رسول الإسلام محمد ﷺ (أمهري)

كتاب "رسول الإسلام محمد ﷺ" يستعرض حياة النبي محمد صلى الله عليه وسلم من نسبه ونشأته إلى زواجه المبارك وبداية الوحي وبدء رسالته الخاتمة، ويبيّن آيات نبوته وعلامات صدقه، ويشرح الشريعة التي جاء بها ودورها في حفظ حقوق الإنسان وكرامته، كما يبرز مواقف خصومه وشهاداتهم له، مع تسليط الضوء على أخلاقه الفاضلة التي جعلته قدوةً للناس وداعيةً لتوحيد الخالق.

  • earth ቋንቋ
    (أمهري)
  • earth ዝግጅት፦:
    اللجنة العلمية برئاسة الشؤون الدينية بالمسجد الحرام والمسجد النبوي
PHPWord

 

 

 

رَسُولُ الإِسْلَامِ مُحَمَّدٌ ﷺ

 

 

የኢስላም መልዕክተኛ የሆኑት ሙሐመድ

 

 

 

اللَّجْنَةُ العِلْمِيَّةُ

بِرِئَاسَةِ الشُّؤُونِ الدِّينِيَّةِ بِالمَسْجِدِ الحَرَامِ وَالمَسْجِدِ النَّبَوِيِّ

 

በመስጂደል ሐረም እና በመስጂድ አን-ነበዊይ

በሃይማኖት ዘርፍ የዕውቀት ነክ ጉዳዮች

ርዕሰ መስተዳድር ኮሚቴ ያዘጋጀው

 


بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ

የኢስላም መልዕክተኛ የሆኑት ሙሐመድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ ይህ መልዕክት ስለ ኢስላቢይ የአላህ መልዕክተኛ ሙሐመድ የአላህ ውዳሴ እና ሰላም በእርሳቸው ላይ ስፈንና አጠር ባለ መልኩ የሚዳስስ ሲሆን ስማቸው፣ የዘር ሀረጋቸው፣ ሀገራቸው፣ የትዳር ሁኔታቸው፣ ተልዕኳቸው፣ የተጣሩበት ጉዳይ፣ የነይነታቸው ተዓምራት፣ ይዘውት የመጡት መመሪያ እና ተቃዋሚዎቻቸውም ስለ እርሳቸው የነበራቸው አቋም ሁሉ ተዳሶበታል።

1 ስማቸው፣ የዘር ሀረጋቸው እና ተወልደው ያደጉበት ሀገር

ኢስላይ መልዕክተኛው ሙሐመድ ቢን ዐብዲላህ ቢን ዐብዱልሙጦሊብ ቢን ሃሺም የኢብራሂም ልጅ የሆኑት ኢስማዒል የአላህ ሰላም በእነርሱ ላይ ይስፈንዝርያ ናቸው።

ነብዩላህ ኢብራሂም ዓለይሂ ሰላም ልጃቸውን ኢስማዒልን እና ባለቤታቸው ሃጀርን ከታላቋ ሶሪያ በመውሰድ በአላህ ትእዛዝ መካ ላይ አሰፈሯቸው። ታዲያ እኚህ ታዳጊ ኢስማዒል አድገው ወጣት በሆኑ ጊዜ የአላህ ነብይ ኢብራሂም ዓለይሂ ሰላም ወደ መካ መጡና ከልጃው ጋር ሆነው የተከበረውን የአላህ ቤት ካዕባን ገነቡ። ሰዎችም በዙሪያው መበራከት ጀመሩና መካ የዓለማቱ ጌታ አላህን የሚያመልኩ ሰዎች የሚያስቧት፤ ሐጅ ለማድረግም የተመረጠች ቦታ ሆነች። ሰዎችም ለዘመናት በኢብራሂም ዓለይሂ ሰላም ጎዳና ላይ ሆነው አላህን በማምለክና እርሱንም በብቸኝነት በመገዛቱ ላይ ቀጠሉ።

ከዚህ ሁሉ በኋላ ግን ቀስበቀስ ከእስልምና ሃይማኖት ማፈንገጥ ተከሰተ። ማለትም ልክ በዙሪያዋ እንዳሉት የዓለም ክፍሎች የባዕድ አምልኮ፣ ሴት ህፃናትን ከነህይወት መቅበር፣ ሴቶችንም መበደል፣ የቅጥፈት ቃል መናገር፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣት፣ ብልግናን መፈፀም፣ ወላጃቸው የሞተባቸውን ህፃናት ገንዘብና አራጣ መብላትና መሰል የባዕድ አምላኪዎች ስራ የተንሰራፋባቸው ሆነቸ ።

የኢስላሙ ነቢይ ረሱል ሙሐመድ ቢን ዐብዲላህ የኢስማዒል ኢብኑ ኢብራሂም ዝሪያ ይህንን በሚመስል ማህበረሰብ ውስጥ ጊዜውም በ571 ዓ. ል ነበር ተወለዱ። አባታቸው ገና ሳይወለዱ የሞቱ ሲሆን እናታቸውም የስድስት ዓመት ህፃን እያሉ ነው የሞተችው። አጎታቸው አቡ ጧሊብ አሳደጋቸው፤ ላባቸውን ጠብ አድረገው ለፍቶ አዳሪ፣ የቲም፣ ሚስኪን ሆነው አደጉ።

2 የተባረከ ጋብቻ ከተባረከችዋ እመቤት ጋር

እድሜያቸው ሃያ አምስት አመት ሲሞላ አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና ከመካ ሴቶች መካከል ኸዲጃህ ቢንት ኹወይሊድ ከተባለች እመቤት ጋር ተጋቡ። ከእርሷም አላህ አራት ሴት ልጆችንና ሁለት ወንድ ልጆችን ለገሳቸው፤ ይሁን እንጂ ወንድ ልጆቻቸው ገና በጨቅላነታቸው ነበር የሞቱት። ከባልተቤታቸውና ከቤተሰባቸው ጋር የነበራቸው አኗኗርም እጅግ በርህራሄና በፍቅር የተሞላ ነበር። ለዚህም ነበር ባለቤታቸው ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ እጅጉን ትወዳቸው የነበረው፤ እርሳቸውም ቢሆኑ ታዲያ ፍቅሯን በፍቅር ነበር የመለሱላት። ከሞተች ረጅም ዓመት አልፏት እንኳ አልረሷትም ነበር። ይልቁኑ ውዴታዋን ፀንቶ እንዲቆይ እና (ከሞተችም በኋላም) ለእርሷ በጎ ከመዋል አኳያ በግ ወይም ፍየል እያረዱ ስጋውን ለእርሷ ጓደኞች ያከፋፍሉ ነበር።

