PHPWord

 

 

التَّحْقِيقُ وَالإِيضَاحُ لِكَثِيرٍ مِنْ مَسَائِلِ

الحَجِّ وَالعُمْرَةِ وَالزِّيَارَةِ عَلَى ضَوءِ الكِتَابِ وَالسُّنَّة

 

 

በቁርኣንና ሐዲሥ መሰረት የሐጅ፣ የዑምራና የዚያራ በርካታ ጉዳዮች ማረጋገጫ እና ማብራሪያዎች

 

 

 

لِسَمَاحَةِ الشَّيْخِ العَلَّامَةِ

عَبْدِ العَزِيزِ بْنِ عَبْدِ اللهِ بْنِ بَازٍ

رَحِمَهُ اللهُ

በተከበሩ እውቁ ሸይኽ

ዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ

 

 


بِسْمِ اللهِ الرَّحمَنِ الرَّحِيمِ

በቁርኣንና ሐዲሥ መሰረት የሐጅ፣ የዑምራና የዚያራ በርካታ ጉዳዮች ማረጋገጫ እና ማብራሪያዎች

 

የአዘጋጁ መግቢያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው

ምስጋና ሁሉ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ነው። የመጨረሻውም ሀገር አላህን ለሚፈሩ ለጥንቁቆቹ ነው። የአላህ ሶለዋትና ሰላም የአላህ ባሪያውና መልዕክተኛው በሆኑት ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸውም ላይ ሁሉ ይስፈን።

በመቀጠልም፦

ይህች ስለ ሐጅ፣ ሰለትሩፋቱና ስነስርዓቱ፣ እንዲሁም ሐጅን ለመፈፀም ጉዞ ያሰበ ሰው ሊሰራቸው ስለሚገቡ ነገር፤ በተጨማሪም በርካታ የሐጅ፣ የዑምራና የዚያራን ወሳኝ ጉዳዮች በአጭሩና በግልፅ የምታብራራ አጠር ያለች መልዕክት ናት። በዚህ መልዕክት ውስጥ ከአላህ ኪታብና ከመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሱና በመነጨው ማስረጃ ላይ ለመገደብ ጥረት አድርጌያለሁ። ያዘጋጀኋትም ለሙስሊሞች ምክር ትሆን ዘንድና ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ሲል ያዘዘበትን ቃል በተግባር ለማዋል ነው፡

﴿وَذَكِّرْ فَإِنَّ الذِّكْرَى تَنْفَعُ الْمُؤْمِنِينَ 55﴾

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገስጽም ግሳጼ አማኞችን ትጠቅማለችና። [አዝ-ዛሪያት፡ 55] አላህ እንዲህ ያለበትንም:

﴿وَإِذْ أَخَذَ اللَّهُ مِيثَاقَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ لَتُبَيِّنُنَّهُ لِلنَّاسِ وَلَا تَكْتُمُونَهُ...﴾

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የእነዚያ መጽሐፍን የተሰጡትን ለሰዎች በእርግጥ «ልታብራሩት እንጂ ላትደብቁት» በማለት የያዘባቸውን ቃል ኪዳን አስታውስ። [አሊ-ዒምራን፡ 187] ልቅና ይገባውና እንዲህ ያለበትንም ቃል፦

﴿...وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَى...﴾

በበጎ ተግባርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ [አል-ማኢዳህ: 2]

ሶሒሕ በሆነ ሐዲሥም ነቢዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፡-

«الدِّينُ النَّصِيحَةُ، ثَلَاثًا، قِيلَ: لِمَنْ يَا رَسُولَ اللَّهِ؟ قَالَ: لِلَّهِ وَلِكِتَابِهِ وَلِرَسُولِهِ وَلِأَئِمَّةِ المُسْلِمِينَ وَعَامَّتِهِمْ».

«"ሃይማኖት (ኢስላም) ማለት መቆርቆር (ቅንነት) ነው" በማለት ሶስት ጊዜ ደገሙት። "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (ቅን የምንሆነው) ለማን ነው?" ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም "ለአላህ፣ ለመጽሐፉ፣ ለመልክተኛው፣ ለሙስሊሞች መሪዎችና ለአጠቃላይ ሙስሊም ማህበረሰብ ነው።" አሉ።»1

ጦበራኒይ ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደዘገቡት: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦

«مَنْ لَمْ يَهْتَمَّ بِأَمْرِ المُسْلِمِينَ فَلَيْسَ مِنْهُمْ، وَمَنْ لَمْ يُصْبِحْ وَيُمْسِ نَاصِحًا لِلَّهِ وَلِرَسُولِهِ وَلِكِتَابِهِ وَلِإِمَامِهِ وَلِعَامَّةِ المُسْلِمِينَ فَلَيْسَ مِنْهُمْ».

ስለ ሙስሊሞች ጉዳይ ግድ ያልሰጠው ከነሱ አይደለም፤ እንዲሁም ነጋ ጠባ ለአላህ፣ ለመልእክተኛው፣ ለመጽሐፉ፣ ለመሪውና ለአጠቃላይ ሙስሊሞች ቅን ያልሆነ ከነሱ አይደለም»2

አላህን በዚህ ሥራ እኔንም ሆነ ሙስሊሞችን እንዲጠቅምበት፣ በውስጡ የተደረገውን ጥረትም ለተከበረው ፊቱ ብቻ የጠራና ጸጋዋ የሞላውን ጀነቶች መጎናፀፊያ እንዲያደርግልን እንጠይቀዋለን። እርሱ ሰሚና ጸሎትን ተቀባይ ነው፤ እርሱም በቂያችን ነው፣ ምንኛ ያማረ መጠጊያም ነው።

 

አዲስ ክፍል:

ሐጅና ዑምራ ግዴታ መሆኑንና ቶሎ መፈፀምም የሚገባ ስለመሆኑ ማስረጃዎቹ

ይህን ካወቅን - አላህ እኔንም እናንተንም ሐቅን አውቆ ለመከተል ይወፍቀንና - የላቀው አላህ በባሮቹ ላይ ወደተከበረው ቤቱ የሐጅ ዚያራ ማድረግን ግዴታ እንዳደረገና ከእስልምና ማእዘናትም አንዱ እንዳደረገውም ይታወቅ። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል:

﴿...وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا وَمَنْ كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ﴾

ለአላህም በሰዎች ላይ ወደ እርሱ መሄድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው። የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው። [አሊ-ዒምራን፡ 97]

በሶሒሕ ቡኻሪይና ሙስሊም ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በተላለፈ ሓዲሥ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-

«بُنِيَ الإِسْلَامُ عَلَى خَمْسٍ: شَهَادَةِ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ، وَإِقَامِ الصَّلَاةِ، وَإِيتَاءِ الزَّكَاةِ، وَصَوْمِ رَمَضَانَ، وَحَجِّ بَيْتِ اللَّهِ الحَرَامِ».

«እስልምና በአምስት ምሰሶዎች ላይ ተገንብቷል፦ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን እና ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መመስከር፣ ሶላትን ደንብና ሥርዓቱን ጠብቆ መስገድ፣ ዘካ መስጠት፣ የረመዳንን ወር መጾም፣ እና የተከበረውን የአላህን ቤት ሐጅ ማድረግ ናቸው።»3

ሰዒድ በሱነናቸው ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደዘገቡት እንዲህ ብለዋል፦ «በእርግጥም ወደ እነዚህ ከተሞች ሰዎችን ልኬ አቅም ኖሯቸው4 ሐጅ ያላደረጉትን ሰዎች ሁሉ እንዲመለከቱና ጂዝያ እንዲጥሉባቸው አስቤ ነበር። እነርሱ ሙስሊሞች አይደሉም፤ እነርሱ ሙስሊሞች አይደሉም5።»

ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል: «ሐጅ ማድረግ እየቻለ የተወ ሰው፤ ሞቱ ከአይሁድ ወይም ከክርስቲያን ሞት የሚለየው ነገር የለም።»6

አቅሙ እያለው ሐጅ ያላደረገ ሰው ወደ ሐጁ መቻኮል ግዴታ ይሆንበታል። ይህም ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና - እንዳስተላለፉት ነቢዩ ﷺ እንዲህ በማለታቸው ነው፦

«تَعَجَّلُوا إِلَى الحَجِّ - يَعْنِي الفَرِيضَةَ - فَإِنَّ أَحَدَكُمْ لَا يَدْرِي مَا يَعْرِضُ لَهُ».

አንዳችሁ የሚያጋጥመውን አያውቅምና ሐጅን (ግዴታውን ሐጅ) ለመፈፀም ተቻኮሉ።"7

ምክንያቱም ሐጅን መፈፀም አቅም ባለው ሰው ላይ ቶሎ ሊፈፀም የሚገባ ግዴታ ነው፤ እንዲህ የሚለው የላቀው አላህ ንግግር ጉልህ አውዱ ይህንን ይጠቁማልና፦

﴿...وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا وَمَنْ كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ﴾

ለአላህም በሰዎች ላይ ወደ እርሱ መሄድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን የመጎብኘት ግዴታ አለባቸው። የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው። [አሊ-ዒምራን፡ 97] ነቢዩም ﷺ በኹጥባቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፦

«أَيُّهَا النَّاسُ، إِنَّ اللَّهَ فَرَضَ عَلَيْكُمُ الحَجَّ فَحُجُّوا».

«ሰዎች ሆይ! አላህ ሐጅን በናንተ ላይ ግዴታ አድርጓልና ሐጅ አድርጉ።»8

ዑምራ ግዴታ መሆኑን የሚያመለክቱ ሐዲሦችም ተዘግበዋል: ከነርሱም መካከል:

ጂብሪል ነቢዩን ﷺ ስለ ኢስላም በጠየቃቸው ጊዜ በሰጡት መልስ እንዲህ ብለዋል፦

«الإِسْلَامُ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ، وَتُقِيمَ الصَّلَاةَ، وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ، وَتَحُجَّ البَيْتَ وَتَعْتَمِرَ، وَتَغْتَسِلَ مِنَ الجَنَابَةِ، وَتُتِمَّ الوُضُوءَ، وَتَصُومَ رَمَضَانَ»

«እስልምና ማለት፦ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን እና ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መመስከር፣ ሶላትን ደንብና ስርዓቷን አሟልተህ መስገድ፣ ዘካን መስጠት፣ ሐጅ ማድረግና ዑምራ ማድረግ፣ ከጀናባ መታጠብ፣ ውዱእን ማሟላት እና የረመዷንን ወር መፆም ነው።»9 ኢብኑ ኹዘይማህ እና ዳረቁጥኒይ ከዑመር ኢብኑል ኸጣብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ዘግበውታል፤ ዳረቁጥኒይም ሰነዱን የተረጋገጠ እና ሶሒሕ ብለውታል።

ከነዚህም ውስጥ የዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- ሐዲሥ ይገኝበታል፤ ዓኢሻህ እንዲህ ብላለች፦

«يَا رَسُولَ اللَّهِ، هَلْ عَلَى النِّسَاءِ مِنْ جِهَادٍ؟ قَالَ: عَلَيْهِنَّ جِهَادٌ لَا قِتَالَ فِيهِ: الحَجُّ وَالعُمْرَةُ»

«የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሴቶች ጂሃድ የማድረግ ግዴታ አለባቸውን? ሲባሉ፤ "በእነርሱ ላይ ውጊያ የሌለበት ጂሃድ ነው ግዴታቸው፤ እሱም ሐጅና ዑምራ ማድረግ ነው።" አሉ።»10 አሕመድ እና ኢብኑ ማጃህ ሶሒሕ በሆነ ዘገባ ዘግበውታል።

ሐጅና ዑምራ በህይወት ዘመን ግዴታ የሚሆኑት አንድ ጊዜ ብቻ ነው፤ ይህም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶሒሕ በሆነ ሐዲሥ ላይ እንዲህ ስላሉ ነው፦

«الحَجُّ مَرَّةٌ، فَمَنْ زَادَ فَهُوَ تَطَوُّعٌ».

«ሐጅ አንድ ጊዜ ነው፤ የጨመረ ሰው በፍላጎቱ ነው።»11

ሐጅና ዑምራን በፈቃደኝነት ማብዛት ሱና ነው፤ ቡኻሪይና ሙስሊም ከአቡ ሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ በዘገቡት ሓዲሥ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

«العُمْرَةُ إِلَى العُمْرَةِ كَفَّارَةٌ لِمَا بَيْنَهُمَا، وَالحَجُّ المَبْرُورُ لَيْسَ لَهُ جَزَاءٌ إِلَّا الجَنَّةُ».

«ከዑምራ እስከ ዑምራ በመካከላቸው ለተሰሩ ወንጀሎች ማስማሪያ ናቸው። ተቀባይነት ያለው ሐጅ ለርሱ ከጀነት ውጪ ምንም ምንዳ የለውም።»12

 

 

 

አዲስ ክፍል:

ከወንጀሎች ተውበት ማድረግና ከበደሎች መላቀቅ ግዴታ ስለመሆኑ፤

ወደ ሐጅ ወይም ዑምራ ጉዞ ለማድረግ የወሰነ ሙስሊም፤ ቤተሰቦቹንና ባልደረቦቹን የአላህን (ዐዘ ወጀለ) ፍራቻ አደራ ማለቱ ይወደድለታል። አላህን መፍራት ማለት ትእዛዛቱን መፈፀምና ክልከላዎቹን መራቅ ነው።

እርሱ ሰዎች ጋር ያለውንና ያለበትን እዳ መፃፍና በዚያ ላይም ማስመስከር ይጠበቅበታል። እንዲሁም ከሁሉም ወንጀሎች ንፁህ ተውበት ለማድረግ መቻኮልም ግዴታ ይጠበቅበታል፤ ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏልና፦

﴿...وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ﴾

{ምዕመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ።} [አን-ኑር፡ 31]

ትክክለኛ ተውበት የሚባለው: ከወንጀሎች መውጣትና መተው፣ ባሳለፈው ወንጀሎች መፀፀት፣ ወደ እርሱም ዳግም ላለመመለስ መቁረጥ ነው። በሰዎች ላይ በነፍስ፣ በገንዘብ ወይም በክብር የፈጸመው በደል ካለበት ደግሞ፤ ከጉዞው በፊት ወደ ባለቤቶቻቸው መመለስ ወይም ከነርሱ ዓፉታቸውን መጠየቅ አለበት፤ ከነቢዩ ﷺ በሶሒሕ ዘገባ እንደተዘገበው እንዲህ ብለዋል፦

«مَنْ كَانَتْ عِنْدَهُ مَظْلَمَةٌ لِأَخِيهِ مِنْ مَالٍ أَوْ عِرْضٍ فَلْيَتَحَلَّلِ اليَوْمَ قَبْلَ أَنْ لَا يَكُونَ دِينَارٌ وَلَا دِرْهَمٌ، إِنْ كَانَ لَهُ عَمَلٌ صَالِحٌ أُخِذَ مِنْهُ بِقَدْرِ مَظْلَمَتِهِ، وَإِنْ لَمْ تَكُنْ لَهُ حَسَنَاتٌ أُخِذَ مِنْ سَيِّئَاتِ صَاحِبِهِ فَحُمِلَ عَلَيْهِ».

«ወንድሙን በገንዘብ ወይም ክብሩን በማጉደፍ የበደለ ሰው ዲናርና ዲርሃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ዛሬ ከራሱ ላይ በደሉን ያስነሳ። (ዛሬ ይህ ካልሆነ በቂያማ እለት) መልካም ስራ ካለው በበደሉ ልክ ይቀነስበታል። ለርሱ መልካም ስራ ከሌለው ደግሞ ከበደለው ባልደረባው ወንጀሎች ተወስደው እርሱ ላይ ይጫንበታል።»13.

ለሐጁና ዑምራው ከሐላል ገንዘብ ጥሩ ሲሳይን መምረጥ ይገባዋል፤ ሶሒሕ በሆነ ዘገባ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

«إِنَّ اللَّهَ تَعَالَى طَيِّبٌ لَا يَقْبَلُ إِلَّا طَيِّبًا».

«የላቀው አላህ መልካም ነው፤ ከመልካም በቀር አይቀበልም።»14

ጦበራኒይም ከአቡ ሁረይራ አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደዘገቡት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

«إِذَا خَرَجَ الرَّجُلُ حَاجًّا بِنَفَقَةٍ طَيِّبَةٍ وَوَضَعَ رِجْلَهُ فِي الغَرْزِ فَنَادَى: لَبَّيْكَ اللَّهُمَّ لَبَّيْكَ، نَادَاهُ مُنَادٍ مِنَ السَّمَاءِ: لَبَّيْكَ وَسَعْدَيْكَ، زَادُكَ حَلَالٌ، وَرَاحِلَتُكَ حَلَالٌ، وَحَجُّكَ مَبْرُورٌ غَيْرُ مَأْزُورٍ، وَإِذَا خَرَجَ الرَّجُلُ بِالنَّفَقَةِ الخَبِيثَةِ فَوَضَعَ رِجْلَهُ فِي الغَرْزِ فَنَادَى: لَبَّيْكَ اللَّهُمَّ لَبَّيْكَ، نَادَاهُ مُنَادٍ مِنَ السَّمَاءِ: لَا لَبَّيْكَ وَلَا سَعْدَيْكَ، زَادُكَ حَرَامٌ، وَنَفَقَتُكَ حَرَامٌ، وَحَجُّكَ غَيْرُ مَبْرُورٍ».

«አንድ ሰው ጥሩ (ሐላል) በሆነ ወጪ ሐጅ ለማድረግ ሲወጣና በመጓጓዣው ላይ ተሳፍሮ "ለበይከሏሁመ ለበይክ" ብሎ ሲጣራ ከሰማይ ተጣሪ እንዲህ ሲል ይመልስለታል፡- "ለበይከ ወሰዕደይክ፤ ስንቅህ ሐላል ነው፤ መጓጓዣህም ሐላል ነው፤ ሐጅህም ተቀባይነት ያለው (መብሩር) እና ወንጀል የሌለበት ነው።" መጥፎ (ሐራም) በሆነ ወጪ ሲወጣና በመጓጓዣው ላይ ተሳፍሮ "ለበይከሏሁመ ለበይክ" ብሎ ሲጣራ ደግሞ ከሰማይ ተጣሪ እንዲህ ሲል ይመልስለታል፡- "ላ ለበይከ ወላ ሰዕደይክ፤ ስንቅህ ሐራም ነው፤ ወጪህም ሐራም ነው፤ ሐጅህም ተቀባይነት የሌለው ነው።"»15

ለሐጅ አድራጊ በሰዎች እጅ ካለ ነገር መብቃቃትና እነርሱንም ከመለመን መጠበቅ ይገባዋል፤ ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋልና፡

«وَمَنْ يَسْتَعْفِفْ يُعِفَّهُ اللَّهُ، وَمَنْ يَسْتَغْنِ يُغْنِهِ اللَّهُ».

«ጥብቅናን የፈለገን ሰው አላህ ጥብቅ ያደርገዋል፤ መብቃቃትንም የፈለገን ሰው አላህ ያብቃቃዋል።»16.

ነቢዩ ﷺ እንዲህም ብለዋል፦

«لَا يَزَالُ الرَّجُلُ يَسْأَلُ النَّاسَ حَتَّى يَأْتِيَ يَوْمَ القِيَامَةِ وَلَيْسَ فِي وَجْهِهِ مُزْعَةُ لَحْمٍ».

«አንድ ሰው ሰዎችን መለመን አያቋርጥም፤ የትንሳኤ ቀን በፊቱ ላይ የሥጋ ቁራጭ እንኳ ሳይኖረው እስከሚመጣ ድረስ።»17

ሐጅ የሚያደርግ ሰው በሐጁና ዑምራው የአላህን ፊትና የመጨረሻይቱን ዓለም ማሰቡ፣ እንዲሁም በነዚያ በተከበሩ ቦታዎች እርሱን በሚያስደስቱ ንግግሮችና ስራዎች ወደ አላህ መቃረቡ ግዴታ ነው። እንዲሁም በሐጁ ዱንያንና ርካሽ ጥቅማጥቅሟን ከማሰብ፣ ወይም ይዩልኝና ይስሙልኝን እንዲሁም በሐጁ መፎካከርን ከማሰብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባዋል። ምክንያቱም ይህ እጅግ ከከፉ አላማዎች አንዱና ስራው እንዲበላሽ እንዲሁም ተቀባይነት እንዲያጣ ምክንያት ነውና። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡

﴿مَنْ كَانَ يُرِيدُ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا وَزِينَتَهَا نُوَفِّ إِلَيْهِمْ أَعْمَالَهُمْ فِيهَا وَهُمْ فِيهَا لَا يُبْخَسُونَ 15 أُولَئِكَ الَّذِينَ لَيْسَ لَهُمْ فِي الاخِرَةِ إِلَّا النَّارُ وَحَبِطَ مَا صَنَعُوا فِيهَا وَبَاطِلٌ مَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ 16﴾

«ቅርቢቱን ህይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሰዎች የሥራዎቻቸውን ምንዳ በእርሷ ውስጥ ወደ እነርሱ እንሞላላቸዋለን። እነርሱም በእርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸዉም።

እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ ከእሳት በስተቀር የሌላቸው ናቸው። የሰሩትም ሥራ በእርሷ ውስጥ ተበላሸ። በቅርቢቱ ዓለም ይሰሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው። [ሁድ: 15-16]

ጥራት ይገባውና እንዲህም ብሏል፡

﴿مَّنْ كَانَ يُرِيدُ الْعَاجِلَةَ عَجَّلْنَا لَهُ فِيهَا مَا نَشَاءُ لِمَنْ نُرِيدُ ثُمَّ جَعَلْنَا لَهُ جَهَنَّمَ يَصْلَاهَا مَذْمُومًا مَدْحُورًا 18 وَمَنْ أَرَادَ الْاخِرَةَ وَسَعَى لَهَا سَعْيَهَا وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَئِكَ كَانَ سَعْيُهُمْ مَشْكُورًا 19﴾

{ጊዜያዊቱን ዓለም (በሥራው) የሚፈልግ ሰው ለእርሱ በእርሷ ውስጥ የፈለግነውን ጸጋ ለምንፈልገው ሰው እናስቸኩልለታለን። ከዚያም ለእርሱ ገሀነምን መኖሪያ አድርገንለታል። ተወቃሽና ከአላህ እዝነት የተባረረ ሆኖ ይገባባታል።

{መጨረሻይቱንም ዓለም የፈለገ ሰው እርሱ አማኝ ሆኖ ለእርሷ ተገቢውን ሥራ የሰራም ሰው እነዚህ ሥራቸው የተመሰገነ ይሆናል።} [አል-ኢስራእ: 18-19]

ነቢዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸውም በሶሒሕ ሐዲሥ ተላልፏል፦

«قَالَ اللَّهُ تَعَالَى: أَنَا أَغْنَى الشُّرَكَاءِ عَنِ الشِّرْكِ، مَنْ عَمِلَ عَمَلًا أَشْرَكَ مَعِي فِيهِ غَيْرِي تَرَكْتُهُ وَشِرْكَهُ».

«ከፍ ያለው አሏህ እንዲህ ብሏል፦ "እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።"»18

እንዲሁም በጉዞው ላይ አላህን ታዛዦች፣ ተቅዋ ያላቸውንና የዲን ዕውቀት ያላቸውን መልካም ሰዎችን መወዳጀት፤ ቂሎችንና ፋሲቆችን ከመወዳጀት ደግሞ መጠንቀቅ ይገባዋል።

በሐጁና በዑምራው ወቅት የሚተገብራቸውን ሊማር፣ ሊገነዘብና የከበደውንም ነገር ሊጠይቅ ይገባዋል፤ ይህም በእውቀት ላይ ሆኖ ስርአቱን እንዲያከናውን ነው። እንስሳው ወይም መኪናው ወይም ፕሌኑ ወይም ከዛ ውጪ ባሉ መሳፈሪያዎች ላይ ሲሳፈር ቢስሚላህ፣ አልሐምዱሊላህ ማለት፤ ከዚያም ሶስት ጊዜ ተክቢራ ብሎ የሚከተለውን ማለቱ ይወደድለታል፡

﴿...سُبْحَانَ الَّذِي سَخَّرَ لَنَا هَذَا وَمَا كُنَّا لَهُ مُقْرِنِينَ 13 وَإِنَّا إِلَى رَبِّنَا لَمُنْقَلِبُونَ 14﴾

{ጥራት ተገባው ይህንን የማንችለው ስንሆን ለእኛ ያገራልን ጌታ 13

እኛም በእርግጥ ወደ ጌታችን አላህ ተመላሾች ነን። 14} [አዝ-ዙኽሩፍ፡ 13 -14]

«اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ فِي سَفَرِي هَذَا البِرَّ وَالتَّقْوَى، وَمِنَ العَمَلِ مَا تَرْضَى، اللَّهُمَّ هَوِّنْ عَلَيْنَا سَفَرَنَا هَذَا، وَاطْوِ عَنَّا بُعْدَهُ، اللَّهُمَّ أَنْتَ الصَّاحِبُ فِي السَّفَرِ، وَالخَلِيفَةُ فِي الأَهْلِ، اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ وَعْثَاءِ السَّفَرِ، وَكَآبَةِ المَنْظَرِ، وَسُوءِ المُنْقَلَبِ فِي المَالِ وَالأَهْلِ».

"አላሁመ ኢንኒ አስአሉከ ፊ ሰፈሪ ሀዛ አል-ቢረ ወት-ተቅዋ፣ ወሚነል ዐመሊ ማ ተርዷ፣ አላሁመ ሀውዊን ዐለይና ሰፈረና ሀዛ፣ ወጥዊ ዓና ቡዕደሁ፣ አላሁመ አንተስ-ሷሒቡ ፊስ-ሰፈር፣ ወል-ኸሊፈቱ ፊል-አህል፣ አላሁመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚን ወዕሣኢ-ሰፈር፣ ወካአባቲል-መንዞር፣ ወሱኢል-ሙንቀለቢ ፊል-ማሊ ወል-አህል"19፤ (ትርጉሙም፡ አላህ ሆይ! እኔ በዚህ ጉዞዬ በጎን ነገርና ፍራቻን፣ ከስራም የምትወደውን እጠይቅሃለሁ። አላህ ሆይ! ይህንን ጉዟችንን አቅልልልን፣ ርቀቱንም ሰብስብልን። አላህ ሆይ! እኛን በጉዟችን የምትጎዳኘን፣ በቤተሰቦቻችን ጉዳይም የምትተካን አንተው ነህ። አላህ ሆይ! እኔ ከጉዞ መከራ፣ በመጥፎ ገፅታ ከመታየትና ወደ ቤተሰቦቼና ንብረቶቼ መጥፎ አመላለስን ከመመለስ በአንተ እጠበቃለሁ።)

ይህ ሐዲሥ ሙስሊም ከኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁማ ሶሒሕ በሆነ ዘገባ ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘግበውታል።

በጉዞው ወቅትም ዚክርን፣ ኢስቲግፋርን፣ አላህን መለመንን፣ ወደርሱ መተናነስን፣ እንዲሁም ቁርኣን መቅራትንና ማስተንተንን ያብዛ። ሶላቶችን በጀማዓ መስገድን ይጠብቅ። ምላሱን ወሬ ከማብዛት፣ በማይመለከተው ነገር ከመግባትና በቀልድ ድንበር ከማለፍ ይጠብቅ። እንዲሁም ምላሱን ከውሸት፣ ከሐሜት፣ ነገር ከማዋሰድና በጓደኞቹም ሆነ በሌሎች ሙስሊም ወንድሞቹ ላይ ከማሾፍ ይጠብቅ።

ለጓደኞቹ በጎ መዋልና እነርሱ ላይ ክፋትን ከመፈፀም ሊቆጠብ፤ እንዲሁም በአቅሙ ልክ በጥበብና በመልካም ግሳፄ በመልካም ሊያዛቸውና ከመጥፎ ሊከለክላቸው ይገባል።

አዲስ ክፍል:

ሐጅ አድራጊ (ኢሕራም ማድረጊያ ስፍራ) ሚቃት ሲደርስ ማድረግ ያለበት፤

ወደ ሚቃት ሲደርስ መታጠብና ሽቶ መቀባት ይወደድለታል። ለዚህም ማስረጃው ነብዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ኢሕራም በሚያደርጉበት ጊዜ የተሰፉ ልብሶችን አውልቀው መታጠባቸው መዘገቡና በቡኻሪይ እና ሙስሊም ላይም ከዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደተዘገበው እንዲህ ማለቷ ነው፦

«كُنْتُ أُطَيِّبُ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ لِإِحْرَامِهِ قَبْلَ أَنْ يُحْرِمَ، وَلِحَلِّهِ قَبْلَ أَنْ يَطُوفَ بِالبَيْتِ».

«የአላህ መልዕክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኢሕራም ከመግባታቸው በፊት ለኢሕራማቸው፣ እንዲሁም ከሐጅ ተግባራቸው ለማጠናቀቅ በአላህ ቤት ጦዋፍ ከማድረጋቸው በፊት ሽቶ እቀባቸው ነበር።»20 ዓኢሻንም ለዑምራ ኢሕራም አድርጋ ሳለ የወር አበባዋ ሲመጣባት ገላዋን እንድትታጠብና ለሐጅ ኢሕራም እንድታደርግ አዘዋታል። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስማእ ቢንት ዑመይስ ዙልሑለይፋ ላይ በወለደች ጊዜ ገላዋን እንድትታጠብ፣ በጨርቅ ታጥቃም ኢሕራም እንድታደርግ አዘዋታል21። ይህም የሚያመላክተው፤ አንዲት ሴት የወር አበባ ወይም የድህረ ወሊድ ደም እያየች ሚቃት በደረሰች ጊዜ ገላዋን ታጥባ ከሌሎች ሰዎች ጋር ኢሕራም ማድረግ እንዳለባትና፣ ነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዓኢሻንም አስማእንም እንዳዘዟቸው ከካዕባ ጠዋፍ በስተቀር ሐጅ አድራጊ የሚፈፅመውን ስርአት ሁሉ መፈፀም እንዳለባት ነው።

ኢሕራም ለማድረግ ያሰበ ሰው ቀድሞ ቀመሱን፣ ጥፍሮቹን እንዲሁም የብብትና የብልት አካባቢ ፀጉሩንና መሰል መወገድ ያለባቸውን ነገሮች ቀድሞ ማስወገዱ ይወደድለታል። ይህን የሚያደርገውም በኢሕራም ላይ እያለ እነዚህን ነገሮች ማስወገድ ክልክል ስለሚሆንበት በዚያን ወቅት እንዳያስፈልገው ነው። ነቢዩም ‐የአላህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና‐ ሙስሊሞች ለነዚህ ነገሮች ሁልጊዜ ትኩረት እንዲሰጡ ደንግገዋል፤ በቡኻሪይና ሙስሊም ከአቡ ሁረይራ ‐አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና‐ እንደተዘገበው የአላህ መልዕክተኛ ‐የአላህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና‐ እንዲህ ብለዋል፦

«الفِطْرَةُ خَمْسٌ: الخِتَانُ، وَالِاسْتِحْدَادُ، وَقَصُّ الشَّارِبِ، وَقَلْمُ الأَظْفَارِ، وَنَتْفُ الإِبْطِ».

ተፈጥሯዊ ሱናዎች አምስት ናቸው፦ እነርሱም: መገረዝ፣ የብልትን ፀጉር መላጨት፣ ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለን ፂም) ማሳጠር፣ ጥፍሮችን መቁረጥና የብብትን ፀጉር መንጨት ናቸው።"22

ሙስሊም ከአነስ ‐አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና‐ ባስተላለፉት ሓዲሥ እንዲህ ብለዋል:

«وَقَّتَ لَنَا فِي قَصِّ الشَّارِبِ، وَقَلْمِ الأَظْفَارِ، وَنَتْفِ الإِبْطِ، وَحَلْقِ العَانَةِ: أَنْ لَا نَتْرُكَ ذَلِكَ أَكْثَرَ مِنْ أَرْبَعِينَ لَيْلَةً».

«ቀድሞ ቀመስን በመቀነስ፣ ጥፍርን በመቁረጥ፣ የብብት ፀጉርን በመንጨትና ብልት አካባቢ የሚበቅልን ፀጉር በመላጨት ዙሪያ ከአርባ ቀናት በላይ ሳናስወግድ እንዳንተወው የጊዜ ገደብ ተቀመጠልን።»23

እንዲሁም ነሳኢይ እንዲህ በሚል ቃል ዘግበውታል፦

«وَقَّتَ لَنَا رَسُولُ اللَّهِ ﷺ».

የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላት እና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) የጊዜ ገደብ ወስነውልናል።"24 እንዲሁም አሕመድ፣ አቡ ዳውድ እና ቲርሚዚይ ነሳኢይ ከዘገቡት ጋር ተመሳሳይ በሆነ ቃል ዘግበውታል። የጭንቅላትን ፀጉር በተመለከተ ግን በኢሕራም ጊዜ ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች አንዳችንም ፀጉር ማስወገድ አልተደነገገም።

ፂምን በተመለከተ በማንኛውም ጊዜያት መላጨት ወይም ማሳጠር ሐራም ነው። ይልቁንም በቡኻሪ እና ሙስሊም ውስጥ ከኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደተላለፈው ፂምን መልቀቅና መተው ግዴታ ነው። ኢብኑ ዑመር ረዺየሏሁ ዓንሁማ ባስተላለፉት ሐዲሥ የአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦

«خَالِفُوا المُشْرِكِينَ، وَفِّرُوا اللِّحَى، وَأَحْفُوا الشَّوَارِبَ».

