጠይቀው ቸርና የተከበረ የሆነውን አላህን ነው። የአላህ ሰላትና ሰላምም በነቢያችን ሙሐመድና በተከታዮቻቸው ከበዛ ሰላሙ ጋር ይስፈንባቸው።

 

 

***

ማውጫ

 

የአስሩ የዙልሒጃ ቀናት ትሩፋት 3

በአስሩ የዙልሒጃ ቀናት የሚሠሩ በላጭነት ያላቸው ስራዎች 5

 

 

 

***


(ቡኻሪይ እና ቲርሚዚይ ዘግበውታል፤ የሰፈረው ቃል የቲርሚዚይ ዘገባ ነው)

(ቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል)

(ቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል)

(ቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል)

(ቡኻሪይና ሙስሊም ዘግበውታል)

(ቲርሚዚይ ዘግበውታል)

(ሙስሊም ዘግበውታል)

(አሕመድ ዘግበውታል)

(የኢብኑ ቁዳማን አል‐ሙግኒ (3/290) እና "ሸርሑል ከቢር መዐል ሙቅኒዕ ወልኢንሷፍ" (5/380) ይመልከቱ)

(ቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል)

(ቡኻሪይ እና ቲርሚዚይ ዘግበውታል፤ ቃሉም የቲርሚዚይ ዘገባ ነው)

ተፍሲር ኢብኑ ከሢር (4/106)፣ ዛዱልመዓድ (1/56)