3 የወሕይ (መለኮታዊ ራዕይ) አጀማመር

የአላህ መልዕክተኛ ሙሐመድ ገና ከመፈጠራቸው ጀምሮ ባማረ ስነምግባር የታነፁ ነበሩ። ያደጉበት ማህበረሰብም "እውነተኛው ታማኙ" ብለው ይጠሯቸው ነበር። በታላላቅ ስራዎችም አብረዋቸው ይሳተፉ ነበር። የባዕድ አምልኮ ስራቸውን ግን አይሳቱፉም ነበር፤ ይጠሉባቸውም ነበር።

እድሜያቸው አርባ አመት በሞላ ጊዜ መልዕክተኛ እንዲሆኑ አላህ መረጣቸው። ከዚያም ጂብሪል ዓለይሂ ሰላም መጀመሪያ የወረደውን የቁርኣን ሱራ (ምዕራፍ) ይዞላቸው መጣ። ይኸውም ተከታዩ የአላህ ቃል ነው፦

﴿اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ 1 خَلَقَ الْإِنسَانَ مِنْ عَلَقٍ 2 اقْرَأْ وَرَبُّكَ الْأَكْرَمُ3 الَّذِي عَلَّمَ بِالْقَلَمِ 4 عَلَّمَ الْإِنسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ 5

{አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም። (1)

ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)። (2)

አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲሆን፤ (3)

ያ በብዕር ያስተማረ። (4)

ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲሆን። (5)}

[አል-ዓለቅ፥ 1-5]

የአላህ መልዕክተልባቸው እየተርበተበተ የተሰጣቸውን መለኮታዊ ቃል ይዘው ወደ ባለቤታቸው መጡ። ሁኔታውንም ተረኩላት፤ እርሷም አረጋጋቻቸውና ተውራትንና ኢንጂልን የሚያነብ ወደሆነው የአጎቷ ልጅ ወረቃህ ኢብን ነውፈል ይዛቸው ሄደች። “የአጎቴ ልጅ ሆይ! እስኪ ይህ የወንድምህ ልጅ የሚነግርህን ነገር ስማው።” አለች። ወረቃም ቀጠል አድርገው “የወንድሜ ልጅ ሆይ! እስኪ ንገረኝ” አሏቸው። የአላህ መልዕክተኛ ሆነውን ሁሉ ተረኩላቸው። የዚህን ግዜ ወረቃህ እንዲህ አላቸው፦

ይህማ በሙሳ ላይ የወረደው ሚስጥረኛ እኮ ነው! ምነው አፍላ ወጣት ሆኜ በነበር! ምነው ህዝቦችህ ከሀገርህ ሲያስወጡህ ህያው ሆኜ በነበር!” ሲላቸው። የአሏህ መልዕክተኛም “ከሀገሬ ያስወጡኛልእንዴ?!” አሉ። እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “አዎ! አንተ ይዘሀው የመጣሀውን ተልዕኮ ይዞ የመጣ ሁሉ ጠላት አጋጥሞታል። ያን እለት አላህ ቢገመኝ የቁርጠኛን እርዳታ ነበር የምረዳህ።”

በመካ ሳሉም ቁርኣን ተከታትሎ ይወርድላቸው ነበር፤ ጂብሪልም ዓለይሂ ሰላም ከአላህ በሚመጣለት መልኩ ተልዕኮውን ማድረሱን ቀጠለ።

እርሳቸውም ህዝባቸውን ወደ እስልምና መጣራታቸውን ቀጠሉ። ህዝባቸው ግን መቃወምና መከራከሩን ተያያዙት፤ ከዚያም አልፈው ገንዘብ፣ ንግስናን እና የመሳሰሉ ነገሮችን እንደመደለያ እያቀረቡ ተልዕኳቸውን እንዲተው ወተወቷቸው። ይሁን እንጅ የአላህ መልዕክተኛ ህንን ሁሉ አልቀበልም ብለው ተልዕኳቸውን ቀጠሉ። ህዝቦቻቸው በዚህ ሳይሳካላቸው ሲቀር ከዚያ በፊት የነበሩ መልዕክተኞች በህዛባቸው እንደተባሉት እርሳቸውንም “ደጋሚ፣ ውሸታም፣ ቀጣፊ” አሏቸው። ሯቸውንም ለማጨናነቅ (ለማመሰቃቀል) ጣሩ፤ የተከበረው አካላቸውም ላይ ድንበር አልፈው ጥቃት ሰነዘሩባቸው፤ ተከታዮቻቸውም አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገቡ ተደረጉ።

ረሱል ግን ከዚህ ሁሉ መሰናክል ጋር በመካ ሆነው የሐጅ አጋጣሚዎችንና የዐረቦችን ወቅታዊ የግብይት ጊዜያቶችን እየተጠባበቁ ወደ አላህ ጥሪ (ዳዕዋ) የማድረግ ተልዕኳቸው ላይ ፀኑ። በዚያም ሰዎችን እያገኙ እስልምናን ይጋብዟቸው ነበር። ስልጣንም ይሁን ንግስና ስላልነበራቸው በዱኒያዊ ጥቅማጥቅምም ይሁን በስልጣን ሳያስጎመጁ በሰይፍም ሳያስፈራሩ ይዘው የመጡት የተከበረውን ቁርኣን የመሰለ ነገር ይዞ መምጣት የሚችል ካለ ማምጣት ይችላል” እያሉ ውርርድ እያቀረቡ፤ ተቃዋሚዎቻቸውን እየተፎካከሩ ዳዕዋቸውን ቀጠሉ። በዚህም ከተከበሩት ሰሓቦች (ባልደረቦቻቸው) መካከል አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ያመነው አመነላቸው።

በመካ ቆይታቸውም ወቅት አላህ ወደ በይተል መቅዲስ (ኢስራእ) እና ወደ ሰማይ ጉዞ (ሚዕራጅ) በማስደረግ በታላቅ ተዓምር አከበራቸው። በክርስትናም በእስልምናም እንደሚታወቀው፥ አላህ ነብዩ ኢልያስንና መሲሑ ዒሳን የአላህ ሰላም በእነርሱ ላይ ይስፈን ወደ ሰማይ ከፍ አድርጓቸዋል።