«ሙሽሪኮችን ተፃረሩ፤ ሪዛችሁን ልቀቁ፤ ቀድሞ ቀመስንም አሳጥሩ»25 ሙስሊም ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በዘገቡት ሶሒሕ ሐዲሥ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

«جُزُّوا الشَّوَارِبَ، وَأَرْخُوا اللِّحَى، خَالِفُوا المَجُوسَ».

«ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለውን ፂም) አሳጥሩ፣ ሪዛችሁን (የመንጋጭላ ፂማችሁን) ልቀቁ፤ መጁሶችን ተኻለፉ»26

በዚህ ዘመን ብዙ ሰዎች—ራሳቸውን ወደ እውቀትና ትምህርት የሚያስጠጉም ጭምር—ይህንን ሱና በመፃረር ፂምን መዋጋት እና ከሀዲያንንና ሴቶችን መመሳሰል በመውደዳቸው መከራው እጅግ ከፍቷል። (ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን) እኛም የአላህ ነን፤ ወደርሱም ተመላሾች ነን። ምንም እንኳ ብዙ ሙስሊሞች ከዚህ ሱና ቢሸሹም፤ እኛንም ሆነ ሌሎችን ሙስሊሞች ሱናን የምንከተል፣ በርሷም አጥብቀን የምንይዝ፣ ወደርሷም የምንጣራ እንዲያደርገን አላህን እንለምነዋለን። አላህ በቂያችን ነው፤ እርሱም ምንኛ ያማረ መመኪያ ነው። በላቀውና በታላቁ አላህ ቢሆን እንጂ ብልሀትም ሆነ ሀይል የለም።

ከዚያም ወንዱ ሽርጥና ኩታ ይለብሳል፤ ሁለቱም ነጫጭና ንጹህ መሆናቸው፣ እንዲሁም በሸበጥ ኢሕራም ማድረጉ ይወደዳል፤ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋልና፦

«وَلْيُحْرِمْ أَحَدُكُمْ فِي إِزَارٍ وَرِدَاءٍ وَنَعْلَيْنِ، فَإِنْ لَمْ يَجِدْ نَعْلَيْنِ فَلْيَلْبَسْ خُفَّيْنِ وَلْيَقْطَعْهُمَا حَتَّى يَكُونَا أَسْفَلَ مِنَ الكَعْبَيْنِ».

«አንዳችሁ በሽርጥና ኩታ እንዲሁም በሸበጥ ጫማዎች ኢሕራም ያድርግ፤ ነጠላ ጫማዎችን ያላገኘ እንደሆነ ኹፎችን ይልበስ፤ ከቁርጭምጭሚት በታች እስከሚሆኑ ድረስም ይቁረጣቸው።»27 ኢማም አሕመድ ረሒመሁሏህ ዘግበውታል።

ሴት ልጅ ግን በአለባበሷ ከወንዶች ጋር በማይመሳሰል መልኩ ጥቁር፣ አረንጓዴ ወይም ሌሎችንም የፈለገችውን ልብስ ለብሳ ኢሕራም ማድረግ ትችላለች። ነገር ግን በኢሕራም ላይ ስትሆን ኒቃብና ጓንት ከመልበስ ትቆጠባለች። ፊቷንና እጆቿን ግን ከኒቃብና ጓንት ውጪ ባለ ልብስ ትሸፍናለች፤ ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ ኢሕራም ያደረገች ሴት ኒቃብና ጓንት እንዳትለብስ ከልክለዋልና። አንዳንድ ሰዎች የሴት ልጅን የኢሕራም ልብስ በአረንጓዴ ወይም በጥቁር ብቻ መገደባቸውም ምንም መሰረት የለውም።

ከዚያም ገላውን ከታጠበ፣ ጽዳቱን ከፈጸመና የኢሕራም ልብሱን ከለበሰ በኋላ፣ ከሐጅ ወይም ከዑምራ ሊሰራው የፈለገውን ስርአት ለመጀመር በልቡ ይነይታል። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ስላሉ ነው፡

«إِنَّمَا الأَعْمَالُ بِالنِّيَّاتِ، وَإِنَّمَا لِكُلِّ امْرِئٍ مَا نَوَى».

«ሥራ የሚለካው በኒያ መሰረት ነው። ሁሉም ሰው (የሚያገኘውም) በነየተው ልክ ነው።»28

የነየተውን በአንደበቱ መናገሩም የተደነገገ ነው። ኒያው ዑምራ ከሆነ «ለበይክ ዑምረተን» ወይም «አልላሁምመ ለበይከ ዑምረተን» ይላል። ኒያው ሐጅ ከሆነ ደግሞ «ለበይከ ሐጀን» ወይም «አልላሁምመ ለበይከ ሐጀን» ይላል፤ ምክንያቱም ነብዩ ﷺ ይህንኑ ፈፅመዋልና። ሁለቱንም አንድ ላይ ከነየተ ደግሞ «አልላሁምመ ለበይከ ዑምረተን ወሐጅጀን» ይላል። በላጩ እንስሳም ይሁን መኪናም ይሁን ወይም ሌላ መጓጓዣው ላይ ከወጣ በኋላ መናገሩ ነው፤ ምክንያቱም ነብዩ ﷺ ተልቢያ ማለት የጀመሩት በመጓጓዣቸው ላይ ከወጡና ከሚቃት ለጉዞ መንቀሳቀስ ከጀመረች በኋላ ነው። ከዑለማዎች አቋም መካከል ይበልጥ ትክክለኛውም ይኸው ነው።

በኢሕራም ወቅት ካልሆነ በቀር የነየተውን በአፍ መናገሩ አልተደነገገም፤ ከነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የተገኘውም በኢሕራም ወቅት ብቻ ነው።

ሶላትን፣ ጦዋፍንና ሌሎችንም አምልኮዎችን በተለመለከተ ግን ኒያውን በአፍ መናገር አይጠበቅበትም። «እንዲህ አይነት ሶላት ልሰግድ ነይቻለሁ» ወይም «እንዲህ አይነት ጦዋፍ ላደርግ ነይቻለሁ» ማለት የለበትም። ይልቁንም ይህን ድምፅን ከፍ ሳያደርጉ በአፍ መናገር አዲስ መጤ የሆነ ፈጠራ ነው። ይህንኑ ድምፅን ከፍ አድርጎ መናገሩ ደግሞ የበለጠ አስቀያሚና ወንጀሉም የከበደ ነው። ኒያን በአፍ መናገር የተደነገገ ቢሆን ኖሮ መልዕክተኛው (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለህዝባቸው በድርጊታቸው ወይም በንግግራቸው ግልፅ ባደረጉት ነበር። ቀደምት ደጋግ ሰለፎችም ይህንን ለማድረግ በተሽቀዳደሙ ነበር።

ይህ ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲሁም ከሶሓቦቻቸው (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) አለመተላለፉ ቢድዓ ለመሆኑ ግልፅ ማሳያ ነው። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦

«وَشَرُّ الأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا، وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ».

«የነገሮች ሁሉ መጥፎ አዲስ መጤዎች ናቸው፤ ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው።»29 ሙስሊም በሶሒሕ ኪታባቸው ላይ ዘግበውታል፤ ነቢዩ ﷺ እንዲህም ብለዋል፡

«مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ مِنْهُ فَهُوَ رَدٌّ».

«በዚህ ጉዳያችን ከእርሱ ያልሆነን አዲስ ነገር የፈጠረ የፈጠረው አዲስ ነገር ተመላሽ ይደረግለታል (ውድቅ ነው)።»30 ሶሒሕ መሆኑን ተስማምተውበታል። በሙስሊም ዘገባም:

«مَنْ عَمِلَ عَمَلًا لَيْسَ عَلَيْهِ أَمْرُنَا فَهُوَ رَدٌّ».

"በርሱ ላይ የኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ነገር የሰራ ሰዉ ስራው ወደርሱ ተመላሽ ነዉ።"31

አዲስ ክፍል:

የሐጅና ዑምራ ኢሕራም ማድረጊያ ስፍራዎችና ድንበራቸው፤

የሐጅና ዑምራ ኢሕራም ማድረጊያ ስፍራዎች አምስት ናቸው:

የመጀመሪያው: ዙል-ሑለይፋ ነው፤ ይህም የመዲና ሰዎች ሚቃት ሲሆን በዛሬ ሰዎች አጠራር አቢያር ዐሊይ ተብሎ ይጠራል።

ሁለተኛው: አል-ጁሕፋህ፣ ይህም የሻም ህዝቦች ሚቃት ነው። ይህቺም ራቢግ አቅራቢያ የምትገኝ የፈረሰች መንደር ስትሆን ሰዎች አሁን ላይ ኢሕራም የሚያደርጉት ከራቢግ ነው። ከራቢግ ኢሕራም ያደረገ ሰው ከሚቃቱ ኢሕራም አድርጓል፤ ምክንያቱም ራቢግ ከእርሷ በጥቂቱ ሳይደርስ የሚገኝ ነውና።

ሶስተኛው: ቀርኑል መናዚል፤ የነጅድ ሰዎች ሚቃት ሲሆን ዛሬ ላይ ሰይል ተብሎ ይጠራል።

አራተኛው: የለምለም ለየመን ሰዎች ሚቃት ነው።

አምስተኛው: ዛቱ ዒርቅ፣ የዒራቅ ሰዎች ሚቃት ነው።

እነዚህ ኢሕራም ማድረጊያ ስፍራዎች ነብዩ ﷺ የወሰኗቸው ቀደም ብለው ለተጠቀሱት ሰዎችና፤ ከነርሱ ውጭ ሆነው ሐጅን ወይም ዑምራን ማድረግ ፈልገው በእነዚህ ስፍራዎች በኩል ለሚያልፉትም ነው።

በነሱ በኩል የሚያልፍ ሰው ከነሱው ኢሕራም ማድረግ ግዴታው ነው። ሐጅን ወይም ዑምራን ለማድረግ አስቦ ወደ መካ የሚጓዝ ሰው ሁሉ በየብስም ይሁን በአየር የሚጓዝም ቢሆን እነሱጋ ኢሕራም ሳያደርግ ሊያልፋቸው አይፈቀድለትም። ይህም የሆነው ነቢዩ ﷺ እነዚህን ሚቃቶች በወሰኑ ጊዜ እንዲህ ሲሉ የተናገሩት ንግግር ሁሉን አቀፍ በመሆኑ ነው፡

«هُنَّ لَهُنَّ، وَلِمَنْ أَتَى عَلَيْهِنَّ مِنْ غَيْرِ أَهْلِهِنَّ، مِمَّنْ أَرَادَ الحَجَّ وَالعُمْرَةَ».

«እነዚህ ለነዋሪዎቻቸው፣ እንዲሁም ከነዋሪዎቻቸው ውጭ ሆነው ሐጅና ዑምራን ለማድረግ አስበው በእነርሱ በኩል ለሚያልፉም ናቸው።»32

ሐጅን ወይም ዑምራን ለማድረግ አስቦ በአየር መንገድ ወደ መካ ለመሄድ ያሰበ ሰው፤ አውሮፕላን ከመሳፈሩ በፊት ገላውን በመታጠብና በመሳሰሉት መዘጋጀቱ የተደነገገ ነው። ከሚቃቱ አካባቢ ሲደርስም ሽርጡንና ኩታውን ይለብሳል። ከዚያም ጊዜው ሰፊ ከሆነ ለዑምራ ተልቢያ ያደርጋል። ጊዜው ጠባብ ከሆነ ደግሞ ለሐጅ ተልቢያ ያደርጋል። ሽርጡንና ኩታውን አውሮፕላን ከመሳፈሩ በፊት ወይም ወደ ሚቃቱ ከመቅረቡ በፊት ቢለብስም ችግር የለውም። ነገር ግን ከሚቃቱ ትይዩ ሲሆን ወይም ሲቀርብ ካልሆነ በቀር ወደ ዒባዳው (ኑሱክ) ለመግባት ኒያ ሊያደርግና ተልቢያ ሊል አይገባውም። ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ ኢሕራም ያደረጉት ሚቃት ዘንድ ብቻ ነውና። በሌሎች የዲን ጉዳዮች ሁሉ ላይ እንደምናደርገው በዚህም ጉዳይ ላይ ኡማው እርሳቸውን ﷺ መከተል ግዴታው ነው። ይህም አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ በማለቱ ነው፦

﴿لَقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ...﴾

{ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነና አላህንም በብዙ ለሚያወሳ ሰው በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ።} [አል-አሕዛብ፡ 21] ነቢዩም ﷺ በመሰናበቻው ሐጅ እንዲህ ስላሉ፦

«خُذُوا عَنِّي مَنَاسِكَكُمْ».

«የሐጅ ተግባራችሁን ከእኔ ውሰዱ።»33

ሐጅንም ይሁን ዑምራን ማድረግ ሳይፈልግ ወደ መካ የሚጓዝ ሰው፤ እንደ ነጋዴ፣ እንጨት ለቃሚ፣ መልእክት አድራሽና የመሳሰሉት፣ በራሱ ፈቃድ ለማድረግ ካልፈለገ በስተቀር ኢሕራም የማድረግ ግዴታ የለበትም። ይህም ነቢዩ ﷺ ቀደም ሲል በተጠቀሰው ሐዲስ ላይ የኢሕራም ማድረጊያ ስፍራዎችን ሲጠቅሱ እንደሚከተለው በማለታቸው ነው፦

«هُنَّ لَهُنَّ، وَلِمَنْ أَتَى عَلَيْهِنَّ مِنْ غَيْرِ أَهْلِهِنَّ، مِمَّنْ أَرَادَ الحَجَّ وَالعُمْرَةَ».

«እነዚህ ለነዋሪዎቻቸው፤ እንዲሁም ከነዋሪዎቻቸው ውጭ ሆኖ ሐጅንና ዑምራን አስቦ በእነርሱ በኩል ለሚያልፍም ሰው ናቸው።»34 ከዚህ የምንረዳው ሐጅን ወይም ዑምራን ማድረግ ሳይፈልግ በኢሕራም ማድረጊያ ስፍራዎች ያለፈ ሰው ኢሕራም ማድረግ እንደማይጠበቅበት ነው።

ይህም ለአላህ ምስጋና ይገባውና አላህ ለባሮቹ ካደረገው እዝነትና ማግራራት መካከል ነው። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመካ ድል (ፈትሕ) ዓመት ወደ መካ ሲገቡ ኢሕራም አለማድረጋቸወ ይህንን ያጠናክርልናል። ይልቁንም የገቡት የራስ ቁር ወይም ጡሩር እንዳጠለቁ ነበር፤ ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ዓላማቸው ከተማዋን በድል መክፈትና በውስጧ የነበረውን ሽርክ ማስወገድ እንጅ ሐጅንም ሆነ ዑምራን የመፈጸም ፍላጎት አልነበራቸውምና።

እንደ ጂዳ፣ ኡሙ ሰለም፣ በህራ፣ አሽ-ሸራኢዕ፣ በድር፣ መስቱራ እና መሰል አካባቢዎች ነዋሪዎች አይነቶቹ መኖሪያ ቤታቸው ከሚቃቶቹ የቀረበ ለሆኑ ሰዎች፤ ከዚህ ቀደም ወደ ተጠቀሱት አምስቱ ሚቃቶች ወደ የትኛውም መሄድ ግዴታ የለባቸውም። ይልቁንም መኖሪያቸው ራሱ ሚቃታቸው ነው፤ ለሐጅም ይሁን ለዑምራ ከዚያው ኢሕራም ያደርጋሉ። ከሚቃቱ ውጪ ሌላ መኖሪያ ቤት ያለው ሰው ከሆነ ደግሞ ምርጫም አለው። ከፈለገ ከሚቃቱ ኢሕራም ያደርጋል፤ ከፈለገም ከሚቃቱ ይልቅ ወደ መካ ከሚቀርበው መኖሪያው ኢሕራም ያደርጋል። ይህም የሆነው ነቢዩ ﷺ በኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ ሐዲስ ላይ ሚቃቶችን ሲጠቅሱ በአጠቃላይ እንዲህ ስላሉ ነው፦

«فَمَنْ كَانَ دُونَهُنَّ، فَمُهَلُّهُ مِنْ أَهْلِهِ، وَكَذَلِكَ حَتَّى أَهْلُ مَكَّةَ يُهِلُّونَ مِنْ مَكَّةَ».

«ከነዚህ የቀረበ የሆነ ሰው ኢሕራም የሚያደርገው35 ከያለበት ስፍራ ነው። እንደዚሁም የመካ ሰዎችም ሳይቀሩ ከመካ ነው ኢሕራም የሚያደርጉት»36 ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ነገር ግን በሐረም ውስጥ ሆኖ ዑምራህ ማድረግ የፈለገ ሰው ከሐረም ውጪ ወጥቶ የዑምራህ ኢሕራም ማድረግ ግዴታው ነው፤ ምክንያቱም ነብዩ ﷺ ዓኢሻ ዑምራህ እንድታደርግ በጠየቀቻቸው ጊዜ ከሐረም ውጪ ይዟት ወጥቶ ከዛ ኢሕራም እንዲያስደርጋት ወንድሟን ዐብዱረሕማንን አዘውታልና። ይህም ዑምራህ አድራጊ ለዑምራህ ኢሕራም የሚያደርገው ከሐረም ውስጥ ሳይሆን ከሐረም ውጪ መሆኑን ያመላክታል።

ይህ ሐዲስ ቀደም ብሎ የተጠቀሰውን የኢብኑ ዐባስ (ዘገባ ላይ ያለውን) ሐዲስ ይገድበዋል፤ እንዲሁም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ ንግግራቸው የፈለጉበትን ዓላማ ያመለክታል፦

«حَتَّى أَهْلُ مَكَّةَ يُهِلُّونَ مِنْ مَكَّةَ».

«የመካ ሰዎችም ኢህላል የሚያደርጉት ከመካ ነው።»37 መካ ውስጥ የሚኖር ሰው ከዛው ኢህራም የሚያደርገው ለሐጅ እንጂ ለዑምራ አለመሆኑን ያስረዳናል፤ ምክንያቱም ከሐረም ውስጥ ለዑምራ ኢህራም ማድረግ የተፈቀደ ቢሆን ኖሮ ለዓኢሻም (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ይህንኑ በፈቀዱላትና ወደ ሒል (ከሐረም ክልል ውጭ) እንድትወጣ አያስገድዷትም ነበር። ይህ ግልፅ የሆነ ጉዳይ ሲሆን የአብዛኞቹ ዑለማዎች (አላህ ይዘንላቸውና) አቋምም ነው። ሁለቱንም ሐዲሦች በአንድነት መተግበርን የሚያስችል በመሆኑ ለምእመኑ የበለጠ ጥንቃቄ ያለው ነው። ለበጎ ነገር የሚገጥመን አላህ ነው።

አንዳንድ ሰዎች ከሐጅ በፊት ዑምራ አድርገው ሳለ ከሐጅ በኋላም ከተንዒምም ይሁን ከጂዕራና ወይም ከሌሎችም ቦታዎች ኢሕራም እያደረጉ ዑምራ ማብዛታቸውን በተመለከተ ለዚህ ተግባር ምንም ሸሪዓዊ ማስረጃ የላቸውም። ይልቁንም ማስረጃዎች የሚያመለክቱት በላጩ መተዉ መሆኑን ነው። ምክንያቱም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) እና ባልደረቦቻቸው (አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና) ሐጃቸውን ከጨረሱ በኋላ ዑምራ ስላላደረጉ ነው። ዓኢሻ ከተንዒም ዑምራ ያደረገችው፤ መካ በገቡ ጊዜ በወር አበባ ምክንያት ከሰዎች ጋር ዑምራ ባለማድረጓ ነው። በመሆኑም ከሚቃት ኢሕራም ላደረገችበት ዑምራ ምትክ እንዲሆናት ዑምራ እንድታደርግ ነው ነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) የጠየቀችው ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ይህንን ጥያቄዋን ነው የተቀበሏት። በዚህም ሁለት ዑምራዎች ተገኝተውላታል፤ ከሐጅዋ ጋር ያደረገችው ዑምራ እና ይህቺ ለብቻዋ ያደረገችው ዑምራ። ስለዚህ እንደ ዓኢሻ ያለ ሰው ሐጁን ከጨረሰ በኋላም ዑምራ ቢያደርግ ችግር የለውም። ይህም ሁሉንም ማስረጃዎች ተግባራዊ ለማድረግና ለሙስሊሞችም ለማግራራት ነው።

ያለጥርጥር ሐጃጆች ሐጃቸውን ከፈጸሙ በኋላ መካ ከገቡባት ዑምራ ውጪ በሌላ ዑምራ መጠመዳቸው፤ የነብዩን ﷺ ፈለግና ሱንና ከመፃረሩም ባሻገር በሁሉም ላይ ችግር እንደሚፈጥር፣ ከፍተኛ መጨናነቅና አደጋዎችን እንደሚያስከትል ምንም ጥርጥር የለውም። ለበጎ ነገር የሚገጥመን አላህ ነው።

አዲስ ክፍል:

ከሐጅ ወራት ውጪ ወደ ሚቃት የደረሰ ሰው ብይን፤

ወደ ሚቃት የደረሰ ሰው ሁለት ሁኔታዎች ይኖሩታል፦

ከሐጅ ወራት ውጪ እንደ ረመዳንና ሸዕባን ባሉ ወራት ለሚደርስ ሰው ሱናው፤ በልቡ ዑምራን ነይቶ በአንደበቱ፡- “ለበይክ ዑምረተን” ወይም “አልላሁምመ ለበይክ ዑምረተን” በማለት ለዑምራ ኢሕራም ማድረግ ነው። ከዚያም የነቢዩን ﷺ ተልቢያ ይላል፤ እሱም፦

«لَبَّيْكَ اللَّهُمَّ لَبَّيْكَ، لَبَّيْكَ لَا شَرِيكَ لَكَ لَبَّيْكَ، إِنَّ الحَمْدَ وَالنِّعْمَةَ لَكَ وَالمُلْكَ، لَا شَرِيكَ لَكَ».

«ለበይከል-ሏሁምመ ለበይክ፤ ለበይከ ላ ሸሪከ ለከ ለበይክ፣ ኢንነል-ሐምደ ወን-ኒዕመተ ለከ ወል-ሙልክ፤ ላ ሸሪከ ለክ» (ትርጉሙም፦ "አላህ ሆይ! ጥሪህን ተቀብያለሁ፤ አሁንም! ጥሪህን ተቀብያለሁ፤ ላንተ አጋር የለህም፤ ምስጋና ሁሉ፤ ጸጋም ሁሉ፤ ንግስናም ላንተ ብቻ ነው፤ አጋር የለህም።")38 ወደተከበረው ቤት እስኪደርስ ድረስም ይህችን ተልቢያህ እና የአላህን ስም ማውሳትን (ዚክር) ያብዛ። ካዕባ ዘንድ ሲደርስ ተልቢያውን አቋርጦ ሰባት ዙር ጦዋፍ ያደርጋል። ከዚያም ከመቃሙ ኢብራሂም ጀርባ ሁለት ረከዓዎችን ከሰገደ በኋላ ወደ ሶፋ ወጥቶ በሶፋና መርዋ መካከል ሰባት ዙር ይሮጣል። ከዚያም የጭንቅላቱን ፀጉር ይላጫል ወይም ያሳጥራል። በዚህም ዑምራው ይጠናቀቅና በኢሕራም ምክንያት የተከለከላቸው ነገሮች ሁሉ የተፈቀዱ ይሆኑለታል።

ሁለተኛው: በሐጅ ወራቶች ሚቃት መድረስ ነው፤ እነርሱም: ሸዋል፣ ዙልቀዒዳና የዙልሒጃ የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ናቸው።

እናም ይህ ሰው ሶስት ምርጫዎች ይኖሩታል። እነርሱም ሐጅን ለብቻ መፈፀም፣ ዑምራን ለብቻ መፈፀምና ሁለቱንም በጋራ ማከናወን ናቸው። ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ በሐጀቱል ወዳዕ (የመሰናበቻው ሐጅ) ወቅት በዙል-ቀዒዳ ወር ሚቃት (ኢሕራም ማድረጊያ) ቦታ በደረሱ ጊዜ ባልደረቦቻቸውን በእነዚህ ሶስቱ የአፈፃፀም አይነቶች መካከል አስመርጠዋቸዋል። ነገር ግን ሱናው ለዚህ ሰውም ቢሆን ከርሱ ጋር ሀድይ (እርድ) ከሌለ ዑምራን ኢሕራም ማድረጉ እና ከሐጅ ወራት ውጪ ሚቃት ለደረሰ ሰው ቀደም ብለን የጠቀስነውን መፈፀሙ ነው። ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ ወደ መካ በተቃረቡ ጊዜ ባልደረቦቻቸውን ኢሕራማቸውን ዑምራ እንዲያደርጉት አዘዋቸዋል፤ በመካም ይህንን አረጋግጠውላቸዋል። ሶሓቦችም የእርሳቸውን ﷺ ትዕዛዝ በመፈፀም ጦዋፍ አድርገዋል፤ ሰዕይ ፈፅመዋል፤ ፀጉራቸውንም አሳጥረው ከኢሕራም ወጥተዋል። ከርሱ ጋር ሀድይ (እርድ) የነበረው ሰው ሲቀር፤ ነቢዩ ﷺ ይህ ሰው የእርድ ቀን ከኢሕራም እስከሚወጣ ድረስ በኢሕራሙ ላይ እንዲቆይ አዘውታል። ሀድይ ይዞ ለመጣ ሰው ሱናው ሐጅና ዑምራን በጋራ ኢሕራም ማድረጉ ነው። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ ሀድይ ይዘው ስለነበር ይህንኑ ፈፅመዋልና። ከባልደረቦቻቸውም መካከል ሀድይ ይዘው መጥተው ዑምራን ኢሕራም ያደረጉትን፣ ከዑምራቸው ጋር ሐጅንም እንዲጨምሩበትና የእርዱ ቀን ሁለቱንም አንድ ላይ እስኪፈቱ ድረስ በኢሕራማቸው እንዲቆዩ አዘዋል። ሀድይ ይዞ የመጣው ሰው ሐጅን ብቻ ኢሕራም ያደረገ እንደሆነም፣ በሁለቱ መካከል እንደሚያቆራኘው (ቃሪን) ሰው የእርዱ ቀን ከኢሕራሙ እስኪፈታ ድረስ በኢሕራሙ ላይ እንዳለ ይቆያል።

ከዚህም ሊታወቅ የሚገባው: ሐጅን ብቻውን ወይም ሀድይ ይዞ ሳይመጣ ሐጅን ከዑምራ ጋር አጣምሮ ኢሕራም ያደረገ ሰው በኢሕራሙ ላይ መቆየት እንደማይጠበቅበት ነው። ይልቁንም ለርሱ ሱና የሚሆነው ኢሕራሙን ወደ ዑምራ መቀየር ነው፤ ከዚያም ጦዋፍና ሰዕይ አድርጎ ፀጉሩን አሳጥሮ ከኢሕራሙ ይፈታል። ነቢዩ ﷺ ከባልደረቦቻቸው መካከል ሀድይ ይዘው ያልመጡትን እንዲህ እንዲያደርጉ አዘዋል። ነገር ግን ይህ ሰው ዘግይቶ በመምጣቱ ሐጅ እንዳያመልጠው ከሰጋ በኢሕራሙ ላይ ቢቆይም ችግር የለውም። አላህም ይበልጥ ያውቃል።

ኢሕራም ያደረገ ሰው በህመሙ ወይም ጠላትን ወይም መሰል ነገርን በመፍራቱ የአምልኮ ሥርዓቱን ማከናወን አልችልም ብሎ ከሰጋ ኢሕራም ሲያደርግ፦ "ፈኢን ሐበሰኒ ሓቢስ ፈመሐሊ ሐይሡ ሐበሰትኒ" (ትርጉሙም: "አንድ ከልካይ ነገር ከከለከለኝ የአምልኮ ስርዓቴ መጠናቀቂያ የታገድኩበት ቦታ ነው።" ማለት ነው) እንዲል ይወደድለታል። ለዚህም የዱባዓ ቢንት አዝ-ዙበይር (አላህ ስራዋን ይውደድላትና) ሐዲስ ማስረጃ ነው፤ እርሷም፦ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ሐጅ ማድረግ እፈልጋለሁ፤ ግን ታምሜያለሁ» ስትል፤ ነብዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሏት፦

«حُجِّي وَاشْتَرِطِي أَنَّ مَحِلِّي حَيْثُ حَبَسْتَنِي».

«ሐጅ አድርጊ፤ የኢሕራሜ ፍፃሜ በታገድኩበት ቦታ ነው በማለትም መስፈርት አስቀምጪ።»39 ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

የዚህ መስፈርት ጥቅሙ፦ ኢሕራም ያደረገ ሰው በህመም ወይም በጠላት መታገድ ምክንያት የሐጅ ወይም የዑምራ ስነ ስርዓቱን አሟልቶ ከመፈፀም የሚያግደው ነገር ካጋጠመው ምንም የማድረግ ግዴታ ሳይኖርበት ከኢሕራሙ መፈታት የሚፈቀድለት ይሆናል።

 

 

አዲስ ክፍል:

የህፃን ልጅ ሐጅ ማድረግ ከኢስላማዊ የግዴታው ሐጅ (ግዴታ ከሆነው ሐጅ) ያብቃቃዋልን? በሚለው ዙሪያ ያለው ብይን፤

የትንሽ ወንድ ልጅም የትንሽ ሴት ልጅም ሐጅ ይበቃል። በሶሒሕ ሙስሊም ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተዘገበው፤ አንዲት ሴት አንድን ህፃን ልጅ ወደ ነብዩ ﷺ ከፍ አድርጋ፡ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለዚህ ሐጅ አለውን?" ስትል፤ እርሳቸውም እንዲህ አሉ፡

«نَعَمْ، وَلَكِ أَجْرٌ».

«አዎን፣ ላንቺም ምንዳ ይኖርሻል»40

በሶሒሕ ቡኻሪ ከአስ-ሳይብ ቢን የዚድ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- ተላልፎ እንደተዘገበው እንዲህ ብሏል: ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር እኔ የሰባት ዓመት ልጅ ሆኜ ሐጅ አድርጌያለሁ።"41 ነገር ግን ለእነዚህ ልጆች ሐጁ ከኢስላማዊው የግዴታ ሐጅ አይብቃቃቸውም።

እንደዚሁም ወንድ ባሪያና ሴት ባሪያ ሐጅ ቢያደርጉ ይቆጠርላቸዋል፤ ከግዴታ ሐጅ ግን አያብቃቃቸውም። ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና - እንዳስተላለፉት ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

«أَيُّمَا صَبِيٍّ حَجَّ، ثُمَّ بَلَغَ الحِنْثَ، فَعَلَيْهِ أَنْ يَحُجَّ حَجَّةً أُخْرَى، وَأَيُّمَا عَبْدٍ حَجَّ، ثُمَّ أُعْتِقَ، فَعَلَيْهِ حَجَّةٌ أُخْرَى».

«ማንኛውም ልጅ ሐጅ አድርጎ አቅመ አዳም ከደረሰ፣ ሌላ ሐጅ ማድረግ ይኖርበታል። ማንኛውም ባሪያም ሐጅ አድርጎ ነፃ ከወጣ፣ ሌላ ሐጅ ማድረግ ይኖርበታል።»42 ኢብኑ አቢ ሸይባህና በይሀቂይ ሐሠን በሆነ ሰነድ ዘግበውታል።

በመቀጠል ህፃኑ ልጅ መለየት የሚችልበት እድሜ (ተምይዝ) ላይ የደረሰ ካልሆነ ወልዩ (አሳዳሪው) ኢሕራምን ይነይትለታል። የተሰፉ ልብሶችንም ያስወልቀውና በሱም ፋንታ ተልቢያ ይላል፤ በዚህም ህፃኑ ልጅ ሙሕሪም ይሆናል። ትልቅ ሙሕሪም ከሚከለከለው ነገር ሁሉ ይከለከላል። ልክ እንደዚሁ መለየት የምትችልበት እድሜ (ተምይዝ) ላይ ላልደረሰች ህፃን ልጅም ወልይዋ (አሳዳሪዋ) ኢሕራምን ይነይትላትና በሷ ፋንታ ተልቢያ ይላል፤ በዚህም ሙሕሪም ትሆናለች፤ ትልቅ ሙሕሪም ሴት ከምትከለከለው ነገርም ሁሉ ትከለከላለች። ጠዋፍ በሚያደርጉበት ጊዜ ልብሳቸውና አካላቸው ንፁህ መሆን ይኖርበታል። ምክንያቱም ጠዋፍ ልክ እንደ ሰላት ነው፤ ጦዋፍም ትክክለኛ እንዲሆን ጦሃራ (ንፅህና) አንዱ መስፈርት ነው።

ወንድና ሴት ህፃናት ነገሮችን መለየት የሚችሉ ከሆኑ በሞግዚታቸው ፈቃድ ኢሕራም ያደርጋሉ። ኢሕራም ሲያደርጉም ትልልቅ ሰዎች የሚፈፅሟቸውን እንደ ገላ መታጠብና ሽቶ መቀባት አይነት ተግባራትን ይፈፅማሉ። ሞግዚታቸው ማለት ጉዳያቸውን የሚከታተልና ጥቅማቸውን የሚያስጠብቅላቸው ሲሆን፤ አባታቸው፣ እናታቸው ወይም ሌላም ሰው ሊሆን ይችላል። ሊፈፅሙት ያቃታቸውን እንደ ጀመራ መወርወርን የመሳሰሉ ድርጊቶችን ሞግዚታቸው በነሱ ምትክ ይፈፅምላቸዋል። ከዚህ ውጭ ያሉትን የሐጅ ስርአቶች እንደ ዐረፋ ላይ መቆም፣ ሚናና ሙዝደሊፋ ማደር፣ ጦዋፍና ሰዕይ ማድረግን የመሳሰሉትን ግን ህፃናቱ እራሳቸው መፈፀም ይኖርባቸዋል። ጦዋፍና ሰዕይ (መሮጥን) ማድረግ ያቃታቸው እንደሆነ በሰው ታዝለው ጦዋፍና ሰዕይ እንዲያደርጉ ይሆናሉ። ለሚያዝላቸውም ሰው የተሻለው የራሱን ጦዋፉንና ሰዕዩን ከነሱ ጋር አጣምሮ ባይሆን ነው። ይልቁንም ጦዋፉንና ሰዕዩን ለነሱ ነይቶ፣ ለራሱ ደግሞ በተናጠል ጦዋፍና ሰዕይ ያድርግ፤ ይህም ለዒባዳው ጥንቃቄ ሲባልና የተከበረውን ሐዲስ መሰረት በማድረግ ነው፦

«دَعْ مَا يَرِيبُكَ إِلَى مَا لَا يَرِيبُكَ».

«የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ!»43 ተሸካሚው ጦዋፉን ለራሱም ለተሸከመውም ከነየተ፤ ከሁለቱ የዑለማዎች አቋም ይበልጥ ትክክል በሆነው መሰረት ያብቃቃለታል። ነቢዩ ﷺ ስለ ህፃኑ ሐጅ የጠየቀቻቸውን ሴት ለርሱ ብቻ ጦዋፍ እንድታደርግ አላዘዟትምና። ይህ ነገር ግዴታ ቢሆን ኖሮ እርሳቸው ﷺ ያብራሩት ነበር። ስኬትን የሚለግስ አላህ ነው።

መለየት የሚችሉበት እድሜ ላይ የደረሱ ወንድና ሴት ልጅ ልክ ኢሕራም እንዳደረገ ትልቅ ሰው ጠዋፍ ከመጀመራቸው በፊት ከሐደሥና ከነጃሳ እንዲፀዱ ይታዘዛሉ። ለትንንሽ ወንድና ሴት ልጆች ኢሕራም ማድረግ በወሊያቸው ላይ ግዴታው አይደለም፤ ይልቁንም ሱና ነው። ይህን ከፈጸመ አጅር አለው፤ ከተወውም ምንም ችግር የለበትም። ወላሁ አዕለም።

አዲስ ክፍል:

በኢሕራም ወቅት የተከለከሉና የተፈቀዱ ነገሮች፤

ኢሕራም ያደረገ ሰው ‐ወንድም ይሁን ሴት‐ ከፀጉሩም ሆነ ከጥፍሩ አንዳችንም ማስወገድ ወይም ሽቶ መቀባት አይፈቀድለትም።

ለወንድ ልጅ ብቻ በሙሉ ሰውነቱ ወይም በከፊሉ ላይ የተሰፋ ልብስ መልበስ አይፈቀድለትም። ይህም ማለት እንደ ቀሚስ፣ ጃፖኒ፣ ሱሪ፣ ኹፎች እና ካልሲዎች ያሉ በሰውነት ቅርጽ ልክ ተለክተውና ተሰፍተው የተዘጋጁ ልብሶች ናቸው። ነገር ግን ግልድም ያላገኘ ሰው ሱሪ መልበስ ይፈቀድለታል። እንደዚሁም ነዕል (ጫማ) ያላገኘ ሰው ኹፎችን ሳይቆርጣቸው መልበስ ይፈቀድለታል። ለዚህም ማስረጃው በሁለቱ ሰሒሖች ላይ የተረጋገጠው የኢብኑ አባስ (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) ሐዲስ ሲሆን፤ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦

«مَنْ لَمْ يَجِدْ نَعْلَيْنِ، فَلْيَلْبَسِ خُفَّيْنِ، وَمَنْ لَمْ يَجِدْ إِزَارًا، فَلْيَلْبَسْ سَرَاوِيلَ».

«ጫማ ያላገኘ ኹፍ ይልበስ፤ ግልድም ያላገኘ ደግሞ ሱሪ ይልበስ»44

በኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ሐዲስ ውስጥ የተዘገበው፤ ጫማዎችን ባለማግኘት ምክንያት ኹፎችን መልበስ አስፈላጊ ሲሆን እንዲቆረጡ የወጣው ትእዛዝ የተሻረ ነው። ምክንያቱም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሙሕሪም ስለሚለብሰው ልብስ በመዲና በተጠየቁ ጊዜ ይህንን አዘው ነበር። ከዚያም ዐረፋ ላይ ለሰዎች ኹጥባ ባደረጉ ጊዜ ደግሞ ጫማ በሌለበት ወቅት ኹፎች እንዲለበሱ ፈቀዱ፤ እንዲቆረጡ ግን አላዘዙም። በዚህ ኹጥባ ላይ ደግሞ በመዲና የሰጡትን መልስ ያልሰማ ሰው ተገኝቶ ነበር። ማብራሪያንም ከሚያስፈልግበት ጊዜ ማዘግየት በኡሱሉል ሐዲስ እና በኡሱሉል ፊቅህ የእውቀት ዘርፎች እንደሚታወቀው አይፈቀድም። ስለዚህም እንዲቆረጥ የወጣው ትእዛዝ መሻሩ በዚህ ተረጋግጧል። ይህ ግዴታ ቢሆን ኖሮ እርሳቸው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ባብራሩት ነበር። አላህ ይበልጥ ያውቃል።

ኢሕራም ላደረገ ሰው ከቁርጭምጭሚት በታች የሆኑ ኹፎችን መልበሱ የነዕል (ጫማ) አይነት ፍርድ ስላላቸው ይፈቀድለታል።

የሚከለክል ማስረጃ ባለመኖሩ ሽርጥን መቋጠር እንዲሁም በክርና (በቀበቶ) በመሳሰሉት ማሰር ይፈቀዳል።

ኢሕራም ያደረገ ሰው ሲያስፈልገው ገላውን መታጠብ፣ ጭንቅላቱን ማጠብና በቀስታና በቀላሉ ማከክም ይፈቀድለታል። በዚህ ምክንያት ከጭንቅላቱ ላይ የሆነ (ፀጉር) ነገር ቢወድቅበትም በእርሱ ላይ ምንም ችግር የለበትም።

ኢሕራም ያደረገች ሴት ለፊቷ እንደ ቡርቃና ኒቃብ፣ ወይም ለእጆቿ እንደ ጓንት ያሉ የተሰፉ ልብሶችን መልበስ ሐራም ይሆንባታል። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋልና፦

«وَلَا تَنْتَقِبِ المَرْأَةُ المُحْرِمَةُ، وَلَا تَلْبَسِ القُفَّازَيْنِ».

«ኢሕራም ያደረገች ሴት ኒቃብ አትልበስ፤ ጓንትንም አትልበስ።»45 ቡኻሪ ዘግበውታል። ጓንት ማለት፡ ከሱፍ ወይም ከጥጥ ወይም ከመሳሰሉት በእጅ ልክ ተመጥኖ የሚሰፋ ወይም የሚሸረብ ነው።

ከዚህ ውጪ ያሉ እንደ ቀሚስ፣ ሱሪ፣ ኹፎች፣ ካልሲዎች እና የመሳሰሉት የተሰፉ ልብሶች ይፈቀዱላታል።

እንዲሁም ሲያስፈልጋት ጉፍታዋን ያለ ማሰሪያ ፊቷ ላይ መልቀቅም ይፈቀድላታል፤ ጉፍታው ፊቷን ቢነካውም ምንም አይጠበቅባትም፤ ዓኢሻ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- ባስተላለፈችው ሐዲሥ እንዲህ ብላለችና፦ «እኛ ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ኢሕራም ላይ እያለን ጋላቢዎች በኛ በኩለ ያልፉ ነበር። በአጠገባችን ሲደርሱ አንዳችን ጅልባቧን ከራሷ ላይ ፊቷ ላይ ታወርድ ነበር። አልፈውን ሲሄዱ ደግሞ እንገልጠው ነበር።»46 አቡ ዳውድና ኢብኑ ማጃህ የዘገቡት ሲሆን፤ ዳረቁጥኒይም ከኡም ሰለመህ ተመሳሳዩን ዘግቧል።

በተመሳሳይም እጆቿን በልብሷ ወይም በሌላ ነገር መሸፈኗ ችግር የለውም። ባዳ ወንዶች ባሉበት ስትሆን ግን ፊቷንና እጆቿን የመሸፈን ግዴታ አለባት፤ ዐውራ በመሆናቸውና ከፍ ያለው አላህም እንዲህ በማለቱ ነው፦

﴿...وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا لِبُعُولَتِهِنَّ...﴾

{ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ካልሆነ በስተቀር አይግለጹ።} [አን-ኑር፡ 31] ፊትና ሁለቱ መዳፎች ከታላላቅ ጌጦች መካከል መሆናቸው ምንም ጥርጥር የለውም።

በተለይ ፊትን መግለጥ ይበልጥ ከባድና ትልቅ ነው። ጥራት ይገባውና እንዲህም ብሏል፡

﴿...وَإِذَا سَأَلْتُمُوهُنَّ مَتَاعًا فَاسْأَلُوهُنَّ مِنْ وَرَاءِ حِجَابٍ ذَلِكُمْ أَطْهَرُ لِقُلُوبِكُمْ وَقُلُوبِهِنَّ...﴾

{እቃንም ለመዋስ በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ሆናችሁ ጠይቋቸው። ይሃችሁ ለልቦቻችሁም ለልቦቻቸዉም የበለጠ ንጽህና ነው።} [አል-አሕዛብ: 53]

በርካታ ሴቶች ጉፍታቸውን ከፊታቸው ከፍ ለማድረግ በጉፍታቸው ስር ጭንቅላት ማሰሪያ ነገር የማድረጉ ልማድ ግን እኛ እስከምናውቀው ድረስ በሸሪዓ መሰረት የለውም። ይህ የተደነገገ ቢሆን ኖሮ የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለህዝቦቻቸው ያብራሩት ነበር፤ በዚህ ጉዳይ ላይም ዝም ማለት አይፈቀድላቸውም ነበር።

ኢሕራም ላደረጉ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ኢሕራም ያደረጉበትን ልብሳቸውን በእድፍ ወይም በመሰል ምክንያቶች የተነሳ ማጠብም ሆነ በሌላ መለወጥ ይፈቀድላቸዋል።

ዛዕፈራን ወይም ወርስ (የሽቶ አይነቶች) የነካውን ማንኛውንም ልብስ መልበስ አይፈቀድለትም፤ ምክንያቱም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኢብኑ ዑመር (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) በተላለፈ ሐዲስ ይህንኑ ከልክለዋልና።

ሙሕሪም የሆነ ሰው ጸያፍ ንግግርን፣ ስሜት ቀስቃሽ ንግግርንና ክርክርን መተው ግዴታ ይሆንበታል፤ የላቀው አላህ እንዲህ ብሏልና፦

﴿الْحَجُّ أَشْهُرٌ مَّعْلُومَاتٌ فَمَنْ فَرَضَ فِيهِنَّ الْحَجَّ فَلَا رَفَثَ وَلَا فُسُوقَ وَلَا جِدَالَ فِي الْحَجِّ...﴾

{ሐጅ ጊዜያቱ የታወቁ ወሮች ናቸው። በእነርሱ ውስጥ ሐጅን ለመስራት ነፍሱን ያስገደደ ሰው በሐጅ ክንውን ውስጥ እያለ ሴትን መገናኘት፤ በአላህ ላይ ማመጽና ክርክር የለም።} [አልበቀራህ: 197]

ነብዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ማለታቸውም በሶሒሕ ሐዲሥ ተዘግቧል፦

«مَنْ حَجَّ، فَلَمْ يَرْفُثْ، وَلَمْ يَفْسُقْ، رَجَعَ كَيَوْمِ وَلَدَتْهُ أُمُّهُ».

«ሳይባልግና ሳያምፅ ሐጅ ያደረገ ሰው፣ እናቱ እንደወለደችው ቀን ከወንጀሉ ፀድቶ ይመለሳል።»47 ረፈሥ"፡- ለሩካቤ ስጋ፣ እንዲሁም ለብልግና ንግግርና ድርጊት ያገለግላል፤ "ፉሱቅ"፡- ወንጀሎች ማለት ነው፤ "ጂዳል"፡- በባጢል ወይም ጥቅም በሌለው ነገር ላይ መከራከር ነው፤ እውነትን ለመግለጽና ባጢልን ለመመለስ ሲባል በመልካሟ መንገድ መከራከር ግን ምንም ችግር የለውም፤ ይልቁንም ትእዛዝ የመጣበት ጉዳይ ነው፤ የላቀው አላህ ቃል እንዲህ ስላለ፡-

﴿ادْعُ إِلَى سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ وَجَادِلْهُمْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ...﴾

{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ በለዘብተኛ ቃልም ሰዎችን ጥራ። በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው ዘዴ ተከራከራቸው።} [አን-ነሕል: 125]

ሙሕሪም የሆነ ወንድ እንደ ኮፊያና ጥምጣም በመሰሉ ከጭንቅላቱ ጋር በሚነካኩ ነገሮች ራሱን እና ፊቱን መሸፈኑ ይከለከላል፤ ይህም ነብዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዐረፋ ቀን ከግመሉ ወድቆ ስለሞተው ሰው እንዲህ በማለታቸው ነው፦

«اغْسِلُوهُ بِمَاءٍ وَسِدْرٍ، وَكَفِّنُوهُ فِي ثَوْبَيْهِ، وَلَا تُخَمِّرُوا رَأْسَهُ، وَلَا وَجْهَهُ، فَإِنَّهُ يُبْعَثُ يَوْمَ القِيَامَةِ مُلَبِّيًا».

«በውሃና በቁርቁራ እጠቡት፤ በሁለቱ ልብሶቹም ከፍኑት። ራሱንና ፊቱን ግን አትሸፍኑ። ምክንያቱም የቂያማ ቀን ተልቢያ እያለ ይቀሰቀሳልና።»48 ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል ቃሉ የሙስሊም ዘገባ ነው።

በመኪና ጣራ፣ በዣንጥላና በመሳሰሉት መከለል ግን ልክ በድንኳንና በዛፍ እንደሚከለሉት ችግር የለውም። ነቢዩ ﷺ ጀምረተል ዓቀባን በሚወረውሩበት ጊዜ በልብስ ጥላ እንደተደረገላቸው እንዲሁም በነሚራም ድንኳን እንደተተከለላቸውና የዐረፋ ቀን ፀሐይ እስክትዘነበል ድረስ ከርሷ ሥር ወርደው እንደነበር በሰሒሕ ተዘግቧልና።

ኢሕራም ላይ ባሉ ወንዶችና ሴቶች ላይ የየብስ ታዳኝን መግደል፣ በዚህ ላይ መተባበር፣ ከቦታው ማባረር፣ ኒካሕ ማሰር፣ ግንኙነት ማድረግ፣ ሴቶችን ማጨትና ከነርሱ ጋር በስሜት መነካካት ይከለከላል። ዑስማን ረዲየላሁ ዐንሁ ባስተላለፉት ሐዲስ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋልና፦

«لَا يَنْكِحُ المُحْرِمُ وَلَا يُنْكِحُ وَلَا يَخْطُبُ».

«ሙሕሪም አያገባም፤ አይድርምም፤ አያጭምም።»49 ሙስሊም ዘግበውታል።

ሙሕሪም (ኢሕራም ያደረገ ሰው) በመርሳት ወይም ባለማወቅ የተሰፋ ልብስ ከለበሰ፣ ራሱን ከሸፈነ ወይም ሽቶ ቢቀባ ፊድያ አይጠበቅበትም፤ ነገር ግን ባስታወሰ ወይም ባወቀ ጊዜ ያንን ነገር ወዲያውኑ ማስወገድ ይኖርበታል። ልክ እንደዚሁ በመርሳት ወይም ባለማወቅ ራሱን የላጨ፣ ከፀጉሩ አንዳች ነገር ያስወገደ ወይም ጥፍሩን የቆረጠ ሰውም በትክክለኛው አቋም መሰረት ምንም ማድረግ አይጠበቅበትም።

ኢሕራም ያደረገም ይሁን ያላደረገ ሙስሊም፣ ወንድም ሆነ ሴት፤ የሐረምን ታዳኝ መግደል እንዲሁም በመሳሪያ፣ በምልክት ወይም በመሰል ድርጊት ለግድያው ተባባሪ መሆንም ይከለከላል።

ከቦታቸው ማባረር፣ የሐረም ዛፍንና አረንጓዴ እፅዋቱን መቁረጥ፣ እንዲሁም የጠፋ ንብረትን "የጠፋበት" እያለ ለሚያፈላልገው ሰው ካልሆነ በቀር ማንሳትም ይከለከላል፤ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋልና፦

«فَإِنَّ هَذَا البَلَدَ - يَعْنِي مَكَّةَ - حَرَامٌ بِحُرْمَةِ اللَّهِ إِلَى يَوْمِ القِيَامَةِ، لَا يُعْضَدُ شَوْكُهُ، وَلَا يُنَفَّرُ صَيْدُهُ، وَلَا يُلْتَقَطُ لُقَطَتُهُ إِلَّا مَنْ عَرَفَهَا، وَلَا يُخْتَلَى خَلَاهَا».

«ይህች ሀገር -መካ- አላህ ክብርን ስለሰጣት እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ሐራም (ክብሯ የተጠበቀ) አድርጓታል። ስለሆነም እሾኋ አይቆረጥም፤ የዱር እንስሳዎቿም አይባረሩም፤ እዚህ የጠፋ ንብረትም የሚያስተዋውቃት ሰው ካልሆነ በቀር አይነሳም፤ ለምለም ሳሯም አይታጨድም።»50 ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

በዚህ ቦታ ሙንሺድ የተባለው (የጠፋውን) የሚያስተዋውቀው ነው። ኸላ ማለት እርጥብ ሳር ነው። ሚናና ሙዝደሊፋ ከሐረም ሲሆኑ፤ ዓረፋ ግን ከሒል (ከሐረም ክልል ውጭ) ነው።

አዲስ ክፍል:

ሐጅ አድራጊ መካ ሲገባ ስለሚያከናውናቸው ተግባራት፤ እንዲሁም ጦዋፍና የመሳሰሉትን መስጂደል ሐራም ከገባ በኋላ ስለሚፈፅማቸው ተግባራት፤

ኢሕራም ያደረገ ሰው መካ ሲደርስ ከመግባቱ በፊት መታጠቡ ይወደድለታል፤ ምክንያቱም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን ፈፅመዋልና። ወደ መስጂደል ሐራም ሲደርስም ቀኝ እግሩን ማስቀደሙ ሱና ነው፤ እንዲህም ይላል፦ "ቢስሚልላህ ወስሰላቱ ወስሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ አዑዙ ቢልላሂል ዐዚም ወቢወጅሂሂል ከሪም ወሱልጣኒሂል ቀዲም ሚነ-ሽ-ሸይጧኒ-ር-ረጂም፤ አልላሁምመ ኢፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲክ።" ይህ ወደ ሌሎች መስጂዶች ሲገባም ይባላል። እኔ እስከማውቀው ድረስ መስጂደል ሐራም ሲገባ ብቻ የሚባል ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተረጋገጠ የተለየ ዚክር የለም።

ተመቱዕ ወይም ዑምራ አድራጊ ከሆነ ካዕባ ሲደርስ ጦዋፍ ከመጀመሩ በፊት ተልቢያ ማለቱን ያቆማል። ከዚያም ወደ ሐጀረል አስወድ በመሄድ ሰዎችን ሳያጨናንቅ በቀኝ እጁ ይዳብሰዋል፤ የሚመች ከሆነም ይስመዋል። በሚዳብስበት ጊዜም "ቢስሚላሂ አላሁ አክበር" ወይም "አላሁ አክበር" ይላል። መሳም የሚከብድ ከሆነ በእጁ ወይም በዱላ ወይም በመሰል ነገር ይዳብስና የዳበሰበትን ነገር ይስማል። መዳበሱ የሚከብድ ከሆነ ደግሞ ወደርሱ በመጠቆም “አላሁ አክበር” ይላል፤ ያመለከተበትን እጁን ግን አይስምም። ጠዋፉ ትክክለኛ ይሆን ዘንድ ጠዋፍ የሚያደርገው ሰው ከትንሹም (ዉዱእ ማድረግ ከሚያስፈልገው) ሐደሥም ሆነ ከትልቁ (ገላ ትጥበት ከሚያስፈልገው) ሐደሥ ንፁህ መሆን አለበት። ምክንያቱም የጠዋፍ ሥርዓት ውስጥ ማውራት ከመፈቀዱ በቀር እንደ ሰላት ነውና። በጠዋፍ ጊዜም ካዕባን በግራ ጎኑ ያደርጋል። በጠዋፉ መጀመሪያ ላይ፡ «አሏሁመ ኢማነን ቢክ ወተስዲቀን ቢኪታቢክ ወወፋአን ቢዐህዲክ ወቲባዐን ሊሱነቲ ነብይከ ሙሐመዲን ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም» (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ባንተ በማመን፣ መጽሐፍህንም እውነት በማለት፣ ቃልኪዳንህንም በመሙላትና የነቢይህ የሙሐመድን ﷺ ሱንና በመከተል) ቢል መልካም ነው፤ ምክንያቱም ይህ ከነብዩ ﷺ ተዘግቦ መጥቷልና። ሰባት ዙር ይዞራል። በመጀመሪያዎቹ ሶስት ዙሮች ላይ ሶምሶማ (ረመል) ያደርጋል፤ ይህም ጦዋፍ መካ እንደደረሰ መጀመሪያ የሚያደርገው ጦዋፍ ነው። ይህን የሚያደርገውም ዑምራ የሚያደርግ፣ ተመቱዕ የሚያደርግ፣ ለሐጅ ብቻ ኢሕራም ያደረገ፣ ወይም በሐጅና በዑምራ መካከል ያጣመረ (ቂራን ያደረገ) ሰው ነው። በቀሪዎቹ አራቱ ዙሮች ላይ ደግሞ በተለመደው ሁኔታ ይሄዳል። እያንዳንዱን ዙር ከሐጀረል አስወድ በመጀመር በዚያው ያጠናቅቃል።

ረመል ማለት እርምጃን በማቀራረብ ፈጠን ብሎ መሄድ ነው። በሌላው ላይ ሳይሆን በነዚህ ጠዋፎች በሙሉ ኢድጢባዕ ማድረግም ለእርሱ የተወደደ (ሙስተሐብ) ነው። ኢድጢባዕ ማለት፦ የኩታውን መሃል በቀኝ ትከሻው ስር አሳልፎ ጫፎቹን በግራ ትከሻው ላይ ማድረግ ነው።

የዙሩን ብዛት ከተጠራጠረ እርግጠኛ በሆነበት ማለትም ቢያንስ በሚለው ላይ ይገነባል። የዞረው ሶስት ዙር ነው ወይስ አራት? ብሎ ከተጠራጠረ ሶስት እንደሆነ ይቆጥረዋል። ሰዕይ ላይም እንደዚሁ ያደርጋል።

ይህንን ጠዋፍ ካጠናቀቀ በኋላ፣ የጠዋፍን ሁለት ረከዓዎች ከመስገዱ በፊት ኩታውን ይለብሳል፤ በትከሻው ላይ ያደርግና ጫፎቹን በደረቱ ላይ ያደርጋል።

ሴቶችን በተመለከተ ሊወገዙና ሊከለከሉ ከሚገቡ ጉዳዮች ውስጥ በጌጥና ሽቶ ተውበው ጦዋፍ ማድረጋቸው፣ እንዲሁም እነሱ ሀፍረተ ገላ ሆነው ሳሉ ተገላልጠው አለመሸፋፈናቸው ነው። ስለዚህም ራሳቸውን መሸፈን፣ እንዲሁም በጦዋፍ ወቅትና ሴቶች ከወንዶች ጋር በሚቀላቀሉባቸው ሌሎች ሁኔታዎች ላይ ጌጥን መተው ግዴታ ይሆንባቸዋል። ምክንያቱም እነሱ ሀፍረተ ገላና ፈተና ናቸውና። የሴት ልጅ ፊት ደግሞ ይበልጥ ግልፅ የሆነው ውበቷ ነው፤ ስለሆነም ከመሕረሞቿ በስተቀር ልትገልጸው አይፈቀድላትም። ይህም የሆነው የላቀው አላህ እንዲህ በማለቱ ነው፡

﴿...وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا لِبُعُولَتِهِنَّ...﴾

{ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ካልሆነ በስተቀር አይግለጹ} [አን-ኑር፡ 31] ሴቶች ሐጀረል አስወድን በሚስሙ ጊዜ ወንዶች የሚያዩዋቸው ከሆነ ፊታቸውን መግለጥ አይፈቀድላቸውም። ድንጋዩን ለመዳበስና ለመሳም ካልገራላቸውም ወንዶችን መገፋፋት አይፈቀድላቸውም፤ ይልቁንም ከኋላቸው ሆነው ጦዋፍ ያድርጉ። ይህም ወንዶችን እየተገፋፉ ከካዕባ አቅራቢያ ጦዋፍ ከማድረግ ለነርሱ የተሻለና በምንዳም የላቀ ነው። ረመልና ኢድጢባዕ ከዚህ ጦዋፍ ውጪ፣ በሰዕይ ወቅት እና ለሴቶች የተደነገገ አይደለም። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ረመልና ኢድጢባዕን ያደረጉት መካ በገቡ ጊዜ ባደረጉት የመጀመሪያው ጦዋፋቸው ላይ ብቻ ነው። በጦዋፍ ጊዜም ከሐደስና ከነጃሳ የፀዳ፣ ለጌታው የተዋደቀና የተናነሰ መሆን አለበት።

በጦዋፍ ወቅት የአላህን ዚክርና ዱዓ ማብዛቱ ይወደድለታል። ከቁርአንም የተወሰነውን ቢቀራ መልካም ነው። በዚህ ጦዋፍም ሆነ በሌሎች ጦዋፎች እንዲሁም በሰዕይ የተለየ ዚክርም ሆነ ዱዓ አይጠበቅበትም።

አንዳንድ ሰዎች ለእያንዳንዱ የጦዋፍ ወይም የሰዕይ ዙር የተለየ አዝካር ወይም ዱዓ መመደባቸው ምንም መሰረት የለውም። ይልቁንም የተመቸውን ዚክርና ዱዓ ማድረግ በቂ ነው። ሩክነል የማኒ ጋር ሲደርስ በቀኝ እጁ ይነካውና፦ “ቢስሚላህ ወላሁ አክበር” ይላል፤ ነገር ግን አይስመውም። እሱን መንካት የሚያስቸግረው ከሆነ ደሞ ወደ እሱ ሳይጠቁምና ተክቢራ ሳያደርግ ትቶ ጦዋፉን ነው የሚቀጥለው። ምክንያቱም እስከምናውቀው ድረስ ይህ ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስላልተረጋገጠ ነው። በሩክነል የማኒ እና በሐጀረል አስወድ መካከል እንዲህ ማለቱ ይወደድለታል፦

﴿...رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْاخِرَةِ حَسَنَةً وَقِنَا عَذَابَ النَّارِ﴾

{ጌታችን ሆይ! በምድር ዓለም ደግን ነገር (ጸጋን) በመጨረሻይቱ ሀገርም ደግን ነገር (ገነትን) ስጠን። ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን።} [አል-በቀራህ፡ 201] ሐጀረል አስወድ ዘንድ በደረሰ ቁጥር ይዳብሰዋልም ይስመዋልም «አላሁ አክበር» ይላልም። መዳበሱና መሳሙ ካልገራለት ደግሞ ከሱ ትይዩ በሆነ ቁጥር በእጁ ወደርሱ እየጠቆመ «አላሁ አክበር» ይላል።

ከዘምዘምና ከመቃም ጀርባ ጠዋፍ ማድረግ ችግር የለውም፤ በተለይም በጭንቅንቅ ጊዜ። መስጂዱ በሙሉ የጠዋፍ ቦታ ነው። በመስጂዱ ኮሪደሮች ላይ ጠዋፍ ቢያደርግ ራሱ ይበቃዋል። ነገር ግን ከተቻለ ከካዕባ አቅራቢያ መዞሩ በላጭ ነው።

ጦዋፉን ሲያጠናቅቅ፣ ከገራለት ከመቃም ኢብራሂም ኋላ ሁለት ረከዓ ይሰግዳል። በሰዎች መጨናነቅና በመሳሰሉ ምክንያቶች ካልገራለት ደግሞ መስጂዱ ውስጥ በሚገኝ በማንኛውም ስፍራ ይሰግዳል። ከፋቲሓ በኋላም የሚከተሉትን ሱራዎች መቅራቱ ሱና ነው:

﴿قُلۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡكَٰفِرُونَ1﴾

{ቁል ያ አዩሃል ካፊሩን} [አል-ካፊሩን፡ 1] በመጀመሪያው ረከዓ እንዲሁም

﴿قُلۡ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ1﴾

{ቁል ሁወሏሁ አሐድ} [አልኢኽላስ:1] በሁለተኛው ረከዓ መቅራት በላጭ ነው፤ በሌሎች ሱራዎች ቢሰግድም ግን ችግር የለውም። ከዚያም የነብዩን ﷺ ፈለግ በመከተል፣ ወደ ሐጀረል አስወድ መጠጋቱ ከተመቸው በቀኝ እጁ ይነካዋል።

ከዚያም በበሩ በኩል ወደ ሰፋ ይወጣና ኮረብታው ላይ ይወጣል ወይም ስፍራው ላይ ይቆማል፤ ከተቻለ ሰፋ ላይ መውጣቱ ይበልጣል፤ የመጀመሪያውን ዙር ሲጀምርም ተከታዩን የኃያሉን አምላክን ቃል ይቀራል፦

﴿إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ مِنْ شَعَائِرِ اللَّهِ...﴾

{የሶፋና የመርዋ (ጋራዎች) የአላህን ትዕዛዝ ከመፈጸሚያ ጉልህ ቦታዎች (ምልክቶች) ናቸው።} [አልበቀራህ፡ 158]

ሶፋ ላይ ሆኖ ወደ ቂብላ በመዞር አላህን ማመስገንና ተክቢራ ማለቱ ይወደዳል። እንዲህም ይላል፦ "ላ ኢላሃ ኢለሏህ፣ ወሏሁ አክበር፤ ላ ኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ዩሕዪ ወዩሚት፣ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር። ላ ኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደህ፤ አንጀዘ ወዕደህ፤ ወነሰረ ዐብደህ፤ ወሀዘመል-አሕዛበ ወሕደህ።" (ትርጉሙም፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። አላህ ታላቅ ነው፤ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ እርሱ አንድ ነው፤ ለእርሱ አጋር የለውም። ንግስናና ምስጋና ለእርሱ ብቻ ነው፤ ህያው ያደርጋልም ይገላልም፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ እርሱ አንድ ነው። የገባውን ቃል ፈጽሟል፤ ባሪያውንም ረድቷል፤ የተሰባሰቡትንም (የጠላት) ኃይሎች ብቻውን ድል ነስቷል።) ከዚያም እጆቹን ወደ ላይ ከፍ አድርጎ የገራለትን ዱዓ ያደርጋል፤ ይህንንም ዚክርና ዱዓ ሶስት ጊዜ ይደግማል። ከዚያም ወርዶ ወደ መርዋ ይሄዳል። ወንድ ከሆነም ከመጀመሪያው ምልክት ጀምሮ እስከ ሁለተኛው ምልክት ድረስ በፈጣን እርምጃ ይሄዳል። ሴት ከሆነች መላ ነገሯ ዐውራ (መሸፈን ያለበት) ስለሆነ ለርሷ በሁለቱ ምልክቶች መካከል መፍጠን አልተደነገገላትም። ይልቁንም ለርሷ የተደነገገው በሁሉም መሮጫ ስፍራ መራመድ ነው። ከዚያም እየተራመደ ወደ መርዋ ይወጣል ወይም ስፍራው ላይ ይቆማል። ከተቻለ (ኮረብታው ላይ) መውጣቱ በላጭ ነው፤ ሰፋ ላይ ያለውን እና የፈፀመውን ሁሉ መርዋ ላይም ይደግማል። እንዲህ የሚለውን የቁርአን አንቀፅ ግን አይደግምም:

﴿إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ مِنْ شَعَائِرِ اللَّهِ...﴾

{የሶፋና የመርዋ (ጋራዎች) የአላህን ትዕዛዝ ከመፈጸሚያ ጉልህ ቦታዎች (ምልክቶች) ናቸው።} [አልበቀራህ፡ 158] ይህን አንቀፅ መቅራት የተደነገገው ነብዩን ﷺ አርአያ በማድረግ በመጀመሪያው ዙር ብቻ ወደ ሶፋ በሚወጣ ወቅት ነው። ከዚያም ይወርዳል፤ መርዋ እስኪደርስ ድረስ መራመድ ባለበት ቦታ እየተራመደ፤ መፍጠን ባለበት ቦታ ደግሞ እየፈጠነ ይጓዛል። ይህንንም ሰባት ጊዜ ይደጋግመዋል። መሄዱ አንድ ዙር ሲሆን መመለሱም ሌላ ዙር ነው። አሁን የተጠቀሱትን ነብዩ ﷺ ፈፅመዋቸዋል። እንዲህም ብለዋል፦

«خُذُوا عَنِّي مَنَاسِكَكُمْ».