ነብዩ የሰላትን መመሪያ የተቀበሉት ሰማይ ላይ በወጡበት ወቅት ነበር። ይህም ዛሬ ድረስ ሙስሊሞች ሁል ጊዜ በየቀኑ የሚሰግዱት የሆነው አምስቱ የሶላት ወቅት ነው። በተከበረችዋ መካ ቆይታቸው ሌላ ታላቅ ተዓምር አሳይተዋል። ይኸውም ሙሽሪኮቹም ጭምር በዐይናቸው ያዩት የሆነ የጨረቃ መሰንጠቅ ነው።

የመካ አጋሪዎችም (ሙሽሪኮችም) ሰዎችን ከእርሳቸው ለማሸሽና በክፉነታቸውም ለመፅናት እንዲያግዛቸው የተለያዩ መንገዶችን ተጠቅመዋል። እርሳቸውን በመከራከር እና ሰዎችንም ከእርሳቸው በመግታት ይረዳቸው ዘንድ በአይሁዶቹም ታግዘው የቁርኣንን አምሳያ ለማምጣት በከንቱ ልፋት ብዙ ተንገላቱ።

የመካ አጋሪዎችም ጭቆና በምእመናኑ ላይ በበረታ ጊዜ ነብዩ ወደ ሓበሻ ምድር እንዲሰደዱ ለምእመናኑ ፍቃድ ሰጧቸው። ስለ ንጉሱም እንዲህ አሏቸው፦ “እርሱ ዘንድ ማንም የማይበደልበት ንጉስ አለና እርሱ ጋ ሂዱ።” ይህ ንጉስ በወቅቱ ክርስትያን ነበር። በዚህም ሁለት ቡድኖችም ወደ ሓበሻ ተሰደዱ። ታዲያ እነዚህ ስደተኞች ወደ ሀበሻ እንደሄዱ ለዚህ ነጃሺይ ተባለ ንጉስ ነብዩ ይዘውት የመጡትን ሃይማኖት አቀረቡለት። እርሱም እስልምናን ተቀበለ፤ እንዲህም አለ፦ “በአላህ ይሁንብኝ! ይህ እና ሙሳ ይዞት የመጣው ሃይማኖት ከአንድ ምንጭ የተቀዳ ነው ።” የመካ አጋርያንም በእርሳቸው እና በባልደረቦቻቸው ላይ መከራን አከታተሉባቸው።

የዛኔ በሚያደርጉት ወቅታዊ ዳዕዋዎች እስልምናን የተቀበሉ እርሳቸውንም እንደሚረዱ ቃል የተጋቡ ከመዲና የመጡ ሰዎች ነበሩ። ከርሳቸው ጋር ይህንን ቃል ተጋብተው ወደ መዲና ተመለሱ። በጊዜው “የሥሪብ” ተብላ ትጠራ ነበር። የተቀሩ መካ የሚገኙት ባልደረቦቻቸውንም ወደ መዲና እንዲሰደዱ ፈቃድ ሰጧቸው። እነርሱም ተሰደዱና እስልምና በመዲና የእያንዳንዱን በር እያንኳኳ ይበልጥ ተስፋፋ።

ነብዩ በመካ ዳዕዋ እያደረጉ ካሳለፉት የአስራ ሶስት አመት የዳዕዋ ቆይታ በኋላ ወደ መዲና ስደት እንዲወጡ አላህ ለእርሳቸውም ፈቀደላቸው። እርሳቸውም ጅራ አድርገው ወደ አላህ የሚያደርጉትን ዳዕዋ ቀጠሉ። የእስልምና ሸሪዓም (ድንጋጌ እና መመሪያ) በተከታታይ ተራ በተራ መውረዱን ቀጠለ። ነቢዩም ወደ ሀገር አስተዳዳሪዎችና ንጉሶች ዳዕዋውን የሚያደርሱ ወደ እስልምና ጥሪ የሚያደርጉ ልዑካንን መላክ ጀመሩ። ከላኩባቸው መካከልም፦ የሩም (የባይዛንታይኑ) ንጉስ፣ የፐርሽያው ንጉስ እና የግብፁ ንጉስ ይገኙበታል።

በመዲና እያሉም የነብዩ ልጅ ኢብራሂም ሞተበት ቀን የፀሃይ ግርዶሽ ተከስቶ ሰዎች ተደናገጡ ፤ የዚህ ጊዜ ታዲያ ሰዎች፦ “ፀሀይ የተጋረደችው እኮ ኢብራሂም በመሞቱ ነው” አሉ። ነብዩ እንዲህ ሏቸው፦

(إِنَّ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ لَا يَكْسِفَانِ لِمَوْتِ أَحَدٍ، وَلَا لِحَيَاتِهِ، وَلَكِنَّهُمَا مِنْ آيَاتِ اللهِ يُخَوِّفُ اللهُ بِهِمَا عِبَادَهُ).

“ፀሓይም ይሁን ጨረቃ ለማንም ሞት ይሁን ውልደት አይጋረዱም፤ ይሁን እንጅ አላህ ባርያዎቹን የሚያስደነግጥባቸው (የሚያስፈራራበት) ተዓምራቶች ናቸው።”1

ነብዩ የውሸት ተጣሪ (ሰባኪ) ቢሆኑ ኖሮ፥ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም እንዲህ ይሉ ነበር፦ “ፀሀይዋ ልጄ በመሞቱ እየተጋረደች እኔን የሚያስተባብለኝ ሰው እንዴት ሊሆን ነው?!”

ጌታችን አላህ የአላህ መልዕክተኛን ባማረ ስነምግባር አስውቧቸዋል፤ እንዲህ በማለትም ነው የገለፃቸው፦

﴿وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍ 5

{አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ።}

[አልቀለም፡ 4]

እንደ እውነተኝነት፣ ኢኽላስ (ከይዩልኝ ይስሙልኝ ሙሉ በሙሉ መራቅ)፣ ጀግንነት፣ ፍትሃነት፣ ከተቃዋሚዎቻቸውም ጋር ቢሆን ቃል አክባሪነት፣ ቸርነት፣ ለድሆችና ሚስኪኖች እንዲሁም ለችግረኞችና ባላቸው ለሞተባቸው ባለትዳሮች ምፅዋት መስጥት፣ ቀናውን ጎዳና እንዲይዙ መጓጓት፣ ለእነርሱ ማዘን እና መተናነስ የመሳሰሉን መልካም ስነምግባሮች ሁሉ የተላበሱ ነበሩ። እርሳቸው ከባልደረቦቻቸው መሀል ሆነው እንግዳ የሆነ ሰው መጥቶ የሚለዩበት ነገር ባለመኖሩ “የትኛችሁ ነው ሙሐመድ?” ብሎ እስከመጠየቅ ይደርስ ነበር።

የህይወት ታሪካቸው በአንክሮ ስናጤነው ከሁሉም ሰው ጋር ከወዳጅም ከጠላትም፣ ከቅርቡም ከሩቁም፣ ከትልቁም ከትንሹም፣ ከሴትም ከወንድም፣ ከእንስሳውም ከበራሪውም ጋር ሁሉ የነበራቸው ግንኙነት የምሉእነት እና የምጡቅ ስብእና የተላበሰ እንደነበር ያስረዳናል።

አላህ መልዕክቱን ባሟላላቸውና እርሳቸውም ተልዕኳቸውን በሚገባ ከተወጡ በኋላ እድሜያቸው ስልሳ ሶስት ሲሞላ ሕይወታቸው አለፈ። ከዚህ እድሜያቸው ዐርባው ነብይ ከመሆናቸው በፊት ሲሆን፥ ሃያ ሶስቱ ደግሞ ነብይም ረሱልም ሆነው ነው ያሳለፉት።

በመዲና ተቀብረዋል። የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን። ሲሞቱ ሲጓጓዙባት ከነበረችው ነጭ በቅሏቸውና ለመንገደኛ ሰደቃ ምፅዋት አድርገው ከሰጡት መሬት ውጭ ለቤተሰቦቻቸው እንኳ ንብረትም ሆነ ውርስም አልተዉም ነበር።2

ባረፉበት ወቅት በእርሳቸው አምነው እስልምናን የተቀበሉና የተከተሏቸውም ቁጥራቸው በርከት ብሎ ነበር። ከእሳቸው ጋር አብረው የመሰናበቻ ሐጅ ያደረጉት እንኳ ከመቶ ሺህ በላይ ነበሩ። ይህም የሆነው ከሕልፈታቸው ሶስት ወር ቀደም ብሎ ነበር። በእስላማዊ እሴቶች እና መርሆዎች ላይ የኮተኮቷቸው (ያነቸው) ባልደረቦቻቸውም ከየትኛውም ባልደረባ ይበልጥ ፍትሀዊ፣ ዛሂድ፣ ቁጥብ፣ ቃላቸውን አክባሪ እና ለዚህ ሃይማኖትም ያላቸውን ይበልጥ የለገሱ ነበሩ። ምናልባትም ይህ የሃይማኖታቸው መጠበቅ እና መስፋፋት አንዱ ምስጢር ሳይሆን አይቀርም።

አላህ የሁሉንም መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ከባልደረቦቻቸውም መካከል በእምነት፣ በእውቀት፣ በተግባር፣ በቅንነት፣ አምኖ በመቀበል፣ በጥረት፣ በጀግንነት እና በቸርነት እጅግ በላጮቹ፡- አቡበክር አስ-ሲዲቅ፣ ዑመር ቢን አል-ኸጣብ፣ ዑስማን ቢን ዐፋን እና ዐሊይ ቢን አቢጧሊብ ረዲየሏሁ ዓንሁም ናቸው። ገና ከጅምሩ በእርሳቸው ካመኑት እና እውነት ብለው ከተቀበሏቸው መካከልም ነበሩ። ከእርሳቸውም በኋላ የኢስላምን ባንዲራ የያዙትም ኸሊፋዎች እነዚሁ ናቸው። ይሁን እንጂ ለነብያት ብቻ ከተሰጡ መለዮዎች መካከል ቅንጣትም አልነበራቸውም፤ ነብዩ ከተቀሩት ባልደረቦች እነረሱን ብቻ የለዩበት ነገር አልነበም።

ነብዩ ዘውት የመጡትን ሱና፣ ታሪክ፣ ንግግርና ተግባር ልክ መጀመሪያውኑ ባስተማሩበት ቋንቋ አላህ ጠብቆላቸዋል። በታሪክ ማህደር የእርሳቸው ታሪክ እንደተጠበቀው የማንም ታሪክ አልተጠበቀለትም። እርሳቸው እኮ እንዴት እንደሚተኙ፣ እንዴት እንደሚበሉና እንዴት እንደሚጠጡና እንዴት እንደሚስቁ ጭምር ነው ታሪካቸው የተጠበቀው።

ቤታቸው ውስጥ ከባለቤታቸው ጋር የነበራቸው መስተጋብር እንኳ እንዴት እንደነበር ተዘግቧል።

የነብዩ ሁኔታቸው ሁሉ በታሪክ መዝገብ ሰፍሯል። እርሳቸው ሰው የሆኑ የአላህ መልእክተኛ ናቸው። ከአምላካዊ መገለጫም ቅንጣት እንኳ ድርሻ የላቸውም። ለራሳቸውም እንኳ ጥቅም የማምጣት እና ጉዳት የመከላከል ስልጣን የላቸውም።

4 ተልዕኳቸው (መልዕክታቸው)፦

አላህ ነብዩ ሙሐመድን የላካቸው ሺርክ፣ ክህደትና ድንቁርና በምድር ላይ ተንሰራፍቶና በምድር ላይም ከጥቂት የአህለል ኪታብ ቅሪቶች በቀር አላህን ምንም ሳያጋራ የሚያመልክ ማንም ባልነበረበት ወቅት ነው። አላህ በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት፥ በሃይማኖቶች ሁሉ ላይ የበላይ ሊያደርግበት ሰዎችንም ከጣዖት አምልኮ፣ ከክህደት እና ከድንቁርና ጨለማ ወደ ተውሒድ እና እምነት ብርሃን ሊያስወጣበት፤ የነብያቶችም የሩሱሎችም መደምደሚያ አድርጎ ወደ ዓለማት ሁሉ ላካቸው። መልዕክታቸው የቀደምት ነብያት ዓለይሂሙ ሰላቱ ወሰላም ተልዕኮ ማሟያ እንዲሆን ተደርገው ተላኩ።