«የሐጅ ስርኣታችሁን ከኔ ውሰዱ።»51 በሰዕይ ጊዜ የፈለገውን ዚክርና ዱዓ ማብዛት እንዲሁም ከትልቅና ከትንሽ ሐደስ ንጹሕ መሆንም የተወደደ ነው። ጦሃራ ሳይኖረው ሰዕይ ቢያደርግም ግን ይበቃለታል። ልክ እንደዚሁ ሴት ልጅ ከጦዋፍ በኋላ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም ቢፈሳት ሰዕይ ታደርጋለች፤ ይህም ይበቃላታል። ምክንያቱም ጦሃራ ለሰዕይ መስፈርት አይደለም፤ ይልቁንም ቀደም ብሎ እንደተገለጸው ከሚወደዱ ተግባራት መካከል ነው።

ሰዕዩን እንዳጠናቀቀ ጭንቅላቱን ይላጫል ወይም ያሳጥራል። ለወንድ መላጨቱ በላጭ ነው። ፀጉሩን አሳጥሮ መላጨቱን ለሐጅ ከተወውም መልካም ነው። መካ የደረሰው የሐጅ ወቅት በተቃረበ ጊዜ ከሆነ በሐጅ ወቅት የቀረውን ፀጉሩን ይላጭ ዘንድ ፀጉሩን ማሳጠር በላጭ ይሆንለታል። ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ እርሳቸውና ባልደረቦቻቸው በዙል-ሒጃ አራተኛው ቀን መካ በገቡ ጊዜ ሀድይ ያልነዱትን ከኢሕራም እንዲወጡና እንዲያሳጥሩ አዘዋል፤ እንዲላጩ ግን አላዘዟቸውም። በማሳጠር ጊዜ መላውን ጭንቅላት ማዳረስ ግድ ነው። ከፊሉን ብቻ ማሳጠር በቂ አይደለም፤ ልክ እንደዚሁ ከፊሉን መላጨትም በቂ አይሆንም። ሴት ልጅ የተደነገገላት ማሳጠር ብቻ ነው። ለእርሷ የተደነገገላት ከእያንዳንዱ ሹሩባዋ የአንጓ ያህል ወይም ከዚያ ያነሰ መጠን መቁረጥ ነው። አንጓ ማለት የጣት ጫፍ ማለት ነው። ሴት ልጅ ከዚህ በላይ አትቆርጥም።

ኢሕራም ያደረገ ሰው የተጠቀሰውን ከፈፀመ ዑምራው ይጠናቀቃል። በኢሕራም ምክንያት እርም ተደርገውበት የነበሩ ነገሮች በሙሉ የተፈቀዱ ይሆኑለታል። ከሐረም ውጭ ሀድይ (እርድ) ይዞ የመጣ ከሆነ ግን ከሐጅና ዑምራ በኋላ በጋራ እስከሚፈታ ድረስ በኢሕራሙ ላይ ይቆያል።

ሐጅን ብቻውን ኢሕራም ያደረገ ወይም ሐጅና ዑምራን አንድ ላይ ኢሕራም ያደረገ ሰው፣ ከርሱ ጋር ሀድይ (እርድ) ይዞ ካልመጣ በቀር ኢሕራሙን ወደ ዑምራ እንዲለውጥና የተመቱዕን አፈፃፀም መፈፀሙ ሱና ይሆንለታል። ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ ሰሓቦቻቸውን (ባልደረቦቻቸውን) እንዲህ እንዲያደርጉ አዝዘዋልና እንዲህም ብለዋል፦

«لَوْلَا أَنِّي سُقْتُ الهَدْيَ لَأَحْلَلْتُ مَعَكُمْ».

«ሀድይን ባልነዳሁ ኖሮ ከእናንተ ጋር እፈታ ነበር»52፡፡

አንዲት ሴት ለዑምራ ኢሕራም ካደረገች በኋላ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም ቢፈሳት ንፁህ እስክትሆን ድረስ በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ አታደርግም፤ በሶፋና በመርዋም መካከል ሰዕይ አታደርግም። ንፁህ ስትሆን ጠዋፍና ሰዕይ ታደርጋለች፤ ከፀጉሯም ታሳጥራለች፤ በዚህም ዑምራዋ ይጠናቀቃል። ነገር ግን ንፁህ ሳትሆን የተርዊያ ቀን ከደረሰ በምትገኝበት ቦታ ሆና ለሐጅ ኢሕራም ታደርጋለች፤ ከሰዎች ጋርም ወደ ሚና ትወጣለች። በዚህም ሐጅንና ዑምራን አጣምራ የምትፈፅም (ቃሪን) ትሆናለች። ሐጃጆች የሚፈፅሟቸውን ስርአቶች ማለትም በዓረፋ መቆምን፣ በመሽዓር (ሙዝደሊፋ) መቆምን፣ የጠጠር ውርወራን፣ በሙዝደሊፋና በሚና ማደርን፣ ሀድይን ማረድንና ፀጉርን ማሳጠርን ሁሉ ትፈፅማለች። ከዚያም ንፁህ ስትሆን በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ታደርጋለች፤ በሶፋና በመርዋም መካከል ሰዕይ ታደርጋለች፤ አንድ ጠዋፍና አንድ ሰዕይ ብቻ። ይህም ለሐጇም ለዑምራዋም ያበቃላታል። ይህም ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ለዑምራ ኢሕራም ካደረገች በኋላ የወር አበባ ሲያጋጥማት ነብዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ስላሏት ነው፡-

«افْعَلِي مَا يَفْعَلُ الحَاجُّ غَيْرَ أَنْ لَا تَطُوفِي بِالبَيْتِ حَتَّى تَطْهُرِي».

«ንፁህ እስክትሆኚ ድረስ በቤቱ ዙሪያ ጠዋፍ ከማድረግ ውጪ ሐጃጆች የሚፈፅሙትን ሁሉ ፈፅሚ።»53 ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም ላይ ያለች ሴት በእርድ ቀን ጠጠር ከወረወረችና ፀጉሯን ካሳጠረች ልክ እንደሌሎቹ ንፁህ ሴቶች ሐጇን እስክታጠናቅቅ ድረስ ከባለቤቷ ጋር ግንኙነት ከመፈፀም ውጪ በኢሕራም ምክንያት ክልክል የነበሩባት እንደ ሽቶና መሰል ነገሮች ሁሉ ይፈቀዱላታል። ከንፅህናዋ በኋላ ጠዋፍና ሰዕይ ከፈጸመች ደግሞ ከባለቤቷ ጋር መገናኘትም ይፈቀድላታል።

አዲስ ክፍል:

በዙልሒጃህ ስምንተኛው ቀን ለሓጅ ኢሕራም ስለማድረግና ወደ ሚና ስለመውጣት ብይን፤

የተርዊያህ ቀን ሲሆን — ይህም የዙልሒጃ ስምንተኛው ቀን ነው — በመካ ሆነው ከኢሕራማቸው ለተፈቱ ሰዎች እና ሐጅ ማድረግ ለሚፈልጉ የመካ ነዋሪዎች ከመኖሪያዎቻቸው ሆነው ለሐጅ ኢሕራም ማድረጋቸው የተወደደ ነው። ምክንያቱም የነብዩ ﷺ ባልደረቦች በአብጠሕ ሰፍረው በተርዊያ ቀን በሳቸው ﷺ ትዕዛዝ ከዚያው ሆነው ለሐጅ ኢሕራም አድርገዋልና። ነብዩም ﷺ ወደ ከዕባ ሄደው ከእርሱ ዘንድ ወይም ከሚዛብ ጎን ኢሕራም እንዲያደርጉ አላዘዟቸውም። እንዲሁም ወደ ሚና በሚወጡበት ጊዜ የመሰናበቻ ጠዋፍ እንዲያደርጉም አላዘዟቸውም። ይህ የተደነገገ ቢሆን ኖሮ ያስተምሯቸው ነበር። ኸይር ነገር ሁሉ ነብዩን ﷺ እና ባልደረቦቻቸውን ረዲየላሁ ዐንሁም በመከተል ውስጥ ነው።

ከሚቃት ኢሕራም ሲያደርግ እንደሚያደርገው ሁሉ፤ ለሐጅ ኢሕራም ሲያደርግም መታጠቡ፣ መፅዳቱ እና ሽቶ መቀባቱ ይወደድለታል። ለሓጅ ኢሕራም ካደረጉ በኋላ በተርዊያ ቀን ፀሀይ ዘምበል ከማለቷ በፊት ወይም በኋላ ወደ ሚና መሄዳቸውም ሱና ነው። ጀምረት አል-ዓቀባን እስከሚወረውሩ ድረስም ተልቢያን ያበዛሉ። በሚናም ዙህርን፣ ዐስርን፣ መግሪብን፣ ዒሻንና ፈጅርን ይሰግዳሉ። ሱናውም እያንዳንዱን ሶላት በወቅቱ ሳይሰበስቡ እያሳጠሩ መስገዳቸው ነው። መግሪብና ፈጅርን ግን አያሳጥሩም።

በመካ ሰዎችና ከነሱ ውጭ ባሉት መካከል ልዩነት የለውም፤ ምክንያቱም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመካ ሰዎችንም ሆነ ሌሎችን ሚና፣ ዐረፋና ሙዝደሊፋ ላይ ሶላትን አሳጥረው አሰግደዋልና። የመካ ሰዎችን ነጥለው እንዲያሟሉ አላዘዙም። በነሱ ላይ ዋጅብ ቢሆን ኖሮ ለነሱ ባብራሩላቸው ነበር።

ከዚያም የዐረፋ ቀን ፀሐይ ከወጣች በኋላ ከሚና ወደ ዐረፋ ይጓዛሉ። ከገራላቸውም ፀሐይ ወደ መግቢያዋ እስክትዘነበል ድረስ ወደ ነሚራ መውረዳቸው ሱና ነው፤ ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይህንኑ አድርገዋልና።

ፀሐይ ወደ መግቢያዋ ስትዘነበል ኢማሙ ወይም ተተኪው ወቅቱን የሚመጥን ኹጥባ ለህዝቡ ማድረጉ ሱና ነው። በዚህ ኹጥባውም በዚህች ዕለትና ከእርሷም በኋላ ለሓጃጆች የተደነገገውን ያብራራበታል፤ አላህን እንዲፈሩ፣ እርሱን በብቸኝነት እንዲያመልኩ (ተውሒድ)፣ በሁሉም ስራዎቻቸው ለእርሱ ብቻ ፍጹም እንዲሆኑ (ኢኽላስ) ያዛል፤ ከክልክል ነገሮችም ያስጠነቅቃል፤ እንዲሁም የአላህን መጽሐፍና የነቢያቸውን ሱና (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) አጥብቀው እንዲይዙ፣ በሁለቱም እንዲዳኙና በሁሉም ጉዳዮች ላይ ወደ እነርሱ እንዲፋረዱ ይመክራል። በዚህ ሁሉ የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ፈለግ በመከተል ከኹጥባው በኋላ ዙህርንና ዐስርን በዝሁር ወቅት በአንድ አዛንና በሁለት ኢቃማ አሳጥረውና ሰብስበው ይሰግዳሉ። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፈፀማቸውን ሙስሊም ከጃቢር (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) በተላለፈ ሓዲሥ ስለተዘገበ ነው።

ከዚያም ሰዎች በዓረፋ ይቆማሉ። ከዑረና ሸለቆ በቀር ሁሉም የዓረፋ ክፍል መቆሚያ ቦታ ነው። ከተቻለ ወደ ቂብላ እና ወደ ጀበለ-ረሕማ (የእዝነት ተራራ) መዞሩ ይወደዳል። ወደ ሁለቱም መዞር ካልተቻለ ተራራውን ባይቅጣጭም እንኳ ወደ ቂብላ ይዙር። ሓጅ አድራጊው በዚህ የመቆሚያ ቦታ ጥራት የተገባውን አላህን በማውሳት፣ ዱዓእ በማድረግ እና ወደርሱ በመተናነስ መጣሩ ይወደድለታል። ዱዓእ ሲያደርግም እጆቹን ከፍ ያደርጋል። ተልቢያ ቢያደርግ ወይም ከቁርኣን የተወሰነውን ቢቀራ መልካም ነው። የሚከተለውን ዚክር ማብዛቱም ሱና ነው: "ላ ኢላሀ ኢልለልላሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ፣ ዩሕዪ ወዩሚቱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር"፤ ከነቢዩ ﷺ እንደተዘገበው እንዲህ ብለዋልና:

«خَيْرُ الدُّعَاءِ دُعَاءُ يَوْمِ عَرَفَةَ، وَأَفْضَلُ مَا قُلْتُ أَنَا وَالنَّبِيُّونَ مِنْ قَبْلِي: لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ المُلْكُ وَلَهُ الحَمْدُ، يُحْيِي وَيُمِيتُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ».

«ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ የዐረፋ ቀን ዱዓ ሲሆን፤ እኔና ከኔ በፊት የነበሩ ነቢያት ከተናገርነው ሁሉ በላጩ ደግሞ 'ላኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ዩሕዪ ወዩሚቱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር' (ትርጉሙ፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ ብቸኛ ነው ለእርሱ ምንም ተጋሪ የለውም፤ ንግስና ሁሉ ለእርሱ ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለእርሱ ነው፤ ህያው ያደርጋል፤ ይገድላልም፤ እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው) የሚለው ነው።»54 ነቢዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸውም በሶሒሕ ሐዲሥ ተላልፏል፦

«أَحَبُّ الكَلَامِ إِلَى اللَّهِ أَرْبَعٌ: سُبْحَانَ اللَّهِ، وَالحَمْدُ لِلَّهِ، وَلَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَاللَّهُ أَكْبَرُ».

«አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ንግግሮች አራት ናቸው። 'ሱብሓነላህ' (አላህ ሆይ! ጥራት ተገባህ)፣ 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው)፣ 'ላኢላሃ ኢለላህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) እና 'አሏሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው)።»55

ይህንን ዚክር በተመስጦና ልብን ሰብስቦ ማብዛትና መድጋገም ይገባል። እንዲሁም በማንኛውም ጊዜ በሸሪዓ የመጡ ዚክሮችንና ዱዓዎችን ማብዛትም ይገባል፤ በተለይም በዚህ ታላቅ ቀን እና ስፍራ ላይ ጠቅለል ያሉ ዚክሮችንና ዱዓዎችንም መምረጥ ይገባል። ከነዚህም መካከል:

* «ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ፣ ሱብሓነላሂል ዐዚም።» (ለአላህ ጥራትና ምስጋና ይገባው፤ ታላቁ አላህ ጥራት ይገባው።)

﴿...لَا إِلَهَ إِلَّا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمِينَ﴾

«ካንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም ጥራት ይገባህ። እኔ በእርግጥ ከበዳዮች ነበርኩ።» [አል-አንቢያእ: 87]

ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከርሱም ሌላ አንገዛም። ፀጋው የርሱ ብቻ ነው፤ ችሮታውም የርሱ ብቻ ነው፤ መልካም ውዳሴም የሚገባው ለእርሱ ብቻ ነው። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከሓዲዎች ቢጠሉም (እኛ) ሃይማኖታችንን ለርሱ ያጠራን ነን።

* በአላህ ካልሆነ በስተቀር ምንም ኃይልና ዘዴ የለም።56

* ﴿...رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْاخِرَةِ حَسَنَةً وَقِنَا عَذَابَ النَّارِ 201﴾

«ጌታችን ሆይ! በምድር ዓለም ደግን ነገር (ጸጋን) በመጨረሻይቱ ሀገርም ደግን ነገር (ገነትን) ስጠን። ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን።»

[አል-በቀራህ፡ 201]

* اللَّهُمَّ أَصْلِحْ لِي دِينِيَ الَّذِي هُوَ عِصْمَةُ أَمْرِي، وَأَصْلِحْ لِي دُنْيَايَ الَّتِي فِيهَا مَعَاشِي، وَأَصْلِحْ لِي آخِرَتِيَ الَّتِي فِيهَا مَعَادِي، وَاجْعَلِ الحَيَاةَ زِيَادَةً لِي فِي كُلِّ خَيْرٍ، وَالمَوْتَ رَاحَةً لِي مِنْ كُلِّ شَرٍّ.

* አልሏሁምመ አስሊሕ ሊ ዲኒየ-ልለዚ ሁወ ዒስመቱ አምሪ፣ ወአስሊሕ ሊ ዱንያየ-ልለቲ ፊሃ መዓሺ፣ ወአስሊሕ ሊ አኺረቲየ-ልለቲ ፊሃ መዓዲ፣ ወጅዐሊል ሐያተ ዚያደተን ሊ ፊ ኩልሊ ኸይር፣ ወልመውተ ራሐተን ሊ ሚን ኩልሊ ሸር" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! የጉዳዮቼ መጠበቂያ የሆነውን ሀይማኖቴን አስተካክልልኝ፤ ኑሮዬ በውስጧ የሆነችውን ዱንያዬንም አስተካክልልኝ፤ መመለሻዬ በውስጧ የሆነውን አኺራዬንም አስተካክልልኝ፤ ህይወትን መልካም ነገር ሁሉ የምጨምርባት አድርግልኝ፤ ሞትንም ከሁሉም መጥፎ ነገር የማርፍበት አድርግልኝ።"57

* أَعُوذُ بِاللَّهِ مِنْ جَهْدِ البَلَاءِ، وَدَرَكِ الشَّقَاءِ، وَسُوءِ القَضَاءِ، وَشَمَاتَةِ الأَعْدَاءِ.

* "አዑዙ ቢልላሂ ሚን ጀህዲል በላእ ወደረኪ-ሽሸቃእ ወሱኢል ቀዿእ ወሸማተቲል አዕዳእ" ትርጉሙም "ከከባድ መከራ ፣ እድለ ቢስነት ከሚያገኘኝ ፣ ከመጥፎ ውሳኔ ፣ የጠላት ደስታ ምንጭ ከመሆን በአላህ እጠበቃለሁ።"58

* اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الهَمِّ وَالحَزَنِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ العَجْزِ وَالكَسَلِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ الجُبْنِ وَالبُخْلِ، وَمِنَ المَأْثَمِ وَالمَغْرَمِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ غَلَبَةِ الدَّيْنِ وَقَهْرِ الرِّجَالِ.

«አልላሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ሀምሚ ወልሐዘኒ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚነል ዐጅዚ ወልከሰሊ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚነል ጁብኒ ወልቡኽሊ፣ ወሚነል መእሠሚ ወልመጝረሚ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚን ጘለበቲድ-ደይኒ ወቀህሪር-ሪጃል» "አላህ ሆይ! ከጭንቀትና ከሀዘን፣ ከአቅም ማነስና ከስንፍና፣ ከፈሪነትና ከስስት ከወንጀልና ከእዳ፣ ከእዳ መብዛትና በሰዎች ከመጨቆን በአንተ እጠበቃለሁ።"59

* اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ البَرَصِ وَالجُنُونِ وَالجُذَامِ وَمِنْ سَيِّئِ الأَسْقَامِ.

"አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል በረሲ ወልጁኑኒ ወልጁዛሚ ወሚን ሰይዪኢል አስቃሚ" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከለምጥ ፣ ከእብደት፣ ከቁምጥና፣ ከመጥፎ በሽታዎችም ባንተ እጠበቃለሁ።"60

«አሏሁመ ኢኒ አስአሉከል ዓፍወ ወልዓፊየተ ፊዱኒያ ወልአኺራህ» አላህ ሆይ! በዚህችም ሆነ በቀጣዩ ዓለም ይቅርታህንና ጤናን እጠይቅሃለሁ።

«አሏሁመ ኢኒ አስአሉከል ዓፍወ ወልዓፊየተ ፊዲኒ ወዱንያይ ወአህሊ ወማሊ» አላህ ሆይ! በሃይማኖቴ፣ በቅርቢቱ ዓለም ህይወቴ፣ በቤተሰቦቼና በንብረቴም ይቅርታህንና ጤናን እጠይቅሃለሁ።

* اللَّهُمَّ اسْتُرْ عَوْرَتِي وَآمِنْ رَوْعَاتِي، اللَّهُمَّ احْفَظْنِي مِنْ بَيْنِ يَدَيَّ وَمِنْ خَلْفِي، وَعَنْ يَمِينِي وَعَنْ شِمَالِي، وَمِنْ فَوْقِي، وَأَعُوذُ بِعَظَمَتِكَ أَنْ أُغْتَالَ مِنْ تَحْتِي.

«አሏሁመስቱር ዓውራቲ ወአሚን ረውዓቲ አሏሁመሕፈዝኒ ሚን በይኒ የደየ ወሚን ኸልፊ ወዓን የሚኒ ወዓን ሺማሊ ወሚን ፈውቂ ወአዑዙ ቢዓዘመቲከ አን ኡጝታለ ሚን ተሕቲ»አላህ ሆይ! ነውሬን ሸፍንልኝ፤ ለስጋቴም (ለፍርሃቴም) ደህንነትን ለግሰኝ። አላህ ሆይ! ከፊት ለፊቴ፣ ከኋላዬም፣ ከበስተቀኜም፣ ከበስተግራዬም እንዲሁም ከበላዬም ጠብቀኝ፤ ከበታቼም እንዳልጠቃ በልቅናህ እጠበቃለሁ።61

* اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي جِدِّي وَهَزْلِي، وَخَطَئِي وَعَمْدِي، وَكُلَّ ذَلِكَ عِنْدِي، اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي مَا قَدَّمْتُ وَمَا أَخَّرْتُ، وَمَا أَسْرَرْتُ وَمَا أَعْلَنْتُ، وَمَا أَنْتَ أَعْلَمُ بِهِ مِنِّي، أَنْتَ المُقَدِّمُ وَأَنْتَ المُؤَخِّرُ، وَأَنْتَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ.

"አሏሁመጝፊርሊ ጀዲ ወሀዝሊ ወኸጦኢ ወዓምዲ ወኩሉ ዛሊከ ዒንዲ አሏሁመጝፊርሊ ማቀደምቱ ወማ አኸርቱ ወማአስረርቱ ወማ አዕለንቱ ወማ አንተ አዕለሙ ቢሂ ሚኒ አንተል ሙቀዲሙ ወአንተል ሙአኺሩ ወአንተ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ትርጉሙ: "አላህ ሆይ! ምሬንም ቀልዴንም፣ ስህተቴንም ሆን ብዬ የሰራሁትንም ማረኝ፤ ይህ ሁሉም ከኔው ነው፡፡ አላህ ሆይ! ያስቀደምኩትን፣ ያዘገየሁትን፣ የደበቅኩትን፣ ግልፅ ያወጣሁትን፣ አንተ ከኔ የበለጠ የምታውቀውንም ማረኝ፡፡ አንተ አስቀዳሚ ነህ፣ አንተም የሚያዘገይ ነህ፤ አንተም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህ፡፡"62

* اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الثَّبَاتَ فِي الأَمْرِ وَالعَزِيمَةَ عَلَى الرُّشْدِ، وَأَسْأَلُكَ شُكْرَ نِعْمَتِكَ وَحُسْنَ عِبَادَتِكَ، وَأَسْأَلُكَ قَلْبًا سَلِيمًا وَلِسَانًا صَادِقًا، وَأَسْأَلُكَ مِنْ خَيْرِ مَا تَعْلَمُ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا تَعْلَمُ، وَأَسْتَغْفِرُكَ لِمَا تَعْلَمُ، إِنَّكَ عَلَّامُ الغُيُوبِ.

"አልላሁመ ኢኒ አስአሉከሥ-ሠባተ ፊልአምሪ፣ ወልዐዚመተ ዓለር-ሩሽዲ፤ ወአስአሉከ ሹክረ ኒዕመቲከ፣ ወሑስነ ዒባደቲከ፤ ወአስአሉከ ቀልበን ሰሊመን ወሊሳነን ሷዲቃ፤ ወአስአሉከ ሚን ኸይሪ ማ ተዕለም፣ ወአዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማተዕለም፣ ወአስተጝፊሩከ ሊማ ተዕለም ኢነከ ዓልላሙል ጙዩብ" "አላህ ሆይ! እኔ በጉዳዩ ላይ ፅናትንና በቀናነት ላይ ቆራጥነትን እጠይቅሀለሁ፤ ለፀጋዎችህ ማመስገንንና አምልኮህን ማሳመርን እጠይቅሀለሁ፤ ንፁህ ቀልብና እውነተኛ ምላስን እጠይቅሀለሁ፤ የምታውቀውን መልካም ነገር እጠይቅሀለሁ፤ ከምታውቀው መጥፎ ነገርም ባንተ እጠበቃለሁ፤ ለምታውቀው (ወንጀሎቼ) ምህረትን እጠይቅሀለሁ። እነሆ አንተ ሩቁን አዋቂ ነህና።"63

* اللَّهُمَّ رَبَّ النَّبِيِّ مُحَمَّدٍ عَلَيْهِ الصَّلَاةُ وَالسَّلَامُ، اغْفِرْ لِي ذَنْبِي، وَأَذْهِبْ غَيْظَ قَلْبِي وَأَجِرْنِي مِنْ مُضِلَّاتِ الفِتَنِ مَا أَحْيَيْتَنَا.

"አልላሁመ ረብበን-ነቢይ ሙሐመዲን ዐለይሂስ-ሶላቱ ወስ-ሰላም፣ ጝፊር ሊ ዘንቢ፣ ወአዝሂብ ጘይዞ ቀልቢ ወአጂርኒ ሚን ሙዺልላቲል ፊተኒ ማ አሕየይተና" "የነብዩ ሙሐመድ ጌታ የሆንክ አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ፤ የልቤን ከባድ ንዴትም አስወግድልኝ፤ ህያው እስካደረግከን ድረስም አጥማሚ ከሆኑ ፈተናዎች ጠብቀኝ።"64

* اللَّهُمَّ رَبَّ السَّمَاوَاتِ وَرَبَّ الأَرْضِ وَرَبَّ العَرْشِ العَظِيمِ، رَبَّنَا وَرَبَّ كُلِّ شَيْءٍ، فَالِقَ الحَبِّ وَالنَّوَى، وَمُنْزِلَ التَّوْرَاةِ وَالإِنْجِيلِ وَالفُرْقَانِ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ كُلِّ شَيْءٍ أَنْتَ آخِذٌ بِنَاصِيَتِهِ، اللَّهُمَّ أَنْتَ الأَوَّلُ فَلَيْسَ قَبْلَكَ شَيْءٌ، وَأَنْتَ الآخِرُ فَلَيْسَ بَعْدَكَ شَيْءٌ، وَأَنْتَ الظَّاهِرُ فَلَيْسَ فَوْقَكَ شَيْءٌ، وَأَنْتَ البَاطِنُ فَلَيْسَ دُونَكَ شَيْءٌ، اقْضِ عَنَّا الدَّيْنَ وَأَغْنِنَا مِنَ الفَقْرِ.

"አላሁመ ረበ-ስሰማዋቲ ወረበል አርዺ ወረበል ዐርሺል ዐዚም፤ ረበና ወረበ ኩሊ ሸይኢን፤ ፋሊቀል ሐቢ ወንነዋ፤ ወሙንዚለ-ትተውራቲ ወልኢንጂሊ ወልፉርቃን፤ አዑዙ ቢከ ሚን ሸርሪ ኩሊ ሸይኢን አንተ አኺዙን ቢናሲየቲህ፤ አላሁመ አንተል አውወሉ ፈለይሰ ቀብለከ ሸይኡን፤ ወአንተል አኺሩ ፈለይሰ በዕደከ ሸይእ፤ ወአንተዝዟሂሩ ፈለይሰ ፈውቀከ ሸይእ፤ ወአንተል ባጢኑ ፈለይሰ ዱነከ ሸይእ፤ ኢቅዺ ዐንነ-ድደይነ ወአጝኒና ሚነል ፈቅር" ትርጉሙም "የሰማያት ጌታ፣ የምድር ጌታ፣ የታላቁ ዐርሽ ጌታ፣ ጌታችን ፣ የሁሉም ነገር ጌታ የሆንከው፣ ቅንጣትንና የቴምር ፍሬን ፈልቃቂ፣ ተውራትን ኢንጂልንና ፉርቃንን አውራጂ የሆንከው አላህ ሆይ! ከሁሉም አንተ አናቱን የምትይዝ ከሆንከው ነገር ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ፤ አላህ ሆይ! አንተ የመጀመሪያ ነህ ከአንተ በፊት አንዳችም የለም፤ አንተ የመጨረሻ ነህ ከአንተ በኋላ አንዳችም የለም፤ አንተ የበላይ ነህ ከአንተ በላይ አንዳችም የለም፤ አንተ ቅርብ ነህ እንዳንተ ቅርብ አንዳችም የለም እዳችንን ክፈልልን ከድህነትም አብቃቃን።"65

* اللَّهُمَّ أَعْطِ نَفْسِي تَقْوَاهَا، وَزَكِّهَا أَنْتَ خَيْرُ مَنْ زَكَّاهَا، أَنْتَ وَلِيُّهَا وَمَوْلَاهَا، اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ العَجْزِ وَالكَسَلِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ الجُبْنِ وَالهَرَمِ وَالبُخْلِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ عَذَابِ القَبْرِ.

"አልሏሁምመ አዕጢ ነፍሲ ተቅዋሃ ወዘክኪሃ አንተ ኸይሩ መን ዘክካሃ አንተ ወሊይዩሃ ወመውላሃ ፤ አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነልዐጅዚ ወልከሰሊ ፤ ወአዑዙ ቢከ ሚነልጁብኒ ወልሀረሚ ወልቡኽሊ ፤ ወአዑዙ ቢከ ሚን ዐዛቢል ቀብሪ" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ለነፍሴ ፍራቻዋን ስጣት ፤ ነፍሴን ለማጥራት የተሻልከው አንተው ነህና ነፍሴን አጥራት ፤ አንተ ረዳቷና ተቆጣጣሪዋ ነህና። አላህ ሆይ! እኔ ከስንፍናና ከመታከት ባንተ እጠበቃለሁ ፣ ከፈሪነት ፣ ከመጃጀትና ከስስትም ባንተ እጠበቃለሁ ፣ ከቀብር ቅጣትም ባንተ እጠበቃለሁ።"66

* اللَّهُمَّ لَكَ أَسْلَمْتُ، وَبِكَ آمَنْتُ، وَعَلَيْكَ تَوَكَّلْتُ، وَإِلَيْكَ أَنَبْتُ، وَبِكَ خَاصَمْتُ، أَعُوذُ بِعِزَّتِكَ أَنْ تُضِلَّنِي، لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، أَنْتَ الحَيُّ الَّذِي لَا يَمُوتُ، وَالجِنُّ وَالإِنْسُ يَمُوتُونَ.

"አልላሁመ ለከ አስለምቱ፣ ወቢከ አመንቱ፣ ወዐለይከ ተወከልቱ፣ ወኢለይከ አነብቱ፣ ወቢከ ኻሶምቱ፤ አዑዙ ቢዒዘቲከ አንቱዲለኒ፣ ላኢላሃ ኢላ አንተ፣ አንተልሐይዩ ለዚ ላየሙት፣ ወልጂኑ ወልኢንሱ የሙቱን" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ላንተ እጅ ሰጥቻለሁ፤ ባንተም አምኛለሁ፤ ባንተም ላይ ተመክቻለሁ፤ ወዳንተም ተመልሻለሁ፤ ባንተ መንገድም ተሟግቻለሁ፤ እንዳታጠመኝ በልቅናህ እጠበቃለሁ፤ ካንተ በቀርም በእውነት የሚመለክ የለም። የማይሞት ህያው አንተው ነህ። ጋኔንም ሰውም ይሞታሉ።" ማለት ነው።67

* اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ عِلْمٍ لَا يَنْفَعُ، وَمِنْ قَلْبٍ لَا يَخْشَعُ، وَمِنْ نَفْسٍ لَا تَشْبَعُ، وَمِنْ دَعْوَةٍ لَا يُسْتَجَابُ لَهَا.

"አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዒልሚን ላ የንፈዑ፣ ወሚን ቀልቢን ላ የኽሸዑ፣ ወሚን ነፍሲን ላ ተሽበዑ፣ ወሚን ደዕወቲን ላ ዩስተጃቡ ለሃ" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከማይጠቅም እውቀት፣ ከማይተናነስ ልብ፣ ከማትጠግብ ነፍስ፣ ተቀባይነት ከሌላት ዱዓም ባንተ እጠበቃለሁ።"68

* اللَّهُمَّ جَنِّبْنِي مُنْكَرَاتِ الأَخْلَاقِ وَالأَعْمَالِ وَالأَهْوَاءِ وَالأَدْوَاءِ.

"አላሁመ ጀንኒብኒ ሙንከራቲል አኽላቂ፣ ወልአዕማሊ፣ ወልአህዋኢ፣ ወአልአድዋእ።" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ከፀያፍ ምግባሮች፣ ከፀያፍ ተግባሮች፣ ከፀያፍ ዝንባሌዎችና በሽታዎች አርቀኝ።"69

* اللَّهُمَّ أَلْهِمْنِي رُشْدِي، وَأَعِذْنِي مِنْ شَرِّ نَفْسِي.

"አላሁመ አልሂምኒ ሩሽዲ ወአዒዝኒ ሚን ሸርሪ ነፍሲ" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ቅናቻን በውስጤ አስርፅብኝ ከነፍሴ ክፋትም ጠብቀኝ።"70

* اللَّهُمَّ اكْفِنِي بِحَلَالِكَ عَنْ حَرَامِكَ، وَأَغْنِنِي بِفَضْلِكَ عَمَّنْ سِوَاكَ.

* "አልላሁመክፊኒ ቢሐላሊከ ዐን ሐራሚክ፤ ወአግኒኒ ቢፈድሊከ ዓመን ሲዋክ" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! በሐላልህ ከሐራምህ ጠብቀኝ፤ በችሮታህም ከአንተ ውጪ ካሉ አብቃቃኝ።"71

* اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الهُدَى وَالتُّقَى وَالعَفَافَ وَالغِنَى.

"አልሏሁምመ ኢንኒ አስአሉከል ሁዳ ወት‐ቱቃ ወልዐፋፈ ወልጚና" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ቅናቻን ፣ ጥንቁቅነትን ፣ ጨዋነትንና መብቃቃትን እጠይቅሃለሁ።"72

* اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الهُدَى وَالسَّدَادَ.