ጥሪያቸውም ሁሉ ነብያትና መልእክተኞች ዐለይሂም ሰላም የተጣሩበት የሆነው ጥሪ ነበር። የኑሕ፣ የኢብራሂም፣ የሙሳ፣ የሱለይማን፣ የዳውድና የዒሳ ሁሉ ጥሪ - ብቸኛው አምላክ አላህ ፈጣሪ፣ ሲሳይ ለጋሽ፣ ህይወትን የሚሰጥና የሚነሳ፣ ንጉሠ_ነገሥት፣ ነገራቶችን ሁሉ የሚያስተናብረው እርሱ ነው ፣ እርሱ በጣም ርኅሩኅ አዛኝ ነው፣ በዓለማት ውስጥም የምናየውንና የማናየውን ነገር ሁሉ ፈጣሪው እርሱው መሆኑንና ከአላህ በስተቀር ያለው ሁሉ ከፍጥረታቱ መካከል የሆነ ፍጡሩ ብቻ ነው የሚል እምነት ነበር ጥሪያቸው።

አላህን በብቸኝነት ማምለክና ከእርሱ ውጪ ያሉትን ሁሉ ማምለክን መተው፣ አላህ አንድ መሆኑንና በተመላኪነቱም ይሁን በባለቤትነቱ፣ በፈጣሪነቱም ይሁን በአስተናባሪነቱ ምንም አጋር እንደሌለው እጅጉን ግልጽ በሆነ መልኩ ዳዕዋ አድርገዋል። የላቀው አላህ: ያልወለደም ያልተወለደም መሆኑን፤ የሚስተካከለው አቻም ይሁን አምሳያም የሌለው መሆኑን፤ በፍጡራኑ ውስጥ የማይሰርፅና የፈጠረው ፍጡር አካልም የማይላበስ መሆኑን ግልፅ አድርገዋል።

እንደ ኢብራሂምና ሙሳ ዓለይሂሙ ሰላም ሱሑፍ እንዲሁም ተውራት፣ ዘቡርና ኢንጅል በመሳሰሉ መለኮታዊ መጽሐፍት እንዲያምኑም ለሰው ልጆች ሁሉ ጥሪ አድርገዋል። እንዲሁም በመልክተኞችም ሁሉ ማመንና አንዱንም ነቢይ ያስተባበለ በነቢያት ሁሉ እንደካደ እጅጉን ግልፅ አድርገው ተጣርተዋል።

የሰው ልጆችን ሁሉ በአላህ እዝነት አብስረዋል፤ እንዲሁም ለመላው የዱኒያ ጣጣቸው ሁሉ አላህ እንደሚበቃቸው፣ አላህም አዛኝ ጌታ እንደሆነ፣ በእለተ ቂያማ ሁሉንም ከመቃብራቸው ቀስቅሶ ፍጡራንን የሚተሳሰባቸው እንደሆነ፣ ምእመናንንም በመልካም ስራዎቻቸው አስር እጥፍ አድርጎ እንደሚመነዳቸው፣ ለሰሩት ክፋት ግን በስራቸው ልክ ብቻ እንደሚተሳሰብና በአኺራ ህይወታቸውም ዘልዓለማዊ ፀጋ እንደሚያጣቅማቸው አብስረዋል። ከከሀዲያን ሆኖ ክፋትንም ለሚሰራ ደግሞ በዱኒያም በአኺራም የስራውን ቅጣት እንደሚያገኝ ሁሉ አስተምረዋል።

እንዲሁም መልእክተኛው ሙሐመድ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን - በተሰጣቸው ተልዕኮ ጎሣቸውን፣ አገራቸውን፣ ክቡር ነፍሳቸውን እንኳ ለማላቅ አልተጠቀሙበትም። ይልቁንም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ የነቢዩላህ ኑሕ፣ ኢብራሂም፣ ሙሳ እና ዒሳ ዐለይሂ-ሰላም ስም የእርሳቸው ስም ከተጠቀሰው በላይ ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል። የእናታቸውም ሆነ የሚስቶቻቸው ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አልተቀሰም የሙሳ እናት ስም ግን በቁርኣን ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፤ የመርየም የአላህ ሰላም በእርሷ ላይ ይስፈን ስም ደግሞ ሰላሳ አምስት ጊዜ ተወስቷል።

እንዲሁም መልእክተኛው ሐመድ የአላህን መመርያ፣ አመክኗዊነትን እና ተፈጥሮን ወይም መልካም ስብእናን ከሚቃረኑ ነገሮች ሁሉ የተጠበቁ ናቸው። ምክንያቱም ነብያት ተልዕኳቸውን የማድረስ ኃላፊነት አላህ የሰጣቸው በመሆናቸውና በሚያደርሱትም ነገር ከአላህ ጥበቃ የሚደረግላቸው በመሆናቸው ነው። ነቢያቶች የጌትነት ወይም የመለኮትነት ባህሪያት የላቸውም። ይልቁንም እንደሌሎች ሰዎች ሁሉ እነርሱም ሰዎች ሆነው ነገር ግን የላቀው አላህ የመልእክቱን ወሕይ (መለኮታዊ ራዕይ) የሚያወርድላቸው ናቸው።

የመልእክተኛው ሙሐመድ ልእክት በትክክል ከአላህ የሆነ ወሕይ ለመሆኑ ሊጠቀሱ ከሚችሉ ታላላቅ ማስረጃዎች መካከል አስተምህሮታቸው ዛሬም ድረስ እርሳቸው በሕይወት እያሉ ይተገበር በነበረው ሁኔታ የዘለቀ መሆኑ ነው። ይሀው ይዘውት የመጡት አስተምህሮ ከቢሊዮን በላይ ሙስሊሞች እየተከተሉት፤ እንደ ሰላት፣ ዘካ፣ ጾም፣ ሐጅ እና ሌሎችም ሃይማኖታዊ ግዴታዎች ሳይቀየሩና ሳይዛቡ ሬም ድረስ እየተተገበሩ ይገኛሉ።

5- የነቢይነታቸው ተዓምራቶች፣ ምልክቶች እና ማስረጃዎቻቸው

አላህ ነብያትን ነብይነታቸውን በሚያመላክቱ ማስረጃዎች ደግፏቸዋል። መልእክታቸውንም በማስረጃዎች እና በመረጃዎች አጠናክሯል። እያንዳንዱ ነብይም የሰው ልጅ ሊያምንበት የሚችልን ተአምር ሰጥቶታል። ነብያት ከተሰጧቸው ታላላቅ ተዓምሮችም እጅግ ታላቁ ተዓምር ነብያችን ሙሐመድ የተሰጣቸው ተዓምር ነው። አላህ እንደ ተአምር የሰጣቸው ቁርኣንን ነውና። ይህም ከነብያት ተዓምር ሁሉ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ የሚዘልቅ ብቸኛው ተዓምር ነው። በእርግጥ ነብያችን ሙሐመድን ከዚህ ውጪ በሆኑ ታላላቅ ተዓምራትም አግዟቸዋል። የአሏህ መልእክተኛ ሙሐመድ የተሰጧቸው ተዓምሮች እጅግ በርካታ ሲሆኑ ከእነርሱም መካከል፡-

የሌሊት ጉዞ እና ማረግ (ኢስራእና ሚዕራጅ)፣ የጨረቃ መሰንጠቅ እና ህዝቡ ድርቅ ገጠማቸው ወቅት በነብዩ ዱዓእ ለበርካታ ጊዜ አሏህ ዝናብ ማውረዱ

ጥቂት የነበረውን የሚበላ ወይም የሚጠጣ ነገር ለብዙ ሰዎች እንዲበሉና እንዲጠጡ በሚችሉበት ብዛት ማበራከታቸው

ማንኛውም ሰው ዝርዝር ሁኔታቸውን የማያውቃቸውን ከዚህ በፊት ያለፉ ጉዳዮች፣ ቀደምት ነብያት የአላህ ሰላም በእነርሱ ላይ ይስፈን ከህዝቦቻቸው ጋር ያሳለፉት ታሪክ እና መሰል ጉዳዮችን አሏህ አሳውቋቸው መናገራቸው

ጥራት ይገባውና የላቀው አሏህ አሳውቋቸው ልክ በሒጃዝ ምድር ተከስቶ በሻም ያሉ ሰዎችም ጭምር የተመለከቱት ከባድ የእሳት ቃጠሎ እና የሰዎችም በፎቅ መፎካከር መሰል ለወደፊቱ ይከሰታሉ ብለው ተንብየው የተከሰቱ እውነታዎች

ከአላህ የተደረገላቸው ጥበቃና ከሰዎችም የተብቃቁ ያደረጋቸው መሆኑ

የሚከተሉትን የመሰሉ ለባልደረቦቻቸው የገቧቸው ቃላት እውን መሆን፦

(لَتُفْتَحَنَّ عَلَيْكُمْ فَارِسُ وَالرُّومُ، وَلَتُنْفَقَنَّ كُنُوزَهُمَا فِي سَبِيلِ اللَّهِ).

(ፋርሶችንና ባይዛንታይኖችን ድል ታደርጋላችሁ፤ ድልባቸውም ለአላህ መንገድ ይውላል።)

የላቀው አላህ በመላእክቶች እገዛ ያደረገላቸው መሆኑ

ነብያቶች የአላህ ሰላም በእነርሱ ላይ ይስፈን ስለ መልእክተኛው ሙሐመድ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን - አስቀድመው የምስራች መናገራቸው፦ ከእነዚህም ነብያት መካከል ሙሳ፣ ዳውድ፣ ሱለይማን፣ ዒሳ የአላህ ሰላም በሁሉም ላይ ይስፈን እና ሌሎችም የበኒ ኢስራኢል ነብያትን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል

ንጹህ አእምሮዎች በሚስማሙበት አሳማኝ ምክንያታዊ ማስረጃዎችም እገዛ ተደርጎላቸዋል3

ይህን መሰል አንቀጾች፣ ማስረጃዎች እና አመክንዮአዊ ምሳሌዎች በተከበረው ቁርኣንና በነብዩ ሱና ውስጥ ተገልፀው ይገኛሉ። ነብዩ የሰሯቸው ተአምራቶች ከገደብ በላይ ናቸው። በዚህ ጉዳይ ሰፋ አድርጎ ለማወቅ የሚፈልግ እጅግ የተጣራ እርግጠኛ የሆነ እውነታውን ሊያገኝበት ዘንድ የተከበረው ቁርኣንን፣ የሱና ኪታቦችንና የነብዩ የታሪክ መጽሐፎችን ይመልከት።

እነዚህ ታላላቅ አንቀጾች እውን ባይሆኑ ኖሮ በአረብያ ምድር የነበሩ ተዋሚ ከሀዲያን ቁረይሾች፣ አይሁዶችና ክርስትያኖች ነብዩ ለማስተባበል አጋጣሚውን ይጠቀሙበት ነበር።

የተከበረው ቁርኣንም አላህ ለመልእክተኛው ሙሐመድ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን - ያወረደው መጽሐፍ፤ የዓለማቱ ጌታ ቃል ነው። አሏህም በቁርአኑ የሰው ልጆችንም ጂኒዎችንም አምሳያውን ወይንም ቢያንስ ከአምሳያው ሊመስል የምትችል አንዲት ምዕራፍን እንኳ ማምጣት ይችሉ እንደሆነ ለውርርድ ጋብዟቸዋል። ውርርዱ ዛሬም ቢሆን እንደቀጠለ ነው። የተከበረው ቁርአን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ግራ ለተጋቡባቸው በርካታ ጥያቄዎች ምላሹን ይዟል። ታላቁ ቁርኣን በወረደበት ዐረብኛ ቋንቋ እስከ ዛሬም ድረስ ልክ በወረደበት ጊዜ እንደነበረው አንዲት ሆሄ እንኳ ሳይጨመር ሳይቀነስበት ተጠብቆ ይገኛል። ታትሞም የተሰራጨ ከሰው ልጆች አቅም በላይ የሆነ ታላቅ መጽሐፍ ነው። ለሰው ልጆች ከመጡላቸው መጽሐፎች መካከል ታላቁ መጽሃፍም ነው። በመሆኑም ሊነበብ ወይም መልዕክተ ትርጉሙ ሊነበብ የሚገባ መጽሐፍ ነው። ቁርአንን ያላነበበ ሰው ያጣው መልካም የሚባል ነገር ሁሉ ነው ።

በተመሳሳይ የመልእክተኛው ሙሐመድ “ሱና” ፣ መመሪያቸው፣ ታሪካቸው ሁሉ በታማኝ የዘጋቢዎች ሰንሰለት መሰረት ተጠብቆ ይገኛልሱናቸው መልዕክተኛው ሙሐመድ በተናገሩበት ቋንቋ ዐረብኛ በመካከላችን እንዳሉ ሆኖ በህትመት ደረጃም የተሰራጨ ነው። ወደ በርካታ ቋንቋዎችም ተተርጉሟል። የተከበረው ቁርአንና የመልክተኛው ሱና ለእስልምና እና ለመመርያ ብቸኛ ምንጮቹ ናቸው።