"አልሏሁምመ ኢንኒ አስአሉከል ሁዳ ወስሰዳድ" "አላህ ሆይ! እኔ ቅናቻንና መገጠምን እጠይቅሃለሁ።"73

* اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ مِنَ الخَيْرِ كُلِّهِ، عَاجِلِهِ وَآجِلِهِ، مَا عَلِمْتُ مِنْهُ وَمَا لَمْ أَعْلَمْ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ الشَّرِّ كُلِّهِ، عَاجِلِهِ وَآجِلِهِ، مَا عَلِمْتُ مِنْهُ وَمَا لَمْ أَعْلَمْ، وَأَسْأَلُكَ مِنْ خَيْرِ مَا سَأَلَكَ مِنْهُ عَبْدُكَ وَنَبِيُّكَ مُحَمَّدٌ ﷺ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا اسْتَعَاذَ مِنْهُ عَبْدُكَ وَنَبِيُّكَ مُحَمَّدٌ ﷺ، اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الجَنَّةَ وَمَا قَرَّبَ إِلَيْهَا مِنْ قَوْلٍ أَوْ عَمَلٍ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ النَّارِ وَمَا قَرَّبَ إِلَيْهَا مِنْ قَوْلٍ أَوْ عَمَلٍ، وَأَسْأَلُكَ أَنْ تَجْعَلَ كُلَّ قَضَاءٍ قَضَيْتَهُ لِي خَيْرًا.

* "አልሏሁምመ ኢንኒ አስአሉከ ሚነል ኸይሪ ኩልሊህ፣ ዓጂሊሂ ወኣጂሊህ፣ ማ ዐሊምቱ ሚንሁ ወማ ለም አዕለም፣ ወአዑዙ ቢከ ሚነሽሸሪ ኩሊህ፣ ዓጂሊሂ ወኣጂሊህ፣ ማ ዐሊምቱ ሚንሁ ወማ ለም አዕለም፣ ወአስአሉከ ሚን ኸይሪ ማ ሰአለከ ሚንሁ ዐብዱከ ወነቢይዩከ ሙሐመዱን ﷺ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ መስተዓዘ ሚንሁ ዐብዱከ ወነቢይዩከ ሙሐመዱን ﷺ፣ አልሏሁምመ ኢንኒ አስአሉከል ጀንነተ ወማ ቀርረበ ኢለይሃ ሚን ቀውሊን አው ዐመል፣ ወአዑዙ ቢከ ሚነንናሪ ወማ ቀርረበ ኢለይሃ ሚን ቀውሊን አው ዐመል፣ ወአስአሉከ አንተጅዐለ ኩለ ቀዿኢን ቀዾይተሁ ሊ ኸይራ" ትርጉሙም "* አላህ ሆይ! እኔ ከሁሉም መልካም ነገር እጠይቅሀለሁ፤ ከፈጣኑም ይሁን ከዘገየው፣ ካወቅኩትም ይሁን ካላወቅኩት። ከሁሉም መጥፎ ነገርም ባንተ እጠበቃለሁ፤ ከፈጣኑም ይሁን ከዘገየው፣ ካወቅኩትም ይሁን ካላወቅኩት። ባሪያህና ነቢይህ ሙሐመድ ﷺ የጠየቁህን መልካም ነገር እጠይቅሀለሁ። ባሪያህና ነቢይህ ሙሐመድ ﷺ ከተጠበቁበት መጥፎ ነገርም ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! እኔ ጀነትንና ወደርሷ የሚያቃርበን ንግግር ወይም ተግባር እጠይቅሀለሁ። ከእሳትና ወደርሷ ከሚያቃርብ ንግግር ወይም ተግባር ባንተ እጠበቃለሁ። ሁሉንም ለኔ የወሰንከውን ውሳኔ መልካም እንድታደርግ እጠይቅሀለሁ።"74

* لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ المُلْكُ وَلَهُ الحَمْدُ، يُحْيِي وَيُمِيتُ بِيَدِهِ الخَيْرُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ، سُبْحَانَ اللَّهِ، وَالحَمْدُ لِلَّهِ، وَلَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَاللَّهُ أَكْبَرُ، وَلَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللَّهِ العَلِيِّ العَظِيمِ.

* "ላ ኢላሀ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ፣ ዩሕዪ ወዩሚት ቢየዲሂል ኸይር ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር። ሱብሓነሏህ፣ ወልሐምዱሊላህ፣ ወላ ኢላሀ ኢለሏህ፣ ወሏሁ አክበር፣ ወላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል ዐሊዪል ዐዚም" (ትርጉሙም፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው አምላክ የለም፤ እርሱ አንድ ነው፤ አጋር የለውም። ንግሥናም ምስጋናም የእርሱ ብቻ ነው። ህያው ያደርጋልም ይገላልም። መልካም ነገር ሁሉ በእጁ ነው። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው። አላህ ጥራት ይገባው። ምስጋናም ለአላህ ነው። ከአላህም በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። አላህም ታላቅ ነው። ልዑልና ታላቅ በሆነው በአላህ ቢሆን እንጅ ብልሃትም ሆነ ሃይል የለም።)75

* اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، وَبَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ.

* "አልላሁመ ሶሊ ዓላ ሙሐመድ ወዓላ አሊ ሙሐመድ፣ ከማ ሶለይተ ዓላ ኢብራሂም ወዓላ አሊ ኢብራሂም፣ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ። ወባሪክ ዓላ ሙሐመድ ወዓላ አሊ ሙሐመድ፣ ከማ ባረክተ ዓላ ኢብራሂም ወዓላ አሊ ኢብራሂም፣ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ።"76 ትርጉሙም፦ "አላህ ሆይ! በኢብራሂምና በቤተሰቦቻቸው ላይ እንዳወደስክ ሁሉ በሙሐመድና በቤተሰቦቻቸው ላይም ውዳሴህን አውርድ፤ አንተ ምስጉንና የላቅክ አምላክ ነህና። አላህ ሆይ! በኢብራሂምና በቤተሰቦቻቸው ላይ በረከትህን እንዳሰፈንክ ሁሉ በሙሐመድና በቤተሰቦቻቸው ላይም በረከትህን አዉርድ፤ አንተ ምስጉንና የላቅክ አምላክ ነህና።

* ﴿...رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْاخِرَةِ حَسَنَةً وَقِنَا عَذَابَ النَّارِ﴾

«ጌታችን ሆይ! በምድር ዓለም ደግን ነገር (ጸጋን) በመጨረሻይቱ ሀገርም ደግን ነገር (ገነትን) ስጠን። ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን።»

[አል-በቀራህ፡ 201]

በዚህ ታላቅ መቆሚያ ላይ ሐጅ አድራጊው ከዚህ ቀደም የተጠቀሱትን ዚክሮችና ዱዓዎች፣ እንዲሁም ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸውን ዚክር፣ ዱዓ እና በነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ላይ ሰለዋት ማውረድን ደጋግሞ ማድረጉ ይወደዳል። ዱዓውንም ችክ ብሎ ደጋግሞ ያድርግ፤ ጌታውንም የዱንያና የአኺራን መልካም ነገር ይጠይቅ። ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዱዓ ሲያደርጉ ሶስት ጊዜ ይደጋግሙት ነበር። ስለሆነም በዚህም ነገር እሳቸውን (አለይሂ ሶላቱ ወሰላም) መከተል ይገባል።

ሙስሊም የሆነ ሰው በዚህ ስፍራ ለጌታው የተዋደቀ፣ ለርሱ የተናነሰ፣ ለታላቅነቱ የተዋረደ፣ አላህ ፊት የተሰበረ፣ እዝነቱንና ምህረቱን የሚከጅል፤ ቅጣቱንና ቁጣውን የሚፈራ፣ ነፍሱንም የሚተሳሰብ፣ ንፁህ የሆነችን ተውባም የሚያድስ መሆን ይገባዋል። ምክንያቱም ይህ ቀን አላህ ለባሮቹ የሚለግስበት፣ በነርሱም በመላኢካዎቹ ፊት የሚኩራራበትና ከእሳት ነፃ ማውጣትን የሚያበዛበት ታላቅ ቀንና ታላቅ መሰባሰቢያ ነው። ሸይጣንም ከበድር ቀን በኋላ በዐረፋ ቀን ከሚሆነው በላይ የተዋረደ፣ ያነሰና የተናቀ ሆኖ በሌላ ቀን አይታይም፤ ይህም የሆነው አላህ በባሮቹ ላይ የሚያሳየውን ቸርነት፣ በጎ አድራጎቱን፣ ከእሳት ነፃ ማውጣቱና ምህረቱ መብዛቱን ስለሚያይ ነው።

በሶሒሕ ሙስሊምም፣ ከዓኢሻ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

«مَا مِنْ يَوْمٍ أَكْثَرَ مِنْ أَنْ يُعْتِقَ اللَّهُ فِيهِ عَبْدًا مِنَ النَّارِ مِنْ يَوْمِ عَرَفَةَ، وَإِنَّهُ لَيَدْنُو ثُمَّ يُبَاهِي بِهِمُ المَلَائِكَةَ، فَيَقُولُ: مَا أَرَادَ هَؤُلَاءِ؟».

«ከዐረፋ ቀን በበለጠ አላህ ባርያን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን የለም። እርሱም ይቀርብና ከዚያም ዓረፋ በተገኙ ባሮቹ መላኢካዎች ላይ ይፎክርባቸዋል፤ እንዲህም ይላል፡ "እነዚህ ምን ፈለጉ?"»77

ሙስሊሞች ዚክርና ዱዓ በማብዛት ከሁሉም ወንጀሎችና ስህተቶች ተውባና ኢስቲግፋርን በማዘውተር አላህ ከነፍሶቻቸው የሚመለከተው መልካም ነገራቸውን እንዲሆን ማድረግና ጠላታቸውን ሸይጧንንም ሊያዋርዱት፣ ሊያስከፉት ይገባቸዋል። ሑጃጆች ፀሀይ እስክትጠልቅ ድረስ በዚህ ቦታ ላይ በዚክር፣ በዱዓና ወደ አላህ በመዋደቅ የተጠመዱ ሆነው ይቆያሉ። ፀሀይ ከጠለቀች በኋላም በእርጋታና በዝግታ ወደ ሙዝደሊፋ ይሄዳሉ። ተልቢያንም ያበዛሉ። ሰፊ በሆነው ቦታም ላይ የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ተግባር በመከተል ፈጠን ይላሉ። ፀሀይ ከመጥለቋ በፊት ወደሌላ ቦታ ግን መንቀሳቀስ የተፈቀደ አይደለም፤ ምክንያቱም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ፀሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ቆመዋልና፤ እንዲህም ብለዋል፡

«خُذُوا عَنِّي مَنَاسِكَكُمْ».

«የሐጅ ስነስርዓታችሁን ከኔ ውሰዱ።»78

ሙዝደሊፋ ሲደርሱም - የደረሱበት ወቅት በመግሪብም ወቅትም ይሁን የዒሻ ወቅት ከገባ በኋላም ቢሆን - እዛው እንደደረሱ የነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተግባር ከመከተል አኳያ መግሪብን ሶስት ረከዓ ዒሻን ደግሞ ሁለት ረከዓ አድርገው በአንድ አዛንና በሁለት ኢቃም ሰብስበው ይሰግዷቸዋል።

አንዳንድ ሰዎች ሙዝደሊፋ እንደደረሱ ሰላት ከመስገዳቸው በፊት የሚወረወረውን ጠጠር መልቀማቸውና ብዙዎቻቸውም ይህ ድርጊት የተደነገገ እንደሆነ ማሰባቸው መሰረት የሌለው ስህተት ነው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ጠጠር እንዲለቀምላቸው ያዘዙት ከመሽዓር ወደ ሚና ከሄዱ በኋላ ነው። ጠጠሩን ከየትኛውም ቦታ ቢለቅም ይበቃለታል። ከሙዝደሊፋ መልቀሙም ግዴታ አይደለም፤ ይልቁንም ከሚና መልቀምም ይፈቀዳል። ሱናው ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) በመከተል በዚህ ቀን ጀምረተል ዓቀባን የሚወረውርባቸውን ሰባት ጠጠሮችን መልቀሙ ነው። በሶስቱ ቀናቶች ግን በየቀኑ ከሚና ሀያ አንድ ጠጠሮችን ይለቅምና በነሱም ሶስቱን ጀመራቶች ይወረውራል።

ጠጠርን ማጠብ የተወደደ አይደለም፤ የሚወረወርበትም ሳይታጠብ ነው። ምክንያቱም ይህ ከነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይሁን ከባልደረቦቻቸው አልተዘገበምና። ከዚህ በፊት በተወረወረበት ጠጠርም መወርወር አይፈቀድም።

ሐጅ አድራጊው በዚህች ሌሊት በሙዝደሊፋ ያድራል። ከሴቶች፣ ከህፃናትና ከመሰሎቻቸው ለሆኑ ደካሞች ግን በሌሊቱ መጨረሻ ወደ ሚና መጓዝ ይፈቀድላቸዋል። ይህም ከዓኢሻ፣ ከኡሙ ሰለማ እና ከሌሎችም (አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና) በተላለፈው ሐዲሥ የተዘገበ ስለሆነ ነው። ሌሎቹ ሐጃጆች ግን ፈጅርን እስከሚሰግዱ ድረስ በዚያው ማሳለፍ በእነርሱ ላይ በአፅንዖት የተገባ ነው። ከዚያም አል-መሽዐረል ሐራም ዘንድ ይቆሙና ወደ ቂብላ ፊታቸውን በመመለስ ንጋቱ በጣም ወገግ እስኪል ድረስ የአላህን ስም ማውሳት፣ ተክቢራ ማለትንና ዱዓ ማድረግን ያበዛሉ። እዚህ ጋር በዱዓ ወቅት ሁለት እጆችን ከፍ ማድረግ ይወደዳል። ከሙዝደሊፋ የትም ቦታ ላይ ቢቆሙም ይበቃቸዋል። ከመሽዐር መቅረብም ሆነ እሱ ላይ የመውጣት ግዴታ የለባቸውም። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ስላሉ ነው:

«وَقَفْتُ هَاهُنَا - يَعْنِي عَلَى المَشْعَرِ الحَرَامِ - وَجَمْعٌ كُلُّهَا مَوْقِفٌ».

እኔ እዚህ ‐ ማለትም አል-መሽዓሪል ሐራም ላይ ‐ ቆሜያለሁ። ጀምዕ (ሙዝደሊፋ) ባጠቃላይ መቆሚያ ቦታ ነው።"79 ሙስሊም በሶሒሓቸው ዘግበውታል።፤ ጀመዕ የተባለውም ሙዝደሊፋ ነው።

ንጋቱ በጣም ወገግ ያለ ጊዜ ፀሐይ ከመውጣቱ በፊት ወደ ሚና ይመለሳሉ። በጉዟቸውም ተልቢያን ያበዛሉ። ሙሐስሲር ሲደርሱ ፍጥነትን ጥቂት መጨመሩ የተወደደ ነው።

ሚና በደረሱ ጊዜ ጀምረተል ዐቀባ ዘንድ ተልቢያ ማለትን ያቆማሉ። እዚያ እንደደረሱ ሰባት ጠጠሮችን አንድ በአንድ አከታትለው ይወረውራሉ። እያንዳንዱ ጠጠር ሲወረወር እጅ ከፍ አድርጎ ተክቢራ እያሉ ነው። ሸለቆው ውስጥ ሆኖ ከዕባን በግራው ሚናን ደግሞ በቀኙ አድርጎ መወርወሩ የተወደደ ነው፤ ይህም የነብዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ፈለግ ለመከተል ነው። ከሌሎች አቅጣጫዎች በኩል ሆኖ ቢወረውርም ግን ጠጠሩ መወርወሪያው ውስጥ እስከወደቀ ድረስ ይበቃለታል። ጠጠሩ መወርወሪያው ውስጥ መቆየቱ መስፈርት አይደለም፤ መስፈርቱ ሲጣል እዛው ውስጥ መውደቁ ብቻ ነው። በመሆኑም በእውቀት ባለቤቶች ንግግር መሰረት አንድ ጠጠር መወርወሪያው ውስጥ ወድቆ ከዚያ ቢወጣም ይበቃል። ይህንንም በግልፅ ከገለፁት መካከል ኢማም አን-ነወዊ (አላህ ይዘንላቸውና) በ‘ሸርሕ አል-ሙሀዘብ’ ላይ አስቀምጠውታል። የጀመራ ጠጠሮች እንደ ወንጭፍ ጠጠር ያሉ ሲሆኑ ከሽንብራ ትንሽ የሚበልጡ መሆን አለባቸው።

ከዚያም ጀመራውን ከወረወረ በኋላ ሀድዩን ያርዳል። በሚወጋበት ወይም በሚያርድበት ጊዜም "ቢስሚላሂ፣ ወሏሁ አክበር፣ አልላሁመ ሃዛ ሚንከ ወለክ" ማለቱ ይወደዳል። ወደ ቂብላም ያዞረዋል። ሱናው ግመልን ግራ እጇ ታስሮ በቆመችበት መውጋት፤ ከብትንና በግን (ፍየልንም) ደሞ በግራ ጎናቸው አጋድሞ ማረድ ነው። ከቂብላ ውጭ አዙሮ ቢያርድ ሱናን ቢተውም እርዱ ግን ይበቃለታል። ይህም የሆነበት ምክንያት በእርድ ጊዜ ወደ ቂብላ ማዞር ሱና እንጂ ግዴታ ባለመሆኑ ነው። ከሀድዩ መብላቱ፣ እንዲሁም ስጦታ መስጠትና መመፅወት ይወደዳል። ይህም አላህ እንዲህ ስላለ ነው:

﴿...فَكُلُوا مِنْهَا وَأَطْعِمُوا الْبَائِسَ الْفَقِيرَ﴾

{ከእርሷም ብሉ። ችግረኛ ድሀንም አብሉ።} [አል‐ሐጅ: 28] በትክክለኛው የዑለማዎች አቋም መሰረት የእርድ ወቅት እስከ አያመ ተሽሪቅ ሶስተኛው ቀን ፀሐይ መጥለቂያ ድረስ ይቆያል። በዚህም የእርዱ ጊዜያት የእርድ ቀን (ዙልሒጃ 10) እና ከእርሱ በኋላ ያሉት ሶስት ቀናት ናቸው።

ከዚያም መስዋእቱን ከወጋ ወይም ካረደ በኋላ ጭንቅላቱን ይላጫል ወይም ያሳጥራል። መላጨቱ በላጭ ነው፤ ምክንያቱም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለሚላጩት እዝነትንና ምህረትን ያገኙ ዘንድ (ሶስት ጊዜ) ዱዓ ስላደረጉ፤ ለሚያሳጥሩት ደግሞ አንድ ጊዜ ዱዓ አድርገውላቸዋል። ከፊል ጭንቅላትን ብቻ ማሳጠር በቂ አይደለም፤ ይልቁንም ልክ እንደ መላጨቱ ሁሉ ማሳጠሩም መላውን ጭንቅላት መሆን አለበት። ሴት ደግሞ ከእያንዳንዱ ሹርባዋ የጣት ጫፍ ወይም ከዚያ ያነሰ መጠን ታሳጥራለች።

ጀምረተል ዓቀባን ከወረወረና ከተላጨ ወይም ካሳጠረ በኋላ ለሙሕሪሙ ከሴቶች በስተቀር በኢሕራም ምክንያት ክልክል የሆኑበት ነገሮች በሙሉ ይፈቀዱለታል። ይህ የመጀመሪያው መፈታት (አት-ተሐሉሉል-አወል) ይባላል። ከዚህ መፈታት በኋላ ሽቶ መቀባቱና ጦዋፈል ኢፋዷን ለማድረግ ወደ መካ መሄዱ ሱና ነው። ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) እንዲህ በማለት የተናገረችው ሐዲስ ለዚህ ማስረጃ ነው፦

«كُنْتُ أُطَيِّبُ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ لِإِحْرَامِهِ قَبْلَ أَنْ يُحْرِمَ، وَلِحَلِّهِ قَبْلَ أَنْ يَطُوفَ بِالبَيْتِ».

«የአላህ መልዕክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኢሕራማቸው ኢሕራም ከማድረጋቸው በፊት፣ እንዲሁም ከኢሕራም ሊወጡ ሲሉም በአላህ ቤት ጦዋፍ ከማድረጋቸው በፊት ሽቶ እቀባቸው ነበር።»80 ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ይህ ጦዋፍም፡ ጦዋፈል ኢፋዷ እና ጦዋፈ ዚያራ ተብሎ ይጠራል። እርሱም ሐጁ ያለ እርሱ የማይጠናቀቅበት ከሐጅ ማዕዘናት መካከል አንዱ ነው። እርሱም ክብር ይግባውና ከፍ ያለው አላህ እንዲህ በሚለው ቃሉ ላይ የፈለገበት ነው፦

﴿ثُمَّ لْيَقْضُوا تَفَثَهُمْ وَلْيُوفُوا نُذُورَهُمْ وَلْيَطَّوَّفُوا بِالْبَيْتِ الْعَتِيقِ 29﴾

«ከዚያም (እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን) ትርፍ አካላቸውንና እድፋቸውን ያስወግዱ። ስለቶቻቸውንም በትክክል ይሙሉ። በጥንታዊዉም ቤት በካዕባ ዙሪያ ይዙሩ።» 29 [አል-ሐጅ: 29]

ከዚያም ጦዋፍ ካደረገና ከመቃም ኋላ ሁለት ረከዓ ከሰገደ በኋላ፤ የተመቱዕን የሐጅ አፈፃፀም ከሆነ በሰፋና መርዋ መካከል ይሮጣል። ይህ መሮጥ ለሐጁ ሲሆን የመጀመሪያው መሮጥ ደግሞ ለዑምራው ነው።

በይበልጥ ትክክለኛ በሆነው የሊቃውንት ንግግር አንድ ሰዕይ በቂ አይደለም፤ ዓኢሻ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- «ከአላህ መልክተኛ ﷺ ጋር ወጣን» ብላ ሐዲሡን ከጠቀሰች በኋላ በውስጡ እንዲህ ብለዋልና፦

«وَمَنْ كَانَ مَعَهُ هَدْيٌ فَلْيُهِلَّ بِالحَجِّ مَعَ العُمْرَةِ ثُمَّ لَا يَحِلُّ حَتَّى يَحِلَّ مِنْهُمَا جَمِيعًا».

«ከእርሱ ጋር ሀድይ (የእርድ እንስሳ) ያለ ሰው ሐጅን ከዑምራ ጋር አጣምሮ ኢሕራም ያድርግ፤ ከዚያም ከሁለቱም በአንድ ላይ እስከሚፈታ ድረስ ከኢሕራሙ አይውጣ።» ... እንዲህ እስከማለት ድረስ

«فَطَافَ الَّذِينَ أَهَلُّوا بِالعُمْرَةِ بِالبَيْتِ وَبِالصَّفَا وَالمَرْوَةِ ثُمَّ حَلُّوا ثُمَّ طَافُوا طَوَافًا آخَرَ بَعْدَ أَنْ رَجَعُوا مِنْ مِنًى لِحَجِّهِمْ».

«ለዑምራ ኢሕራም ያደረጉት በቤቱ (በከዕባ) ጦዋፍ አደረጉ፤ በሶፋና በመርዋም መካከል ተመላለሱ፤ ከዚያም ከኢሕራማቸው ወጡ፡፡ ከዚያም ለሐጃቸው ከሚና ከተመለሱ በኋላ ሌላ ጦዋፍ አደረጉ፡፡»81 ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።

ዓኢሻ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላና) ዑምራን አስበው ኢህራም ስላደረጉት ሰዎች «ከዚያም ለሐጃቸው ከሚና ከተመለሱ በኋላ ሌላ ጠዋፍ አደረጉ» ያለችው ንግግር፤ ይህን ሐዲሥ በማብራራት ረገድ ከተሰጡት አንድምታዎች መካከል ይበልጥ ትክክለኛ በሆነው አባባል መሰረት በንግግሯ ያመለከተችው በሶፋና በመርዋ መካከል የሚደረገውን መመላለስ ነው። በንግግሯ ያመለከተችው ጠዋፈል ኢፋዳን ነው የሚለው የሌሎች አባባል ግን ትክክል አይደለም፤ ምክንያቱም ጠዋፈል ኢፋዳ በሁሉም ላይ ማእዘን በመሆኑ ሁሉም ፈፅመውታልና። ይልቁንም በዚህ የተፈለገው ሙተመትዕን የሚመለከተው ነው፤ እርሱም ሐጁን ለማሟላት ከሚና ከተመለሰ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በሶፋና በመርዋ መካከል የሚያደርገውን መመላለስ ነው። ይህም አላህ የተመሰገነ ይሁንና ግልፅ ሲሆን የአብዛኞቹ የዕውቀት ባለቤቶችም ንግግር ነው።

ቡኻሪ በሶሒሐቸው ላይ እርግጠኛ በሆነ መልኩ በተዕሊቅ ከኢብኑ ዐባስ (አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና) ያስተላለፉት ዘገባም እንደዚሁ የዚህን ነገር ትክክለኛነት የሚያመላክት ነው፤ እርሳቸውም ስለ ሐጅ ሙትዓ ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፡- «ሙሃጂሮች፣ አንሷሮችና የነብዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤቶች በመሰናበቻ ሐጅ ኢሕራም አደረጉ፤ እኛም ኢሕራም አደረግን። መካ በደረስን ጊዜም የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፡- “ሀድይ (ለእርድ የሚሆን እንስሳ) ይዞ ከመጣ ሰው በስተቀር ለሐጅ ያደረጋችሁትን ኢሕራም ዑምራ አድርጉት።” ከዚያም በቤቱ (በካዕባ) እንዲሁም በሶፋና በመርዋ ጠዋፍና ሰዒይ አደረግን፤ ከባለቤቶቻችን ጋር ተገናኘን፤ ልብሶቻችንንም ለበስን። እርሳቸውም፡- “ሀድይ ይዞ የመጣ ሰው ሀድዩ የሚታረድበት ቦታ እስኪደርስ ድረስ ከኢሕራሙ አይወጣም።” አሉ። ከዚያም በተርዊያ ቀን ዋዜማ ለሐጅ ኢሕራም እንድናደርግ አዘዙን። ከመናሲኮቹ (ከሐጅ ስርአቶች) ስንጨርስም መጥተን በቤቱ (በካዕባ) እንዲሁም በሶፋና በመርዋ ጠዋፍና ሰዒይ አደረግን።»82 ከእርሱ የተፈለገው መልዕክት አበቃ፤ ይህም ሙተመትቲዕ ሁለት ጊዜ ሰዕይ እንደሚያደርግ በግልፅ ያስረዳል። አላህም ይበልጥ ያውቃል።

ሙስሊም ከጃቢር (ረዲየላሁ ዐንሁ) የዘገቡትን በተመለከተ ደሞ፦ «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲሁም ባልደረቦቻቸው በሰፋና በመርዋ መካከል አንድ ጠዋፍ እንጂ አላደረጉም»83፣ የመጀመርያው ጦዋፋቸው የሚያመለክተው ከሶሐባዎች መካከል ሀድይ ይዘው የመጡትን ነው፤ ምክንያቱም እነርሱ ከነቢዩ ሰ.ዐ.ወ ጋር ከሐጅም ከዑምራም በአንድነት እስከሚፈቱ ድረስ በኢሕራማቸው ላይ ቆይተዋልና። ነቢዩም ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም በሐጅና በዑምራ ኢሕራም አድርገዋል፤ ሀድይ ይዘው የመጡትም ዑምራን ከሐጅ ጋር አጣምረው ኢሕራም እንዲያደርጉና ከሁለቱም በአንድነት እስከሚፈቱ ድረስ እንዳይፈቱ አዘዋል። ሐጅንና ዑምራን አቆራኝቶ በሚፈፅም ሰው ላይ የተጠቀሰው የጃቢር ሐዲስና ሌሎችም ትክክለኛ ሐዲሶች እንዳመላከቱት ከአንድ ሰዒይ ውጪ አይጠበቅበትም።

በተመሳሳይ መልኩ ሐጅን በኢፍራድ ያደረገና እስከ ዒድ እለት ድረስ በኢሕራሙ ላይ የቆየ ሰውም አንድ ሰዕይ ብቻ ነው የሚጠበቅበት። ቃሪኑና ሙፍሪዱ ከጦዋፈል ቁዱም በኋላ ሰዕይ ካደረጉ ይህ ከጦዋፈል ኢፋዷ በኋላ ከሚደረገው ሰዕይ ያብቃቃቸዋል። የዓኢሻንና የኢብኑ ዐባስን ሐዲሦች ከተጠቀሰው የጃቢር ሐዲስ ጋር በዚህ መልኩ ይታረቃሉ። በዚህም መጋጨቱ ይቅራል፤ በሐዲሦቹም ሁሉ መስራት ይቻላል።

ይህንን አቀራራቢ ሃሳብ ከሚያጠናክሩት መካከል የዓኢሻና የኢብኑ ዓባስ ሐዲሦች ሁለቱም ሶሒሕ ከመሆናቸው በተጨማሪ ለሙተመትቲዕ ሁለተኛ ሰዕይ እንዳለበት ማፅደቃቸው ነው። የጃቢር ሐዲሥ ግልፅ መልዕክት ደግሞ ይህንን ውድቅ ያደርጋል። በኡሱልና በሙስጦላሐል-ሐዲሥ የእውቀት ዘርፎች እንደፀደቀው ደግሞ ያፀደቀው ማስረጃ ውድቅ ካደረገው ይቀደማል። ትክክለኛውንም ነገር የሚገጥመው ጥራትና ልዕልና የተገባው አላህ ነው። ከአላህም በስተቀር ብልሀትም ኃይልም የለም።

አዲስ ክፍል:

በእርድ ቀን ሐጅ አድራጊው የሚፈፅመው ተግባር በላጭ መሆኑን ማብራሪያ፤

ለሓጅ አድራጊ የነሕር ቀን ላይ እነዚህን አራት ነገሮች እንደተጠቀሰው በቅደም ተከተል መፈፀሙ በላጭ ነው፡ በመጀመሪያ ጀምረተል ዐቀባን በመወርወር ይጀምራል፣ ከዚያም በማረድ፣ ከዚያም ፀጉርን በመላጨት ወይም በማሳጠር፣ ከዚያም በበይቱ ጦዋፍ ማድረግና ከሱም በኋላ ሰዕይ ማድረግ ነው። ይህ ለተመቱዕ እና ከጦዋፈል ቁዱም ጋር ሰዕይ ላላደረጉ ሙፍሪድና ቃሪንም ነው። ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዱን ከሌላው ቢያስቀድምም ይበቃለታል፤ ምክንያቱም ከነቢዩ ﷺ በዚህ ላይ የተገኘ ፍቃድ መኖሩ ስለተረጋገጠ ነው። ሰዕይን ከጦዋፍ ማስቀደምም በዚህ ውስጥ ይካተታል። ምክንያቱም በነሕር ቀን ከሚፈፀሙ ተግባራት ውስጥ አንዱ ስለሆነ ነው። በሰሓባው ንግግር ውስጥም ይካተታል፤ «በዚያች ቀን አንድ ነገር ስለማስቀደሙ ወይም ስለማዘግየቱ አልተጠየቁም እንዲህ ያሉ ቢሆን እንጂ፦

«افْعَلْ وَلَا حَرَجَ».

"ይሁን፤ ችግር የለውም።"»84 መርሳትና አለማወቅ ከሚከሰቱባቸው ጉዳዮች አንዱ በመሆኑ በዚህ አጠቃላይ መርህ ስር መካተቱም ግድ ሆኗል፤ ይህም ነገሩን የሚያቀልና የሚያገራ በመሆኑ ነው።

ነቢዩም - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከጠዋፍ በፊት ሰዕይ ስላደረገ ሰው ተጠይቀው እንዲህ ማለታቸው ተረጋግጧል፦

«لَا حَرَجَ».

"ችግር የለውም።"85 አቡ ዳውድ ከኡሳማ ኢብኑ ሸሪክ በሶሒሕ ሰነድ ዘግበውታል። በዚህም ያለምንም ጥርጥር በአጠቃላይ ድንጋጌ ውስጥ መካተቱ ግልጽ ሆኗል። ስኬትን የሚሰጥ አላህ ነው።

ቀደም ብለን ከጠቅሰነውም አንፃር ሐጅ አድራጊው ሙሉ ለሙሉ ከኢሕራም የሚፈታባቸው ሶስት ነገሮች አሉ። እነሱም፦ ጀምረተል ዓቀባን መወርወር፣ መላጨት ወይም ማሳጠር እና ጦዋፈል ኢፋዷን ከሰዒይ ጋር ማድረግ ናቸው። እነዚህን ሶስቱን ከፈፀመ፣ ሴቶችን መገናኘት፣ ሽቶ መቀባትና ሌሎችንም ጨምሮ በኢሕራም ምክንያት ክልክል የሆኑበት ነገሮች ሁሉ ይፈቀዱለታል። ከነዚህ ውስጥ ሁለቱን የፈፀመ ሰው ግን ሴቶችን ከመገናኘት ውጪ በኢሕራም ምክንያት ክልክል የነበሩበት ነገሮች ሁሉ ይፈቀዱለታል። ይህም የመጀመሪያው መፈታት ይባላል።

ሐጅ ላደረገ ሰው የዘምዘም ውሃን እስኪረካ ድረስ መጠጣትና የገራለትን ጠቃሚ ዱዓ ማድረጉ ይወደድለታል፤

«مَاءُ زَمْزَمَ لِمَا شُرِبَ لَهُ».

«የዘምዘም ውኃ ለተጠጣለት ዓላማ ነው፡፡»86 እንዲሁም ሙስሊም በሶሒሓቸው ከአቡ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደዘገቡት ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስለ ዘምዘም ውኃ እንዲህ ብለዋል፦

«إِنَّهُ طَعَامُ طُعْمٍ».