6- ነቢዩ ሙሐመድ ይዘውት የመጡት ሸሪዓ (መመርያ):-

መልእክተኛው ሙሓመድ ይዘውት የመጡት ሸሪዓ የእስልምና መመርያ የመለኮታዊ ህግጋቶች እና ተልዕኮዎ መደምደሚያ ነው። አመጣጡም ምንም እንኳ በዝርዝር አኳኃናቸው ቢለያዩም መሰረቱ ግን ከቀደምት ነብያት ህግጋቶች ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ነው።

ለሁሉም ጊዜና ቦታ የሚመጥን እና የሚስማማ፤ ለሰው ልጆች የዱኒያዊም ሆነ አኺራዊ ህይወታቸው ማስተካከያ ሙሉ መመርያ ነው። የዓለማት ጌታ የሚመለክባቸውን እንደ ሶላት፣ ዘካና መሰል በሰው ልጆች ላይ ግዴታ የሆኑ አምልኮዎችንም ሁሉ ያጠቃልላል። እንዲሁም ለሰው ልጆች አስፈላጊ የሆኑ የተፈቀዱና የተከለከሉትን ገንዘባዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካ፣ ወታደራዊ እና የአካባቢ ግብይቶች አበጥሮ ያብራራል።

ይህ ሸሪዓ የሰዎችን ሃይማኖት፣ ደም፣ ክብር፣ ገንዘብ፣ አእምሮ እና ዘራቸውንም ይጠብቅላቸዋል። ሁሉንም መልካም ምግባራት እና ፅድቅን ያጠቃለለ ሲሆን ከማንኛውም ወራዳነት እና ክፋትም የሚያስጠነቅቅ ነው። የሰው ልጅንም ወደ ክብር፣ ሚዛናዊነት፣ ፍትሃዊነት፣ ከይዩልኝና ይስሙልኝ ርቆ ለአሏህ ብሎ ወደ መስራት፣ ንፅህና፣ ብልሀት፣ መዋደድ፣ ለሰዎችም መልካሙን መውደድ፣ ደም መፋሰስንም እንዲተዉ፣ የሀገራቸውንም ሰላም እንዲያስጠብቁ ጥሪ የሚያደርግ ሲሆን ሰዎችን አላግባብ ከማስደንገጥና እንዲሰጉ ከማድረግም ያስጠነቅቃል። መልእክተኛው ሙሐመድ ሁሉም ድንበር ማለፍ እና ብክለት በሁሉም አይነና ቅርፁ ተዋግተውታ። የእንቶ ፈንቶ እምነት፣ ከማህበረሰቡ ራስን ማግለልንና ምንኩስናን ይቃወሙ ነበር።

እንዲሁም መልእክተኛው ሙሐመድ አላህ የሰው ልጅን - ወንድንም ይሁን ሴትን - እንዳከበረ እና መብታቸውን ባጠቃላይም እንዳረጋገጠላቸው፤ በምርጫቸው ፈልገው ለሚያደርጉት ድርጊት እና እንቅስቃሴም ኃላፊነቱ እንዳለባቸው፤ ራስንም ይሁን ሌላን በሚጎዳ ድርጊታቸውም ተጠያቂነት እንዳለባቸው ግልፅ አድርገዋል። በእስልምና ወንድም ይሁን ሴት ከኢማን፣ ከኃላፊነት፣ ከሽልማትና ምንዳ አኳያ እኩል ናቸው። በዚህ ሸሪዓ ውስጥ ሴት እንደ እናትም፣ እንደ ሚስትም፣ እንደ ሴት ልጅም እንደ እህትም ስትሆን የሚገባትን ልዩ ትኩረት ተችራለች።

እንዲሁም መልእክተኛው ሙሐመድ ይዘውት የመጡት ሸሪዓ አእምሮን ከመጠበቅ አኳያ እንደ አስካሪ መጠጥ አይነት የሚያበላሹትን ነገሮች ሁሉ ሐራም (እርም) አድርጓል። እስልምና ሃይማኖት ብሩህ አእምሮ አስፈላጊ የሆ ብርሃን አድርጎ ይቆጥረዋል። በዚህም ማንኛውም ሰው ጌታውን በአስተዋይነት እና በእውቀት ሆኖ ያመልከዋል። በእስልምና መመርያ የአዕምሮ ደረጃ ከፍ ያለና የኃላፊነትም ወሳኙ ማዕከል ነው። ከአጉል እምነት እና ጣኦታዊነት እስራትም ነፃ አውጥቶታል።

የእስልምና መመርያ ትክክለኛ አመክኖ (ሎጂክን) ይቀበላል፣ ከስሜታዊነት የጠራ አመክኖዋዊ ምርምር እንዲካሄድም ያበረታታል፣ ስለ ራስም ስለ ፍጥረተ ዓለምም ወደ ማሰላሰል ጥሪ ያደርጋል። ትክክለኛ አመክኖዋዊ ውጤቶችም መልእክተኛው ይዘውት ከመጡት ጋር የሚጣረስ አይደለም።

በእስልምና መመርያ (ሸሪዓ) ውስጥ አንዱ ጎሳ ከሌላኛው ጎሳ፣ አንዱ ህዝብም ከሌላኛው ህዝብ የሚበላለጥበት አንዳች ልዩነት የለም። ይልቁንም ሁሉም በኢስላማዊ ሸሪዓ መነጽር እኩል ናቸው። ምክንያቱም ሁሉም ሰዎች በአፈጣጠራቸው እኩል ናቸውና። አንዱ ዘር ከሌላኛው ዘር ህዝብም ከህዝብ የሚበላለጥበት ሚዛን ቢኖር አሏህን በመፍራት ብቻ ነው። መልእክተኛው ሙሀመድ ሁሉም ልጅ በተፈጥሮው በእስልምና ላይ ሆኖ እንደሚወለድም ተናግረዋል። በመሆኑም ማንም ቢሆን በስህተት ላይ ሆኖ አልያም ኃጢአትን ወርሶ የሚወለድ የለም።