"እርሱ ለምግብ ፈላጊ ምግብ ነው"87 አቡ ዳውድ ጨምረዋል:

«وَشِفَاءُ سُقْمٍ».

«ለበሽታም ፈውስ ነው።»88

ከኢፋዷ ጠዋፍና ከሰዕይ በኃላ ሰዕይ ማድረግ ግዴታ የሆነባቸው ደግሞ ሰዕይ ካደረጉ በኋላ ሑጃጆች ወደ ሚና ይመለሳሉ። እዚያም ሶስት ቀናትን ከነሌሊቶቻቸው ያሳልፋሉ። ከሶስቱ ቀናት በእያንዳንዳቸው ፀሐይ ወደ መግቢያዋ ከተዘነበለች በኋላ ሶስቱንም ጀመራዎች ይወረውራሉ። ሲወረውሩም ቅደም ተከተላቸውን መጠበቁ ግዴታ ነው።

በመጀመሪያው ጠጠር መወርወሪያ ይጀምራል፤ ይህም መስጂደል ኸይፍን ተከትሎ የሚገኘው ነው። ሰባት ጠጠሮችን አከታትሎ ይወረውርበታል። ከእያንዳንዱ ጠጠር ውርወራ ጋርም እጁን ከፍ ያደርጋል። ከእርሷ ወደ ኋላ መራቁና በግራ ጎኑ ማድረጉ ሱና ነው። ወደ ቂብላም ይዞርና እጆቹን ከፍ አድርጎ ዱዓና መዋደቅን ያበዛል።

ቀጥሎ ሁለተኛውን ጠጠር መወርወሪያ ዘንድ ልክ እንደ መጀመሪያው ይወረውራል። ከወረወረ በኋላም ጥቂት ወደ ፊት ይራመድና ጠጠር መወርወሪያውን በቀኙ በኩል አድርጎ ወደ ቂብላ ይዞራል። እጆቹንም ከፍ አድርጎ በብዛት ዱዓ ያደርጋል።

ቀጥሎ ሶስተኛው ጠጠር መወርወሪያ ዘንድ ይወረውራል እርሷ ዘንድ ግን አይቆምም።

ቀጥሎ በሁለተኛው የተሽሪቅ ቀንም ፀሐይ ከተዘነበለች በኋላ ልክ በመጀመሪያው ቀን እንደወረወረው ይወረውራል። ነቢዩ ﷺ በፈፀሙት መልኩ የመጀመሪያውና ሁለተኛው ጠጠር መወርወሪያ ዘንድም ልክ በመጀመሪያው ቀን እንዳደረገው ያደርጋል።

በአያመ-ተሽሪቅ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት መወርወር ከሐጅ ግዴታዎች ውስጥ አንዱ ነው። እንዲሁም በመጀመሪያውና በሁለተኛው ሌሊት በሚና ማደር ግዴታ ነው። በውሃ አጠጪዎችና በእረኞች እንዲሁም በመሰሎቻቸው ላይ ግን ግዴታ አይደለም።

ከዚያም በተጠቀሱት ሁለት ቀናት ከወረወረ በኋላ ከሚና ፈጥኖ መውጣት የፈለገ ሰው ፀሐይ ከመግባቷ በፊት መውጣት ይችላል። የዘገየ ሰው ደግሞ ሶስተኛዋን ሌሊት አድሮ በሶስተኛውም ቀን ቢወረውር ይህ በላጭና ምንዳውም ታላቅ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል:

﴿وَاذْكُرُوا اللَّهَ فِي أَيَّامٍ مَعْدُودَاتٍ فَمَنْ تَعَجَّلَ فِي يَوْمَيْنِ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ وَمَنْ تَأَخَّرَ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ لِمَنِ اتَّقَى...﴾

{(ሙስሊሞች ሆይ!) በእነዚያ በተወሰኑ ቀናት ውስጥ አላህን አውሱ። በሁለት ቀናት ውስጥ ለመሄድ የተቻኮለ ሰው በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም። የቆየም ሰው ኃጢአት የለበትም። ይህም አላህን ለፈራ ሰው ሁሉ ነው።} [አል‐በቀራህ: 203] ነቢዩ ﷺ ለሰዎች ፈጥነው እንዲወጡ ቢፈቅዱላቸውም እሳቸው ግን አልቸኮሉም፤ ይልቁንም በአስራ ሶስተኛው ቀን ፀሐይ ከተዘነበለች በኋላ ጠጠሮችን እስከሚወረውሩ ድረስ ሚና ቆይተው ከዚያም ዙህርን ከመስገዳቸው በፊት ተጉዘዋል።

በቀጥታ ጠጠር መወርወር የማይችል ለሆነው ህፃን ልጅ ወሊዩ ለራሱ ከወረወረ በኋላ ጀምረተል ዓቀባን እና ሌሎች ጀማራዎችን ለህፃኑም ሊወረውርለት ይፈቀድለታል። እንዲሁም መወርወር የማትችል ህፃን ሴት ልጅም ወሊይዋ ለርሷ ይወረውርላታል፤ ጃቢር -አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና- ባስተላለፉት ሐዲስ ላይ እንዲህ ብለዋል፦

«حَجَجْنَا مَعَ رَسُولِ اللَّهِ ﷺ، وَمَعَنَا النِّسَاءُ وَالصِّبْيَانُ، فَلَبَّيْنَا عَنِ الصِّبْيَانِ وَرَمَيْنَا عَنْهُمْ».

«ከአላህ መልክተኛ ﷺ ጋር ሐጅ አደረግን። ከኛ ጋርም ሴቶችና ህፃናት ነበሩ። ለህፃናቱ ተልቢያም አደረግንላቸው፤ ለነሱም ወረወርንላቸው።»89 ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል።

በበሽታ ወይም በእርጅና ወይም በእርግዝና ምክንያት መወርወር ላልቻለ ሰው ለርሱ የሚወረውርለትን እንዲወክል ይፈቀድለታል። ይህም አላህ እንዲህ ስላለ ነው፦

﴿فَاتَّقُوا اللَّهَ مَا اسْتَطَعْتُمْ...﴾

{አላህንም የቻላችሁትን ያህል ፍሩት።} [አት‐ተጋቡን: 16] እነዚህ ሰዎች ጀመራት ላይ ከሰዎች ጋር መገፋፋትም አይችሉም፤ ጠጠር የመወርወሪያ ጊዜም አላፊ በመሆኑ ቀዷእ እንዲያወጡም አልተደነገገላቸውም። ስለዚህም ከሌሎች የሐጅ ስርአቶች በተቃራኒ ውክልና መስጠት ተፈቀደላቸው። በሌሎቹ ስርአቶች ግን አንዴ ኢሕራም ካደረገ ሐጁ ነፍል (ትርፍ) ቢሆንም እንኳ በምትኩ የሚፈጽምለትን ሰው መወከል አይችልም። ምክንያቱም በሐጅ ወይም በዑምራ ኢሕራም ያደረገ ሰው ሁለቱም (ሐጁም ዑምራውም) ነፍል (ትርፍ) ቢሆኑም እንኳ ሁለቱንም ማሟላት ግዴታው ነውና፤ ይህም ከፍ ያለው አላህ እንዲህ በማለቱ ነው፦

﴿وَأَتِمُّوا الْحَجَّ وَالْعُمْرَةَ لِلَّهِ...﴾

{ሐጅንና ዑምራንም ለአላህ ሙሉ።…} [አል‐በቀራህ: 196] የጦዋፍና የሰዕይ ወቅት ግን እንደ መወርወሪያው ወቅት የሚያልፍ አይደለም።

ዐረፋ ላይ መቆምንና በሙዝደሊፋና ሚና ላይ ማደርን በተመለከተም ጊዜያቸው እንደሚያልፍ ጥርጥር የሌለው ቢሆንም አቅም የሌለው ሰው ከችግር ጋርም ቢሆን በእነዚህ ቦታዎች ላይ መገኘት ይችላል። ይህም ጀመራትን ከመወርወር ይለያል፤ ምክንያቱም ጀመራትን መወርወር ችግር ላለበት ሰው ውክልና የተፈቀደ መሆኑን ከደጋግ ቀደምቶች ተዘግቧልና። ጠጠር ከመወርወር ውጪ ግን ውክልና መስጠት አልተዘገበም።

አምልኮ በቁርአንና ሐዲሥ የተገደበ ነው። ማንም ይሁን አንድንም አምልኮ ያለ ማስረጃ መደንገግ አይፈቀድለትም። ይበልጥ ትክክለኛ በሆነው የዑለማዎች አቋም መሰረት አንድ ተወካይ በአንድ የቆመበት ቦታ ሆኖ ከሶስቱም ጀመራዎች ዘንድ በመጀመሪያ ለራሱ ከዚያም ለወከለው ሰው መወርወር ይፈቀድለታል። ለራሱ ሶስቱንም ጀምራዎች ወርውሮ ከጨረሰ በኋላ ተመልሶ ለወከለው ሰው መወርወር ግን ግዴታው አይሆንበትም፤ ይህን ግዴታ የሚያደርግ ማስረጃ ስለሌለና በውስጡም ችግርና መጣበብ ስላለበት ነው። አላህም እንዲህ ይላል፦

﴿...وَمَا جَعَلَ عَلَيْكُمْ فِي الدِّينِ مِنْ حَرَجٍ...﴾

{በናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም…} [አል'ሐጅ፡ 78] ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦

«يَسِّرُوا وَلَا تُعَسِّرُوا».

"አግራሩ አታክብዱ!"90 እንዲሁም ይህ ከአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባልደረቦች ለህፃናቶቻቸውና ከነሱ መካከል አቅም ለሌላቸው በወረወሩ ጊዜ (ተወካይ ለወካይ ሲል መገደዱ) ስላልተዘገበ ነው፤ ይህን አድርገውት ቢሆን ኖሮ ለመዘገብ ትልቅ ትኩረት ከሚሰጣቸው ነገሮች መካከል በመሆኑ በተዘገበ ነበርና። አላህም ይበልጥ ያውቃል።

አዲስ ክፍል:

ተመቱዕና ቂራን ፈፃሚ በሆኑት ላይ ደም ግዴታ ስለመሆኑ፤

ሓጅ አድራጊው ተመቱዕን ወይም ቂራንን የሚፈፅም ከሆነና የመስጂደል ሐረም ነዋሪ ካልሆነ መስዋእትነት ማረዱ ግዴታ ይሆንበታል። እርሱም፥ አንድ በግ፣ ወይም የግመል አንድ ሰባተኛ፣ ወይም የከብት አንድ ሰባተኛ ነው። ይህም ከሐላል የሆነ ገንዘብና ከመልካም ገቢ መሆን አለበት፤ ምክንያቱም አላህ መልካም ነው ከመልካም ውጪም አይቀበልምና።

አላህ ከገንዘቡ ለራሱ የሚሆነውንና በሰዎች እጅ ካለው ነገር የሚያብቃቃውን ነገር ያገራለት ሙስሊም የሆነ ሰው የሚለመኑት ሰዎች ንጉሶችም ሆኑ ሌሎች ቢሆኑም ስጦታም ሆነ ሌላ ነገር ከመለመን ሊጠበቅ ይገባዋል። ይህም በበርካታ ሐዲሶች ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - መለመንን በመውቀስና ነውሩንም በመግለጽ፤ የተወውንም በማወደስ የተናገሩት ሐዲሥ ስላለ ነው።

የተመቱዕና የቂራን ሐጅ ፈፃሚ ሀድይ ማቅረብ ካቃተው በሐጅ ወቅት ሶስት ቀናትን፤ ወደ ቤተሰቦቹ ሲመለስ ደግሞ ሰባት ቀናትን መጾሙ ግዴታ ይሆንበታል። ሶስቱን ቀናት በመጾም ረገድም ምርጫ አለው፤ ከፈለገ የእርድ ቀን ከመድረሱ በፊት ይጾማቸዋል፤ ከፈለገም በሶስቱ የአያመ ተሽሪቅ ቀናት ውስጥ ይጾማቸዋል። ይህም አላህ እንዲህ ስላለ ነው፦

﴿...فَمَنْ تَمَتَّعَ بِالْعُمْرَةِ إِلَى الْحَجِّ فَمَا اسْتَيْسَرَ مِنَ الْهَدْيِ فَمَنْ لَمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَاثَةِ أَيَّامٍ فِي الْحَجِّ وَسَبْعَةٍ إِذَا رَجَعْتُمْ تِلْكَ عَشَرَةٌ كَامِلَةٌ ذَلِكَ لِمَنْ لَمْ يَكُنْ أَهْلُهُ حَاضِرِي الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ...﴾

{እስከ ሐጅ በዑምራ የተጣቀመ ሰው ከመስዋእቱ የተገራውን (የቻለዉን) መሰዋት አለበት። ያላገኘም ሰው ሶስትን ቀናት በሐጅ (ወራት) ላይ ሰባትንም ቀናት ደግሞ በተመለሳችሁ ጊዜ መፆም አለበት። እነዚህ ሙሉ አስር (ቀናት) ናቸው። ይህም (ህግ) ቤተሰቦቹ ከቅዱሱ መስጊድ አቅራቢያ ላልሆኑ ነው።} [አልበቀራህ፡ 196] እስከ አንቀፁ መጨረሻ ድረስ ...

በሶሒሕ አል-ቡኻሪም ከእናታችን ዓኢሻና ኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦

«لَمْ يُرَخَّصْ فِي أَيَّامِ التَّشْرِيقِ أَنْ يُصَمْنَ إِلَّا لِمَنْ لَمْ يَجِدِ الهَدْيَ».

«በአያመ-ተሽሪቅ ቀናት እንዲፆሙ አልተፈቀደም፤ ሀድይ (የእርድ እንስሳ) ላላገኘ ሰው ቢሆን እንጂ።»91، ይህም ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በቀጥታ የተነገረን ያህል ብይን አለው። የተሻለው የዐረፋን ቀን ፆመኛ ሳይሆኑ ለማሳለፍ ሲባል የሶስቱን ቀናት ጾም ከዐረፋ ቀን አስቀድሞ መጾም ነው፤ ምክንያቱም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የዐረፋን ቀን ፆመኛ ሳይሆኑ ያሳለፉ ሲሆን በዐረፋ ላይ ሆኖ የዐረፋን ቀን መጾምን ከልክለዋልና። በተጨማሪም በዚህ ቀን አለመጾም ለዚክርና ለዱዓእ የበለጠ ያነቃቃል። የተጠቀሱትን ሶስት ቀናት በተከታታይም ሆነ በተበታተነ መልኩ መጾም ይፈቀዳል። እንዲሁም የሰባቱን ቀናት ጾም በተከታታይ መጾም ግዴታ አይደለም፤ ይልቁንም በአንድ ላይም ሆነ በተበታተነ መልኩ መጾም ይፈቀዳል። ምክንያቱም አላህም መልዕክተኛውም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲሁ በተከታታይ እንዲጾሙ መስፈርት አላደረገምና፤ የተሻለው የሰባቱን ቀናት ጾም ወደ ቤተሰቦቹ እስከሚመለስ ድረስ ማዘግየት ነው፤ ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏልና፦

﴿...وَسَبْعَةٍ إِذَا رَجَعْتُمْ...﴾

{ሰባትንም ቀናት ደግሞ በተመለሳችሁ ጊዜ…} [አልበቀራህ: 196]

ሀድይ ለማቅረብ አቅም ላጣ ሰው፤ ለራሱ የሚያርደውን ሀድይ ነገስታትንም ሆነ ሌሎችን ከመለመን ይልቅ መፆሙ ይበልጥለታል። በሌላ ሰው ስም ሐጅ የሚያደርግ ቢሆንም እንኳን ሳይለምንና ነፍሱም ሳትቋምጥ ሀድይንም ሆነ ሌላን ነገር ቢሰጡት ምንም ችግር የለውም፤ ይህም የሚሆነው ወካዮቹ ለሱ ከተሰጠው ገንዘብ ሀድይ እንዲገዛ መስፈርት ካላስቀመጡበት ነው። አንዳንድ ሰዎች መንግስትንም ሆነ ሌላን አካል በውሸት በሚጠቅሷቸው ሰዎች ስም ሀድይ መለመናቸው ግን፤ ሐራም መሆኑ ላይ ምንም ጥርጥር የለውም። ምክንያቱም በውሸት መብላት ነውና። አላህ እኛንም ሙስሊሞችንም ከዚህ ይጠብቀን።

 

አዲስ ክፍል:

ሐጅ የሚያደርጉ ሰዎችና ሌሎችም ላይ በመልካም ማዘዝ ግዴታ ስለመሆኑ፤

ሐጃጆችና ሌሎችም ላይ ካለባቸው ታላላቅ ግዴታዎች መካከል፤ በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል፣ እንዲሁም አላህ በቁርአኑና በመልእክተኛው ﷺ አንደበት እንዳዘዘው አምስቱን ሶላቶች በጀማዓ ጠብቆ መስገድ ይገኙበታል።

በመካና በሌሎችም የሚኖሩ ብዙ ሰዎች ቤቶቻቸው ውስጥ በመስገድ መስጂዶችን ከሶላት ባዶ ማድረጋቸው ሸሪዓን የሚፃረር ስህተት ነው። ስለሆነም ከዚህ ድርጊት መከልከልና ሰዎችም በመስጂዶች ውስጥ ሶላትን አዘውትረው እንዲጠብቁ ማዘዝ ይገባል። ይህም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለኢብኑ ኡሙ መክቱም - ረዲየላሁ ዐንሁ - ማየት የተሳነውና ቤቱም ከመስጂድ የራቀ በመሆኑ በቤቱ መስገድን በጠየቃቸው ጊዜ እንዲህ ሲሉ ለርሱ ከተናገሩት ቃል አንፃር ነው፦

«هَلْ تَسْمَعُ النِّدَاءَ بِالصَّلَاةِ؟ قَالَ: نَعَمْ، قَالَ: فَأَجِبْ».

{"የሶላቱን ጥሪ ትሰማለህን?" እርሱም "አዎን" አለ። "እንግዲያውስ ጥሪውን ተቀበል!" አሉት።}92 በሌላ ዘገባም:

«لَا أَجِدُ لَكَ رُخْصَةً».

«ለአንተ ምንም ፍቃድ አላገኘውልህም»93 ነቢዩ ﷺ እንዲህም ብለዋል፡

«لَقَدْ هَمَمْتُ أَنْ آمُرَ بِالصَّلَاةِ فَتُقَامَ، ثُمَّ آمُرَ رَجُلًا فَيُؤُمَّ النَّاسَ، ثُمَّ أَنْطَلِقَ إِلَى رِجَالٍ لَا يَشْهَدُونَ الصَّلَاةَ فَأُحَرِّقَ عَلَيْهِمْ بُيُوتَهُمْ بِالنَّارِ».

«በርግጥ ሶላት እንዲሰገድ አዝዤ፤ ሰዎችን እንዲያሰግድም አንድ ሰው ወክየ፤ ከዚያም ጀመዓ ሶላት ወደማይገኙ ወንዶች በመሄድ በነሱ ላይ ቤቶቻቸውን በእሳት ላቃጥል አስቤም ነበር።»94 በሱነን ኢብኑ ማጃህና በሌሎችም በሐሰን ሰነድ ከኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተዘገበው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፡

«مَنْ سَمِعَ النِّدَاءَ فَلَمْ يَأْتِ فَلَا صَلَاةَ لَهُ إِلَّا مِنْ عُذْرٍ».

«ያለበቂ ምክንያት የአዛን ጥሪን ሰምቶ ያልመጣ ሰው ሰላት የለውም።»95 በሶሒሕ ሙስሊምም ከኢብኑ መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡ «ነገ ሙስሊም ሆኖ አላህን መገናኘት የሚያስደስተው ሰው የእነዚህን ሶላቶች ጥሪ ለመቀበል ይጠባበቅ። አላህ ለነብያችሁ የቅናቻ መንገዶችን ደንግጓልና፤ እነርሱም ከቅናቻ መንገዶች ናቸው። ይህ ከመስጂድ የሚቀረው ሰው በቤቱ እንደሚሰግደው እናንተም በቤቶቻችሁ ብትሰግዱ ኖሮ የነብያችሁን ሱና በተዋችሁ ነበር። የነብያችሁን ሱና ብትተው ኖሮም በጠፋችሁ ነበር። ንፅህናውን ፈፅሞና አሳምሮ ከዚያም ከእነዚህ መስጂዶች ወደ አንዱ ያቀና ሰው፤ በሚራመደው እያንዳንዱ እርምጃ አላህ መልካም ስራ ይፅፍለታል፣ በርሷም ደረጃ ከፍ ይደረግለታል፣ በርሷም ኃጢኣት ይራገፍለታል። በእርግጥም አይተናቸዋል፤ ከርሷ ንፍቅናው የታወቀ ሙናፊቅ በስተቀር ማንም አይቀርም ነበር። በእርግጥም አንድ ሰው በሁለት ሰዎች መካከል ተደግፎ ይመጣና በሰልፍ ውስጥ እንዲቆም ይደረግ ነበር።»96

በሐጃጆችም ሆኑ በሌሎች ላይ የሁሉን ቻይ አላህ ክልከላዎችን መራቅና ከመፈፀማቸውም መጠንቀቅ ግዴታ ነው፤ እንደ ዝሙት፣ ግብረ-ሰዶም፣ ስርቆት፣ ወለድ መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ በግብይት ላይ ማታለል፣ አደራን መብላት፣ አስካሪ መጠጦችን መጠጣት፣ ጢስ (ሲጋራ) ማጨስ፣ ልብስን (ከቁርጭምጭሚት በታች) ማስረዘም፣ ኩራት፣ ምቀኝነት፣ ይዩልኝ፣ ሀሜት፣ ነገር ማሳበቅ፣ በሙስሊሞች ላይ መሳለቅ፣ እንደ የሙዚቃ ሲዲዎች፣ ዋሽንት፣ ከበሮ፣ ጊታር እና መሰል የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጠቀም፤ ዘፈኖችን እና ከሬድዮና ከመሳሰሉት የሚተላለፉ የሙዚቃ ዜማዎችን ማዳመጥ፣ ዳይ እና ዳማ መጫወት፣ ቁማር መጫወት፣ የሰው ልጆችንና የሌሎችንም ነፍስ ያላቸውን ነገሮች ምስል መስራትና በዚህም መደሰት። እነዚህ ሁሉ አላህ በየትኛውም ጊዜና ቦታ በባሮቹ ላይ ክልክል ካደረጋቸው ፀያፍ ነገሮች መካከል ናቸው። ስለሆነም ሐጃጆችና የተከበረው የአላህ ቤት ነዋሪዎች ከሌሎች በበለጠ ሊጠነቀቋቸው ይገባል፤ ምክንያቱም በዚህች በተከበረች ሀገር የሚሰሩ ወንጀሎች ሀጢያታቸው የከፋና ቅጣታቸውም የገዘፈ ነውና።

የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏልና:

﴿...وَمَنْ يُرِدْ فِيهِ بِإِلْحَادٍ بِظُلْمٍ نُّذِقْهُ مِنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ﴾

{በእርሱም ውስጥ ከትክክለኛ መንገድ በመዘንበል በዳይ ሆኖ (ማንኛውንም ነገር) የሚያስብ ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን።} [አል‐ሐጅ: 25] አላህ በሐረም ውስጥ በደል ለመፈፀም ያሰበን ሰው እንኳ ካስፈራራ፣ የፈፀመው ሰው ቅጣት እንዴት ሊሆን ነው?! ቅጣቱ ያለጥርጥር እጅግ የከበደና በጣም ብርቱ ነው። በመሆኑም ከዚህና ከሌሎችም ወንጀሎች ሁሉ መጠንቀቅ የግድ ነው።

ሐጃጆች አላህ በእነርሱ ላይ ከከለከላቸው ከእነዚህና ከሌሎች ወንጀሎች በመጠንቀቅ ካልሆነ በቀር የሐጃቸው ቅቡልነትና የወንጀላቸው ስርየት አይገኝም፤ ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሐዲስ እንዲህ ብለዋል፡-

«مَنْ حَجَّ فَلَمْ يَرْفُثْ وَلَمْ يَفْسُقْ رَجَعَ كَيَوْمِ وَلَدَتْهُ أُمُّهُ».

«ሳይባልግ (ከሚስቱ ጋር ግንኙነት ሳይፈጽም) እና ሳያምፅ ሐጅ ያደረገ እናቱ እንደወለደችው ቀን ከወንጀሉ ፀድቶ ይመለሳል።»97

ከእነዚህ መጥፎ ድርጊቶች ይበልጥ የከፋና የከበደው፤ አላህ ዘንድ እንዲማፀኑላቸው፣ ወይም የታመመን እንዲፈውሱ፣ ወይም የጠፋን እንዲመልሱላቸው እና የመሳሰሉትን ተስፋ በማድረግ ሙታንን መለመን፣ እርዳታ ከነርሱ መፈለግ፣ ለእነርሱም ስለት መግባትና እርድ ማቅረብ ነው።

ይህ አላህ እርም ያደረገው ትልቁ ሺርክ ነው። ይህም የጃሂሊያ ሙሽሪኮች ሀይማኖት ነው። አላህም ይህንን ለማውገዝና ለመከልከል መልክተኞችን ልኳል መፅሀፍትንም አውርዷል።

እናም ሐጅ አድራጊም ሆነ ሌላ እያንዳንዱ ግለሰብ ይህን ተግባር መጠንቀቅ፣ ከዚህ በፊት የፈፀመው መሰል ተግባር ካለ ወደ አላህ መመለስና፣ ከሱ ተውበት ካደረገ በኋላም አዲስ ሐጅ መጀመር ግዴታ ይሆንበታል። ትላቁ ሽርክ ስራዎችን በሙሉ ያበላሻልና። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል:

﴿...وَلَوْ أَشْرَكُوا لَحَبِطَ عَنْهُمْ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ﴾

{በአላህ ባጋሩም ኖሮ ይሰሩት የነበሩት መልካም ተግባር ሁሉ ከእነርሱ በታበሰባቸው ነበር።} [አልአንዓም፡ 88]

ከትንሹ ሺርክ አይነቶችም መካከል፦ ከአላህ ውጪ በሆነ መማል ነው፤ ለምሳሌም በነብዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)፣ በከዕባ፣ በአደራና በመሳሰሉት መማል ይጠቀሳል።

ከእነዚህም መካከል፦ ይዩልኝና ይስሙልኝ፣ "አላህና አንተ የሻችሁት ሆነ።"፣ "በአላህና በአንተ ባይሆን ኖሮ"፣ "ይህ ከአላህና ከአንተ ነው።" እና የመሳሰሉ ንግግሮች ይገኙበታል።

ከእነዚህ ሺርካዊ ውግዝ ተግባራት መጠንቀቅና ለመተውም መመካከር ግዴታ ነው፤ ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸው ተረጋግጧልና፦

«مَنْ حَلَفَ بِغَيْرِ اللهِ فَقَدْ كَفَرَ أَوْ أَشْرَكَ».

{"ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ በእርግጥም ክዷል ወይም አጋርቷል።"}98 አሕመድ፣ አቡ ዳውድ እና ቲርሚዚይ ሶሒሕ በሆነ ዘገባ ዘግበውታል።

ሶሒሕ በሆነ ሐዲሥ ከዑመር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው - እንደተዘገበው፤ የአላህ መልዕክተኛ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦

«مَنْ كَانَ حَالِفًا فَلْيَحْلِفْ بِاللهِ أَوْ لِيَصْمُتْ».

«የሚምል ሰው በአሏህ ይማል ወይም ዝም ይበል።»99. ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህም ብለዋል፦

«مَنْ حَلَفَ بِالأَمَانَةِ فَلَيْسَ مِنَّا».

"(በአማና) በአደራ የማለ ሰው ከኛ አይደለም"100 አቡ ዳውድ ዘግበውታል።

ነቢዩ ﷺ እንዲህም ብለዋል፦

«أَخْوَفُ مَا أَخَافُ عَلَيْكُمُ الشِّرْكَ الأَصْغَرَ، فَسُئِلَ عَنْهُ فَقَالَ: الرِّيَاءُ».

«"በናንተ ላይ ከምፈራቸው ነገሮች መካከል እጅግ አስፈሪው ነገር ትንሹ ሺርክ ነው።" አሉ። ስለርሱም ተጠየቁ። እርሳቸውም "ይዩልኝ ነው።" አሉ።»101 ነቢዩ ﷺ እንዲህም ብለዋል፡

«لَا تَقُولُوا: مَا شَاءَ اللهُ وَشَاءَ فُلَانٌ، وَلَكِنْ قُولُوا مَا شَاءَ اللهُ ثُمَّ شَاءَ فُلَانٌ».

«"አላህ እና እከሌ ከፈለጉ ..." አትበሉ። ይልቁንም "አላህ ከፈለገ ከዚያም እከሌ ከፈለገ... " በሉ።»102 ነሳኢይ ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደዘገቡት፦ አንድ ሰውዬ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የአላህና የእርሶ መሻት ሆነ።" አላቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦

«أَجَعَلْتَنِي لِلَّهِ نِدًّا، بَلْ مَا شَاءَ اللهُ وَحْدَهُ».

"ለአላህ ቢጤ አደረከኝን? ይልቁንም አላህ ብቻውን የሻው ሆነ።"103

እነዚህ ሐዲሦች ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተውሒድን ዳር ድንበር መጠበቃቸውን፣ ህዝባቸውንም ከትልቁም ከትንሹም ሽርክ ማስጠንቀቃቸውን፤ እንዲሁም ለኡመታቸው ኢማን ደህንነትና የአላህን ቅጣትና ቁጣ ከሚያደርሱባቸው ሰበቦች ለማዳን የነበራቸውን ጥረት ያመለክታሉ። ለዚህም አላህ በላጩን ምንዳ ይመንዳቸው። መልዕክቱን አድርሰዋል፤ አስጠንቅቀዋልም፤ ለአላህና ለባሮቹም ምክር ለግሰዋል። እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ዘውታሪ የሆነ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን።

በሐጃጆችም ሆኑ በአላህ የተከበረች አገር እና በክቡር መልዕክተኛው -በእርሳቸው ላይ የአላህ ሰላትና ሰላም ይስፈን- አገር ነዋሪ በሆኑ የእውቀት ባለቤቶች ላይ አላህ ለሰዎች የደነገጋቸውን ህግጋት ማስተማርና እርም ያደረገባቸውን የሽርክና የወንጀል አይነቶች ማስጠንቀቅ ግዴታ ነው። ይህንንም ከማስረጃዎች ጋር በስፋትና ግልጽ በሆነ መልኩ ሊያብራሩ ይገባል፤ በዚህም ሰዎችን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ሊያወጡና አላህ ግዴታ ያደረገባቸውን የማድረስና የማብራራት ኃላፊነት ሊወጡ ዘንድ ያስችላቸዋል። ጥራት የተገባው አላህ እንዲህ ብሏል፦

﴿وَإِذْ أَخَذَ اللَّهُ مِيثَاقَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ لَتُبَيِّنُنَّهُ لِلنَّاسِ وَلَا تَكْتُمُونَهُ...﴾

{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የነዚያን መጽሐፉን የተሰጡትን ለሰዎች በእርግጥ «ልታብራሩት እንጂ ላትደብቁት» በማለት የያዘባቸውን ቃል ኪዳን አስታውስ።} [አሊ-ዒምራን 187]

ከዚህም የተፈለገው፥ የዚህ ኡማ ዑለማዎች፣ የቅርቢቱን ዓለም ከመጨረሻይቱ አስበልጠው እውነትን በመደበቅ ረገድ ከመጽሐፉ ባለቤቶች የሆኑትን የበዳዮችን መንገድ ከመከተል እንዲጠነቀቁ ነው። ክብሩ የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦

﴿إِنَّ الَّذِينَ يَكْتُمُونَ مَا أَنْزَلْنَا مِنَ الْبَيِّنَاتِ وَالْهُدَى مِنْ بَعْدِ مَا بَيَّنَّاهُ لِلنَّاسِ فِي الْكِتَابِ أُولَئِكَ يَلْعَنُهُمُ اللَّهُ وَيَلْعَنُهُمُ اللَّاعِنُونَ 159 إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ 160﴾

{እነዚያ ከአንቀጾችና ከቅን መመሪያ ያወረድነውን ለሰዎች በመጽሐፉ ከገለጽነው በኋላ የሚደብቁ፤ እነዚያ አላህ ይረግማቸዋል። ረጋሚዎችም ሁሉ ይረግሟቸዋል።

እነዚያ (ከመደበቅ) የተጸጸቱና፤ (ያበላሹትን) ያስተካከሉና (የደበቁትንም) የገለጹ ሲቀሩ። የእነርሱን ጸጸትንማ እቀበላለሁ። እኔም ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነኝ።} [አል-በቀራህ 159-160] ጥራት ወደተገባው አላህ ጥሪ ማድረግና ሰዎች ወደ ተፈጠሩለት ነገር መጠቆም ከበላጭ ዒባዳዎችና ከዋነኛ ግዴታዎች መካከል መሆኑን፣ እስከ የውመል ቂያማ ድረስ ያለ የመልእክተኞችና የተከታዮቻቸው መንገድ መሆኑን የቁርኣን አንቀፆችና የነብዩ ሓዲሶች ጠቁመዋል። እንዲሁም ጥራት የተገባው አላህ እንዲህ ብሏል፦

﴿وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِمَّنْ دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ 33﴾

{ወደ አላህ ከጠራንና መልካምንም ከሰራ፤ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለ ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?} [ፉሲለት፡ 33] የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦

﴿قُلْ هَذِهِ سَبِيلِي أَدْعُو إِلَى اللَّهِ عَلَى بَصِيرَةٍ أَنَا وَمَنِ اتَّبَعَنِي وَسُبْحَانَ اللَّهِ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ 108﴾

{«ይህቺ መንገዴ ናት። ወደ አላህ እጠራለሁ። እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን። ጥራትም ለአላህ ብቻ ይገባው። እኔም ከአጋሪዎች አይደለሁም።» በል።} [ዩሱፍ፡ 108]

ነቢዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፡

«مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ».

«ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው ለእርሱ የሰሪው አምሳያ አጅር አለው»104

«لَأَنْ يَهْدِيَ اللهُ بِكَ رَجُلًا وَاحِدًا خَيْرٌ لَكَ مِنْ حُمْرِ النَّعَمِ».

«አላህ አንተን ሰበብ አድርጎህ አንድን ሰው ቢመራልህ ላንተ ከቀያይ ግመሎች የተሻለ ነው።»105 ይህን መሰል መልዕክት ያዘሉ የቁርኣን አንቀጾችና ሐዲሦች በርካታ ናቸው።

የእውቀትና የኢማን ባለቤቶች በተለይም ዝንባሌዎች በነገሱበት፣ አፍራሽ መርሆዎችና አሳሳች መፈክሮች በተስፋፉበት፣ የቅኑ መንገድ ዱዓቶች በመነመኑበትና የኢልሓድና የጋጠወጥ ዱዓቶች በበዙበት በዚህ ዘመን፤ ወደ አላህ (ሱብሃነሁ) ጥሪ በማድረግ፣ ባሮችን ወደ መዳኛ መንገዶች በመምራትና ከጥፋት ሰበቦች በማስጠንቀቅ ረገድ ጥረታቸውን እጥፍ ድርብ ማድረግ ይገባቸዋል። አላህ ነው እርዳታ የሚለመነው፤ በላጩና ታላቅ በሆነው በአላህ ቢሆን እንጂ ብልሃትም ሆነ ሀይል የለም።

አዲስ ክፍል:

አምልኮዎችን መሰነቅ እንደሚወደድ፤

ሐጅ አድራጊዎች በመካ በሚቆዩበት ጊዜ የአላህን ስም ማውሳት (ዚክር)፣ እርሱን መታዘዝና መልካም ስራን ማዘውተር፤ እንዲሁም ሶላትንና በበይት (በከዕባ) ጦዋፍ ማድረግን ማብዛት የተወደደ ተግባር ነው። ምክንያቱም በሐረም ውስጥ መልካም ስራዎች (ምንዳቸው) ይነባበራሉ፤ መጥፎ ስራዎችም በውስጡ እጅግ ታላቅና ከባድ ናቸውና። እንዲሁም በአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ሶላትና ሰላምን ማብዛትም ይወደድላቸዋል።

ሐጅ አድራጊዎች ከመካ መውጣት ሲፈልጉ፣ የመጨረሻ ተግባራቸው በቤቱ እንዲሆን የመሰናበቻ ጦዋፍን ማድረግ ግዴታ ይሆንባቸዋል። ነገር ግን የወር አበባና የወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች የመሰናበቻ ጦዋፍ የለባቸውም፤ ምክንያቱም ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ (አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው) እንዲህ ብለዋልና፦

«أُمِرَ النَّاسُ أَنْ يَكُونَ آخِرُ عَهْدِهِمْ بِالبَيْتِ، إِلَّا أَنَّهُ خُفِّفَ عَنِ المَرْأَةِ الحَائِضِ».

«ሰዎች የመጨረሻ ተግባራቸው በቤቱ (በካዕባ) ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግ እንዲሆን ታዘዙ፤ በወር አበባ ላይ ላለች ሴት ግን አግራርተዋል።»106

ቤቱን ተሰናብቶ ከመስጂድ መውጣትን የፈለገ ጊዜ እስከሚወጣ ድረስ ፊቱን ወደፊት አድርጎ ይሄዳል። ወደ ኋላ መራመድም አይጠበቅበትም፤ ምክንያቱም ይህ ከነብዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲሁም ከባልደረቦቻቸውም አልተገኘምና ነው፤ ይልቁንም ከጊዜ በኋላ የተፈጠረ አዲስ ነገር (ቢድዓ) ነው፤ ነብዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦

«مَنْ عَمِلَ عَمَلًا لَيْسَ عَلَيْهِ أَمْرُنَا فَهُوَ رَدٌّ».

"በርሱ ላይ የኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ነገር የሰራ ሰዉ ስራው ወደርሱ ተመላሽ ነዉ።"107 ነቢዩ ﷺ እንዲህም ብለዋል፡

إِيَّاكُمْ وَمُحْدَثَاتِ الأُمُورِ، فَإِنَّ كُلَّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ، وَكُلَّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ».

«አዲስ መጤ ጉዳዮችን ተጠንቀቁ፤ አዲስ መጤ በሙሉ ፈጠራ ነው፤ ፈጠራም ሁሉ ጥመት ነው»108

አላህን በዲኑ ላይ ፅናትን እንዲሰጠን፣ ዲንን ከሚቃረን ነገርም እንዲጠብቀን እንለምነዋለን። እነሆ እርሱ ቸርና ለጋስ ነውና።

አዲስ ክፍል:

የዚያራ ህግጋትና ስነ-ስርዓቶቹ፤

ከሐጅ በፊትም ይሁን በኋላ የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈን) መስጂድ መዘየር ሱና ነው፤ በቡኻሪ እና ሙስሊም ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተረጋገጠው የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦

«صَلَاةٌ فِي مَسْجِدِي هَذَا خَيْرٌ مِنْ أَلْفِ صَلَاةٍ فِيمَا سِوَاهُ إِلَّا المَسْجِدَ الحَرَامَ».

"በዚህ መስጂዴ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ ከሚሰገዱ አንድ ሺህ ሶላቶች የተሻለ ነው። የተከበረው መስጊድ (መስጂደል ሐራም) ሲቀር።"109 ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

«صَلَاةٌ فِي مَسْجِدِي هَذَا أَفْضَلُ مِنْ أَلْفِ صَلَاةٍ فِيمَا سِوَاهُ إِلَّا المَسْجِدَ الحَرَامَ».

«በዚህ መስጂዴ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ ከሚሰገድ አንድ ሺህ ሶላት ይበልጣል። ከተከበረው መስጊድ (መስጂደል ሐራም) ሲቀር።»110 ሙስሊም ዘግበውታል። ከዓብደላህ ቢን ዙበይር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦

«صَلَاةٌ فِي مَسْجِدِي هَذَا أَفْضَلُ مِنْ أَلْفِ صَلَاةٍ فِيمَا سِوَاهُ إِلَّا المَسْجِدَ الحَرَامَ، وَصَلَاةٌ فِي المَسْجِدِ الحَرَامِ أَفْضَلُ مِنْ مِائَةِ صَلَاةٍ فِي مَسْجِدِي هَذَا».

«በዚህ መስጂዴ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ ከሚሰገዱ አንድ ሺህ ሶላቶች ይበልጣል፤ የተከበረው መስጊድ (መስጂደል ሐራም) ሲቀር፤ እንዲሁም በተከበረው መስጊድ የሚሰገድ ሶላት በዚህ መስጂዴ ከሚሰገድ ሶላት በመቶ ሶላት ይበልጣል።»111 አሕመድ፤ ኢብኑ ኹዘይማህና ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።

ከጃቢር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡

«صَلَاةٌ فِي مَسْجِدِي هَذَا أَفْضَلُ مِنْ أَلْفِ صَلَاةٍ فِيمَا سِوَاهُ، إِلَّا المَسْجِدَ الحَرَامَ، وَصَلَاةٌ فِي المَسْجِدِ الحَرَامِ أَفْضَلُ مِنْ مِائَةِ أَلْفِ صَلَاةٍ فِيمَا سِوَاهُ».

«በዚህ መስጂዴ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ ከሚሰገድ ሶላት በአንድ ሺህ በላጭ ነው። የተከበረው መስጊድ (መስጂደል ሐራም) ሲቀር። በተከበረው መስጊድ (መስጂደል ሐራም) የሚሰገድ ሶላት ደግሞ ከርሱ ውጪ ከሚሰገድ ሶላት በመቶ ሺህ በላጭ ነው።»112 አሕመድ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል። ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው ሐዲሶችም በርካታ ናቸው።

ዘያሪው መስጂድ ሲደርስ ሲገባ ቀኝ እግሩን ማስቀደሙ ይወደድለታል፤ እንዲህም ይላል፦ "ቢስሚልላህ ወስሰላቱ ወስሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ አዑዙ ቢልላሂል ዐዚም ወቢወጅሂሂል ከሪም ወሱልጣኒሂል ቀዲም ሚነ-ሽ-ሸይጧኒ-ር-ረጂም፤ አልላሁምመ ኢፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲክ።"

ወደ ሌሎች መስጂዶች ሲገባም ይህንኑ ይላል፤ ወደ እርሳቸው (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂድ ለመግባት ግን የተለየ ዚክር የለውም።

ከዚያም ሁለት ረከዓ ይሰግዳል፤ በውስጣቸውም ከዱንያና ከአኺራ መልካም ነገር የፈለገውን አላህን ይለምናል። እነዚህን ሁለት ረከዓዎችም በተከበረችው ረውዷ ውስጥ ከሰገዳቸው ደግሞ ይበልጥ የተሻለ ነው። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ስላሉ ነው:

«مَا بَيْنَ بَيْتِي وَمِنْبَرِي رَوْضَةٌ مِنْ رِيَاضِ الجَنَّةِ».

«በቤቴና በሚንበሬ መካከል ከጀነት ጨፌዎች መካከል የሆነ ጨፌ አለ።»113 ከዚያም ከሶላት በኋላ የነቢዩን ﷺ ቀብርና የሁለቱን ባልደረቦቻቸውን የአቡበክርን እና የዑመርን - ረዲየሏሁ ዐንሁማ - ቀብሮች ይጎበኛል። ከዚያም በነቢዩ ﷺ ቀብር ፊት ለፊት በስርዓትና ድምፁን ዝቅ በማድረግ ይቆምና እንዲህ በማለት በሳቸው ﷺ ላይ ሰላምታን ያቀርባል፡ “አስሰላሙ ዓለይከ ያ ረሱለላህ ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ”፤ በሱነን አቢ ዳውድ ሐሰን በሆነ ሰነድ ከአቡ ሁረይራ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡

«مَا مِنْ أَحَدٍ يُسَلِّمُ عَلَيَّ إِلَّا رَدَّ اللهُ عَلَيَّ رُوحِي حَتَّى أَرُدَّ عَلَيْهِ السَّلَامَ».

«አንድም በኔ ላይ ሰላምታን የሚያቀርብ የለም ለርሱ ሰላምታን እስክመልስ ድረስ አላህ ለኔ ነፍሴን የሚመልስልኝ ቢሆን እንጂ።»114 ጎብኝውም በሰላምታው ወቅት እንዲህ ቢል ችግር የለውም፦ «አስ-ሰላሙ ዐለይከ ያ ነቢየሏህ፣ አስ-ሰላሙ ዐለይከ ያ ኺረተሏሂ ሚን ኸልቂህ፣ አስ-ሰላሙ ዐለይከ ያ ሰይደል-ሙርሰሊን ወኢማመል-ሙተቂን፣ አሽሃዱ አንነከ ቀድ በለጝተር-ሪሳላህ ወአደይተል-አማናህ ወነሰሕተል-ኡመተ ወጃሃድተ ፊላሂ ሐቀ ጂሃዲህ»፤ ምክንያቱም ይህ ሁሉ ከእርሳቸው ﷺ መገለጫዎች ነውና። በሸሪዓም በእርሳቸው ላይ ሶላትንና ሰላምን ማጣመር እንደተደነገገውና የላቀውን የአላህ ቃልም ስራ ላይ ለማዋል በእርሳቸው ﷺ ላይ ሶላት ያውርድ። ዱዓም ያድርግላቸው።

﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا 56﴾

{አላህና መላዕክቱ በነብዩ (ሙሐመድ) ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ። እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ። የማክበርን ሰላምታንም ሰላም በሉ።} [አል-አሕዛብ: 56] ቀጥሎም በአቡ በከርና ዑመር (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) ላይ ሰላምታን ያቀርባል፤ ዱዓም ያደርግላቸዋል፤ የአላህንም ውዴታ ይለምንላቸዋል።

ኢብኑ ዑመር (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) በረሱል ﷺ እና በሁለቱ ባልደረቦቻቸው ላይ ሰላምታን ሲያቀርብ፣ ብዙ ጊዜ ከዚህ ንግግሩ በላይ አይጨምርም ነበር፦ “አስ-ሰላሙ ዐለይከ ያ ረሱለልላህ፣ አስ-ሰላሙ ዐለይከ ያ አባ በክር፣ አስ-ሰላሙ ዐለይከ ያ አበታህ።”

“ትርጉሙም: የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የአላህ ሰላም በእርሶ ላይ ይስፈን፤ አቡበክር ሆይ! የአላህ ሰላም በእርሶ ላይ ይስፈን፤ አባቴ ሆይ! የአላህ ሰላም በእርሶ ላይ ይስፈን።” ከዚያም ይሄዳል።

ይህ ዝያራ ለወንዶች ብቻ የተደነገገ ሲሆን ሴቶች ግን የትኛውንም ቀብር መዘየር አይፈቀድላቸውም፤ ይህም ከነቢዩ ﷺ እንደተረጋገጠው እርሳቸው

«لَعَنَ زُوَّارَاتِ القُبُورِ مِنَ النِّسَاءِ وَالمُتَّخِذِينَ عَلَيْهَا المَسَاجِدَ وَالسُّرُجَ».

"ቀብርን አዘውትረው የሚጎበኙ ሴቶችንና በመቃብር ላይ መስገጃዎችንና መብራቶችን የሚይዙትን ረግመዋል።"115

በመልዕክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) መስጂድ ውስጥ ሶላት ለመስገድ፣ ዱዓ ለማድረግ እንዲሁም በሌሎች መስጂዶች ውስጥ የሚፈቀዱ መሰል ተግባራትን ለመፈፀም አስቦ ወደ መዲና መጓዝ ግን፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ቀደም ሲል ባሉት ሐዲሶች መሰረት ለሁሉም የተፈቀደ ነው።

ለዘያሪው በአላህ መልዕክተኛ መስጂድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) አምስቱን ወቅት ሶላቶች መስገዱና በውስጡም ዚክርን፣ ዱዓንና የሱና ሶላቶችን ማብዛቱ ሱና ነው። ይህም በውስጡ ያለውን ታላቅ ምንዳ ለመሸመት ነው።

በተከበረችው ረውዷ ውስጥ ሱና ሶላቶችን ማብዛት ይወደዳል፤ ይህም ስለ ክብሯ በመጣው ትክክለኛ ሐዲስ ላይ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ስላሉ ነው፦

«مَا بَيْنَ بَيْتِي وَمِنْبَرِي رَوْضَةٌ مِنْ رِيَاضِ الجَنَّةِ».

"በቤቴና በሚንበሬ መካከል ከጀነት ጨፌዎች መካከል የሆነ ጨፌ አለ።"116

ፈርድ ሶላትን በተመለከተ ዘያሪውም ሆነ ሌላ ሰው መስጂዱ በቂብላ በኩል በተጨመረው የማስፋፊያ ክፍል በኩል ቢሆንም እንኳ፣ በቻለው አቅም ወደ ሶላቱ ቀደም ብሎ በመሄድ የመጀመሪያውን ሶፍ ሊይዝ ይገባዋል። ይህም የመጀመሪያ ሶፍን አስመልክቶ ከነቢዩ ﷺ በትክክለኛ ሐዲሶች ጠንካራ ማነሳሳት ስለተዘገበ ነው። ለምሳሌም ተከታዩ የርሳቸው ﷺ ንግግር:

«لَوْ يَعْلَمُ النَّاسُ مَا فِي النِّدَاءِ وَالصَّفِّ الأَوَّلِ ثُمَّ لَمْ يَجِدُوا إِلَّا أَنْ يَسْتَهِمُوا عَلَيْهِ لَاسْتَهَمُوا».

«ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ ያለውን ምንዳ ቢያውቁና እርሱንም እጣ ካልተጣጣሉ በቀር የማያገኙት ቢሆኑ ኖሮ እጣ ይጣጣሉበት ነበር።»117 ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፣ በሌላ ምሳሌ ነቢዩ ﷺ ለሶሐቦቻቸው እንዲህ ብለዋል:

«تَقَدَّمُوا فَأْتَمُّوا بِي وَلْيَأْتَمَّ بِكُمْ مَنْ بَعْدَكُمْ، وَلَا يَزَالُ الرَّجُلُ يَتَأَخَّرُ عَنِ الصَّلَاةِ حَتَّى يُؤَخِّرَهُ اللهُ».

«ቅደሙና በእኔ ተከተሉ፤ ከእናንተ በኋላ ያሉትም በእናንተ ይከተሉ። ሰው ከሶላት ወደ ኋላ ከመቅረት አይወገድም በመጨረሻም አላህ ወደ ኋላ የሚያስቀረው ቢሆን እንጂ ።»118 ሙስሊም ዘግበውታል።

አቡ ዳውድም ከዓኢሻ አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና በሐሰን ሰነድ እንደዘገቡት ነቢዩ ‐የአላህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና‐ እንዲህ ብለዋል:

«لَا يَزَالُ الرَّجُلُ يَتَأَخَّرُ عَنِ الصَّفِّ المُقَدَّمِ حَتَّى يُؤَخِّرَهُ اللهُ فِي النَّارِ».

«ሰውዬው ከመጀመሪያው ሶፍ ወደ ኋላ ከመቅረት አይወገድም፤ አላህ ወደ ኋላ እሳት ውስጥ የሚያስቀረው ቢሆን እንጂ።»119 ከእርሳቸውም ﷺ ለባልደረቦቻቸው እንዲህ እንዳሉ ተረጋግጧል፦

«أَلَا تَصُفُّونَ كَمَا تَصُفُّ المَلَائِكَةُ عِنْدَ رَبِّهَا؟ قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، وَكَيْفَ تَصُفُّ المَلَائِكَةُ عِنْدَ رَبِّهَا؟ قَالَ: يُتِمُّونَ الصُّفُوفَ الأُوَلَ، وَيَتَرَاصُّونَ فِي الصَّفِّ».

« (የአላህ መልዕክተኛ) "መላእክት በጌታቸው ዘንድ እንደሚሰለፉት አትሰለፉምን?" (ሲሉ ሱሓቦችም እንዲህ) አሉ፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! መላእክት በጌታቸው ዘንድ እንዴት ነው የሚሰለፉት?" እርሳቸውም አሉ፦ "የፊተኞቹን ሰልፎች ይሞላሉ፤ በሰልፉም ይጠጋጋሉ።"»120 ሙስሊም ዘግበውታል።

በዚህ ዙሪያ የመጡ ሐዲሶች በርካታ ናቸው። እነሱም የመስጂድ ግንባታ ከመስፋፋቱ በፊትም ሆነ በኋላ የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂድና ሌሎችንም መስጂዶች ያካትታሉ። ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በትክክል እንደተዘገበው ባልደረቦቻቸውን በሰልፎቹ ቀኝ በኩል እንዲቆሙ ያነሳሱ ነበር። በመጀመሪያው መስጂዳቸው የሰልፉ ቀኝ ክፍል ከረውዷ ውጪ እንደነበርም ይታወቃል። ከዚህም የምንረዳው (ግዴታ ሶላቶች ላይ) የመጀመሪያ ሰልፎችንና የሰልፎችን ቀኝ ክፍል መያዝ ለተከበረችው ረውዷ ከሚሰጠው ትኩረት እንደሚቀድምና እነዚህን ሁለት ነገሮች መጠበቅም በረውዷ ውስጥ ከመስገድ የበለጠ ተመራጭ መሆኑን ነው። ይህ ጉዳይ በዚህ ርዕስ ስር የመጡ ሐዲሶችን ላስተነተነ ሰው በጣም ግልጽ ነው። አላህም ለበጎ ነገር አጋዥ ነው።

ለአንድም ሰው ክፍሉን መዳበስ ወይም መሳም ወይም በዙሪያው ጦዋፍ ማድረግ አይፈቀድለትም፤ ይህ ከቀደምት ደጋግ ሰለፎች አልተገኘምና። እንደውም የተወገዘ ቢድዓ ነው።

ለአንድም ሰው ረሱልን (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጉዳይ እንዲፈፅሙለት፣ ወይም ከጭንቀት እንዲገላግሉት፣ ወይም የታመመን እንዲፈውሱለት፣ ወይም የመሳሰሉትን ከሳቸው መጠየቅ አይፈቀድለትም። ይህ ሁሉ ከአላህ ሱብሓነሁ ብቻ ነው እንጂ ከሌላ ከማንም አይከጀልምና። ሙታንን መማፀን በአላህ ላይ ማጋራትና (ሽርክ) ከርሱ ውጪ ያለን ማምለክ ነው። የእስልምና ሃይማኖት ደሞ በሁለት መሰረቶች ላይ የተገነባ ነው፦

አንደኛው፦ ከአላህ በስተቀር ሌላ ላይመለክ ነው።

ሁለተኛው: መልዕክተኛው ﷺ በደነገጉት ካልሆነ በቀር አላህን አለማምለክ ነው።

ይህም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ ሌላ አምላክ በፍፁም እንደሌለ እና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን የመመስከር ፍሬ ሃሳብ ነው።

እንደዚሁም ለአንድም ሰው ከረሱል (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ምልጃን መጠየቅ አይፈቀድለትም፤ ምክንያቱም ምልጃ የላቀው የአላህ በመሆኗ ከእርሱ በቀር አትከጀልምና። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦

﴿قُلْ لِلَّهِ الشَّفَاعَةُ جَمِيعًا...﴾

«ምልጃ ሁሉም የአላህ ብቻ ነው... በል» [አዝ_ዙመር፡ 44] ይልቁንም: «አላህ ሆይ! ነብይህንም አማላጅ አድርግልኝ፤ አሏህ ሆይ! መላኢካዎችህን አማላጅ አድርግልኝ፤ አማኝ ባሮችህንም፣ እንዲሁም ቀድመውኝ የሞቱ ልጆቼን ለኔ አማላጅ አድርግልኝ» እና የመሳሰለውን ትላለህ። ከሙታኖች ግን ነብያትም ይሁኑ ሌሎች ምልጃም ይሁን ሌላ ምንም ነገር አይከጀልም። ምክንያቱም ይህ በሸሪዓ ያልተደነገገ ከመሆኑም በላይ ሸሪዓው ነጥሎ ካስቀረው ውጭ የሟች ስራ ተቋርጧልና።

በሶሒሕ ሙስሊምም አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

«إِذَا مَاتَ ابْنُ آدَمَ انْقَطَعَ عَمَلُهُ إِلَّا مِنْ ثَلَاثٍ: صَدَقَةٍ جَارِيَةٍ، أَوْ عِلْمٍ يُنْتَفَعُ بِهِ، أَوْ وَلَدٍ صَالِحٍ يَدْعُو لَهُ».

«የአደም ልጅ ሲሞት ከሶስት ነገሮች በስተቀር ስራው ይቋረጣል፤ እነሱም፦ ተሻጋሪ ምፅዋት (ሰደቀተን ጃሪያ)፣ ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት፣ ወይም ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ ናቸው።»121.

ምልጃን በህይወታቸው ጊዜም ሆነ በቂያማ ቀን ቀጥታ ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መጠየቅ የተፈቀደው ያኔ ይህን ማድረግ የሚችሉበት አቅም ስላላቸው ብቻ ነው። ምክንያቱም እርሳቸው ወደ ፊት መቅረብና ለጠያቂው ጌታቸውን መጠየቅ ይችላሉና። በዱንያ ላይ ያለውማ የታወቀ ነው። ይህ ደግሞ ለእርሳቸው ብቻ የተለየ ሳይሆን ለእርሳቸውም ሆነ ለሌሎች የተፈቀደ ነው። በመሆኑም አንድ ሙስሊም ለወንድሙ “እንዲህ እንዲህ ባለ ነገር ላይ ወደ ጌታዬ አማልደኝ” ብሎ ሊጠይቀው ይፈቀድለታል። ይህም “ዱዓ አድርግልኝ” የሚል ትርጉም አለው። የተጠየቀውም ሰው፤ የተጠየቀው ነገር አላህ እንዲጠየቅ ከፈቀደው እስከሆነ ድረስ አላህን በመጠየቅ ለወንድሙ ማማለድ ይፈቀድለታል።

በቂያማ (ትንሳኤ) ቀን ግን ጥራት ከተገባው ከአላህ ፈቃድ በኋላ ቢሆን እንጂ ለማንም ማማለድ አይፈቀድለትም፡፡ የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፦

﴿...مَنْ ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِنْدَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ...﴾

{ያ እርሱ ዘንድ በፍቃዱ ቢሆን እንጂ የሚያማልድ ማን ነው?} [አል-በቀራህ: 255]

የሞት ሁኔታን በተመለከተ ግን እሱ ለየት ያለ ሁኔታ ነው ያለው። ሰው ከመሞቱ በፊት ከነበረው ሁኔታ ጋርም ሆነ ከትንሳኤ በኋላ ካለው ሁኔታ ጋር ማያያዝ አይፈቀድም። ምክንያቱም ሸሪዐው ነጥሎ ካወጣቸው ጉዳዮች በስተቀር የሟች ስራው ስለሚቋረጥና በስራውም የተገደበ ስለሚሆን ነው፤ ከሙታን ምልጃን መለመንም ሸሪዐው ከፈቀዳቸው ነገሮች ውስጥ አይካተትም። ስለሆነም ከዚህ ጋር ማያያዝ አይፈቀድም። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከሞቱ በኋላ ከሰማዕታት ህይወት የበለጠ ሙሉ የሆነ የበርዘኽ ህይወት እንደሚኖሩ ጥርጥር የለውም። ነገር ግን ይህ ህይወት ከመሞታቸው በፊት ከነበራቸው የህይወት አይነትም ሆነ የትንሳኤ ቀን ከሚኖራቸው የህይወት ጋር የሚመሳሰል አይደለም። ይልቁንም እውነታውንና እንዴትነቱን ጥራት የተገባው አላህ እንጅ ሌላ ማንም የማያውቀው ህይወት ነው። ለዚህም ነው በተከበረው ሐዲሥ ላይ እርሳቸው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ማለታቸው የመጣው፦

«مَا مِنْ أَحَدٍ يُسَلِّمُ عَلَيَّ إِلَّا رَدَّ اللهُ عَلَيَّ رُوحِي حَتَّى أَرُدَّ عَلَيْهِ السَّلَامَ».

«አንድም በኔ ላይ ሰላምታን የሚያቀርብ የለም ለርሱ ሰላምታን እስክመልስ ድረስ አላህ ለኔ ነፍሴን የሚመልስልኝ ቢሆን እንጂ።»122

ይህም እርሳቸው ሙት መሆናቸውንና ሩሓቸውም አካላቸውን መለየቷን ያመላክታል። ነገር ግን ሰላምታ በሚቀርብላቸው ጊዜ ነፍሳቸው ወደ እርሳቸው ትመለሳለች። ከቁርኣንና ከሱና የእርሳቸውን መሞት (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሚያመላክቱ መረጃዎች የታወቁ ናቸው። ይህም በዑለማዎች መካከል ስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ ነው። ይሁን እንጂ ይህ የእርሳቸውን የበርዘኽ ህይወት አይከለክልም፤ ልክ የሰማዕታት ሞት ከፍ ያለው አላህ በተከታዩ ንግግሩ የጠቀሰውን የበርዘኽ ህይወታቸውን እንዳልከለከለው ሁሉ ማለት ነው።

﴿وَلَا تَحْسَبَنَّ الَّذِينَ قُتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَمْوَاتًا بَلْ أَحْيَاءٌ عِنْدَ رَبِّهِمْ يُرْزَقُونَ169﴾

{(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም በአላህ መንገድ የተገደሉትን ሰማዕታት ሙታን አድርገህ አትገምታቸው። በእርግጥ እነርሱ ጌታቸው ዘንድ ሕያው ናቸውና። ከጌታቸው ዘንድም ሲሳይ ይለገሳሉ።} [አሊ-ዒምራን 169]

በዚህ ጉዳይ ላይ ንግግሩን ያሰፋነው፣ በዚህ ርዕስ ላይ የሚያምታቱ ወደ ሽርክ እንዲሁም ከአላህ ውጭ ሙታንን ወደ ማምለክ የሚጣሩ ሰዎች በመብዛታቸው ነገሩ አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ነው። በመሆኑም አላህን ለእኛም ለመላው ሙስሊሞችም ሸሪዓውን ከሚፃረር ነገር ሁሉ ሰላም እንዲያደርገን እንለምነዋለን። ይበልጥ የሚያውቀው አላህ ነው።

አንዳንድ ዘያሪዎች የሚፈፅሙት የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀብር ዘንድ ድምፅን ከፍ ማድረግና ረጅም ሰአት እዛው መቆም ይህ የተደነገገውን መቃረን ነው። ምክንያቱም ከጥራት ጋር ልቅና የተገባው አላህ ኡመቱን ድምፃቸውን ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ድምፅ በላይ ከፍ ከማድረግ፣ እንዲሁም አንዳቸው ለሌላቸው ድምፃቸውን ከፍ እንደሚያደርጉት ሁሉ ለርሳቸው በንግግር ከመጮህ ከልክሏቸዋልና። እርሳቸው ዘንድ ድምፅን ዝቅ እንዲያደርጉም በሚከተለው የላቀ ቃሉ አዟቸዋል፦

﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَرْفَعُوا أَصْوَاتَكُمْ فَوْقَ صَوْتِ النَّبِيِّ وَلَا تَجْهَرُوا لَهُ بِالْقَوْلِ كَجَهْرِ بَعْضِكُمْ لِبَعْضٍ أَنْ تَحْبَطَ أَعْمَالُكُمْ وَأَنْتُمْ لَا تَشْعُرُونَ 2 إِنَّ الَّذِينَ يَغُضُّونَ أَصْوَاتَهُمْ عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ أُولَئِكَ الَّذِينَ امْتَحَنَ اللَّهُ قُلُوبَهُمْ لِلتَّقْوَى لَهُمْ مَّغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ عَظِيمٌ 3﴾

{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ድምፆቻችሁን ከነብዩ ድምጽ በላይ ከፍ አታድርጉ። ከፊላችሁ ለከፊሉ እንደሚጮህም ሁሉ በንግግር ለርሱ ስትናገሩ አትጩሁ። እናንተ የማታውቁ ስትሆኑ ስራዎቻችሁ እንዳይበላሹ (ከዚህ ተከልከሉ)።}

እነዚያ በአላህ መልዕክተኛ ዘንድ ድምፆቻቸውን ዝቅ የሚያደርጉ እነዚህ እነዚያ አላህ ልቦቻቸውን ለፍርሃት የፈተናቸው ናቸው። ለእነርሱም ምህረትና ታላቅ ምንዳ አለላቸው።} [አልሑጁራት: 2-3]

የርሳቸው ቀብር ዘንድ ረጅም ሰአት መቆምና ሰላምታን በመደጋገም ማብዛቱ እርሳቸው ቀብር ዘንድ ወደ መገፋፋት፣ የጫጫታ መብዛትና የርሳቸው ቀብር ዘንድ ድምፅ ከፍ ማለትን ያስከትላል። ይህም አላህ ግልፅ በሆኑት የቁርአን አንቀጾቹ ለሙስሊሞች የደነገገውን ይቃረናል። ነቢዩ (ﷺ) በህይወት እያሉም ሆነ ሞተው የተከበሩ ናቸው። አማኝ ለሆነ ሰውም ሸሪዓዊ ስነ ስርዓትን የሚፃረር ነገር ሊፈፅም አይገባውም።

ልክ እንደዚሁ አንዳንድ ዘያሪዎችና ሌሎችም ወደ ቀብራቸው በመዞር፣ እጆቻቸውን ከፍ በማድረግ ቀብራቸው ዘንድ ዱዓ የሚያደርጉ ይህ ሁሉ ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈን) ባልደረቦችና እነርሱን በመልካም የተከተሉት ቀደምት ደጋግ አበዎች ከነበሩበት ተቃራኒ ነው። ይልቁንም አዲስ ፈጠራ መጤ ነው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦

«فَعَلَيْكُمْ بِسُنَّتِي وَسُنَّةِ الخُلَفَاءِ الرَّاشِدِينَ المَهْدِيِّينَ مِنْ بَعْدِي، تَمَسَّكُوا بِهَا وَعَضُّوا عَلَيْهَا بِالنَّوَاجِذِ، وَإِيَّاكُمْ وَمُحْدَثَاتِ الأُمُورِ، فَإِنَّ كُلَّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلَّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ».

«በኔ ሱናና ከኔ በኋላ ባሉት የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን! እርሷን አጥብቃችሁ ያዙ፤ በማኘኪያ ጥርሳችሁም ነክሳችሁ ያዟት። አደራችሁን አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ! ሁሉም አዲስ መጤ ነገር ቢድዓ ነው፤ ሁሉም ቢድዓም ጥመት ነውና።»123.

ነቢዩ ﷺ እንዲህም ብለዋል፡

«مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ مِنْهُ فَهُوَ رَدٌّ».

"በዚህ ጉዳያችን ከእርሱ ያልሆነን አዲስ ነገር ያመጣ ይዞት የመጣው አዲስ ፈሊጥ ውድቅ ነው።"124

«مَنْ عَمِلَ عَمَلًا لَيْسَ عَلَيْهِ أَمْرُنَا فَهُوَ رَدٌّ».

"በርሱ ላይ የኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ነገር የሰራ ሰዉ ስራው ወደርሱ ተመላሽ ነዉ።"125.