በእስልምና መመርያ አሏህ “ተውባ” (ንስሀን) ደንግጓል፤ ይውም፡- የሰው ልጅ ኃጢአቱን ትቶ ወደ ጌታው በመመለስ፤ እስልምናን ከመቀበሉ በፊት የነበሩትን ወንጀሎች ደግሞ እስልምና በተቀበለበት ጊዜ ይሰረዝለታል። ለዚህም በሰው ልጅ ፊት የሰውን ሀጢያት መናዘዙ አስፈላጊ ባለመሆኑ እስልምና ከልክሎናል። በእስልምና የሰው ልጅ ቁርኝቱ ቀጥታ ከአምላኩ ጋር ነው። በአንተ እና በአሏህ መካከል አማላጅ አያስፈልግህም። እስልምና የሰው ልጅን አምላክ ማድረግህን ወይም ከአሏህ ጌትነት አልያም መለኮታዊነት ድርሻ ልታደርግለት ሐራም አድርጓል።

እንዲሁም መልእክተኛው ሙሐመድ ይዘውት የመጡት ሸሪዓ ከእርሳቸው በፊት ያለፉትን ሸሪዓዎች በሙሉ የሚሽር ነው። ምክንያቱም ሐመድ ከአላህ ዘንድ ይዘውት የመጡት የእስልምና ሸሪዓ እስከ እለተ ፍፃሜ ድረስ ለዓለማቱ ሁሉ የመጨረሻው ሸሪዓ ነውና። ስለዚህም ከእርሱ በፊት የነበሩ ሸሪዓዎችን በሙሉ የሚሽር ተደረገ። በዚህም መሰረት ኃያሉ አላህ የአሏህ መልዕክተኛ ሙሐመድ ይዘውት ከመጡት የእስልምና ሸሪዓ ውጪ ሌላ ሃይማኖትን አይቀበልም፤ ስለዚህም ከእስልምና ሌላ ሃይማኖት የተከተለ ሃይማኖቱ ተቀባይነት የለውም። በዚህ ረገድ ሰፋ ያለ ዝርዝር ማብራርያ የፈለገ የዚህን ሸሪዓ ድንጋጌዎች ዝርዝር ሚገልጹ ታማኝ መጽሐፍትን ይመልከት።

የእስልምና ሸሪዓ ግብ - ልክ እንደ ሁሉም መለኮታዊ ተልዕኮዎች ግብ ሁሉ፡- የሰው ልጅ እውነተኛው ሃይማኖት ተቀብሎ የአለማቱ ጌታ የአላህ ንፁህ ባሪያ እንዲሆን እና ለሰው፣ ለቁስ ወይም ለአጉል እምነት ባርያ ከመሆን መታደግ ነው።

የእስልምና ሸሪዓ ለማንኛውም ጊዜና ቦታ የሚመጥን (የሚስማማ) ነው። በመሆኑም የሰውን ትክክለኛ ጥቅም የሚጻረር አንዳችም ነገር የለውም። ምክንያቱም ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ከሚያውቅ ከአላህ ዘንድ የወረደ ነውና። ሰዎች ትክክለኛ መመርያ ያለው ሃይማኖ ይፈልጋሉ። እስልምና ደግሞ እርስ በራሱ የማይጣረስ፣ የሰው ልጆችን የሚያስተካክል፣ ማንኛውም የሰው ልጅ ሊደነግገው የማይቻለውና ይልቁንም ከአሏህ ዘንድ የመጣ፣ ሰዎችንም ወደ መልካምነትና ወደ ቀናነት የሚመራ፣ ወደ እርሱም የተመሩ እንደሆነ ጉዳያቸውን አስተካክሎ አንዱ ሌላኛውን ከመበደል የሚታደጉበት ሃይማኖት ነው።

7- ተቃዋሚዎቻቸው በእርሳቸው ላይ ያላቸው አቋምና ስለ እርሳቸው የሰጡት ምስክርነት፦

ሁሉም ነብያት የሚቃወማቸውና በጥሪያቸው መንገድ ላይ ተደንቅሮ የሚደቀንባቸው፣ ወደ ጥሪያቸውም ከመሄድ ሰዎችን የሚገታ ጋሬጣ እንዳጋጠማቸው የማያወላዳ እውነታ ነው። የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን - በህይወት ዘመናቸውም ይሁን ከህልፈታቸውም በኃላ ብዙ ተቃዋሚዎች ነበሯቸው። ይሁን እንጂ አላህም በሁሉም ላይ ረድቷቸዋል። የብዙዎቹ ምስክርነት - የጥንቶቹም ይሁን የአሁኖቹ - ነቢይ መሆናቸውን፤ ይዘውት የመጡትም መመርያ ቀደምት ነብያት የአላህ ሰላም በሁሉም ላይ ይስፈን ይዘውት እንደመጡት አይነት መለኮታዊ መመርያ መሆኑን ነው። እርሳቸው ትክክል እንደሆኑ ያውቃሉ ነገር ግን አብዛኛዎቹ በእርሳቸው እንዳያምኑ በብዙ መሰናክሎች ተከበዋል፤ ለምሳሌ የስልጣን ፍቅር ወይም ማህበረሰባቸውን መፍራት ወይም በዝና ያገኙትን ንብረት እንዳያጡ መስጋት ይገኙበታል።

ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን።

 

 

****************

ማውጫ

 

1 ስማቸው፣ የዘር ሀረጋቸው እና ተወልደው ያደጉበት ሀገር 2

2 የተባረከ ጋብቻ ከተባረከችዋ እመቤት ጋር 3

3 የወሕይ (መለኮታዊ ራዕይ) አጀማመር 3

4 ተልዕኳቸው (መልዕክታቸው)፦ 9

5- የነቢይነታቸው ተዓምራቶች፣ ምልክቶች እና ማስረጃዎቻቸው 12

6- ነቢዩ ሙሐመድ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን - ይዘውት የመጡት ሸሪዓ (መመርያ):- 14

7- ተቃዋሚዎቻቸው በእርሳቸው ላይ ያላቸው አቋምና ስለ እርሳቸው የሰጡት ምስክርነት፦ 17

 

 

***

 


ሰሒሕ አልቡኻሪይ (4461) 6/15.

ለዚህ ምሳሌ የበላይ የሆነው አላህ ንግግር ነው:- "እናንተ ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ፡፡ ለእርሱም አድምጡት፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው (ጣዖታት) ዝንብን ፈጽሞ አይፈጥሩም፡፡ እርሱን (ለመፍጠር) ቢሰበሰቡም እንኳን (አይችሉም)፡፡ አንዳችንም ነገር ዝንቡ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም፡፡ ፈላጊውም ተፈላጊውም ደከሙ።" [አል-ሐጅ፡ 73]

ሶሒሕ ሙስሊም ሐዲሥ ቁጥር (901)