ዐሊይ ቢን አል-ሑሰይን ዘይኑል-ዓቢዲን (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - አንድን ሰው በነቢዩ (ﷺ) ቀብር ዘንድ ዱዓእ ሲያደርግ አይተው ከለከሉት። እንዲህም አሉት፦ «ከአባቴ፣ እርሱም ከአያቴ፣ እርሱም ከአላህ መልክተኛ (ﷺ) የሰማሁትን ሐዲሥ አልነግርህምን? እርሳቸው እንዲህ ብለዋል፦

«لَا تَتَّخِذُوا قَبْرِي عِيدًا، وَلَا بُيُوتَكُمْ قُبُورًا، وَصَلُّوا عَلَيَّ، فَإِنَّ تَسْلِيمَكُمْ يَبْلُغُنِي أَيْنَمَا كُنْتُمْ».

"ቀብሬን ዒድ አታድርጉት፤ ቤቶቻችሁንም መቃብር አታድርጉ። በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ፤ ሰላምታችሁ የትም ብትሆኑ ይደርሰኛልና።"126.

ልክ እንደዚሁ አንዳንድ ዘያሪዎች በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ሰላምታን ሲያቀርቡ ልክ ሶላት የሚሰግድ ሰው እንደሚያደርገው ቀኝ እጃቸውን ግራ እጃቸው ላይ አጣምረው ከደረታቸው በላይ ወይም ከደረታቸው ስር ማድረጋቸው ይህ ሁኔታ በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ሰላምታን ሲያቀርቡም ሆነ ከርሳቸው ውጪ ባሉ ሌሎች ንጉሶች፣ መሪዎችና ሌሎችም ላይ አይፈቀድም። ምክንያቱም ኢብኑ ሐጀር ፈትሑልባሪ ውስጥ የተለያዩ ዑለሞችን ጠቅሰው እንዳወሱት ይህ የመዋደቅ፣ የመተናነስና የአምልኮ ሁኔታ ስለሆነ ከአላህ ውጪ ለማንም አይሆንም። ጉዳዩም ሁኔታውን በጥሞና ላስተዋለና አላማው የቀደምት ደጋግ አበዎችን መንገድ መከተል ለሆነ ሰው እጅግ ግልፅ ነው።

በጭፍን ወገንተኝነት፣ በስሜት መከተል፣ በጭፍን ተከታይነትና ወደ ደጋግ ቀደምቶች መንገድ በሚጣሩት ላይ መጥፎ ጥርጣሬ ያሸነፈውማ የርሱን ጉዳዩ ወደ አላህ የተተወ ነው። አላህንም ለእኛም ሆነ ለእርሱ ሐቅን ከሌላው ነገር ሁሉ አስበልጠን እንድንመርጥ ቅናቻና መገጠምን እንዲለግሰን እንማፀነዋለን። እርሱ ሊማፀኑት ዘንድ እጅግ የተገባው ነውና።

ልክ እንደዚሁ አንዳንድ ሰዎች ወደተከበረው ቀብር ከሩቅ በመዞርና ከንፈሮቻቸውን በሰላምታ ወይም በዱዓ ማንቀሳቀሳቸው፤ ይህ ሁሉ ከዚህ በፊት ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ የሆነ አዲስ መጤ ነው። ለሙስሊም በዲኑ ውስጥ አላህ ያልፈቀደውን አዲስ ነገር ሊፈጥር አይገባውም። በዚህ ስራውም ከወዳጅነትና ከንጹህ ልቦና ይልቅ ከአላህ ለመራቅ ይዳረጋል። ኢማሙ ማሊክ (አላህ ይዘንላቸውና) ይህንና መሰል ስራዎችን አውግዘዋል፤ እንዲህም ብለዋል፦ "የዚህች ኡማ መጨረሻዋ አይቃናም፤ የመጀመሪያዋን ያቃናው ነገር ቢሆን እንጂ።"127.

የዚህች ኡመት የመጀመሪያዎቹ የተስተካከሉት በነቢዩ ﷺ፣ በቅን ምትኮቻቸው፣ መልካም ስራቸው በተወደደላቸው ባልደረቦቻቸው ፈለግ እና እነርሱን በመልካም በተከተሏቸው (ሰዎች) መንገድ ላይ በመጓዝ ነው። የዚህች ኡመት ኋለኞችም የሚስተካከሉት ያንኑ አጥብቀው በመያዝና በዚያው ላይ በመጓዝ ብቻ ነው።

አላህ ሙስሊሞችን በዱንያም ሆነ በአኼራ መዳንን፣ ደስታንና ክብርን የሚያገኙበትን ነገር ያድላቸው። እነሆ እርሱ ቸርና ለጋስ ነውና።

ማስሰቢያ

የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቀብር የመዘየር ብይን፤

የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈን) ቀብር መዘየር አንዳንድ ተራ ሰዎችና መሰሎቻቸው እንደሚያስቡት ግዴታም ሆነ የሐጅ መስፈርት አይደለም። ይልቁንም የረሱልን (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈን) መስጂድ የዘየረ ወይም በአቅራቢያው ያለን ሰው በሚመለከት የሚወደድ ተግባር ነው።

ከመዲና የራቀ ሰው ቀብር መዘየርን በማሰብ ጓዝን ሸክፎ መውጣት አይፈቀድለትም። ነገር ግን የተከበረውን መስጂድ መዘየር በማሰብ ጓዝን መሸከፍ ይወደድለታል። መስጂዱ ዘንድ የደረሰ ጊዜም የተከበረውን ቀብርና የሁለቱን ባልደረቦች (የአቡበከርና ዑመርን) ቀብር ይዘይራል። የርሳቸውን (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀብርና የሁለቱን ባልደረቦቻቸውን ቀብሮች መዘየር መስጂዳቸውን ﷺ መዘየርን ተከትሎ እግረ መንገድ የሚደረግ ነው። ይህም በሰሒሐይን እንደተረጋገጠው ነቢዩ ﷺ እንዲህ በማለታቸው ነው፡

«لَا تُشَدُّ الرِّحَالُ إِلَّا إِلَى ثَلَاثَةِ مَسَاجِدَ: المَسْجِدِ الحَرَامِ، وَمَسْجِدِي هَذَا، وَالمَسْجِدِ الأَقْصَى».

«ከሶስቱ መስጊዶች በስተቀር ጓዝ ሸክፎ ጉዞ አይወጣም። እነርሱም: መስጂደል ሐራም፣ ይህ መስጂዴ እና መስጂደል አቅሷ ናቸው።»128

የርሳቸውን (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀብር ወይም የሌላን ቀብር ለመዘየር አስቦ ጓዝን ሸክፎ መውጣት የተደነገገ ቢሆን ኖሮ ለህዝቦቻቸው ያመላክቱና ለትሩፋቱም ይመሯቸው ነበር። ምክንያቱም እርሳቸው ከሰዎች ሁሉ ለህዝባቸው የበለጠ መካሪ፣ አላህንም ከማንም በላይ የሚያውቁና ከማንም በላይም እርሱን የሚፈሩ ናቸውና። በእርግጥም ተልዕኳቸውን ግልፅ በሆነ መልእክት ተወጥተዋል። ህዝባቸውንም ወደ መልካም ነገር ሁሉ አመላክተዋል፤ ከመጥፎ ነገርም ሁሉ አስጠንቅቀዋቸዋል። ከሶስቱ መስጂዶች ውጭ ጓዝን ሸክፎ ከመውጣት አስጠንቅቀው ሳለ እንዴት ሊፈቀድ ይችላል?! እንዲህም ብለው ሳለ፦

«لَا تَتَّخِذُوا قَبْرِي عِيدًا، وَلَا بُيُوتَكُمْ قُبُورًا، وَصَلُّوا عَلَيَّ، فَإِنَّ صَلَاتَكُمْ تَبْلُغُنِي حَيْثُ كُنتُمْ».

«ቀብሬን የሚጎበኝ የበአል ስፍራ አታድርጉት፤ ቤቶቻችሁንም መቃብር አታድርጉ። በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ፤ የትም ብትሆኑ ሶለዋታችሁ ትደርሰኛለችና።»129

የርሳቸውን (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀብር ለመዘየር ጓዝን ሸክፎ መውጣት ይፈቀዳል የሚባል ከሆነ ቀብሩን እንደ በዓል እንዲይያዝ ያደርጋል። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፈሩትንና የተከለከለውን ነገር ማለትም በሃይማኖት ድንበር ማለፍንና ከልክ በላይ ማወደስን ያስከትላል። የርሳቸውን (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀብር ለመዘየር ጓዝን ሸክፎ መውጣት እንደሚፈቀድ በማመናቸው ምክንያት ብዙ ሰዎች እዚህ ስህተት ውስጥ ወድቀዋል።

ወደ እርሳቸው (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁንና) ቀብር ጓዝን ሸክፎ መጓዝ ይፈቀዳል የሚሉ ወገኖች ማስረጃ አድርገው የሚያቀርቧቸውን ሐዲሶችን በተመለከተ፣ ሰነዶቻቸው ያልተረጋገጡ (ዶዒፍ) እንዲያውም የተቀጠፉ ናቸው። እንደ ዳረቁጥኒይ፣ በይሀቂይ፣ ሓፊዝ ኢብኑ ሐጀር እና ሌሎችም ያሉ የሐዲሥ ሊቃውንት ዶዒፍነታቸውን ገልፀዋል። ስለሆነም ከሶስቱ መስጂዶች ውጭ ወደ ሌላ ስፍራ ጓዝን ሸክፎ መጓዝን ክልክል የሚያደርጉትን ትክክለኛ ሐዲሶች በእነዚህ (ዶዒፍ) ሐዲሦች ተንተርሶ መፃረር አይፈቀድም።

ውድ አንባቢ ሆይ! የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀብር በመዘየር ጉዳይ የተወሰኑ የተፈበረኩ ሐዲሦችን እንድታውቃቸውና በነዚህ ሐዲሦችም ከመሸወድ እንድትጠነቀቅ ሲባል ከዚህ በታች እንዘረዝርልሃለን:

የመጀመሪያ: "ሐጅ አድርጎ እኔን ያልዘየረኝ በርግጥም ችላ ብሎኛል።"

ሁለተኛ: «ከሞትኩ በኋላ የዘየረኝ ሰው በህይወት እያለሁ እንደዘየረኝ ነው።»

ሶስተኛ: «በአንድ አመት ውስጥ እኔንና አባቴን ኢብራሂምን የዘየረ ሰው ጀነት እንዲገባ አላህ ዘንድ ዋስትና እሆንለታለሁ።»

አራተኛ: «ቀብሬን የዘየረ ሰው የኔ ምልጃ ለርሱ ፀንታለታለች።»

እነዚህና የመሳሰሉት ሐዲሦች አንዳቸውም ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) አልተረጋገጡም።

ሓፊዝ ኢብኑ ሐጀር "ተልኺስ" በሚባለው መጽሐፋቸው አብዛኛዎቹን ዘገባዎች ካወሱ በኋላ እንዲህ ብለዋል: "የነዚህ ሐዲሦች ሁሉም ሰነዶች ያልተረጋገጡ (ዶዒፎች) ናቸው።

ሓፊዝ አልዑቀይሊይ እንዲህ ብለዋል፦ "በዚህ ርዕሰ ጉዳይ አንድም ትክክለኛ የሆነ ሐዲሥ አልተላለፈም።

ሸይኹል ኢስሊም ኢብን ተይሚያም አላህ ይዘንላቸውና እነዚህ ሐዲሦች ሁሉም የተቀጠፉ መሆናቸውን በቁርጠኝነት ገልጿል። በእውቀት፣ በሒፍዝ እና በጥልቅ ጥናትም እርሳቸው በቂ ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ የተረጋገጠ ነገር ቢኖር ኖሮ፤ ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) እርሱን በመተግበር፣ ለህዝቡ በማብራራትና ወደርሱም በመጥራት ረገድ ከሰዎች ሁሉ ቀዳሚ በሆኑ ነበር። ምክንያቱም እነርሱ ከነቢያት ቀጥለው ከሰዎች ሁሉ በላጭ፣ የአላህንም ድንጋጌዎችና ለባሮቹ የደነገገውንም ከማንም በላይ አዋቂ፣ ለአላህና ለፍጡራኑም የበለጠ ቅኖች ናቸውና። እናም ከእነርሱ በዚህ ጉዳይ ላይ የተዘገበ አንዳችም ነገር አለመኖሩ፤ ድርጊቱ ያልተደነገገ መሆኑን ያስረዳናል።

ከነዚህ ውስጥ ትክክለኛ (ሶሒሕ) ነገር ቢገኝ እንኳ፤ ሐዲሦቹን ለማጣጣም ሲባል ቀብርን ብቻውን ለመዘየር በማሰብ ጓዝ መሸከፍ የሌለበት ሸሪዓዊ ዚያራ ላይ ሊተረጎም ይገባዋል። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የበለጠ ያውቃል።

አዲስ ክፍል:

የቁባእ መስጂድንና በቂዕን መዘየር ስለመወደዱ፤

መዲናን ለሚዘይር ሰው የቁባእን መስጂድ መዘየርና እዛም መስገዱ ይወደድለታል። በሁለቱ ሶሒሖች ከኢብኑ ዑመር (አላህ ከሁለቱም ስራ ይውደድላቸውና) እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋልና፦

«كَانَ النَّبِيُّ ﷺ يَزُورُ مَسْجِدَ قُبَاءٍ رَاكِبًا وَمَاشِيًا وَيُصَلِّي فِيهِ رَكْعَتَيْنِ».

«ነቢዩ ﷺ የቁባእን መስጂድ እየጋለቡም በእግራቸውም ይዘይሩና ሁለት ረከዓ ይሰግዱበት ነበር።»130

ከሰህል ቢን ሑነይፍ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፥ የአሏህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦

«مَنْ تَطَهَّرَ فِي بَيْتِهِ ثُمَّ أَتَى مَسْجِدَ قُبَاءٍ فَصَلَّى فِيهِ صَلَاةً كَانَ لَهُ كَأَجْرِ عُمْرَةٍ».

«ከቤቱ ጦሀራ አድርጎ (ዉዱእ አድርጎ) ከዚያም ወደ ቁባእ መስጂድ መጥቶ ሶላትን በውስጧ የሰገደ ለርሱ የዑምራ ምንዳ ይኖረዋል።»131

መዲናን የሚዘይር ሰው የበቂዕን መቃብር ስፍራ፣ የሰማዕታትን መቃብር ስፍራ፣ እና የሐምዛን (አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና) ቀብር መዘየሩ ሱና ነው። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይዘይሯቸውና፣ ዱዓም ያደርጉላቸው ስለነበር ነው። እንዲሁም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ስላሉም ነው:

«زُورُوا القُبُورَ فَإِنَّهَا تُذَكِّرُكُمْ بِالآخِرَةِ».

«መቃብርን ዘይሩ! እርሷ መጪውን አለም ታስታውሳችኋለችና።»132. ሙስሊም ዘግበውታል።

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶሐቦቻቸው ቀብርን በዘየሩ ወቅት እንዲህ እንዲሉ ያስተምሯቸውም ነበር:-

«السَّلَامُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الدِّيَارِ مِنَ المُؤْمِنِينَ وَالمُسْلِمِينَ، وَإِنَّا إِنْ شَاءَ اللهُ بِكُمْ لَاحِقُونَ، نَسْأَلُ اللهَ لَنَا وَلَكُمُ العَافِيَةَ».

“አሰላሙ ዐለይኩም ያ አህለ ዲያር ሚነል ሙእሚኒነ ወልሙስሊሚን ወኢና ኢንሻአላሁ ቢኩም ላሒቁን ነስአሉላሀ ለኩም ወለና አል ዓፊያ” (ትርጉሙም፦ “በዚህ መቃብር ውሰጥ የምትገኙ ሙእሚኖችና ሙስሊሞች ሆይ! ሰላም ይስፈንባችሁ! እኛም በአላህ ፈቃድ እንከተላችኋለን፤ ለእኛም ለእናንተም ከአላህ ዘንድ ደህንነትን እንጠይቃለን።”)133 ሙስሊም ከሱለይማን ኢብን ቡረይዳ፣ እርሳቸውም ከአባታቸው ዘግበውታል።

ቲርሚዚይ ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደዘገቡት: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመዲና ቀብሮች በኩል አለፉና ፊታቸውን ወደነርሱ አዙረው እንዲህ አሉ፦

«السَّلَامُ عَلَيْكُمْ يَا أَهْلَ القُبُورِ، يَغْفِرُ اللهُ لَنَا وَلَكُمْ، أَنْتُمْ سَلَفُنَا وَنَحْنُ بِالأَثَرِ».

("አስ-ሰላሙ ዐለይኩም ያ አህለል ቁቡር፤ የጝፊሩላሁ ለና ወለኩም፤ አንቱም ሰለፉና ወነሕኑ ቢል አሠር።")134 (ትርጉሙም፦ “የመቃብር ሰዎች ሆይ ሰላም ይስፈንባችሁ! አላህ ለእኛም ለእናንተም ይማርልን፤ እናንተ ቀዳሚዎቻችን ናችሁ፤ እኛም የናንተን ፈለግ ተከታዮች ነን።”)

ከእነዚህ ሐዲሶች የምንረዳው ሸሪዓዊ በሆነው የቀብር ጉብኝት የሚፈለገው መጪውን አለም ማስታወስ፣ ለሟቾች መልካም መዋል፣ ለእነርሱ ዱዓ ማድረግና እዝነትን መለመን መሆኑን ነው።

ነገር ግን መቃብራቸው ዘንድ ዱዓ ለማድረግ በማሰብ ወይም በአጠገባቸው ለመዘውተር (ኢዕቲካፍ ለማድረግ) ወይም ጉዳይን እንዲያስፈፅሙና የታመመን እንዲፈውሱ እነርሱን ለመጠየቅ ወይም በነርሱ አማካኝነት ወይም በክብራቸው አማካኝነት አላህን ለመጠየቅና የመሳሰሉትን ዓላማ በማድረግ መዘየር፣ ይህ የተወገዘ መጤ (ቢድዓዊ) የሆነ መዘየር ነው። አላህም ሆነ መልክተኛው አልደነገጉትም። ደጋግ አበዎችም (አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና) አልፈፀሙትም። ይልቁንም መልክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከከለከሉት መተው ከሚገባው የሚመደብ ነው። እርሳቸውም እንዲህ ብለዋልና፡

«زُورُوا القُبُورَ، وَلَا تَقُولُوا هُجْرًا».

«መቃብርን ዘይሩ፤ ጸያፍ ቃልንም አትናገሩ»135.

እነዚህ የተጠቀሱት ጉዳዮች በደረጃቸው ቢለያዩም ቢድዓ በመሆናቸው በአንድ ላይ ይጠቃለላሉ። ከፊሉ ሺርክ ደረጃ ባይደርስም ቢድዓ ነው፤ መቃብር ዘንድ አላህን እንደመለመን፣ በሟቹ ሐቅና በክብሩ አማካኝነት እሱን መጠየቅና የመሳሰሉት አይነቶቹ በምሳሌነት ይጠቀሳሉ። ከፊሉ ደግሞ ከትልቁ ሺርክ ይመደባል፤ ሙታንን እንደመለመን፣ ከነርሱ እርዳታ መፈለግና የመሳሰሉት አይነቱ ለምሳሌነት ይጠቀሳሉ።

የዚህ ማብራሪያም ከዚህ በፊት በዝርዝር አልፏልና ንቃ፤ ተጠንቀቅም። ጌታህንም ወደ ሐቅ እንዲገጥምህና እንዲመራህ ለምነው። እርሱ የሚገጥምና የሚመራ ነውና፤ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ ከእርሱ ሌላም ጌታ የለም።

በጽሑፍ ልናሰፍረው የፈለግነው የመጨረሻው ነጥብ ይህ ነው። ምስጋና በመጀመሪያም በመጨረሻም ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላትና ሰላምም በባሪያው፣ በመልእክተኛውና ከፍጡራኑ ሁሉ ምርጥ በሆኑት በሙሐመድ ላይ፣ በቤተሰቦቻቸው ላይ፣ በባልደረቦቻቸው ላይ እና እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ በመልካም በተከተሏቸው ላይ ሁሉ ይስፈን።

 

***

ማውጫ

 

የአዘጋጁ መግቢያ 2

አዲስ ክፍል: 5

ሐጅና ዑምራ ግዴታ መሆኑንና ቶሎ መፈፀምም የሚገባ ስለመሆኑ ማስረጃዎቹ 5

አዲስ ክፍል: 10

ከወንጀሎች ተውበት ማድረግና ከበደሎች መላቀቅ ግዴታ ስለመሆኑ፤ 10

አዲስ ክፍል: 17

ሐጅ አድራጊ (ኢሕራም ማድረጊያ ስፍራ) ሚቃት ሲደርስ ማድረግ ያለበት፤ 17

አዲስ ክፍል: 25

የሐጅና ዑምራ ኢሕራም ማድረጊያ ስፍራዎችና ድንበራቸው፤ 25

አዲስ ክፍል: 32

ከሐጅ ወራት ውጪ ወደ ሚቃት የደረሰ ሰው ብይን፤ 32

አዲስ ክፍል: 36

የህፃን ልጅ ሐጅ ማድረግ ከኢስላማዊ የግዴታው ሐጅ (ግዴታ ከሆነው ሐጅ) ያብቃቃዋልን? በሚለው ዙሪያ ያለው ብይን፤ 36

አዲስ ክፍል: 39

በኢሕራም ወቅት የተከለከሉና የተፈቀዱ ነገሮች፤ 39

አዲስ ክፍል: 48

ሐጅ አድራጊ መካ ሲገባ ስለሚያከናውናቸው ተግባራት፤ እንዲሁም ጦዋፍና የመሳሰሉትን መስጂደል ሐራም ከገባ በኋላ ስለሚፈፅማቸው ተግባራት፤ 48

አዲስ ክፍል: 58

በዙልሒጃህ ስምንተኛው ቀን ለሓጅ ኢሕራም ስለማድረግና ወደ ሚና ስለመውጣት ብይን፤ 58

አዲስ ክፍል: 87

በእርድ ቀን ሐጅ አድራጊው የሚፈፅመው ተግባር በላጭ መሆኑን ማብራሪያ፤ 87

አዲስ ክፍል: 94

ተመቱዕና ቂራን ፈፃሚ በሆኑት ላይ ደም ግዴታ ስለመሆኑ፤ 94

አዲስ ክፍል: 98

ሐጅ የሚያደርጉ ሰዎችና ሌሎችም ላይ በመልካም ማዘዝ ግዴታ ስለመሆኑ፤ 98

አዲስ ክፍል: 108

አምልኮዎችን መሰነቅ እንደሚወደድ፤ 108

አዲስ ክፍል: 110

የዚያራ ህግጋትና ስነ-ስርዓቶቹ፤ 110

ማስሰቢያ 129

የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቀብር የመዘየር ብይን፤ 129

አዲስ ክፍል: 134

የቁባእ መስጂድንና በቂዕን መዘየር ስለመወደዱ፤ 134

am396v3.1 - 24/06/2026


ጦበራኒይ በ"አልአውሰጥ" በቁጥር (7469) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (8) እና ሙስሊም በቁጥር (16) ዘግበውታል።

ማለትም፡ የሀብት ስፋት

በጃሚዑል አሓዲሥ በቁጥር (31221) ወደ ሱነን ሰዒድ ኢብኑ መንሱር አስጠግተውታል፤ ነገር ግን እኔ ዘንድ በሚገኘው ቅጂ ላይ አላገኘሁትም።

ቲርሚዚይ በቁጥር (812) ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ በቁጥር (1732) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (1337) ዘግበውታል።

ኢብኑ ኹዘይማህ በቁጥር (1) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1520) ዘግበውታል።

ነሳኢይ በቁጥር (2620) ዘግበውታል።

ቡኻሪይ በቁጥር (1773) እና ሙስሊም በቁጥር (1349) ዘግበውታል።

ቡኻሪይ በቁጥር (2449) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (1015) ዘግበውታል።

ጦበራኒይ በ«አል-ከቢር» (2989) ዘግበውታል።

ቡኻሪይ በቁጥር (1427) እና ሙስሊም በቁጥር (1035) ዘግበውታል።

ቡኻሪይ በቁጥር (1474) እና ሙስሊም በቁጥር (4040) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (2985) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (1342) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1539) እና ሙስሊም በቁጥር (1189) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (1218) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (5891) እና ሙስሊም በቁጥር (257) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (258) ዘግበውታል።

ነሳኢይ በቁጥር (14) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (2892) እና ሙስሊም በቁጥር (259) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (260) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (1177) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1) እና ሙስሊም በቁጥር (1907) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (867) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (2697) እና ሙስሊም በቁጥር (1718) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (2550) እና ሙስሊም በቁጥር (1718) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1524) እና ሙስሊም በቁጥር (1181) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (1297) ዘግበውታል።

ዘገባውን ቀደም ብለን አሳልፈናል።

በዓረብኛው "ሙሀሉ" የተባለው፡ ማለትም፡ ኢሕራም አድርጎ በተልቢያ ድምጹን ከፍ የሚያደርግበት ቦታ ማለት ነው።

ቀደም ብሎ የተጠቀሰው ሐዲስ ክፍል ነው፡፡

ዘገባው ቀደም ብሎ አልፏል።

ቡኻሪ በቁጥር (1549) እና ሙስሊም በቁጥር (1184) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (5089) እና ሙስሊም በቁጥር (1207) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (1336) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1858) ዘግበውታል።

ኢብን አቢ ሸይባህ በቅፅ (4/444) ዘግበውታል።

ቲርሚዚይ በቁጥር (2518) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1841) እና ሙስሊም በቁጥር (1179) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1838) ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ በቁጥር (1833) ዘግበውታል።

ቡኻሪ ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) በቁጥር (1521) እና ሙስሊም በቁጥር (1350) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1521) እና ሙስሊም በቁጥር (1350) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (1409) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1834) እና ሙስሊም በቁጥር (1353) ዘግበውታል።

ዘገባውን ቀደም ብለን አሳልፈናል።

ቡኻሪ በቁጥር (1568) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (305) እና ሙስሊም በቁጥር (1211) ዘግበውታል።

ቲርሚዚይ በቁጥር (3585) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (2137) ዘግበውታል።

ሙስሊም ከኢብኑ ዙበይር ረዲየላሁ ዐንሁ በቁጥር (594) ዘግበውታል።

ሙስሊም ከአቡ ሁረይራ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና በቁጥር (2720) ዘግበውታል።

ቡኻሪ ከአቡ ሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ በቁጥር (6347) ዘግበውታል።

በዚሁ ቃል አቡ ዳውድ (ወሚነል መእሠሚ ወልመጝረም) የሚለው ቃል ሳይኖርበት ከአቢ ኡማማ አል-አንሷሪይ በቁጥር (1554) ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ በቁጥር (1554) ከአነስ ‐አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና‐ ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ ከኢብኑ ኡመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) በቁጥር (5074) ዘግበውታል።

ሙስሊም ከአቡ ሙሳ አል-አሽዐሪይ ረዲየላሁ ዐንሁ በቁጥር (2719) ከዘገቡት ሐዲስ የተወሰደ።

ቲርሚዚይ ከሸዳድ ኢብኑ አውስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በቁጥር (3407) ዘግበውታል።

ኢማሙ አሕመድ “ሙስነድ” ላይ (6/301) ከኡሙ ሰለመህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (2713) ከአቡ ሁረይራ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና ዘግበውታል።

ሙስሊም ከዘይድ ኢብኑ አርቀም ረዲየላሁ ዐንሁ በቁጥር (2722) ዘግበውታል።

ሙስሊም ከኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁማ በቁጥር (2717) ዘግበውታል።

ይህ ከዚህ በፊት በቁጥር (2722) ከተዘገበው የዘይድ ኢብኑ አርቀም ረዲየላሁ ዐንሁ ሐዲስ ውስጥ የተወሰደ ክፍል ነው።

ቲርሚዚይ ከዚያድ ኢብኑ ዐላቀህ ከአጎቱ በቁጥር (3591) ዘግበውታል።

ቲርሚዚይ ከዒምራን ኢብኑ ሑሰይን (ረ.ዐ) በቁጥር (3483) ዘግበውታል።

ቲርሚዚይ ከዓሊይ ረዲየላሁ ዐንሁ ሐዲስ በቁጥር (3563) ዘግበውታል።

ሙስሊም ከአብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በዘገቡት ሐዲስ በቁጥር (2721) ዘግበውታል።

ሙስሊም ከዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁ በቁጥር (2725) ዘግበውታል።

ኢብኑ ማጀህ ከዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ በቁጥር (3846) ዘግበውታል።

ቡኻሪ ከዑባዳ ኢብን አስ-ሷሚት (ረዲየላሁ ዐንሁ) በቁጥር (1154) ዘግበውታል።

ቡኻሪ ከከዕብ ኢብን ዑጅራ ረዲየላሁ ዐንሁ በቁጥር (3370) ዘግበውታል።

ሙስሊም ከዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ በቁጥር (1348) ዘግበውታል።

ዘገባውን ቀደም ብለን አሳልፈናል።

ሙስሊም ከጃቢር (ረዲየላሁ ዐንሁ) በቁጥር (1218) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1539) እና ሙስሊም በቁጥር (1189) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1556) እና ሙስሊም በቁጥር (1211) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1572) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (1215) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (83) እና ሙስሊም በቁጥር (1306) ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ በቁጥር (2015) ዘግበውታል።

ኢብኑ ማጃህ ከጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና በቁጥር (3062) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (2473) ዘግበውታል።

ማለትም፡ አቡ ዳውድ አጥ-ጠያሊሲ ሲሆኑ በ "ሙስነድ አቢ ዳውድ አጥ-ጠያሊሲ" ቁጥር (459) የአቡ ዘር ረዲየላሁ ዐንሁ የመስለም ታሪክ በያዘው ሐዲስ ውስጥ ዘግበውታል።

ቲርሚዚይ በቁጥር (927) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (69) ከአነስ ‐አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና‐ ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1998) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (2420) እና ሙስሊም በቁጥር (651) ዘግበውታል።

ሙስሊም ከአቡ ሁረይራ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና በቁጥር (653) ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ ከዐብደላህ ኢብን ኡሙ መክቱም በቁጥር (552) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (654) ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ ከኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁማ በቁጥር (551) ዘግበውታል።

ቡኻሪ ከአቡ ሁረይራ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) በቁጥር (1521)፣ እና ሙስሊም በቁጥር (1350) ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ በቁጥር (3251) ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ በቁጥር (3253) ዘግበውታል።

ቡኻሪ ከዐብደላህ በቁጥር (2679) እና ሙስሊም በቁጥር (1646) ዘግበውታል።

ኢማሙ አሕመድ በቁጥር (5/428) ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ በቁጥር (4980) ዘግበውታል።

ኢብኑ ማጀህ በቁጥር (2117) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (1893) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (3009) እና ሙስሊም በቁጥር (2406) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1755) እና ሙስሊም በቁጥር (1328) ዘግበውታል።

ዘገባውን ቀደም ብለን አሳልፈናል።

ሙስሊም ከጃቢር ኢብን ዐብዲላህ ረዲየላሁ ዐንሁ በቁጥር (867) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (1190) እና ሙስሊም በቁጥር (1394) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (1395) ዘግበውታል።

ኢማሙ አሕመድ በቁጥር (4/5) ዘግበውታል።

ኢብኑ ማጃህ በቁጥር (1406) ላይ ዘግበውታል።

ቡኻሪ ከዐብደላህ ኢብኑ ዘይድ አል-ማዚኒይ በቁጥር (1195) እና ሙስሊም በቁጥር (1390) ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ በቁጥር (2041) ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ በቁጥር (3236) ዘግበውታል።

ዘገባውን ቀደም ብለን አሳልፈናል።

ሙስሊም ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና በቁጥር (438) ዘግበውታል።

ቡኻሪ በቁጥር (615) እና ሙስሊም በቁጥር (437) ዘግበውታል።

ሙስሊም ከጃቢር ኢብን ሰሙራ በቁጥር (430) ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ በቁጥር (679) ዘግበውታል፤ ሐዲሱም፡ “ሰዎች ከመጀመሪያው ሶፍ ወደኋላ ከመቅረት አይወገዱም፤ በመጨረሻም አላህ እሳት ውስጥ ቢያዘገያቸው እንጂ።”

ሙስሊም ከአቡ ሁረይራ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና በቁጥር (1631) ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ በቁጥር (2041) ዘግበውታል።

አቡ ዳውድ ዒርባድ ኢብን ሳሪያህ በተላለፈ ሐዲስ በቁጥር (4607) ዘግበውታል።

ዘገባውን ቀደም ብለን አሳልፈናል።

ዘገባውን ቀደም ብለን አሳልፈናል።

የዘይኑል-ዓቢዲን ዘገባ ሲሆን ሸይኹ አልሐፊዝ አል-መቅዲሲ አስጠግተውታል። ሐዲሱንም እርሳቸው ያለ ታሪኩ፣ ኢማሙ አሕመድም በሙስነዳቸው (2/367) ዘግበውታል።

ኢጋሠቱል ለህፋን ፊ መሷይዲ ሸይጣን (1/ 363)

ቡኻሪ ከአቡ ሁረይራ በቁጥር (1189) እና ሙስሊም በቁጥር (1397) ዘግበውታል።

ዘገባውን ቀደም ብለን አሳልፈናል።

ቡኻሪ በቁጥር (1193) እና ሙስሊም በቁጥር (1399) ዘግበውታል።

ኢብኑ ማጀህ በቁጥር (1412) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (976) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (975) ዘግበውታል።

ቲርሚዚይ በቁጥር (1035) ዘግበውታል።

ሙስሊም ከኢብኑ ቡረይዳህ እሳቸውም ከአባታቸው በቁጥር (977) ዘግበውታል።

ሙስሊም በቁጥር (55) ዘግበውታል።